TIKVAH-ETHIOPIA
" በመደበኛ የሕግ ማስከበር ስርአት ለመቆጣጠር አዳጋች ሁኔታ ተገኝቷል " - የአማራ ክልል መንግሥት በቀን 27/11/2015 ዓ/ም በአማራ ክልል ፕሬዜዳንት ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ተፈርሞ ለኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር በተላከ ደብዳቤ ፤ አሁን ላይ በአማራ ክልል ያለውን የፀጥታ ችግር በመደበኛው የሕግ ማስከበር ስርዓት ለመቋቋም የማይቻልበት ሁኔታ እንደተፈጠረ ይገልጻል። የፀጥታ መደፍረሱ በክልሉ ከፍተኛ ሰብዓዊ…
#NewsAlert
በአማራ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ አሳለፈ።
የሚኒስትሮች ም/ቤት በዛሬው ዕለት 23ኛ መደበኛ ስብሰባ አካሂዶ ነበር።
በዚህም ስብሰባ ፤ " የሕዝብን ሠላም እና ደህንነት ለማስጠበቅ " በቀረበው የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6 /2015 ላይ መመምከሩ ተነግሯል።
ምክር ቤቱ ፤ " በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሚታየውን በትጥቅ የተደገፈ ህገወጥ እንቅስቃሴ በመደበኛ የህግ ማስክበር ስርዓት ለመቆጣጠር ወደ ማይቻልበት ደረጃ የተሸጋገረ በመሆኑ፤ ይህ እንቅስቃሴ የክልሉን ነዋሪ አጠቃላይ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ እንቅስቃሴ በከፍተኛ ደረጃ ያወከ እና ህገ መንግስታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ የጣለ በመሆኑ፤ የሕዝብን ሠላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ እንዲሁም ህግ እና ስርዓት ለማስከበር የአስቸኳይ ጊዜ እርምጃዎችን መውሰድ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፣ እንቅስቃሴው በሃገር ደህንነት እና በህዝብ ሰላም ላይ የደቀነው አደጋ ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ መጥቷል፡፡ " ብሏል።
" መንግስት ትጥቅ አንስተው የሚንቀሳቀሱ ሃይሎች ሁሉ የሰላም እና ህጋዊ መንገድን እንዲከተሉ ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪዎችን ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ " ያለው ምክር ቤቱ " የታጠቁ ፅንፈኛ ቡድኖች እየፈፀሙ ባለዉ ጥቃት ምክንያት የክልሉ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰ ይገኛል፡፡ " ሲል ገልጿል።
የክልሉ መንግስትም በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ያጋጠመው የፀጥታ መደፍረስ በክልሉ ከፍተኛ ሰብዓዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት እያስከተለ የሚገኝ መሆኑን በመግለጽ፣ ሁኔታውን በመደበኛው የህግ ማስከበር ሥርዓት ለመቆጣጠር አዳጋች ሆኖ በመገኘቱ፣ የፌደራል መንግስት አስፈላጊውን የህግ ማዕቀፍ በኢፌድሪ ህገ መንግስት መሰረት እንዲደነግግ እና ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ ጥያቄ አቅርቧል ሲል አመልክቷል።
" በመደበኛ የህግ ስርዓትን መሰረት አድርጎ ይህን ፈር የለቀቀ እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር አዳጋች ሁኔታ በመፈጠሩ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ " ሲል ምክር ቤቱ አሳውቋል።
በዚህም ፤ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6/2015 እንዲታወጅ በሙሉ ድምጽ ወስኗል።
@tikvahethiopia

#Update የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመጪው ረቡዕ፣ ሐሙስ እና ዓርብ ወደ ፦ - ደሴ (ኮምቦልቻ) - ጎንደር - ላሊበላ - ባህርዳር የሚደረጉ በረራዎች #የተሰረዙ መሆናቸውን አሳውቋል። ወደሥፍራው ለመጓዝ ትኬት የቆረጡ ደንበኞቹ ትኬታቸው ለአንድ (1) ዓመት ያህል የሚያገለግል መሆኑን አውቀው ወደፊት በፈለጉበት ቀን ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ መቀየር የሚችሉ መሆኑን ገልጿል። ነገር ግን ገንዘብ ተመላሽ…
#NewsAlert
ወደ ጎንደር እና ባህር ዳር በረራ ነገ ይጀምራል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ባህር ዳር እና ጎንደር ከተሞች በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረው መደበኛ በረራ ነገ ነሐሴ 4 ቀን 2015 ዓ.ም. የሚጀምር መሆኑን ዛሬ አሳውቋል።
መንገደኞች በአቅራቢያቸው በሚገኙት የአየር መንገዱ ሽያጭ ቢሮዎች ወይም ወደጥሪ ማዕከሉ የስልክ ቁጥሮች 6787 / +251116179900 በመደወል መስተናገድ እንደሚችሉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ገልጿል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከክልል በታች ያሉ መዋቅሮች እንዲደራጁ ለመወሰን የቀረበው ሞሽን በአብላጫ ድምፅ ፀደቀ።
ሁለት መዋቅሮች በዞን እና ሶስት መዋቅሮች በልዩ ወረዳነት እንዲደራጁ የቀረበውን ሞሽን ነው ምክር ቤቱ በአብላጫ ድምጽ የወሰነው።
በዚህም መሠረት :-
- የም ዞን
- ምስራቅ ጉራጌ ዞን
- ጠምባሮ ልዩ ወረዳ
- ቀቤና ልዩ ወረዳ
- ማረቆ ልዩ ወረዳ ሆነው የአስተዳደር መዋቅራቸው እንዲሻሻል በሞሽኑ ቀርቦ ፀድቋል።
የምክር ቤቱ ጉባኤም ተጠናቋል፡፡
መረጃው የደ/ሬ/ቴ/ድ ነው።

