#AddisAbaba
" ከሁለትና ሶስት ወር በላይ ውል አልታደሰልንም፤ ተገቢውም ክፍያ አልተከፈለንም " ያሉ በአዲስ አበባ የሸገር ድጋፍ ሰጪ አውቶብሶች ስራ ካቆሙ ቀናት አልፈዋል።
እነዚህ አውቶብሶች በከተማይቱ ያለውን የትራንስፖርት ችግር እንዲያቀሉ ድጋፍ እንዲሰጡ ተመድበው ከአመት በላይ አገልግሎት የሰጡ ሲሆን ካለፈው ሚያዚያ 30 ጀምሮ ግን " ከሁለት እና ሶስት ወር በላይ ውል አልታደሰልንም፤ ተገቢ ክፍያ አልተከፈለንም " በሚል ስራ ማቆማቸውን ባለንብረቶቹ ተናግረዋል።
ቃላቸውን ለሸገር ኤፍ ኤም 1021.1 የሰጡት ባለንብረቶች ሌላ ጊዜ ውላቸው በየ3 ወሩ ይታደስ እንደነበር አስታውሰው ፤ አሁን ላይ ከሁለት እና ሶስት ወራት በላይ ውል ሳይታደስላቸው እና ክፍያ ሳይሰጣቸው መቆየቱን ጠቁመዋል።
እነዚሁ ባለንበረቶች ከተማው ውል እንዲያደስ ማህበራት በደብዳቤ ቢያሳውቅም ውሉን ለማደስ ፍቃደኛ አልሆኑም ሲሉም ገልፀዋል።
ክፍያን በተመለከተም በደብዳቤ እንዲከፈል ጠይቀው እንደነበር ፤ ከተጀመረ ጊዜ አንስቶም በጭቅጭቅ እንደሚከፈል ገልፀው ቅሬታቸውን አሰምተዋል።
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ከቀናት በፊት የነዳጅ ጭማሪን ተከትሎ ስራ ያቆሙትን እንደ የሸገር ድጋፍ ሰጪ ትራንስፖርት አገልግሎት ባለንብረቶች በፍጥነት በውላቸው መሰረት ወደ አገልግሎት ካልተመለሱ ውል እንደማያድስ አሥጠንቅቆ ነበር ነገር ግን ባለንብረቶች ስራ ያቆሙት በነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ሳይሆን ውል ስላልታደሰላቸው እና ክፍያ ስላልተከፈለን ነው ሲሉ ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ተናግረዋል።
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#ESP2022 በአ/አ የአሜሪካ ኤምባሲ ለEducationUSA Scholars Program (ESP) 2022 ማመልከቻ ክፍት መደረጉን ዛሬ አሳውቋል። ኤምባሲው ፤ ESP የነገዋን ኢትዮጵያ ለመገንባት በአካዳሚክ የላቁ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በአሜሪካ ኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች በማመልከት የሰለጠኑ እና በደንብ የተማሩ መሪዎችን ለማፍራት የሚረዳ የ4 ሳምንት የስልጠና ፕሮግራም መሆኑን አስታውሷል። ተጨማሪ…
#ማስታወሻ #ጥቆማ #ESP2022
በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ ለEducationUSA Scholars Program (ESP) 2022 ማመልከቻ ክፍት መደረጉን ከቀናት በፊት ማሳወቁ ይታወሳል።
ይኸው ክፍት የተደረገው የማመልከቻ ጊዜ ሊጠናቀቅ ጥቂት ቀናት ቀርቶታል።
ተጨማሪ ዝርዝር መረጃንና የማመልከቻ ቅፆችን በዚህ http://ow.ly/B6b750J0X7q ማግኘት ይቻላል።
እንደአሜሪካ ኤምባሲ መረጃ ESP የነገዋን ኢትዮጵያ ለመገንባት በአካዳሚክ የላቁ #የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎች በአሜሪካ ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች በማመልከት የሰለጠኑ እና በደንብ የተማሩ መሪዎችን ለማፍራት የሚረዳ የአራት ሳምንታት የስልጠና ፕሮግራም ነው።
