TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.52K videos
215 files
4.13K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#Update

የፊንላንድ መሪዎች ሀገራቸው NATOን መቀላቀል እንደምትፈልግ በይፋ አስታውቀዋል።

የፊንላንድ ፕሬዚዳንት ሳውሊ ኒኒስቶ ከካቢኔያቸው ጋር ስብሰባ አድርገው ነበር።

በዚህ ስበስባ ላይ ፊንላንድ የNATO አባል ለመሆን በምታቀርበው የአባልነት ጥያቄ ላይ ስምምነት ላይ ተደርሷል።

ይህን የካቤኒ ስምምነት ተከትሎም የአባልነት ጥያቄው ለመጽደቅ የፓርላማ ይሁንታ ማግኘት ይኖርበታል ተብሏል።

የፊንላንድ ጠ/ሚ ሳና ማሪን ውሳኔውን " ታሪካዊ ነው " ያሉ ሲሆን " ዋናው ነገር የፊንላንድና የህዝቦቿ ደህንነት ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

ውሳኔው የኖርዲክ አካባቢ ሃገራትን ፀጥታና ትብብር ያጠናክራልም ብለዋል።

የሃገሪቱ ፓርላማ የአባልነት ጥያቄውን ያጸድቀዋል ብለው እንደሚጠብቁ ገልፀዋል።

ሩስያ ከሰሞኑን የፊንላንድ የNATO አባል የመሆን ፅኑ ፍላጎትን ተከትሎ ማስጠንቀቂያዎችን እየሰጠች ትገኛለች።

ሀገሪቱ የNATO አባል ከሆነች ወታደራዊን ጨምሮ ሌሎች እርምጃዎችን ልትወስድ እንደምትችል ዝታለች።

በሌላ በኩል የሩስያ ፕሬዜዳንት ቭላድሚር ፑቲን ፊንላንድ የNATP አባል ለመሆን የምታደርገውን ጥረት እንድታቆምና ገለልተኛ መሆኗን ማቆሟ ትልቅ ስህተት እንደሚሆን አስጠቅቀዋል።

ለፊንላንዱ ፕሬዝዳንት ሳኡሊ ኒኒስቶ ባስተላላፉት መልዕክት ለፊንላንድ ደህንነት ምንም የሚያሰጋት ነገር እንደሌለና የNATO አባል መሆን እንደማይጠበቅባት ገልጸዋል።

ሩስያ በአሁን ሰዓት ከዩክሬን ጋር በጦርነት ውስጥ የምትገኘው ሀገሪቱ የNATO አባል የመሆን ፍላጎት ማሳየቷን ተከትሎ እንደሆነ ይታወቃል።

መረጃው የRT እና ቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Somalia ጎረቤታችን ሶማሊያ ነገ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ታካሂዳለች። ይህን ተከትሎ የሶማሊያ ፖሊስ ምርጫ እስኪጠናቀቅ በዋና ከተማዋ ሞቃዲሾ በጸጥታ ሥጋት ሳቢያ ከአስቸኳይ አገልግሎቶች ውጪ ሁሉንም ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች የሚያግድ የሰዓት ዕላፊ ተግባራዊ አድርጓል። የታወጀው ሰዓት እላፊ ከዛሬ ምሽት 3 ሰዓት እስከ ሰኞ ጧት ድረስ የሚቆይ ነው ተብሏል። ነገ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት የሚመርጠው የታችኛው…
ፎቶ ፦ በጎረቤታችን ሶማሊያ ቀጣዩ የሀገሪቱ ፕሬዜዳንት የሚታወቅበት ምርጫ እየተካሄደ ይገኛል።

በአሁን ሰዓት የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ እየተካሄደ ነው።

ይህ የዛሬው ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ለ6ኛ ጊዜ የሚካሄድ ሲሆን ረጅም ጊዜ ሲጠበቅ ነበር። ቀጥተኛ ባልሆነው በዚህ ምርጫ ላይ 30 በላይ እጩዎች እየተወዳደሩ ይገኛሉ።