#NewsAlert በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከክልል በታች ያሉ መዋቅሮች እንዲደራጁ ለመወሰን የቀረበው ሞሽን በአብላጫ ድምፅ ፀደቀ። ሁለት መዋቅሮች በዞን እና ሶስት መዋቅሮች በልዩ ወረዳነት እንዲደራጁ የቀረበውን ሞሽን ነው ምክር ቤቱ በአብላጫ ድምጽ የወሰነው። በዚህም መሠረት :- - የም ዞን - ምስራቅ ጉራጌ ዞን - ጠምባሮ ልዩ ወረዳ - ቀቤና ልዩ ወረዳ - ማረቆ ልዩ ወረዳ ሆነው…
#NewsAlert
የደቡብ ኢትያጵያ ክልላዊ መንግስት አዲስ ዞን እና የወረዳ አስተዳደር መዋቅርን ለማደራጀት የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ አፅድቋል።
በዚህም መሰረት ፦
- የአማሮ ፣ የደራሼ ፣ የባስኬቶ፣ የቡርጂ፣ የአሌ ልዩ ወረዳዎች እያንዳንዳቸው እራሳቸውን ችለው #በዞን ይደራጃሉ።
- በኮንሶ ዞን የኮልሜ ወረዳ እንዲደራጅ ተወስኗል።
- የደቡብ ኦሞ ዞን በሁለት ዞን እንዲደራጅ ተወስኗል።
• ከደቡብ ኦሞ ዞን የማሌ፣ የሐመር፣ የበና ጸማይ ፣የሰላማጎ፣ የኛንጋቶም የዳሰነች ወረዳ እና የቱርሚ ከተማ አስተዳደር በጋራ #በዞን የሚደራጁ ይሆናል።
• ከደቡብ ኦሞ ዞን የደቡብ አሪ፣ የወባ አሪ የባካ ዳውላ ፣ የሰሜን አሪ ወረዳዎች እንዲሁም የጂንካ ከተማ አስተዳደር እና የገሊላ ከተማ አስተዳደር መዋቅሮች በጋራ ሆነው #በዞን ይደራጃሉ ተብሏል።
መረጃ የክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ ነው።

#Update በ5 ሃገሮች (ብራዚል ፣ ህንድ ፣ ቻይና ፣ ሩስያ ፣ ደቡብ አፍሪካ) የተመሠረተው የBRICS ቡድን መሪዎች ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ጉባኤያቸውን እያካሄዱ ይገኛሉ። በዚሁ የBRICS ጉባኤ ላይ ተካፋይ ለመሆን የአፍሪካ ሀገራት በተደረገላቸው ግብዣ ደቡብ አፍሪካ ይገኛሉ። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ለዚሁ ስብሰባ ደቡብ አፍሪካ የገቡ ሲሆን የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ…
#NewsAlert
ኢትዮጵያ ብሪክስን ለመቀላቀል ያቀረበችው ጥያቄ ተቀባይነት አገኘ።
በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ ያለው 15ኛው የብሪክስ አባል ሀገራት ጉባኤ ኢትዮጵያን ጨምሮ አርጀንቲና፣ ግብጽ፣ ኢራን፣ ሳዑዲ አረቢያን እና የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶችን በአዲስ አባልነት መቀበላቸውን ታውቋል።
BRICS በብራዚል፣ ሩስያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ቻይና፣ ህንድ ምጣኔኃብት ተኮር ሆኖ የተፈጠረው ቡድን ነው።
አሁን ላይ ይኸው ቡድን ወደ ጂዖ-ፖለቲካ ኃይልነት በመቀየር ‘ የምዕራባውያኑን ተፅዕኖ ለመገዳደር ያስችለናል ’ የሚለውን መፍትሄ ለማበጀት እንቅስቃሴ ላይ እንደሆነ እየተነገረ ነው።
ይህንን ቡድን ለመቀላቀል በርካታ ሀገራት ጥያቄ ሲያቀርቡ የነበረ ሲሆን ሀገራችን ኢትዮጵያም አንዷ ጠያቂ ነበረች። BRICSም ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎችን ሀገራት በይፋ ተቀብሏል።