#ለወላጆች
#ለተማሪዎች

#እንድታውቁት
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅ ተጓዦች ምዝገባ መጀመሩን አስታውቋል።
በዚህም መሰረት የ2014 ዓ.ም የሐጅ ተጓዦች አጠቃላይ አገልግሎት ዋጋ 👉 183 ሺህ 500 ብር መሆኑንም ምክር ቤቱ ያወጣው የዋጋ ዝርዝር ያመለክታል።
ምክር ቤቱ የዋጋ ዝርዝሩን እና ብር የሚገባባቸው ባንክ እና ቁጥሮቻቸውን ይፋ ያደረገ ሲሆን ሀጃጁ ባንክ ያስገባበትን ደረሰኝ ፎቶ ኮፒ አድርጎ በመያዝ ኦርጅናሉን ይዞ መምጣት እንደሚጠበቅበት ነው ያስታወቀው።
የሐጅ ተጓዦች ሊያሟሉ የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ፦
1. ለሐጅ የሚሄደው ግለሰብ ከ65 ዓመት በታች የሆነ
2.የኮቪድ 19 ክትባት የወሰደ እና የማረጋገጫ ወረቀቱን የያዘ
3. የታደሰ ፓስፖርት ያለው፤ ፓስፓርት የሌለውና ጊዜው ያለቀ ከሆነ ወደ ጦር ሃይሎች ሆላንድ ኢምባሲ አጠገብ ዋናው ቢሮ በመምጣት ሂደቱን ማፋጠን ይችላል።
4. ባልና ሚስት አብረው የሚሄዱ ከሆነ የጋብቻ ማረጋገጫ ያስፈልጋል። ግዴታ ነው!
5. ልክ የዛሬ ወር በረራ ስለሚጀመር ቶሎ በመመዝገዝ ሂደቱን የተቀላጠፈ ማድረግ እንደሚቻል የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አሳውቋል።
(ዝርዝር መረጃ ከላይ ተያይዟል)

#ጥንቃቄ
" ... በግለሰብም ሆነ በድርጅት ደረጃ ለፕሮጀክት ማስፈጸሚያ ሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን የእርዳታ ገንዘብ አያድልም " - ገንዘብ ሚኒስቴር
ገንዘብ ሚኒስቴር አርማና ስሙን በመጠቀም #በተሳሳተ_መረጃ ህዝብን በማጭበርብር ላይ ያሉ አካላት እንዳሉ በመግለፅ ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳስቧል።
ሚኒስቴሩ በግለሰብም ሆነ በድርጅት ደረጃ ለፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የእርዳታ ገንዘብ የማያድል መሆኑ በአጽንኦት ገልጿል።
ለህብረተሰቡ ፥ " ፎርም ሞልታችሁ ላኩ፤ የአባልነት መመዝገቢያ በግል ከሆነ 175 ዶላር በድርጅት ከሆነ 225 ዶላር ላኩ " እያሉ ከሚያጭበረብሩ አካላት እንዲጠነቀቅ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ፤ አርማውን እና ስሙን በመጠቀም የሚያጭበረብሩ አካላትን በተመከተ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ክትትል እያደረግን መሆኑን ገልጿል።
በሌላ በኩል ፤ ሚኒስቴሩ ትክክለኛው የፌስቡክ ገፁ " Ministry of Finance - Ethiopia የሚለውና ከ70ሺ በላይ ተከታዮች ያሉትና ማረጋገጫ (Verification ) ልዩ ምልክት ያለው መሆኑን አሳውቋል።

#Russia #Finland #Sewden ሩስያ NATOን ለመቀላቀል ከሞከራችሁ እጅግ " ጎጂ " የሆኑ ውጤቶች [ኢኮኖሚያዊና ወታደራዊ] ይኖራል ስትል ካስጠነቀቀቻቸው ስውዲን እና ፊንላንድ መካከል ስውዲን NATOን ለመቀላቀል ለማመልከት መወሰኗ ተሰምቷል። የስዊዲን ጠ/ሚ ማግዳሌና አንደርሰን ሀገራቸው በሰኔ ወር መጨረሻ ላይ ለNATO ጥምረት አባልነት ለማመልከት መወሰኗን ገልፀዋል። ፊንላንድ በበኩሏ…
ፊንላንድ እና ሩስያ ... ሌላኛው የዓለም ስጋት !
