TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለዶ/ር ዊሊያም ሩቶ በዓለ ሲመት ኬንያ ገብተዋል። አብረዋቸው የብሄራዊ ደህንነት አማካሪያቸው አምባሳደር ሬድዋን ሁሴንም አሉ። የኢጋድ ዋና ፀሀፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁም ለሩቶ በዓለ ሲመት ኬንያ ገብተዋል። ከዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተጨማሪ ፦ - የሶማሊያ ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ መሀመድ ፣ - የጅቡቲ ፕሬዜዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌ ፣…
#Update

#PresidentWilliamRuto

ተመራጩ ፕሬዜዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ የጎረቤታችን ኬንያ 5ኛው ፕሬዜዳንት ሆነው ቃለ መሃላ ፈፀሙ።

ከአሁን በኃላም ሩቶ የኬንያ ፕሬዜዳንት እየተባሉ የሚጠሩ ይሆናል።

ኡሁሩ ኬንያት ስልጣናቸውን ለዶ/ር ዊሊያም ሩቶ አስረክበዋል።

በአሁን ሰዓት ናይሮቢ ከተማ ውስጥ እየተካሄደ ባለው የሩቶ በዓለ ሲመት የኢትዮጵያ (ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ) ፣ የጅቡቲ፣ የሶማሊያ እና የሌሎችም ሀገራት መሪዎችና የተለያዩ ሀገራት መንግስታት እና የተቋማት ተወካዮች ተገኝተዋል።

ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ብዙም ተጠናክሮ ባልዳበረበት አህጉራችን አፍሪካ ኬንያ እያካሄደች ያለችው የዴሞክራሲ ግንባታ ለብዙ ሀገራት ምሳሌ እንደሚሆን በማንሳት በበርካቶች ዘንድ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል።

Video Credit : NTV KENYA

@tikvahethiopia