#Amhara ለአንድ ቀን ይቆያል የተባለው የአማራ ክልል ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤ በባሕር ዳር እየተካሄደ ይገኛል። ጉባኤው በክልሉ ወቅታዊ የጸጥታ ችግሮች ዙሪያ እየመከረ ነው ተብሏል። የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኅላፊና የኮማንድፖስቱ አባል አቶ ደሳለኝ ጣሰው ለምክር ቤቱ ንግግር አሰምተዋል። በዚህም ንግግራቸው ፤ በክልሉ የተፈጠረው ወቅታዊ ግጭት " ድህረ ጦርነት የፈጠረው ልዩነት ነው " ብለዋል።…
#NewsAlert
የአማራ ክልል ፕሬዜዳንት ዶክተር ይልቃል ከፋለ የስልጣን መልቀቂያ ጥያቄ ማቅረባቸውና ምክር ቤቱም እንደተቀበላቸው ተነግሯል።
ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ፤ ለፖርቲያቸው ብልፅግና የመልቀቂያ ደብዳቤ ካስገቡ ከ8 ወራት በላይ እንደሆነ ገልጸው ፤ ወቅታዊ ሁኔታው እንዲቆዩ እንዳስገደዳቸው ጠቁመዋል፡፡
" በቀውስ ወቅት ወደ ሥልጣን መጥቶ በቀውስ ወቅት ኃላፊነትን መልቀቅ ህመሙን የማውቀው እኔ ብሆንም የምንችለውን ሁሉ ግን ሰጥቻለሁ ፤ጥያቄየንም ፓርቲዬ ተቀብሎኛል " ሲሉ ተናግረዋል።
የአማራ ክልል ምክር ቤትም የክልሉን ፕሬዜዳንት የስልጣን መልቀቂያ ጥያቄ መቀበሉ ተገልጿል።

#NewsAlert የአማራ ክልል ፕሬዜዳንት ዶክተር ይልቃል ከፋለ የስልጣን መልቀቂያ ጥያቄ ማቅረባቸውና ምክር ቤቱም እንደተቀበላቸው ተነግሯል። ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ፤ ለፖርቲያቸው ብልፅግና የመልቀቂያ ደብዳቤ ካስገቡ ከ8 ወራት በላይ እንደሆነ ገልጸው ፤ ወቅታዊ ሁኔታው እንዲቆዩ እንዳስገደዳቸው ጠቁመዋል፡፡ " በቀውስ ወቅት ወደ ሥልጣን መጥቶ በቀውስ ወቅት ኃላፊነትን መልቀቅ ህመሙን የማውቀው እኔ…
#NewsAlert
በአማራ ክልል አዲስ ፕሬዜዳንት ተሾመ።
ባለፉት ዓመታት በርካታ ፕሬዜዳንቶች የተፈራረቁበት አማራ ክልል ዛሬ አዲስ አስተዳዳሪ ተሹሞለታል።
አቶ አረጋ ከበደ የአማራ ክልል ፕሬዜዳንት ሆነው መሾማቸው ተገልጿል።
የአማራ ክልል ምክር ቤት በባህር ዳር እያካሄደ ባለው 6ኛ ዙር፤ 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን፤ 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ የቀድሞው ፕሬዜዳንት ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ያቀረቡትን የመልቀቂያ ጥያቄ ተቀብሎ በምትካቸው አቶ አረጋ ከበደን የክልሉ ፕሬዜዳንት በማድረግ ሹሟል፡፡
አቶ አረጋ ከበደ በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።
የት የት ስፍራዎች አገልግለዋል ? የትምህርት ደረጃቸውስ ?
- መጀመሪያ ዲግሪያቸውን በልማት አስተዳደር ሰርተዋል።
- የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ረዳት የህዝብ ተሳትፎ አማካሪ ነበሩ።
- የክልሉ ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ነበሩ።
- የክልሉን ሚሊሺያ ጽህፈት ቤት በኃላፊነት ለአንድ ዓመት መርተዋል።
- የክልሉ ቴክኒክ ሙያ እና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ኃላፊ ነበሩ።
- ወደ ክልል ኃላፊነት ከመምጣታቸው በፊት፤ የምስራቅ ጎጃም ዞንን በምክትል አስተዳዳሪ እና በዋና አስተዳዳሪነት መርተዋል።
- እስከ ዛሬ ድረስ የአማራ ክልል የስራ ፈጠራና ስልጠና ቢሮ ኃላፊ ነበሩ።
ፎቶ፦ AMC