" ፊንላድ NATOን ከተቀላቀለች የአፀፋ እርምጃ እንወስዳለን " - ሩስያ
የሩስያ እና ዩክሬን ጦርነት ምንም ሰላማዊ መፍትሄ ሳያገኝ ወራትን ያሳለፈ ሲሆን ጦርነቱ ለሺዎች ሞት ፣ ለሚሊዮኖች መፈናቀል፣ ለመላው ዓለም የከፋ የኢኮኖሚ መናጋት ምክንያት ሆኗል።
ሩስያ ከዩክሬን ጋር ጦርነት ከገጠመችበት አንዱ እና ዋነኛው ምክንያት NATOን እቀላቀላለሁ ማለቷ እንደነበር አይዘነጋም።
ከዩክሬን ጦርነት በኃላ ሩስያ ፥ ፊንላንድ እና ስውዲን NATOን ለመቀላቀን ብታስቡ እጅግ " ጎጂ " የሆኑ ውጤቶች [ኢኮኖሚያዊና ወታደራዊ] ይኖራል ስትል አስጠንቅቃቸው ነበር።
በኃላም ሀገራቱ NATOን ለመቀላቀል ለማመልከት መወሰናቸውን ተከትሎ ሌላ ውጥረት አንግሷል።
በዛሬው ዕለት ይፋ በሆነ መረጃ ፊንላንድ ያለምንም መዘግየት NATOን ለመቀላቀል ለማመልከት እንደምትፈልግ ገልፃለች። ስውዲንም ፊንላንድን ትከተላለች እየተባለ ነው።
ይህ ደግሞ ሩስያን ክፉኛ አስቆጥቷል።
ሞስኮ ፊንላንድ NATOን ለመቀለቀል ያሳየችውን ፅኑ ፍላጎት እና ዝግጁነት " ቀጥተኛ ስጋት " ስትል የጠራችው ሲሆን " ወታደራዊ-ቴክኒካል " እርምጃዎችን ጨምሮ አፀፋዊ ምላሽ እንደምትሰጥ አስፈራርታለች።
የዩክሬንና ሩስያ ጦርነት አንዳች መፍትሄ ባላገኘበት ሁኔታ ሌላ ዓለም አቀፋዊ ውጥረት እየተፈጠረ ይገኛል ፤ ይህ በኢኮኖሚው ላይ የሚያሳድረው ጫና ለታዳጊ ሀገራትና ለመላው ዓለም የሚተርፍ ነው።

Tikvah-Sport 👉 https://yangx.top/tikvahethsport/29320
Telegram
TIKVAH-SPORT
ዋልያዎቹ ቀጣይ ጨዋታቸውን የት ያደርጋሉ !
