TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#ItsMyDam🇪🇹

" የተርባይኖቹ ሃይል ማመንጨት ተከዜና ጣና በለስ ግድቦችን በአንድ ጊዜ የማጠናቀቅ ያህል ነው " - ፕሮፌሰር ይልማ ስለሺ

የታላቁ የህዳሴ ግድብ 2 ተርባይኖች ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጨት መጀመር ተከዜንና ጣና በለስ ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ግድቦችን በአንድ ጊዜ የማጠናቀቅ ያህል መሆኑን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህርና የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ተደራዳሪ አባል ፕሮፌሰር ይልማ ስለሺ ገለጹ።

ፕሮፌሰር ይልማ ስለሺ ለኢፕድ በሰጡት ቃል ፥ በጣና በለስና በተከዜ ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ግድቦች የሚመረተው የኤሌክትሪክ ሃይል የህዳሴው ግድብ ሁለቱ ተርባይኖች ከሚመነጩት ኤሌክትሪክ ሃይል እኩል ነው ብለዋል።

ሁለቱ ተርባይኖች ተጠናቀው ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጨት መጀመር ሁለት ግዙፍ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ግድብ ፕሮጀክቶች በአንድ ጊዜ እንደማጠናቀቅ ይቆጠራል ሲሉም ገልፀዋል።

ፕሮፌሰሩ ፥ ጣና በለስና ተከዜ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ግድቦች እንደቅደም ተከተላቸው 460ና 300 ሜጋ ዋት ሃይል እንደሚያመነጩ አውስተው፤ የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ሃይል ማመንጫ ግድብ ሁለት ተርባይኖች ስራ መጀመር 750 ሜጋ ዋት ሃይል ስለሚያመነጩ ሁለት ትልልቅ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ግድቦችን የማጠናቀቅ ያህል ነው ብለዋል።

Credit : EPA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba : የኑሮ ዉድነትን ለመቀነስ "የእሁድ ገበያን" በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች መጀመራቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ አሳውቀዋል። ገበያዎቹ በየሳምንቱ እሁድ የተለያዩ መሰረታዊ የፍጆታ ሸቀጦችን ለከተማው ነዋሪ በአነስተኛ ዋጋ አንደሚቀርቡም ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል ። በዚህም በአምራቾችና በሸማቾች መካከል ቀጥተኛ እና አጭር የግብኝት ግንኙነት እንዲኖር ማድረግ ይቻላል ያሉት ከንቲባ…
ፎቶ ፦ በአዲስ አበባ በተመረጡ ቦታዎች የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶች ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ እየቀረበ ይገኛል።

ዛሬ ፦
- በንፋስ ስልክ ላፍቶ ጀሞ 67 ቁጥር ማዞሪያ፣
- በመገናኛ፣
- በፒያሳ፣
- በሜክሲኮ አደባባይ እና በቃሊቲ መናኸሪያ በርካታ ነዋሪዎች የተለያዩ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶችን በመገበያየት ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የሸማቾች ኅብረት ስራ ማኅበራት፣ የሰብልና አትክልት አቅራቢዎች ፣የጅምላ ነጋዴዎች እና በምግብ ማቀነባበር የተሰማሩ ፋብሪካዎች እንዲሁም በአዲስ አበባ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን የሚገኙ የኅብረት ስራ ማህበራትና አምራች አርሶ አደሮች ተሳትፈዋል ።

ለህብረተሰቡ እየቀረበ ካለው የግብርና ምርቶች መካከል ፦
- የጤፍ፣
- የስንዴ ዱቄት፣
- የአትክልትና ፍራፍሬ ይገኝበታል።

ከኢንዱስትሪ ምርቶች ደግሞ ዘይት፣ ማካሮኒና ፓስታ እንዲሁም የባልትና ውጤቶች ቀርበዋል እንደ አዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬተሪያት መረጃ።

@tikvahethiopia
#Aykel : የሠላም ምክክር መድረክ በአይከል !