#ኢትዮጵያ #ሶማሌላንድ በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ እና በሶማሌ ላንድ መካከል የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈርሟል። ይህ ስምምነት ኢትዮጵያ የባሕር በር የምታገኝበትን መንገድ ይጠርጋል ተብሏል። ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና የሶማሌላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ ታሪካዊ ነው የተባለውን የመግባቢያ ሠንድ በአዲስ አበባ ተፈራርመዋል፡፡ የኢፌዴሪ መንግሥት እና የሶማሌላንድ መንግሥት የፈረሙት የትብብር…
#NewsAlert የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና ፀጥታ ምክር ቤት ዛሬ ስብሰባ አካሂዶ ነበር።
በስበባውም ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል ያለውን ሁኔታ ተመልክታል።
ምክር ቤቱ ፤ እኤአ ጥር 1 በኢትዮጵያ እና ሰሜናዊ የሶማሊያ ክልል ሲል በጠራት " ሶማሌላንድ " መካከል የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ከተፈረመ በኃላ በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል የተፈጠረው ውጥረት በእጅጉ እንዳሳሰበው ገልጿል።
ሁኔታው በቀጠናው ሰላም፣ ፀጥታ እና መረጋጋት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል በሚልም ስጋት እንደገባው አመልክቷል።
ምክር ቤቱ ፦
➡ እኤአ ጥር 3/2024 የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሀመት የኢትዮጵያን እና የሶማሊያን ጨምሮ የሁሉም አባል ሀገራት አንድነት፣ የግዛት አንድነት እና ሉዓላዊነት ሊከበር እንደሚገባው አፅንኦት የሰጡበትን መግለጫ እንደሚደግፍ አሳውቋል።
➡ የኢትዮጵያ እና የሶማሊያን ጨምሮ የሁሉም አባል ሀገራት አንድነት፣ የግዛት አንድነት፣ ነፃነት እና ሉዓላዊነት መጠበቅ እንዳለበት ያለውን ጠንካራ ቁርጠኝነት እና ድጋፍ በማያሻማ መልኩ አረጋግጧል።
➡ ኢትዮጵያ እና የሶማሊያ የሁለትዮሽ እና የዓለም አቀፍ ግንኙነታቸውን የአፍሪካ ህብረት እና የዓለም አቀፍ ህግ መርሆዎችን ባከበረ መልኩ እንዲመሩ አሳስቧል።
➡ የውጭ አካላት በሁለቱ የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ አለመግባት የሚለውን መርህ እንዲያከብሩ አሳስቧል።
➡ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በመካከላቸው ያለውን ጠንካራ መልካም ጉርብትና፣ ወዳጅነት እና አብሮነት ትስስር ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ከሚያሳድሩ ተጨማሪ እርምጃዎች እና መግለጫዎች እንዲቆጠቡ አበረታቷል።
➡ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ በሚለው መርህ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ትርጉም ያለው ውይይት እንዲያደርጉ እና ውጥረቶችን እንዲያረግቡ ጥሪ አቅርቧል።
➡ ምክር ቤቱ የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል ውይይት እንዲያመቻቹና በየወቅቱ ለምክር ቤቱ መረጃዎችን እንዲያቀርቡ ብሏል።
➡ ኢጋድ በዩጋንዳ ካምፓላ ለነገ የጠራውን ልዩ የመሪዎች ስብሰባ በደስታ እንደተቀበለው ገልጿል።
ምክር ቤቱ ጉዳዩን በንቃት እንደሚከታተል አሳውቋል።

#Update አቶ ተመስገን ጥሩነህ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ። 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን በ15ኛ መደበኛ ስብሰባው የአቶ ተመስገን ጥሩነህን ሹመት አጽድቋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአቶ ተመስገንን የሥራ ልምድ ዘርዝረው ለምክር ቤቱ ባቀረቡት መሰረት ምክር ቤቱ በሙሉ ድምጽ ሹመቱን ማጽደቁን ብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ / etv ዘግቧል። …
#NewsAlert
አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ።
6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን በ15ኛ መደበኛ ስብሰባው አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ ሹመት አጽድቋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ የሥራ ልምድ ዘርዝረው ለምክር ቤቱ ባቀረቡት መሰረት ምክር ቤቱ በሙሉ ድምጽ ሹመቱን ማፅደቁን ብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ (etv) ዘግቧል።

ዶክተር መቅደስ ዳባ የጤና ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ።
6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን በ15ኛ መደበኛ ስብሰባው የዶክተር መቅደስ ዳባ ሹመትን አጽድቋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዶክተር መቅደስ ዳባን የሥራ ልምድ ዘርዝረው ለምክር ቤቱ ባቀረቡት መሰረት ምክር ቤቱ በሙሉ ድምጽ ሹመቱን ማፅደቁን ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ (etv) ዘግቧል።