ኢትዮጵያ በሜዳዋ የምታደርገውን ጨዋታ በገለልተኛ ስታዲየም እንድታካሂድ ካፍ ውሳኔ ማስተላለፉን ተከትሎ ፌዴሬሽኑ ብሔራዊ ቡድናችን የሚጫወትበትን ስታዲየም አሳውቋል ።
ይህንንም ተከትሎ በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታ ዋልያዎቹ ከ ግብፅ የሚያደርጉትን ጨዋታ በማላዊ ለማድረግ ከውሳኔ መደረሱ ይፋ ሆኗል ።
@tikvahethsport @kidusyoftahe

" ትክክለኛ ፍትህ እንፈልጋለን " ህይወታቸውን ሙሉ ደክመው ያፈሩት ንብረታቸው በአንድ ቀን ሙሉ በሙሉ ዶግ አመድ ሆኖባቸው የሰው እጅ ለማየት የተገደዱ ወገኖቻችን " ፍትህ እንፈልጋለን " እያሉ ነው። ሰሞኑን በደቡብ ክልል፤ ደቡብ ኦሞ ዞን ፤ ደቡብ አሪ ወረዳ ከዞን የመዋቅር ጥያቄ ጋር በተያያዘ በተነሳው የፀጥታ ችግር በርካቶች ንብረታቸው ወድሞ ከገዛ ቤታቸው ተፈናቅለው በየትምህርት ቤቱ እና መንግስት…
#ደቡብ_ኦሞ
🗣 " መልሶ ማቋቋም የተባለው ፖለቲካዊ ይዘት ያለው እንጂ ያለውን ችግር የሚፈታ አይደለም አቤት የምንልበት አጥተናል " - ተፈናቃዮች
🗣 " 72 ሚሊዮን ብር ለማሰባሰብ እየተሰራ ሲሆን እስከ ሰኔ ድረስ የወደሙ ቤቶች ለመገንባትና ነዋሪዎችን ወደቀያቸው ለመመለስ ጥረት እየተደረገ ነው " - አቶ ባንቄ ኩሜ
በፀጥታ ችግር ሳቢያ በደቡብ ኦሞ ዞን " አሪ ወረዳ " የተፈናቀሉ ዜጎች ችግር ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል።
አንድ ተፈናቅለው በመጠላያ ጣቢያ የሚገኙ የቶልታ ነዋሪ ፥ " ያለንበት ችግሩ ተዘርዝሮ አያልቅም " ብለዋል ። መንግስት ነገሮችን የማለሳለስ ስራ ነው የሰራው አንድም የተሰራ ስራ የለም፤ ህዝቡ ያለው ሜዳ ላይ ነው እስካሁን ድረስ ፣ ዝናብ እና ፀሃይ ይፈራረቅበታል፣ ተጨናንቆ ነው ያለው አንድ ትምህርት ቤት ውስጥ በአንድ ክፍል እስከ 50 እና 60 ሰው ነው ያለው ፤ ይህ ለጤናም አስጊ ነው " ሲሉ አስረድተዋል።
እኚሁ ተፈናቃይ የጠየቀን አካል የለም መልሶ ማቋቋም የተባለውም ፖለቲካዊ ይዘት እንጂ የተፈናቃዮችን ችግር የሚፈታ አይደለም ፤ አቤት የምንልበትንም አጥተናል ሲሉ ገልፀዋል።
ተፈናቃዩ ፥ " ሰላሙን በትክክል አስጠብቆ ፣ ህዝቡን ወደቦታው መልሶ ማቋቋም አለበት ብለን ነው እኛ እየጮህን ያለነው። ነገር ግን የተደረገ ነገር የለም። ከወር በላይ ሆኖናል አሁን ዝም ብሎ ቦታውን በዶዘር እንደለድላለን ብሎ የአንድ ሰው ነው የሁለት ሰው ቤት እንደደለደለ ይኸው ሰላም ወርዷል በሚል የተለያየ ነገር በሚዲያ የማሰራጨት ስራ ነው እየተሰራ ያለው ይሄ የፖለቲካ ስራ ነው እየተሰራብን ያለው " ብለዋል።
አንድ ሌላ የቶልታ ተፈናቃይ መምህር ደግሞ ለስምንት አመታት ባስተማሩበት ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኙ ገልፀው ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለችግር መጋለጣቸውን ገልፀዋል።
