TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
ዛሬ የኢትዮጵያ መንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ መግለጫ የሰጡ ሲሆን ፤በመግለጫቸው ላይ ተከታዮቹን ነጥቦች አንስተዋል ፦

• ህወሓት በኮምቦልቻ ከተማ ሰርጎ በመግባት ሌሊቱን ከ100 በላይ የከተማዋን ወጣቶችን አሰልፎ መጨፍጨፉን ገልፀዋል።

• ህወሓት በደሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞች የግል እና የመንግስት ሀብቶችን እየዘረፈ እና እያወደመ ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

• በቦርከና ዳዋ ጨፌ አካባቢዎች ሕወሀት እየመጣ ነው በሚል በህ/ተ/ም/ቤት ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀው "ሸኔ" መንገድ የመዝጋት እና ሌሎች አፍራሽ ድርጊቶችን ለመፈፀም ቢሞክርም በአካባቢው ወጣቶችና በመከላከያ ሰራዊት አላማው ከሽፎበታል ብለዋል።

• መከላከያ ሰራዊቱ በክህደት የተፈጠሩበትን የውጊያ መዛነፎች እንደገና በማስተካከል አሁንም ከፍተኛ ተጋድሎ እያደረገ ይገኛል ብለዋል።

• "መንግስት ተዳክሟል፣ ሕወሀት አሸንፎ እየመጣ ነው" በሚል ደሴ ላይ እንደተፈፀመው አዲስ አበባን ጨምሮ ወደ ጭፈራ የገቡ ሀይሎች ከድርጊታቸው ሊታቀቡ ይገባል ፤ ይህንን አስመልክቶ መንግስት እርምጃ እየወሰደ ነው ብለዋል።

@tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ከዋግህምራ ዞን ተፈናቅለው በእብናት ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላው ድጋፍ ማድረጉን ገለጸ።

ማኅበሩ ከአለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ጋር በመተባበር ነው በእብናት ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች የምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች ድጋፍ ያደረገው።

ድጋፉ የተደረገው ለ 3 ሺ አባዎራዎች መሆኑን የገለጸው ማህበሩ ለእያንዳንዱ አባዎራ ፦
- የስንዴ ዱቄት፣
- የምግብ ዘይት፣
- ብሰኩቶች፣
- ምንጣፍ ፣
- ብርድልብስ፣
- መብራቶች፣
- የመመገቢያና የማብሰያ ዕቃዎች፣
- ጀሪካን፣ ሳሙና እና የሴቶች የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ያካተተ የተሟላ ጥቅል ተሰጥቷል ብሏል።

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በአገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል፣ በአፋር፣ በምስራቅ እና ሰሜን ወለጋ እንዲሁም መተከል አካባቢዎች ትኩረት አድርጎ ላለፉት አራት ወራት በሰጠው ሰብዓዊ አገልግሎት ከ600 ሺህ በላይ ዜጎችን መድረስ እንደቻለ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ዛሬ የሱዳን ጦር 2 ሰልፈኞችን ገደለ። በሱዳን የተካሄደውን ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት በመቃወም በ100 ሺ የሚቆጠሩ ሱዳኒያውያን ዛሬ አደባባይ ወጥተው ነበር። ሰልፉን ጠርተው የነበረው የዴሞክራሲ ተሟጋች ቡድኖች ናቸው። በመላ ሀገሪቱ እንዲካሄድ ዛሬ የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ የጀመረው ኦምዱርማን በተባለችው ከተማ ሲሆን ካርቱም ያሉ ሰልፈኞች ወዲያው ሰልፉን በመከተል የሲቪል አስተዳደሩ ወደ ቦታው እንዲመለስ…
#SUDAN : አብደላ ሃምዶክ እስር ላይ ናቸው።

ከሳምንት በፊት ከሱዳን ሽግግር መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትርነታቸው የተነሱት አብደላ ሃምዶክ አሁንም በእስር ላይ መሆናቸውን ጽ/ቤታቸው አሳውቋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት የአብደላ ሃምዶክን የቤት ውስጥ እስር በተመለከተ ዛሬ መግለጫ አውጥቷል፡፡

ጽ/ቤታቸው እንደገለጸው ከሆነ ከአብደላ ሃምዶክ ጋር ያለው የመገናኘት ሁኔታ ውስን ነው፡፡

ነፃነትን፣ ሰላምንና ፍትህን ለማስፈን የአብዮታዊ ሃይሎች አንድነትና ቅንጅት አስፈላጊ መሆኑንም ጽ/ቤቱ ጠቁሟል፡፡

ትላንት በሱዳን የተመድ ልዩ መልዕክተኛ ቮከር ፔርዝ በአብደላ ሃምዶክ መኖሪያ ቤት ተገኝተው ውይይት ማድረጋቸውን አድርገው የነበረ ሲሆን አሁንም የቤት ውስጥ እስረኛ ሆነው እንደሚገኙ ተናግረዋል።

