TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.52K videos
215 files
4.13K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#DrAbrahamBelay

የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ ፥ ኢትዮጵያ የተደቀነባት የደህንነት ፈተና የመነጨው ከ100 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ያላትን አገር ለማፍረስና ለማዳከም አልመው ከሚሰሩ የውስጥና የውጭ ሃይሎች መሆኑን ገለፁ።

ዶ/ር አብርሃም ፥ " እነዚህ አጭበርባሪ ተዋናዮች ግባቸውን ይፋ አድርገው በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠውን የኢትዮጵያን መንግስት በመጣል በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ሊኖረው የማይችል የራሳቸውን አሻንጉሊት መንግስት ለማስቀመጥ ፍላጎት አላቸው " ብለዋል።

“የዓለም ዓቀፍ አጋሮቻች ይህንን ተረድተው የህዝብ ምርጫ የሆነውን የኢትዮጵያ መንግስት መደገፍና ከፋፋይ አጀንዳ ካለው አሸባሪው ህወሃት በተቃራኒ ሊቆሙ ይገባል” ሲሉ ገልፀዋል።

የአገሪቱንና የመላ ዜጎቿን ደህንነት ለማስጠበቅ የኢትዮጵያ መንግስት ያለእረፍት እየሰራ እንደመገኝ የጠሱት ዶ/ር አብርሃም፤ “በአገራችን ውስጥ ሆነው ለአሸባሪው ህወሃት የሚሰሩ ሃይሎች አሉ” ብለዋል።

እነዚህ ሃይሎች ምናልባት ንጹሐን ትግራዋዮችን በመክሰስ የአሸባሪውን አጀንዳ አስርገው ለማስገባት ሽፋን እያደረጉት እንደሆነ ገልጸዋል።

ከነዚህ በተጨማሪ ሌሎች ተዋናዮች እንዳሉ ጠቁመው፤ የአገሪቱን ቀውስ ለማባባስ የተቻላቸውን እየሞከሩ እንደሆነ ተናግረዋል።

ይህንን ችግር ለመፍታትና እነዚህን ተዋናዮች ተጠያቂ ለማድረግ የሚያስችል ኮሚቴ መቋቋሙን ጠቁመዋል።

ኮሚቴው በፌዴራል ፖሊስና በሌሎች አጋር ተቋማት የሚወሰደው እርምጃ ስህተት እንዳያጋጥመው የሚያስችል እንደሆነም አመልክተዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ንጹሀን ትግራዋዮች ላይ ጉዳት እንዳይደርስባቸው ለመጠበቅ ከትግራይ ተወላጆች ቡድን ጋር በቅርበት በመስራት ሂደቱን የመመርመርና የመገምገም ስራ እየተሰራ እንደሆነ አመልክተዋል።

Credit : ENA

@tikvahethiopia