ሌላ ጥቃትም ይደርስብናል ብለን ስጋት ላይ ነን ሲሉም አስረድተዋል።
"ያየን ሰው የለም" የሚሉት እኚሁ መምህር የተደረገም ድጋፍ እንደሌለ አንስተዋል።
የደቡብ ኦሞ ዞን እርሻና ተፈጥሮ ሃብት መምሪያ ኃላፊ አቶ ባንቄ ኩሜ የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ወደ ቀያቸው ለመመለስ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው ብለዋል። ምግብ ነክ እንም ምግብ ነክ ያልሆኑ ድጋፎች እየቀረበ ነው ሲሉም ተፈናቃዮች የሚያነሱትን ቅሬታ ውድቅ አድርገዋል።
የተሠጠው ድጋፍ ለ1 ወር ከ15 የሚበቃ ነው ሲሉም ገልፀዋል።
መልሶ ለማቋቋም ፤ 72,000,000 ብር ለማሰባሰብ እየተሰራ መሆኑን እና እስከ ሰኔ ድረስ የወደሙ ቤቶች ተመልሰው ተገንብተው ተፈናቃዮች ወደ ቤታቸው እና ቀያቸው እንዲመለሱ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል።
የዞኑ የሰላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ደሞ በዛብህ በበኩላቸው የፀጥታ ችግር ተፈጥሮ የነበረባቸው ወረዳዎች ወደ ቀደመው ሰላማቸው ተመልሰዋል ብለዋል።
በወንጀል የተጠረጠሩ ከ1400 በላይ ሰዎች በወቅቱ ታስረው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን እና ከፍተኛ ተሳትፎ ያላቸውን እና መሪ ሚና የተጫወቱት ላይ ክስ ለመመስረት በሂድት ላይ ነው ብለዋል።
ለአሁን ላይ ተፈናቃዮች የማያቀርቡትን የደህንነት ስጋት በተመለከተ ፥ " አሁን ባለው ሁኔታ ጥቃት የሚያደርስ አካል አለ ወይ ብለን ስንገመግም ብዙም የለም " ሲሉ ተናግረዋል።
Credit : ቪኦኤ / ጋዜጠኛ ዮናታን ዘብዲዮስ

ፊንላንድ እና ሩስያ ... ሌላኛው የዓለም ስጋት ! " ፊንላድ NATOን ከተቀላቀለች የአፀፋ እርምጃ እንወስዳለን " - ሩስያ የሩስያ እና ዩክሬን ጦርነት ምንም ሰላማዊ መፍትሄ ሳያገኝ ወራትን ያሳለፈ ሲሆን ጦርነቱ ለሺዎች ሞት ፣ ለሚሊዮኖች መፈናቀል፣ ለመላው ዓለም የከፋ የኢኮኖሚ መናጋት ምክንያት ሆኗል። ሩስያ ከዩክሬን ጋር ጦርነት ከገጠመችበት አንዱ እና ዋነኛው ምክንያት NATOን እቀላቀላለሁ…
#Update
" ስውዲን እና ፊንላንድን የNATO አባል የማድረጉ ሂደት 'በፍጥነት' ይካሄዳል ብለን እንጠብቃለን " - የNATO ዋና ጸሐፊ ጄንስ ስቶለተንበርግ
ከሩስያ ጋር 1300 ኪሎ ሜትር የሚረዝም ድንበር የምትጋራው ፊንላንድ NATOን ለመቀላቀል የአባልነት ጥያቄዋን የፊታችን እሁድ ይፋ ታደርጋለች ተብሎ ይጠበቃል።
ስውዲንም የአባልነት ጥያቄዋን በተመሳሳይ ቀን ታቀርባለች ተብሎ ነው የሚጠበቀው።
የNATO ዋና ጸሐፊ ጄንስ ስቶለተንበርግ ፥ ስውዲን እና ፊንላንድን የNATO አባል የማድረጉ ሂደት 'በፍጥነት' ይካሄዳል ብለው እንደሚጠብቁ ተናግረዋል።
ከሩስያ ጋር ክፉኛ የተቃቃረችው አሜሪካ የ2ቱን አገራት የአባልነት ጥያቄ እንደምትደግፍ አስታውቃለች ፤ ዩናይትድ ኪንግደም እና ፈረንሳይም ሁለቱ ሀገራት የNATO አባል እንዲሆኑ ፍላጎት አላቸው።