በዛሬው ዕለት የአማራና ቅማንት ህዝቦች የሠላም ምክክር መድረክ በአይከል ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በሠላም ምክክር መድረኩ ከሶስቱ የጎንደር ዞኖች የተሰባሰቡ የሃይማኖት አባቶች፣ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የመከላከያ ሰራዊትና የአማራ ልዩ ሃይል አባላት፣ የአካባቢው የጸጥታ አካላትና ነዋሪዎች መገኘታቸው ተገልጿል።

በዚህ መድረክ የአይከል ከተማ ተወካይ ከንቲባ አቶ ለገሰ ብርቄ ÷ በአሁኑ ሰአት በአካባቢው የሚታየው የሰላም እጦት፣ የሰዎች እገታና ዘረፋ መሠረቱ ህገወጥ የንግድ እንቅስቃሴና የሰዎች ዝውውር ነው ብለዋል።

አቶ ለገሰ ፥ " ድርጊቱ በአሸባሪው ህወሓትና በቅማንት ጽንፈኛ ቡድን ሴራ ለዓመታት ሲተገበር ቆይቷል" ሲሉ ገልፀዋል።

እጩ ዶ/ር ያሬድ ደበበ የጠገዴ አርማጭሆና አካባቢው በጎ አድራጎት ማህበር አባል የመወያያ ፅሁፍ ያቀረቡ ሲሆን " የዜጎች ሰላም መደፍረስና የሀገር ህልውና አደጋ ላይ የወደቀው አሁን ሳይሆን አሸባሪው ህወሓት ከተመሰረተ ጀምሮ ነው " ሲሉ አስረድተዋል።

አክለውም ፤ " አሁን ላይ አሸባሪ ቡድኑ በጥቅም የሚገዙ የአማራ እና ቅማንት ሰዎችን አሰማርቶ የጥፋት ስራውን ቀጥሎበታል " ብለዋል።

" በግጭት ውስጥ የሚያተርፉ በርካታ ሰዎች አሉ " ያሉት እጩ ዶ/ር ያሬድ ÷ " በአማራና ቅማንት ህዝቦች መካከል የሚፈጥረውን ግጭት ለማስቀጠል በርካታ ጥረቶችን እያደረገ ቆይቷል " ሲሉ ተናግረዋል።

በአንድ ሀገር ላይ የሚኖሩ ሰዎች ሰላማቸውን ማረጋገጥ ይገባል ፤ የሁለቱ ብሔሮች ህዝቦችም ይህንን በትኩረት ሊሰሩበት ይገባልም ሲሉ ገልፀዋል።

telegra.ph/AYKEL-10-31 (ኤፍቢሲ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የመምህራን ጉዳይ ! " በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችና የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ጊዚያዊ ምደባ ይሰጣቸዋል " - ዶ/ር ሰለሞን አብርሃ በትግራይ ክልል የሚገኙ 4 ዩኒቨርሲቲዎች እና የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ጉዳይን በተመለከተ ለትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደርና መሰረተ-ልማት ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) ጠይቀናል። የትግራይ ዩኒቨርሲቲዎች እና የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ…
#Update

ትምህርት ሚኒስቴር ፦
• በመቐለ ፣
• በዓዲግራት፣
• በአክሱም ፣
• በራያ እና በወልድያ ዩኒቨርስቲዎች ሲያስተምሩ የነበሩ መምህራን በሙሉ ወደ ሌሎች ዩኒቨርስቲዎች ጊዜያዊ ምደባ ለመመደብ እንዲያስችል መምህራን በሚከተለው ሊንክ https://forms.gle/uEmVwqqDFQ7dFk5dA ተጠቅመው ከነገ ጀምሮ እስከ እሮብ 24/2/2014 ዓ.ም እንዲመዘገቡ መልዕክት አስተላልፏል።

@tikvahethiopia
ዛሬ የኢትዮጵያ መንግሥት የኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ በደሴ ግንባር ጉዳይ መግለጫ ሰጥተዋል:: በመግለጫቸውም ተከታዮቹን ነጥቦች አንስተዋል :

- የመከላከያ ሰራዊቱ ዛሬም ከፍተኛ ተጋድሎ በማድረግ ላይ ይገኛል ብለዋል::

- መከላከያ የሚወስዳቸውን ስልታዊ እርምጃዎች በተሳሳተ መንገድ በመገንዘብም ሆነ ህዝብን ለማደናገጥ የተዛባ መረጃ የሚያሰራጩ አክቲቪስቶች እና ህዝብን የከዱ ባንዳዎች መንግሥት ፈፅሞ አይታገስም ብለዋል::

- ህወሓት በተወስደበት ተደጋጋሚ እርምጃ ከባድ መሳሪያዎቹ እና የቡድን መሳሪያዎቹ ወድመዋል: በዚህም ቡድኑ ከሁሉም ግንባሮች ሀይሉን በማሰማራት የደረሰበትን ከፍተኛ ኪሳራ ለማካካስ እና መሳሪያዎችን ለመቀማት መጠነ ሰፊ የማጥቃት ሙከራዎችን እያደረገ ይገኛል ሲሉ ገልፀዋል::

