TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.7K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ትላንት ለሊት አሜሪካ ሰኞ ሊደረግ ከታቀደው የሰላም ንግግር ጋር በተያያዘ መግለጫ አውጥታለች። በዚህ መግለጫ በኢትዮጵያ መንግስት እና በትግራይ ክልል ባለስልጣናት መካከል በአፍሪካ ህብረት መሪነት ሊደረግ የታቀደውን የሰላም ንግግር በደስታ እንደምትቀበለው ገልፃለች። አሜሪካ ፤ " ደቡብ አፍሪካ ውይይቱን ስላስተናገደች እናደንቃለን " ያለች ሲሆን የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ ተወካይ ኦሉሴጉን…
#USA

ትላንት ለሊት የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ መግለጫ ሰጥተው ነበር በዚህ መግለጫቸው ስለ ደቡብ አፍሪካድ የሰላም ንግግር አንስተው ነበር።

ምን አሉ ?

- የሰላም ንግግር 4 ጉዳዮችን ለማሳካት ያለመ ነው።
1ኛ. በአስቸኳይ ግጭት ማቆም፣
2ኛ. የሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ኢትዮጵያውያን በሙሉ ማቅረብ፣
3ኛ. የሰላማዊ ዜጎችን ደኅንነት ለማረጋገጥ ተጨማሪ እርምጃዎችን መውሰድ
4ኛ. #የኤርትራን_ጦር ከሰሜን ኢትዮጵያ ማስወጣት ነው።

- በደቡብ አፍሪካ እየተደረገ ያለው ንግግር በአራቱ ግቦች ላይ ልዩነቶችን ለማጥባብ ይረዳል።

- የፕሬዜዳንት ባይደን የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር በደቡብ አፍሪካው ንግግር ላይ እየተሳተፉ ነው። እሳቸው ‘ተሳታፊ እና ታዛቢ’ ሆነው ይቀጥላሉ።

- የሰላም ንግግሩ ሁለቱ የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት ልዩነቶቻቸውን ለማጥበብ እና 4ቱ ግቦች ላይ አዎንታዊ ለውጥ እንዲያመጡ ዕድል ይሰጣቸዋል።

- የውይይቱ መራዘም ተወያይ አካላት በመካከላቸው የተራራቀ አቋም ይዘው ደቡብ አፍሪካ ማቅናታቸውን ያመላክታል።

- የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት ውይይቱን መቀጠላቸው ለመነጋገር ያላቸውን ፍላጎት ያሳያል።

- ተቀምጦ ለመወያየት ፈቃደኛ ሆነው መቀጠላቸውን ልዩነታቸውን የሚነጋገሩበት እና በመካከላቸው ያለውን ርቀት ለማጥበብ የሚነጋገሩበት ይሆናል።

ምንጭ፦ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ

@tikvahethiopia