NATOን ለመቀላቀል ፍላጎት ካሳየችው ዩክሬን ጋር ጦርነት ውስጥ ያለችው እና ወታደራዊ እርምጃ እየወሰደች የምትገኘው ሩስያ የፊንላንድ እና ስውዲን እንቅስቃሴ ክፉኛ አስቆጥቷታል።
ሩስያ ፤ የፊንላንድ የNATO አባልነት ጥያቄ የሩሲያ-ፊንላንድን የሁለትዮሽ ግንኙነትን እጅጉን እንደሚጎዳውን እና ለሰሜን አውሮፓ ቀጠና መረጋጋት እና ሰላም አደጋ እንደሆነ አስገዝባለች።
ይህንን የደኅንነት ስጋት ለማስወገድም ቴክኒካዊ የሆነ #የጦር እና ሌላ መልክ ያለው የአጸፋ እርምጃ ለመውሰድ እንደምትገደድ ዝታለች።
መረጃው ከቢቢሲ / ከሩስያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት የተውጣጣ ነው።

#Soufflet
60 ሚሊዮን ዩሮ ወጪ ተደርጎበት የተገነባው " ሱፍሌት ማልት ኢትዮጵያ " የተሰኘ ብቅል አምራች ፋብሪካ ዛሬ ተመረቀ።
የብቅል ፋብሪካው የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፓሬሽን ስር በሚተዳደረው በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ነው የተገነባው።
በዛሬው የምረቃ ስነስርዓት ላይ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ፤ የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፓሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳንዶካን ደበበ ፤ የፋብሪካው አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ፋብሪካው 10 ሔክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን በአመት 60 ሺህ ቶን ብቅል የማምረት አቅም አለው ተብሏል።
በግብርና ላይ የሚሰራ " ኢንቪቮ ግሩፕ " በተባለ የፈረንሳይ 🇫🇷 ኩባንያ ስር የሚገኘው ሱፍሌት ማልት በ38 ሀገራት የተለያዩ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች ፤ 90 የኢንዱስትሪ መንደሮች እና 13 ሺህ ሰራተኞች አሉት።
ኢንቪቮ ግሩፕ በተለያዩ ሀገሪት በገነባቸው 28 የብቅል ማምረቻዎች አማካኝነት በየአመቱ 2.6 ሚሊዮን ቶን ብቅል ለአለም ገበያ እያቀረበ ይገኛል።
መረጃው የኢትዮ ንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ ነው።

#Update " ስውዲን እና ፊንላንድን የNATO አባል የማድረጉ ሂደት 'በፍጥነት' ይካሄዳል ብለን እንጠብቃለን " - የNATO ዋና ጸሐፊ ጄንስ ስቶለተንበርግ ከሩስያ ጋር 1300 ኪሎ ሜትር የሚረዝም ድንበር የምትጋራው ፊንላንድ NATOን ለመቀላቀል የአባልነት ጥያቄዋን የፊታችን እሁድ ይፋ ታደርጋለች ተብሎ ይጠበቃል። ስውዲንም የአባልነት ጥያቄዋን በተመሳሳይ ቀን ታቀርባለች ተብሎ ነው የሚጠበቀው።…
#Update