- በትናንትናው እለት በደሴ ቡድኑ አስቀድሞ ያስገባቸው ሰርጎ ገቦች እና ሲቪል የቡድኑ ተልዕኮ አስፈጻሚዎች በመከላከያ ሀይሉ ላይ የኃላ ጥቃት ፈፅመዋል ብለዋል::

- የትላንናው ተግባር ብዙ እልቂት እንዳያስከትል የመከላከያ ሰራዊት ልዩ የማፈግፈግ ስልቶችን አድርጎ ዛሬም ከፍተኛ ተጋድሎ በማድረግ ላይ ይገኛል ብለዋል::

- ሰራዊቱ ከአማራ ልዩ ሀይል እና ከአማራ ህዝብ ጋር በመተባበር ይዞታውን ወደ ጭፍራ፣ወረባቦ እና በጋሸና በኩል በማስፋፋት ላይ ይገኛል ብለዋል::

- ዛሬ በደሴ ግንባር እና በኮምቦልቻ ከፍተኛ ውግያ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

- ሁሉም ክልሎች ያወጁትን የክተት ጥሪ በመቀበል ህዝቡ በቀረበለት ጥሪ መሰረት በመዝመት፣ የስንቅ ድጋፍ በማድረግ እና የተፈናቀሉትን በመደገፍ እንዲተባበር ብለዋል::

ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ

@tikvahethiopia
#DebreBirhan : በደብረ ብርሃን ከተማ የባጃጅና ሌሎች ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ላልተወሰነ ጊዜ መቋረጡ ተገለፀ።

በከተማ አስተዳደሩ የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ለጊዜው እንዲቋረጥ የተደረገበት ምክንያት በከተማው ያለውን የሰዎች እንቅስቃሴ መቆጣጠር እንዲቻል መሆኑ ተጠቁሟል።

የከተማው ወጣቶችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ከጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር በየአካባቢው ሰርጎ ገቦችን በመከታተልና የአካባቢያቸውን ሰላም በማስጠበቅ ሃገራዊ ኃላፊነታቸውን እዲወጡ ከተማ አስተዳደሩ ጥሪ አቅርቧል::

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#DebreBirhan : በደብረ ብርሃን ከተማ የባጃጅና ሌሎች ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ላልተወሰነ ጊዜ መቋረጡ ተገለፀ። በከተማ አስተዳደሩ የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ለጊዜው እንዲቋረጥ የተደረገበት ምክንያት በከተማው ያለውን የሰዎች እንቅስቃሴ መቆጣጠር እንዲቻል መሆኑ ተጠቁሟል። የከተማው ወጣቶችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ከጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር በየአካባቢው ሰርጎ ገቦችን በመከታተልና የአካባቢያቸውን…
#Update

በደብረ ብርሃን ከተማ ከዛሬ ጀምሮ ከምሽቱ 1:00 ሰዓት እስከ ጠዋት 12::00 ሰዓት ድረስ የሰው እንቅስቃሴ እንዳይኖር ገደብ ተጣለ።

በደብረ ብርሃን ከተማ የባጃጅና ሌሎች ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ላልተወሰነ ጊዜ መቋረጡ ይታወቃል ይኸም
በከተማው ያለውን ከፍተኛ የሰዎች እንቅስቃሴ መቆጣጠር እንዲቻል ታሳቢ በማድረግ መሆኑን የከተማው ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ ደስታ አንዳርጌ አስታውቀዋል።

አክለውም ለከተማዋ ሰላምና ደህንነት ሲባል እንዲሁም ያለውን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር ያስችል ዘንድ ከተሽከርካሪ እንቅስቃሴ በተጨማሪ የሰው እንቅስቃሴ እስከ ምሽት 1 ሰአት ድረስ ብቻ የተፈቀደ ሲሆን ከምሽቱ 1 ሰአት እስከ ሌሊቱ 12 ሰአት ድረስ የሰው እንቅስቃሴ ላይ ገደብ ተጥሏል ብለዋል።

ይህን ውሳኔ ጥሶ በሚገኝ ማንኛውም አካል ላይ ለህዝቡ ደህንነት ሲባል ህጋዊ ርምጃ የሚወስድ መሆኑን ከተማ አስተዳደሩ አስጠንቅቋቸዋል::

