TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.7K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
September 15, 2023
September 16, 2023

#ዓለምአቀፍ

ሃማስ እስራኤል ላይ ድንገተኛ የተባለ ጥቃት መክፈቱ ተሰማ።

የፍልስጤሙ ሃማስ በዓመታት ውስጥ ከፍተኛው ነው የተባለ ድንገተኛ ጥቃት መክፈቱን ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን እየዘገቡ ይገኛሉ።

ሃማስ ከጋዛ ሰርጥ ወደ እስራኤል 5000 ሮኬቶችን ያስወነጨፈ ሲሆን የሰው ህይወት መጥፋቱም ተነግሯል።

እየሩሳሌምን ጨምሮ በደቡባዊ እና መካከለኛው እስራኤል የማስጠንቀቂያ ድምፅ እየተሰማ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የጸጥታ ባለስልጣናትን ለአስቸኳይ ስብሰባ ጠርተዋል ተብሏል።

የሃማስ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥ መሐመድ ዴይፍ በሃማስ ሚዲያ ቀርበው " የአልአቅሳ ማዕበል ኦፕሬሽን " በሚል ወታደራዊ ዘመቻ መጀመራቸውን ገልጸዋል።

" በየቦታው ያሉ ፍልስጤማውያን እንዲዋጉ " ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ዲፍ " በቃ ልንል ወስነናል " ያሉ ሲሆን ሁሉም ፍልስጤማውያን እስራኤልን እንዲጋፈጡ አሳስበዋል።

" ይህ በምድር ላይ የመጨረሻውን ወረራ ለማስወገድ ታላቅ ጦርነት የሚካሄድበት ቀን ነው " ብለው እስካሁን 5,000 ሮኬቶች ተወንጭፈዋል ሲሉ ተናግረዋል።

ሃማስ ኦፕሬሽኑ በአል-አቅሳ እየተካሄደ ላለው ትንኮሳ እና በእስራኤል እስር ቤቶች ውስጥ በፍልስጤም እስረኞች ላይ እየተወሰደ ያለውን እርምጃ ምላሽ ለመስጠት ነው ብሏል።

በደቡባዊ እስራኤል በሲዴሮት ከተማ የታጠቁ ተዋጊዎች በአላፊ አግዳሚ ላይ ተኩስ እንደከፈቱ የእስራኤል ሚዲያዎች ዘግበዋል


በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የፍልስጤም ዩኒፎርም የለበሱ ተዋጊዎች በድንበር ከተማ ውስጥ ግጭት ሲፈጥሩ እንዲሁም የሚነድ የእስራኤል ታንክ ታይቷል።

" ሃማስ ለድርጊቱ እጅግ ከባድ ዋጋ ይከፍላል " - እስራኤል

የእስራኤል ጦር በጋዛ ሰርጥ ዙሪያ የሚኖሩ እስራኤላውያንን በቤታቸው እንዲቆዩ አሳስቧል።

ሃማስ "ለድርጊቶቹ እጅግ ከባድ ዋጋ " እንደሚከፍል ዝቷል።

ጦሩ ሃማስ ላይ ኦፕሬሽን መጀመሩ ተነግሯል።

" ከዚህ ጥቃት ጀርባ ያለው ሃማስ፣ ለቀጣይ ውጤት እና ክስተቶች ሁሉ ሃላፊነቱን ይወስዳል። " ያለው የእስራኤል ጦር ' ሰራዊቱ ለጦርነት ዝግጁ " እንዲሆን አውጇል።

አሜሪካ ሁኔታውን ብቻ ቅርበት እየተከታተለች እንደሆነ አሳውቃለች።

@tikvahethiopia
October 7, 2023
August 5, 2024
October 5, 2024
November 11, 2024