TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#እንድታውቁት

#የታለመለት_የነዳጅ_ድጎማ

ኢትዮ ቴሌኮም በሂደት ላይ የሚገኘውን የታለመለት የነዳጅ ድጎማ በቴክኖሎጂ በማገዝ ተግባራዊ ለማድረግ ከትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ጋር በጋራ እየሠራ እንደሚገኝ ገልጿል።

በዚህም መሠረት በድጎማው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለተለዩ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪ ባለንብረቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎች አገልግሎቱ የሚሰጠው #በቴሌብር አማካኝነት መሆኑን ድርጅቱ ገልጿል።

በኢትዮ ቴሌኮም የሸያጭ ማዕከላት ዋና ወይም ቅጂ #ሊብሬ እንዲሁም #የታደሰ_መታወቂያ በመያዝ የተሸከርካሪውን ባለቤት የስልክ ቁጥር በማሳወቅ የቴሌብር አገልግሎት ምዝገባ ከወዲሁ እንዲያከናውኑ እንዲሁም ተጨማሪ መረጃዎችን እንዲያሟሉ ተጠይቋል።

@tikvahethiopia