@tikvahethiopia
#ውበት

ውፍረትን እና ቦርጭን መቀነስ ይፈልጋሉ?
0911607446
ያሉበት ድረስ ከነፃ ማድረሻ ጋር!              
ሙሉ ከወገብ በላይ(ቦዲ) - 950ብር
የቦርጭ ብቻ(ጉርድ) -650  ብር

ቦርጭን በአጭር ጊዜ የሚቀንስ እና
ማራኪ-ቁመና የሚያላብስ ።

ተጨማሪ : የቴሌግራም አድራሻችን ይጎብኙ @wibet1
( ክልል ከተሞች እንገኛለን ) @አ.አ = ቦሌ ቤዛ ህንፃ 2nd floor # webet
#Kombolcha

#ሙሉ_በሙሉ የግንባታ ወጭው በውጭ ሀገራት በሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዳያስፖራዎች የሚሸፈን መልቲ ጀነራል ሆስፒታል የመሰረት ድንጋይ የቀመጠ።

ሆስፒታሉ በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ኮምቦልቻ ወረዳ የሚገነባ ሲሆን ከ300 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ይሆንበታል ተብሏል።

ፕሮጀክቱ በ1 ነጥብ 6 ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፍ ሲሆን ወጪው ሙሉ በሙሉ በውጭ ሀገራት በሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሚሸፈን ነው።

በወረዳው ለሚገነባው ሆስፒታል የሐረማያ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ጀማል ዪስፍ፣ የኮምቦልቻ ወረዳ አስተዳደር አቶ አልዪ ኢብራሂም እና የዲያስፖራ ተወካይ አቶ ፈረሃን አህመድ የመሰረት ድንጋዩን አስቀምጠዋል።

#ENA

@tikvahethiopia
#Somali #Afar

በሶማሌ እና አፋር ክልል አዋሳኝ ቀበሌዎች የሚከሰቱ ግጭቶችን በዘላቂነት መፍታት እንዲቻል 2ቱ ክልሎች ከስምምነት መድረሳቸውን አስታወቁ።

ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት ያስችላል የተባለው መሠረታዊ ስምምነት የታጠቁ ኃይሎች ከግጭት አካባቢዎች እንዲወጡ እና የፌደራል ፀጥታ ኃይሎች ወደነዚህ ቦታዎች እንዲገቡ የሚፈቅድ መሆኑን የሶማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ዑስማን መናገራቸውን የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።

በአዋሳኝ ቀበሌዎች በየቦታው ተኩስ ፣ ስርቆት እና መፈናቀል ይከሰቱ እንደነበር የተናገሩት አቶ ኢብራሂም ዘላቂ ሰላም ለማምጣትም የተፈናቀሉ ሰዎችን ወደቀያቸው መመለስ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

አቶ ኢብራሂም « ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ችግር እንዳይከሰት፣… ዘላቂ የሆነ ሰላም እንዲመጣ እና ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ሚና መሆን እንዳለበትም ነው ትናንት ከስምምነት ላይ የደረስነው።» ብለዋል።

የሶማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ዑስማን ማሣረጊያ እንዲሆን የሁለቱ ክልሎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ኮንፈረንስ እንደሚያካሂዱም ተናግረዋል።

በሶማሌ ክልል መቀመጫ ጅግጅጋ በተካሄደው ውይይት የሰላም ሚንስትሩ አቶ ብናልፍ አንዱአለም ጨምሮ የአፋር እና የሶማሌ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት ተገኝተው እንደነበር ሬድዮ ጣቢያው ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ በጎረቤታችን ሶማሊያ ቀጣዩ የሀገሪቱ ፕሬዜዳንት የሚታወቅበት ምርጫ እየተካሄደ ይገኛል። በአሁን ሰዓት የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ እየተካሄደ ነው። ይህ የዛሬው ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ለ6ኛ ጊዜ የሚካሄድ ሲሆን ረጅም ጊዜ ሲጠበቅ ነበር። ቀጥተኛ ባልሆነው በዚህ ምርጫ ላይ 30 በላይ እጩዎች እየተወዳደሩ ይገኛሉ። @tikvahethiopia
#Update