@tikvahethiopia
#Amhara

የአማራ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ጥቅምት 21 ቀን 2014 ዓ.ም ባካሄደው 6ኛ ዙር፣ 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ አስቸኳይ ስብሰባ አስቸካይ ጥሪ ውሳኔዎች አስተላልፏል፡፡

ውሳኔዎቹ ከላይ የተዘረዘሩ ሲሆን ከውሳኔዎቹ መካከል የተለያዩ አገልግሎቶችን እንዲሰጡ ከተፈቀደላቸው ተቋማት ውጭ በሁሉም ከተሞች ከምሽቱ 2፡00 በኋላ እንቅስቃሴ ማድረግ አይቻልም ተብሏል።

ከሚሰጡት አገልግሎት አስፈላጊነት አኳያ እየተመዘነ የሚወሰን መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ማንኛውም የመንግስት ተቋም መደበኛ አገልግሎቱን አቋርጦ በጀቱን ጨምሮ ሁሉንም ነገር የገጠመንን የህልውና ዘመቻ ለመቀልበስ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ እንዲረባረብ ተወስኗል።

ሁሉም የመንግስት ተሸከርካሪ ወደ አንድ ማዕከል በማሰባሰብ ለሕልውናው ዘመቻ አገልግሎት እንዲውል እንዲደረግ ተብሏል።

የግል ተሸከርካሪ ባለቤቶች ለሕልውና ዘመቻው ስኬት ሲባል በተፈለገ ጊዜ ሁሉ ተሸከርካሪዎቻቸውን በመስጠት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ተወስኗል።

በየደረጃው የሚገኝ አመራርም የሕልውና ዘመቻውን ተቀብሎ የሚሰለፈውን ሕዝብ አደራጅቶ ከፊት ሆኖ እየመራ ወደ ግንባር እንዲዘምት ይህን በማያደርጉ አመራሮች ላይ ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ተወስኗል።

* ሙሉ ውሳኔዎችን ከላይ ያንብቡ !

@tikvahethiopia
#ባቲ

ወደ ባቲ ከተማ የተሽከርካሪዎች መግቢያ እና መውጫ የሰዓት እላፊ ገደብ ተግባራዊ እየተደረገ ነው።

ይህ የሰዓት እላፊ ገደብ ከጥቅምት 17 ጀምሮ ነው ተግባራዊ የሆነው።

የባቲ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ም/ ቤት ለአጠቃላይ ተሽከርካሪዎች ወደ ባቲ ከተማ አስ/ር መግቢያና መውጫ ያስቀመጠው የሰአት እላፊ ገደብ ከ12፡00 ጀምሮ ሲሆን ከዚህ ሰዓት በኃላ ወደ ባቲ ከተማ መግባትም ሆነ መውጣት አይቻልም (ይህ ባለሶስት እግር ተሽከርካሪ /ባጃጅ/ ጨምሮ ነው) ።

ውስጥ ለውጥ ተሽከርካሪ ማንቀሳቀስም በጥብቅ የተከለከለ ነው።

ተግባራዊ እየሆነ ያለው የሰዓት እላፊ ገደብ የፀጥታ አካላት የሚጠቀሙባቸው ተሽከርካሪዎችን አይጨምርም።

ገደቡን በሚጥስ አካል ላይ ጠበቅ ያለ እርምጃ የሚወሰድ ሲሆን ሁሉም አካል ለሰላሙ ሲል ይህንን የሰዓት እላፊ ገደብ እንዲያከብር መልዕክት ተላልፏል።

@tikvahethiopia
#GIBE1 : በጊቤ አንድ ኃይል ማመንጫ ግድብ ውሃው ሳይፈስ ከ18 ሜትር ጥልቀት በላይ ወደ ውሃ ውስጥ በመግባት ስኬታማ ጥገና ተከናወነ።

የጣቢያው ሥራ አስኪያጅ አቶ ደሳለኝ ንጉሳ ፥ ግድቡ ላይ 1.5 ሜትር ክበት ስንጥቅ በመኖሩ ግድቡ ውሃ የማስረግ ችግር ገጥሞት እንደነበር የገለፁ ሲሆን በዘመነ ቴክኖሎጂ አማካኝነት ውሃው ሳይፈስ ጥገናውን በማከናውን ችግሩን መቅረፍ ተችሏል ብለዋል፡፡