ምንጭ፦ አል ዓይን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የ12ኛ ክፍል ፈተና ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 02/2014 ዓ.ም ለመስጠት ዝግጅት ተጠናቋል:: ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 02/2014 ዓ.ም ለመስጠት ዝግጅት ማጠናቀቁን አሳውቋል፡፡ ኤጀንሲው ከባለድርሻ አካላት ጋር በዋናነት የ2013 ፈተና ዝግጅት ላይ ያተኮረ ውይይት አካሂዷል። ከ617 ሺህ በላይ ተማሪዎች ለፈተናው…
የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተጠናቀቁ እንደሆነ ተገለጸ።

ፈተናዎች በቀጣይ ቀናት ወደ ፈተና ጣቢያዎች እንደሚሰራጩ የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ይልቃል ወንድሜነህ ተናግረዋል።

ፈተናዎቹ ወደ ፈተና ጣቢያዎች ከተሰራጩ በኋላ በየደረጃው ከተቋቋመው የኮማንድ ፖስት አባላት ጋር የፈተናውን ደህንነት ለማስጠበቅ በቅንጅት እንደሚሰራም ገልጸዋል፡፡

ፈተናው ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 02/2014 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይታወቃል።

@tikvahuniversity
#ችሎት

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ የክስ መዝገብ ተከሳሾች ላይ የዐቃቤ ሕግ መስክሮችን ለመስማት የያዘው ቀጠሮ ተፈጻሚ ሳይሆን ቀርቷል።

ፍርድ ቤቱ የዐቃቤ ሕግ ምስክሮችን ሳይሰማ የቀረበው የተከሳሽ ጠበቆች ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቤቱታ ማቅረባቸውን ተከትሎ ነው።

ከተከሳሽ ጠበቆች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ከድር ቡሎ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጃዋር መሐመድን ጨምሮ አራት ተከሳሾች በሌሉበት የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች ይሰሙ ሲል ያሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቤቱታ አቅርበዋል።

ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የቀረበው ይግባኝ መርምሮ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች እንዳይሰሙ ማዘዙንም ጠበቃው ከድር ቡሎሎ ተናግረዋል።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ በተከሳሾቹ ላይ የዐቃቤ ሕግ መስክሮችን ከዛሬ ሰኞ ጥቅምት 22/2014 ዓ.ም ጀምሮ ለመስማት ቀጠሮ ይዞ ነበር።

ሥራ አስፈጻሚው አካል ሕግ እስካላከበረ ድረስ ፍርድ ቤት አንገኝም" በማለታቸው አራቱ ተከሳሾች በሌሉበት ጉዳያቸው እንዲታይ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ አስተላልፎ እንደነበረ ይታወሳል።

የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተከሳሽ ጠበቆች አቤቱታን መርምሮ ውሳኔ ለመስጠት ለኅዳር 07 2014 ዓ.ም ቀጠሮ መስጠቱን ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
አቶ ተወልደ ገ/ማርያም የለውጥ አስመዝጋቢ የእውቅና ሽልማትን አሸነፉ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ተወልደ ገብረማርያም፣ የለውጥ አስመዝጋቢ የእውቅና ሽልማትን እንዳሸነፉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሳውቋል።

በጥቅምት 17 ቀን 2014 ዓ/ም በአቪየሽን አመራር ስራ አስፈጻሚዎች መድረክ/በአቪየተርስ አፍሪካ ታወር በተዘጋጀው መድረክ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተቋማዊ አመራር ሽልማት ዘርፍ 2021ን የእውቅና ሽልማትንም መቀዳጀታቸውን አየር መንገዱ ገልጿል።

@tikvahethiopia
#Somali : የሶማሊ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ የመሩት የሶማሊ ክልል የፀጥታ ኮሚቴ ሳምንታዊውን ስብሰባ ዛሬ አካሂዷል።

በፀጥታ ኮሚቴ ስብሰባው ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እና የፀጥታ አካላት የተገኙ ሲሆን፣ በወቅታዊ ሀገራዊ እና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት መደረጉ ተገልጿል።

ስብሰባው አራት ነጥቦችን በማውጣት የተጠናቀቀ ሲሆን እነዚህም ፦

1ኛ. ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮችን ትኩረት መስጠት፤
2ኛ. የክልሉን ውስጣዊ ሰላምና ፀጥታ ማጠናከር፤
3ኛ. ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያለውን ድንበር በንቃት መጠበቅና ሽብርተኛ ቡድኖች ወደ ክልሉ እንዳይገቡ መከላከል፤
4ኛ. የብሄር ግጭቶችን የሚያነሱ አካላት መከላከል የሚሉት ናቸው።

Credit : SMMA

@tikvahethiopia
#Ethiopia : የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች ማብራሪያ መስጠታቸውን ብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ ማምሻውን ዘግቧል።

