TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለዶ/ር ዊሊያም ሩቶ በዓለ ሲመት ኬንያ ገብተዋል። አብረዋቸው የብሄራዊ ደህንነት አማካሪያቸው አምባሳደር ሬድዋን ሁሴንም አሉ። የኢጋድ ዋና ፀሀፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁም ለሩቶ በዓለ ሲመት ኬንያ ገብተዋል። ከዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተጨማሪ ፦ - የሶማሊያ ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ መሀመድ ፣ - የጅቡቲ ፕሬዜዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌ ፣…
#Update
#PresidentWilliamRuto
ተመራጩ ፕሬዜዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ የጎረቤታችን ኬንያ 5ኛው ፕሬዜዳንት ሆነው ቃለ መሃላ ፈፀሙ።
ከአሁን በኃላም ሩቶ የኬንያ ፕሬዜዳንት እየተባሉ የሚጠሩ ይሆናል።
ኡሁሩ ኬንያት ስልጣናቸውን ለዶ/ር ዊሊያም ሩቶ አስረክበዋል።
በአሁን ሰዓት ናይሮቢ ከተማ ውስጥ እየተካሄደ ባለው የሩቶ በዓለ ሲመት የኢትዮጵያ (ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ) ፣ የጅቡቲ፣ የሶማሊያ እና የሌሎችም ሀገራት መሪዎችና የተለያዩ ሀገራት መንግስታት እና የተቋማት ተወካዮች ተገኝተዋል።
ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ብዙም ተጠናክሮ ባልዳበረበት አህጉራችን አፍሪካ ኬንያ እያካሄደች ያለችው የዴሞክራሲ ግንባታ ለብዙ ሀገራት ምሳሌ እንደሚሆን በማንሳት በበርካቶች ዘንድ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል።
Video Credit : NTV KENYA
@tikvahethiopia

#Update #PresidentWilliamRuto ተመራጩ ፕሬዜዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ የጎረቤታችን ኬንያ 5ኛው ፕሬዜዳንት ሆነው ቃለ መሃላ ፈፀሙ። ከአሁን በኃላም ሩቶ የኬንያ ፕሬዜዳንት እየተባሉ የሚጠሩ ይሆናል። ኡሁሩ ኬንያት ስልጣናቸውን ለዶ/ር ዊሊያም ሩቶ አስረክበዋል። በአሁን ሰዓት ናይሮቢ ከተማ ውስጥ እየተካሄደ ባለው የሩቶ በዓለ ሲመት የኢትዮጵያ (ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ) ፣ የጅቡቲ፣…
ፎቶ : በዛሬው የዶ/ር ዊሊያም ሩቶ በዓለ ሲመት ላይ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የሌሎችም ሀገራት መሪዎች እና የመንግስታትና የተቋማት ተወካዮች ተገኝተው ነበር።
@tikvahethiopia
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
ፕሬዜዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ ስለ #ኢትዮጵያ እና ታላላቅ ሀይቆች ቀጠና ምን አሉ ?
ዛሬ ቃለ መሀላ የፈፀሙት የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ባደረጉት ንግግር በኢትዮጵያ ሰላም ለማምጣት በሚደረገው ጥረት የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የሚያከናውኑትን ተግባር እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።
ሩቶ ፤ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በኢትዮጵያ እና በታላላቅ ሐይቆች ቀጠና (ግሬት ሌክስ) ሰላም ለማምጣት የሚያስመሰግን ተግባር አከናውነዋል ያሉ ሲሆን " በኢትዮጵያ እና በታላለቅ ሐይቆች ቀጠና የተጀመሩ የሰላም ጥረቶች ለማጠናከር ቁርጠኛ ነኝ " ሲሉ ተደምጠዋል።
የቀድሞው ፕሬዝዳንት የጀመሩትን ሰላም የማምጣት ጥረት ለመቀጠል ተስማምተዋል ሲሉም ተናግረዋል።
የቀድሞው ፕሬዜዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ወዲህ ሰላማዊ መፍትሄ በመፈለግ ረገድ ጥረት እያደረጉ ስለመሆኑ በተደጋጋሚ ስማቸው ሲነሳ ቆይቷል ፤ በሌላ በኩል ዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ፣ ቡሩንዲ፣ ሩዋንዳ እና ኡጋንዳን በሚያጠቃልለው የታላላቅ ሐይቆች ቀጠና ላለው የደኅንነት እና የፀጥታ ችግር መፍትሔ በማፈላለግ ሲሳተፉ ቆይተዋል።
ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ በዛሬው ንግግራቸው " የቀድሞ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በጀመሩት የሰላም ጥረት ለመቀጠል ፈቃደኛ መሆናቸውን እንዳረጋገጡላቸው አመልክተው የኬንያ ሕዝብን በመወከል የሰላም ንግግሮችን ለመምራት ተስማምተዋል ሲሉ አሳውቀዋል።
ፕሬዜዳንት ሩቶ፤ ኬንያታ ሊረዱን እና ሊደግፉኝ ፍቃደኛ ስለሆኑ አመስግንዎታለሁ ሲሉም ምስጋና ማቅረባቸውን ቢቢሲ አስነብቧል።

