TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
#HappeningNow የሀሳብ ቅኝት የተሰኘው በሀሰተኛ መረጃ እንዲሁም የጥላቻ ንግግርን ለመግታት የሚደረጉ ጥረቶች ላይ ያተኮረው ልዩ የወጣቶች መድረክ በሸራተን አዲስ መካሄድ ጀምሯል። ዝግጅቱን ኦላይን መከታተል ለምትፈልጉ https://fb.watch/g3zmdGYwI6/ @tikvahethmagazine
#የሐሳብ_ቅኝቶች

የሐሳብ ቅኝቶች የተሰኘው የወጣቶች መርሐግብር የመጀመሪያ ቀን ዛሬ በአዲስ አበባ ሸራተን አዲስ ሆቴል ተካሂዷል።

በመድረኩ " ሀሰተኛ መረጃ እና የጥላቻ ንግግር " ን ለመግታት የሚደረጉ ጥረቶች ከተሳታፊዎች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

እንዲሁም ልዩ ልዩ መርሐግብሮች ተከናውነዋል።

በነገው ዕለት የዝግጅቱ ሁለተኛ ክፍል የሚቀጥል ሲሆን በዕለቱ ለመገኘት #ከተመዘገቡ በተጨማሪ #ላልተመዘገቡ ተሳታፊዎች ጭምር እንዲሳተፉ እድሉ ተመቻችቷል።

ነገ ከጠዋቱ 3:00 ላይ በ " ሸራተን አዲስ ሆቴል " በመገኘት መሳተፍ ትችላላችሁ። ዝግጅቱ ምንም አይነት መግቢያ የሌለው (ነፃ) መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን።

በተጨማሪም ለተሳታፊዎች የተሳትፎ " ሰርተፊኬት " በማጠቃለያው መርሐግብር የሚሰጥ ይሆናል።

@tikvahethiopia