የጎረቤት ሀገር ሶማሊያ ምርጫ ፦

የመጀመሪያው ዙር ውጤት :

👉 ሰዒድ አብዱላሂ ዴኒ ➡️ 65
👉 ሞሀመድ አብዱላሂ ፈርማጆ ➡️ 59
👉 ሀሰን ሼክ ሞሐመድ ➡️ 52
👉 ሀሰን አሊ ኻይሬ ➡️ 47

⬇️

👉 ሸሪፍ ሼክ አህመድ ➡️ 39
👉 አብዲራህማን ዋርሳሜ ➡️ 15
👉 አብዱልቃድር ኦሶብል ➡️ 12
👉 አዶው አሊ ጊስ ➡️ 8


328 የፓርላማ አባላት ድምጽ የሰጡ ሲሆን 4 ከፍተኛ ድምፅ ያገኙ ወደ 2ኛው ዙር አልፈዋል።

በአሁን ሰዓት የሁለተኛ ዙር ድምፅ አሰጣጥ እየተካሄደ ይገኛል።

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ሀሩን ማሩፍ (ቪኦኤ)

@tikvahethiopia
" አሽከርካሪዎች የሚያሽከረክሩትን የመኪና አቅምና በወንበር ልክ ጭነው በማሽከርከር የህብረተሰቡን ህይወት መጠበቅ ይገባቸዋል " - ፖሊስ

ዛሬ ጥዋት 2 ሰዓት ላይ በቦረና ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ6 ሠዎች ህይወት ማለፉ ተሰምቷል።

በደቡብ ወሎ ዞን በቦረና ወረዳ 019 ቀበሌ " መንደዩ " ከተባለው ቦታ መነሻውን መካነ-ሠላም አድርጎ ወደ መርጦለማሪያም ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ ተሽከርካሪ በደረሠበት የመገልበጥ አደጋ አሽከርካሪውን ጨምሮ የ6 ሠዎች ህይወት ሲያልፍ 9 ሰዎች ከባድ የአካል ጉዳትና የ11 ሠዎች ቀላል የአካል ጉዳት መከሰቱን የቦረና ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት አስታውቋል።

ፖሊስ እንደገለፀው አደጋው የደረሰበት ኮድ 3 ታርጋ ቁጥር 18872 አ.ማ የሆነ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ሲሆን ከጠዋቱ በግምት 2:00 ሰዓት ሲሆን 26 ተሳፊሪዎችን ጭኖ ከ75 ሜትር ገደል ገብቷል።

እንደ ፖሊስ መረጃ መኪናው ከአቅም በላይ መጫኑ ነው የተገለፀው።

ፖሊስ አሽከርካሪዎች የሚያሽከረክሩትን የመኪና አቅምና በወንበር ልክ ጭነው በማሽከርከር የህብረተሰቡን ህይወት መጠበቅ ይገባቸዋል ብሏል።

መረጀው የወረዳው መንግስት ኮሙንኬሽን አገልግሎት ፅ/ቤት ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የጎረቤት ሀገር ሶማሊያ ምርጫ ፦ የመጀመሪያው ዙር ውጤት : 👉 ሰዒድ አብዱላሂ ዴኒ ➡️ 65 👉 ሞሀመድ አብዱላሂ ፈርማጆ ➡️ 59 👉 ሀሰን ሼክ ሞሐመድ ➡️ 52 👉 ሀሰን አሊ ኻይሬ ➡️ 47 ⬇️ 👉 ሸሪፍ ሼክ አህመድ ➡️ 39 👉 አብዲራህማን ዋርሳሜ ➡️ 15 👉 አብዱልቃድር ኦሶብል ➡️ 12 👉 አዶው አሊ ጊስ ➡️ 8 328 የፓርላማ አባላት ድምጽ የሰጡ ሲሆን 4 ከፍተኛ…
#Update