ቪድዮ : ድብድብ በኬንያ 🇰🇪 ፓርላማ ! ዛሬ ከሰአት #በኬንያ የፓርላማ አባላት አወዛጋቢ ነው በተባለው የፖለቲካ ፓርቲዎች (ማሻሻያ) ረቂቅ ህግ ላይ ሲያደርጉት የነበረው ጠንከር ያለ ክርክር ተካሮ የፓርላማው አባላት ሲደባደቡ ታይተዋል። ከሰሞኑን ብቻ ፓርላማ ውስጥ የተከሰቱ መሰል ክስተቶችን ስናጋራችሁ ይህ ለሶስተኛ ጊዜ ሲሆን ዛሬ ጥዋት የጆርንዳን ፓርላማ አባላት እንዲሁም ከቀናት በፊት በጋና የፓርላማ…
ቪድዮ : የሴኔጋል ፓርላማ አባላት እርስበርሳቸው ተደባደቡ።
ከአንድ ወር በፊት በሀገሪቱ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ ተካሂዶ ነበር ፤ በዚህ ምርጫ ገዥው ፓርቲ አብዛኛውን መቀመጫ በተቃዋሚ ፓርቲዎች የተነጠቀ ሲሆን ተመራጭ የሆኑ የምክር ቤት አባላት ትላንት ስራቸው ጀምረዋል።
አባላቱ በስብሰባቸው የም/ቤቱን ተጠሪ ፕሬዝዳንት መምረጥ የነበረባቸው ቢሆንም ወደ ስምምነት መምጣት አቅቷቸው ከፍተኛ አለመግባባት ውስጥ ገብተው ነበር። በተፈጠረው አለመግባባትም ወንበር እና የውሀ መያዣ ፕላስቲኮች በመወራወር እርስ በርስ እንደተደባደቡ ተገልጿል።
ይህን ተከትሎም ሁኔታውን ለመቆጣጠር እና የድምፅ አሰጣጡን ደህንነት ለማስጠበቅ የሀገሪቱ ፖሊስ ተጠርቶ ወደ ምክር ቤቱ ገብቷል ፤ የምርጫ ኮሮጆውን በኃይል ለመውሰድ የሞከሩ የም/ቤቱ የህግ አውጪዎች በፖሊስ በኃይል ከምክር ቤቱ እንዲወጡ መደረጉን ሮይተርስ ዘግቧል።
መረጃው ከሮይተርስ፣ ሲጂቲኤን እና አል አይን የተሰባሰበ ነው።
Video Credit : RTS

#UPDATE የደሴ ከተማ የፀጥታ ምክር ቤት ተጨማሪ ውሳኔዎች አሳለፈ። ምክር ቤቱ ነሀሴ 22/2014 ዓ.ም በከተማው ልዩ ልዩ ክልከላዎችን በማስቀመጥ የተቀመጡ ህጎችን እያስተገበረ የሚገኝ ሲሆን ዛሬ ተጨማሪ ክልከላዎች አሳልፏል። ክልከላዎቹ ከነሀሴ 30/2014 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆኑ ናቸው። ነዋሪዎች ተባባሪ እንዲሆኑም ተጠይቋል። ከክልከላዎቹ መካከል ፦ - የሀገር መከላከያ አባል ሳይሆን…
#Update
ደሴ !
በደሴ ከተማ በተላለፉ ክልከላዎች ላይ መጠነኛ የሰዓት ማሻሻያ ተደርጓል።
የደሴ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት መስከረም 3/2015 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተለያዩ የውሳኔ ማስተካከያ አድርጓል።
በዚህም ከነገ መስከረም 4/2015 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን መጠነኛ የሰዓት ማሻሻያ የሚከተለው ነው ፦
1. ሆቴሎች፣ መጠጥ ቤቶች እንዲሁም የንግድ ቤቶች አገልግሎታቸውን እስከ ምሽቱ ሁለት 2:30 ድረስ መስጠት ይችላሉ።
እንደአስፈላጊነቱ ለፀጥታ ስጋት የሚሆኑ እንቅስቃሴዎችን ካስተዋሉ ቀድመው ለፀጥታ አካላት በመደወል ጥሪ ማድረግ አለባቸው።
2. በከተማው ውስጥ ስምሪት ያላቸው ተሽከርካሪዎችን ብቻ የሚመለከት ሆኖ ባጃጅ እስከ ምሽቱ 2:00 መስራት ይችላሉ። ታክሲዎችና ሌሎች ተሺከርካሪዎች እስከ ምሽቱ 3:00 ድረስ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ተወስኗል።
ሌሎች ከዚህ በፊት የወጡ ገደቦች እንደተጠበቁ ናቸው።
እነዚህን ተላልፎ የተገኘ አካል ላይ ፀጥታ ኃይሉ ተቆጣጥሮ እርምጃ እንደሚወስድ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል።

