TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#RecepTayyipErdoğan
#AmbassadorAdemMohammed

በቱርክ የኢትዮጵያ አምባሳደር አደም መሃመድ የሹመት ደብዳቤያቸውን በአንካራ ቤተመንግሥት ለቱርክ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን አቅርበዋል።

ፕሬዝዳንት ጣይብ ኤርዶጋን በስነስርዓቱ ላይ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ላላት ግንኙነት ትልቅ ቦታ እንደምትሰጥ ገልፀዋል።

ሁለቱ አገራት ትብብራቸውን ወደ ከፍተኛ ደረጃ ለማድረስ በመካከላቸው ያለውን ሰፊ ኢኮኖሚያዊ፣ባህላዊና ዲፕሎማሲያዊ ዕድሎች መጠቀም እንዳለባቸው አሳስበዋል።

አምባሳደር አደም መሃመድ በበኩላቸው በኢትዮጵያ እና በቱርክ መካከል ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት በመጥቀስ በሀገራቱ መካከል ያለውን የላቀ አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከር ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል።

መረጃው በአንካራ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ነው።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia