TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
"ጥበብ እንደ መፈወሻ መንገድ/  Art as a path to healing" ኦላይን የስዕል ኤግዚቢሽን

በትግራይ መቐለ ከተማ ከወርሃ የካቲት እስከ ሚያዝያ 2016 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየውና ከ387 ተመዝጋቢዎች የተመረጡ 61 ታዳጊና ወጣት ሰአልያን የተሳተፉበት የቡድን የስእል ውድድር አሸናፊዎችን በመለየት ተጠናቋል።

በውድድሩ ወጣቶቹ በ10 ቡድን በመከፋፈል 10 ስዕሎችን ያቀረቡ ሲሆን፤ ስዕሎቹም ጦርነትን፣ ዘረኝነትን፣ የእርስ በርስ ግጭትና ጠባብነት በማውገዝ ሰላም አንድነት ስር እንዲሰድ የሚሰብኩ ነበሩ።

እነዚህን ስዕሎች ኦላይን በተዘጋጀው ኤግዚቢሽን እንድትመለከቷለቸው እንጋብዛለን።

ወደ ኤግዚቢሽኑ ጎራ ለማለት ተከታዩን ሊንክ ይጠቀሙ https://redeem.tikvahethiopia.net/paintings

#USAID     #RTG   #TikvahEthiopia