በጎረቤታችን ሶማሊያ እየተካሄደ በሚገኘው ምርጫ የ2ኛው ዙር ድምፅ አሰጣጥ ሂደት አብቅቷል ፤ ይህን ተከትሎ የድምጽ ቆጠራው ይካሄዳል።

#ማስታወሻ ፦ የመጀመሪያው ዙር ውጤት ፦

👉 ሰዒድ አብዱላሂ ዴኒ ➡️ 65
👉 ሞሀመድ አብዱላሂ ፈርማጆ ➡️ 59
👉 ሀሰን ሼክ ሞሐመድ ➡️ 52
👉 ሀሰን አሊ ኻይሬ ➡️ 47

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በጎረቤታችን ሶማሊያ እየተካሄደ በሚገኘው ምርጫ የ2ኛው ዙር ድምፅ አሰጣጥ ሂደት አብቅቷል ፤ ይህን ተከትሎ የድምጽ ቆጠራው ይካሄዳል። #ማስታወሻ ፦ የመጀመሪያው ዙር ውጤት ፦ 👉 ሰዒድ አብዱላሂ ዴኒ ➡️ 65 👉 ሞሀመድ አብዱላሂ ፈርማጆ ➡️ 59 👉 ሀሰን ሼክ ሞሐመድ ➡️ 52 👉 ሀሰን አሊ ኻይሬ ➡️ 47 @tikvahethiopia
#ሶማሊያ

እጅግ ከባድ ፉክክር እየታየበት በሚገኘው የሶማሊያ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ የሁለተኛው ዙር ድምፅ አሰጣጥ ተጠናቆ የድምፅ ቆጠራው እየተካሄደ ይገኛል።

የ2ኛው ዙር የምርጫ ውጤትን እንዲሁም አጠቃላይ የምርጫውን ሂደት ከሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን እየተከታተል እንልክላችኃለን።

ቀጣዩ የጎረቤታችን ሶማሊያ ፕሬዜዳንት ማን ይሆን ? አብረን የምናየው ይሆናል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሶማሊያ እጅግ ከባድ ፉክክር እየታየበት በሚገኘው የሶማሊያ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ የሁለተኛው ዙር ድምፅ አሰጣጥ ተጠናቆ የድምፅ ቆጠራው እየተካሄደ ይገኛል። የ2ኛው ዙር የምርጫ ውጤትን እንዲሁም አጠቃላይ የምርጫውን ሂደት ከሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን እየተከታተል እንልክላችኃለን። ቀጣዩ የጎረቤታችን ሶማሊያ ፕሬዜዳንት ማን ይሆን ? አብረን የምናየው ይሆናል። @tikvahethiopia
#Update

የሶማሊያ ምርጫ ሁለተኛው ዙር ውጤት ፦

በሁለተኛው ዙር የቀድሞ ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐመድ አንደኛ አሁን ሶማሊያን በፕሬዜዳንትነት እየመሩ ያሉት ሞሀመድ አብዱላሂ ፈርማጆ ሁለተኛ ሆነው አጠናቀዋል።

እንዲሁም ሰዒድ አብዱላሂ ዴኒ ሶስተኛ ፤ ሀሰን አሊ ኻይሬ አራተኛ ሆነው የ2ኛውን ዙር የምርጫ ፉክክር አጠናቀዋል።

የምርጫው ውጤት በቁጥር ፦

👉 ሀሰን ሼክ ሞሐመድ ➡️ 110

👉 ሞሀመድ አብዱላሂ ፈርማጆ ➡️ 83

👉 ሰዒድ አብዱላሂ ዴኒ ➡️ 68

👉 ሀሰን አሊ ኻይሬ ➡️ 63

በፋርማጆ እና ሀሰን ሼክ መካከል ሶስተኛውና የመጨረሻው ዙር የፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ፉክክር ይካሄዳል።

የምርጫውን ሂደት ተከታትለን እናሳውቃለን።

@tikvahethiopia