* ብሔራዊ ፈተና የ2014 ዓ/ም 12ኛ ክፍል ፈተናን በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው። በዚህም መሰረት ዩኒቨርሲቲዎች በአካዳሚክ ካላንደራቸው ላይ ማስተካከያ እያደረጉ ይገኛሉ። ይህ እየተደረገ ያለው ተማሪዎች ፈተናቸውን በሚወስዱበት ወቅት በቅጥር ግቢዎቹ ውስጥ ማንኛውም የዩኒቨርሲቲ ተማሪ መገኘት ስለሌለበት ነው። በሌላ በኩል ፤ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት #ለሪፖርተር_ጋዜጣ…
" በአዲስ አበባ 49,203 ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ ተመዝግበዋል " - የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ቅድመ ዝግጅት ዙሪያ ፈተናው ከሚሰጥባቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራሮች ጋር ውይይት አካሂዷል።
ዘንድሮ ፈተናው በሀገር አቀፍ ደረጃ ከመስከረም 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንደሚሰጥ ቀደም ብሎ በትምህርት ሚኒስቴር የተገለጸ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ፈተናውን ፦
- አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፤
- ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፤
- ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ
- አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ ተገልጻል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ዘንድሮ ፈተናው ለመጀመሪያ ጊዜ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚሰጥ እንደመሆኑ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የፈተና ሂደቱ በስኬት እንዲጠናቀቅ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ፈተናው የተማሪዎችን የቀጣይ የህይወት ምዕራፍ የሚወስን በመሆኑ በአዲስ አበባ ፈተናው የሚሰጥባቸው ተቋማትም ሆኑ ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል፡፡
በአዲስ አበባ 49,203 ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ መመዝገባቸውንና ፈተናውም ከመስከረም 30 ጀምሮ በቅድሚያ የሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች ተፈትነው ሲጨርሱ የናቹራል ሳይንስ ተማሪዎች ቀጥለው እንደሚፈተኑ የተገለጸ ሲሆን ተፈታኝ ተማሪዎች በፈተና ወቅት የምግብና የመኝታ አገልግሎቶችን በየተቋማቱ እንደሚያገኙም ተጠቁማል፡፡
(የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ)

#AddisAbaba
" ከቤት ውጣ ብላኛለች " በሚል ምክንያት ሴት አያቱን የገደለው ተከሳሽ በ16 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት በፅኑ እስራት ተቀጣ።
ተከሳሽ ሮቤል ቴዎድሮስ የወንጀል ድርጊቱን የፈፀመው ነሃሴ 26 ቀን 2012 ዓ/ም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ቦታው ቀጠና 5 ወጣት ማዕከል አካባቢ ነው፡፡
ተከሳሽ ሮቤል ቴዎድሮስ የ79 ዓመት ዕድሜ ካላቸው ከአባቱ እናት ጋር ይኖር የነበረ ሲሆን " ከቤት ውጣ ብላኛለች " በሚል ምክንያት ከምሽቱ 2፡30 ሰዓት ላይ አያቱን በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ጭንቅላታቸውን በመዶሻ ደጋግሞ በመምታት ህይወታቸው እንዲያልፍ ማድረጉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል።
ፖሊስ ክስ ለመመስረት የሚያስችሉ ልዩ ልዩ የቴክኒክና የታክቲክ ማስረጃዎችን በማሰባሰብ የምርመራ መዝገቡን ለአቃቢ ህግ ልኮ ክስ እንዲመሰረትበት አድርጓል፡፡
የተከሳሽ ሮቤል ቴዎድሮስን ጉዳይ ሲመለከት የቆየው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ ከባድ ውንብድና እና ግድያ ወንጀል ችሎት ግለሰቡ ጥፋተኛ መሆኑን በማረጋገጡ በ16 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
(አዲስ አበባ ፖሊስ)

#ATTENTION ወልድያ ! በዛሬው ዕለት የወልድያ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ም/ ቤት ከዚህ ቀደም ካሳለፈው ውሳኔ ተጨማሪ ውሳኔዎችን አሳልፏል። የከተማውን አሁናዊ ሁኔታ መነሻ ከተማ በማድረግ የሰዓት እላፊ ገደብ መውጣቱ የሚታወቅ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ሌሎች ክልከላዎችን ማስቀመጥ አስፈልጓል ተብሏል። ከተላለፉ ውሳኔዎች መካከል ፦ - ከፀጥታ መዋቅሩ ውጭ በየትኛውም ቦታ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ…
#Update
ወልድያ !
የወልድያ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት የሰዓት እላፊ ገደብ ላይ የማሻሻያ ውሳኔ ዛሬ መስከረም 4 ቀን 2015 ዓ/ም አሳልፏል።
ሌሎች ክልከላዎች እንደቀጠሉ ሆኖ በሰዓት እላፊ ገደብ ላይ የተደረገው ማሻሻያ ፦
- ከቀኑ 12:00 ሰዓት ጀምሮ የነበረው የተሽከርካሪ የሰዓት እላፊ ወደ ምሽቱ 1:00 ሰዓት፤
- ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ የነበረው የሰዎች እንቅስቃሴ የሰዓት እላፊ ገደብ ወደ ምሽቱ 2:00 ሰዓት ድረስ ተራዝሟል።