የዩክሬን እና የፊንላንድ ፕሬዜዳንቶች በስልክ ተነጋገሩ።
በዋነኝነት NATOን ለመቀላቀል ባሳየችው ፍላጎት ሳቢያ ከሩስያ ጋር ዛሬም ድረስ መፍትሄ ያላገኘ አስከፊ ጦርነት ውስጥ የገባቸው #ዩክሬን እና NATOን ለመቀላቀል ጥያቄ ለማቅረብ ዝግጅት ላይ የምትገኘው #ፊንላንድ ፕሬዜዳንቶች በስልክ ተነጋግረዋል።
የፊንላዱ ፕሬዜዳንት ሳውሊ ኒኒስቶ፤ ከፕሬዜዳንት ቮልድሚር ዜሌንስኪ ጋር በነበራቸው ውይይት ሀገራቸው ለዩክሬን ያላትን ፅኑ ድጋፍ በድጋሜ እንዳረጋገጡላቸው ገልፀዋል።
ፕሬዜዳንቱ ፊንላንድ የNATO አባል ለመሆን እየሄደችበት ስላለው ሂደት እንዳሳወቋቸው ገልፀው የዩክሬኑ ፕሬዜዳንትም ያላቸውን ድጋፍ እንደገለፁለቸው በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ፅፈዋል።
የዩክሬን ፕሬዜዳንት ዜሌንስኪ በበኩላቸው ከፊንላዱ ፕሬዜዳንት ጋር በነበራቸው የስልክ ውይይት ፊንላንድ ለNATO አባልነት ለማመልከት ያላትን ዝግጁነት አድንቀው አመስግነዋል ፤ በተጨማሪ ስለ ዩክሬን የአውሮፓ ውህደት በተመለከተ መነጋገራቸውን አሳውቀዋል።

#GERD🇪🇹
" የታላቁ ህዳሴ ግድብ 3ኛውን የውሃ ሙሌት ለማከናወን በ21 ሺ ሄክታር መሬት ላይ የምንጣሮ ስራ እየተከናወነ ነው ፤ ሰራተኞች ያለምንም የፀጥታ ስጋት ስራቸውን እንዲያከናውኑ በትኩረት እየተሰራ ነው " - ሌ/ጀኔራል ደስታ አብቼ
የመተከል ዞን የተቀናጀ ኮማንድ ፖስት ዋና አስተባባሪ ሌ/ጀኔራል ደስታ አብቼ ፥ ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ እየገነባችው የምትገኘው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ያለምንም ፀጥታ ችግር እንዲከናወን በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
ሌ/ጀኔራል ደስታ " ሠራዊቱ የተሠጠውን ተልኮ ሌት ተቀን በቁርጠኝነት መፈፀም በመቻሉ ለህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውሉ ግብአቶች በሰላም ተጓጉዘው እንዲደርሱ እና ሰራተኞችም ደህንነታቸው ተጠብቆ እንዲሰሩ ማድረግ ተችሏል " ብለዋል።
የታላቁ ህዳሴ ግድብ #3ኛውን_የውሃ_ሙሌት ለማከናወን በ21 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የምንጣሮ ስራ እየተከናወነ መሆኑን የገለፁት ሌ/ጀኔራሉ " የግድቡ ግንባታ ሰራተኞች ያለምንም የፀጥታ ስጋት ስራቸውን እንዲያከናውኑ የተቀናጀ የፀጥታ ሃይሉ በትኩረት እየሰራ ነው " ብለዋል።
አክለውም " የተቀናጀ የፀጥታ ሃይሉ ዕድገታችንን ለማደናቀፍ #ከሱዳን ሰርገው የሚገቡ ኃይሎችን እየተከታተለ ሴራቸውን እያከሽፈው ይገኛል ፤ በቀጣይም ከአካባቢው ማህበረሰብ እና ሲቪል አመራሮች ጋር ተቀናጅቶ ግዳጁን በአስተማማኝ ለመወጣት ዝግጁነቱ የላቀ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
#FDRE_Defense_Force🇪🇹
ፎቶ ፦ ፋይል