TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#update ኢህአዴግ የደርግ መሰል #የቤት_ልማት_ፖሊስ ተግባራዊ ሊያደርግ ነው ተብሏል። በሀዋሳ በተደረገው የድርጅቱ 11ኛ ጉባኤ ላይ በቀረበው ሰነድ መሰረት #የመጠለያ ችግርን ከመቅረፍ አንፃር መሬት እና ፋይናንስ በማቅረብ ዜጎች ቤታቸውን #በራሳቸው ገንብተው የቤት ባለቤት የሚሆኑበት አሰራር ተግባራዊ ይደረጋል። መንግስት ቤት በራሱ ገንብቶ ለህብረተሰቡ ተደራሽ አደርጋለሁ ሲል ቢቆይም ከፍላጎት አንፃር መሄድ ያልቻለ እና #በሙስና እና #ብልሹ አሰራር የተተበተበ መሆኑ ሲያስተቸው መቆየቱ አይዘነጋም። በአዲሱ እቅድ መሬት እና ብድር ተመቻችቶ ቤት ፈላጊዎች በራሳቸው ይገነባሉ። ይህ አሠራር ደርግ እስከ መውደቂያው እለት ሲተገብረው የነበረ እና በርካቶችን እንዳ አቅማቸው የቤት ባለቤት እንዲሆኑ ያደረገበት ፖሊሲ እንደነበር ይታወሳል።

ምንጭ፦Muluken Yewondwossen,ENF
@tsegabwolde @tikvahethiopia