የጥገና ስራውን ያከናወነው የቻይናው ሲጂጂሲ ኩባንያ ሲሆን ሌሎች ታዋቂ አለም አቀፍ ኩባንያዎች ውሃው ካልፈሰሰ መጠገን አንችልም ቢሉም ሲጂጂሲ ውሃው ሳይፈስ በመጠገን ለኃይል ማመንጫው በቂ የውሃ ክምችት እንዲኖር አስችሏል፡፡

በተጨማሪ የደለል ማስወገጃ እና መቆጣጠሪያ አሸንዳ በጉዳት ምክንያት አገልግሎት መስጠት አቋርጦ የነበረ ሲሆን ጥገና ተከናውኖለት ወደ ሥራ ለማስገባት የሙከራ እና የፍተሻ ሥራዎች የተከናወኑ መሆኑን ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡

አቶ ደሳለኝ ለጥገናው አጋዥ የሆኑ የመቆጣጠሪያ ሰሌዳ እና የሞተር ፓምፕ ገጠማ ሥራዎች መከናወኑን አሳውቀዋል።

በጥገና ሥራው ላይ 31 ያህል ቻይናውያን የተሳተፉ ሲሆን የጣቢያው ሠራተኞችም በሥራው ላይ በመሳተፍ ጠቃሚ እውቀትና ክህሎት ማግኘታቸው ተገልጿል።

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

ሀገራቸውን የሚወዱ ፣ የሀገራቸውንና የህዝባቸውን ሰላምና ደህንነት አጥብቀው የሚሹ የኢትዮጵያ ዜጎች በሀገራቸው ጉዳይ በእጅጉ ንቁ፣ ስሜታዊም ናቸው።

የእናት ሀገራችን ስም በየትም ቦታ ሲነሳ ልባቸው ቀጥ የሚል፣ ኢትዮጵያ የሚለውን ስም ሲሰሙ ከላይ እስከታች የሚነዝራቸው ፣ የህዝባቸው ስቃይ፣ ሰቆቃ እና መከራ እንቅልፍ የሚነሳቸው የኢትዮጵያ ልጆች እልፍ አእላፍ ናቸው።

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የእነዚህ ወገኖችን ስሜት ጠንቅቀው የሚያውቁ ሰዎች ይህን ሁኔታ ሲፈልጉ ለግል ጥቅማቸው፣ ሲፈልጉ ለፖለቲካ ትርፍ ማካበቻ ሲጠቀሙበት ይታያል።

የኢትዮጵያ ልጆች ስለሀገራቸው ጉዳይ ስሜታዊ ስለሆኑ ምኑም የማይጨበጥ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨት የሚያታልሉ፣ በዚህም ገንዘብ የሚሰበስቡ ተበራክተዋል።

በተለይ በሰሜን ኢትዮጵያ ትክክለኛ የመረጀ ፍሰት እና ወጥነት አለመኖር፣ የግንኙነት መስመሮች መቋረጥ ማህበራዊ ሚዲያው የሀሰተኛ ፕሮፖጋንዳ፣ የሀሰተኛ መረጃ መፈንጫ እንዲሆን አድርጎታል።

የጥላቻ ንግግሩ በፊትም የነበረ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መስመሩን ለቋል፤ ተቆጣጣሪም አጥቷል።

ውድ ቤተሰቦቻችን የኢትዮጵያ ልጆች ስለሀገራችሁ ብዙ የምታስቡ፣ ሁኔታዋ የሚያሳስባችሁ ፣ ወቅታዊ ጉዳይ እንቅልፍ የሚነሳችሁ የማህበራዊ ሚዲያ የመረጃ ዝውውሮችን በጥንቃቄ እንድታዩ፣ በግጭት ፣ በዜጎች ስቃይ እና እንግልት፣ በእናቶች እና ህፃናት እንባ ገንዘብ የሚሰበስቡ ብዙ ናቸውና እንድትጠነቀቁ አደራ እንላለን።

ባልተገባ እንቅስቃሴ ያሉ፣ በንፁሃን ስቃይና እንግልት እንዲሁም በግጭት ውስጥ ትርፍ ለማግኘት ማህበራዊ ሚዲያውን የሚበጠብጡና ጭራሽ ስለሀገራቸው ደንታ የሌላቸው ወገኖች ድርጊታቸው ሚሊዮኖችን ችግር ላይ እየጣለ መሆኑን አውቀው ቢታቀቡ መልካም ነው።

#TikvahFamily

@tikvahethiopia