በሽብርተኛ ድርጅትነት የተፈረጀው የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) የከፈተውን ጦርነት እና ጦርነቱን እየመራበት ያለው ህዝባዊ አካሄድ አስመልክቶ ማብራሪያ መስጠታቸውን የገለፀው ቴሌቪዥን ጣቢያው ህዝብ ለመከላከያ ሠራዊቱ ያሳየው ድጋፍ የሚበረታታ እንደነበር አስታውሰዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፥ በቅስቀሳ የመጣውን የህዝብ ኃይል ለማስተናገድ በመንግስት በኩል በቂ ዝግጅት እንዳልነበር በዛሬው መድረክ የተናገሩ ሲሆን አሁን ላይ ከዛ ሁኔታ እርምት ተወስዶ ስትራቴጂካዊ በሆነ መልኩ እየተሰራበት እንደሆነ መግለፃቸውን የቴሌቪዥን ጣቢያው ዘገባ ያስረዳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia : የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች ማብራሪያ መስጠታቸውን ብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ ማምሻውን ዘግቧል። በሽብርተኛ ድርጅትነት የተፈረጀው የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) የከፈተውን ጦርነት እና ጦርነቱን እየመራበት ያለው ህዝባዊ አካሄድ አስመልክቶ ማብራሪያ መስጠታቸውን የገለፀው ቴሌቪዥን ጣቢያው ህዝብ ለመከላከያ…
#ተጨማሪ

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በወሎ ግንባር በነበረ ውጊያ ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ ኃይሎች ተሳትፈዋል አሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት ለከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው።

" በወሎ ግንባር በነበረው ውጊያ ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ ኃይሎች ከአሸባሪው ቡድን ጋር ተሳትፈዋል" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጦርነቱ የተሳተፉት እንነዚህ አካላት ኢትዮጵያውያን ያልሆኑና የኢትዮጵያውያን ዝርያ የሌላቸው #ነጮች እና #ጥቁሮች ናቸው ብለዋል ፤ በጦርነቱ ላይ ተሳትፈውም መስዋትነት መክፈላቸውን ገልፀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ የገጠመችው ጦርነት ከአንድ ወገን ጋር ብቻ እንዳልሆነ በመረዳት ህዝቡ ዋጋ ለመክፈል ያለውን ፍቅር በተግባር ሊገልጽ እንደሚገባ አሳስበዋል ሲል ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#US : አሜሪካ TPLF ከአማራ እና አፋር ክልሎች እንዲወጣ በድጋሚ አሳሰበች። ዛሬ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) ከአማራ እና አፋር ክልል እንዲወጣ፤ ወደ ደሴ እና ኮምቦልቻ ከተማ የሚያደርገውን ግስጋሴ እንዲገታ አሳስቧል። ሚኒስቴሩ TPLF በከተሞች ላይ ከባድ መሳሪያዎችን ከመተኮስ እንዲቆጠብ ያሳሰበ ሲሆን ሁሉም ወገኖች ያለ ምንም…
#US #EU #USEmbassyAA

አሜሪካ በድጋሚ ተኩስ እንዲቆምና ድርድር እንዲጀመር ጠየቀች (ይህን ስትል በዚህ ሳምንት ብቻ ሁለተኛዋ ነው)

የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን በሰሜን ኢትዮጵያ የቀጠለው ጦርነት አሜሪካን እጅግ እንዳሳሰባት አሳውቀዋል።

ብሊንከን ጦርነቱ በስፋት መዛመቱ ሰብዓዊ ቀውሱን እንደሚያከፋው ጠቁመዋል።

ሁሉም ተፋላሚ ወገኖች ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ በድርድር ላይ የተመሠረተ ተኩስ አቁም እንዲያደርጉም በመግለጫቸው ላይ አሳስበዋል።

ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በተጨማሪ የአውሮፓ ህብረት የውጭ ግንኙነር ኃላፊ ጆሴፕ ቦሬል ሁሉም ወገኖች ያለ ቅድመ ሁኔታ ተኩስ እንዲያቆሙ ጥሪ አቅርበዋል።

ሁሉም ወገኖች የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦቱን እንዲያቀላጥፉ እና የጥላቻ ንግግሮችን እንዲያቆሙም አሳስበዋል።

የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ በአፍሪካ ቀንድ የአፍሪካ ኅብረት ልዩ ልዑክ ኦሌሴጎን ኦባሳንጆ ቁልፍ ሚና ሊጫወቱ እንደሚችሉ ህብረቱ እምነቱን ገልጿል።

በሌላ መረጃ ፦

አዲስ አበባ ያለው የአሜሪካ ኤምባሲ በሰሜን ኢትዬጵያ ያለውን ሁኔታ እየተከታተለ እንደሚገኝ ገልጿል።

በአማራ ክልል፤ ደሴና ኮምቦልቻን ጨምሮ ግጭት ተባብሷል ብሏል።

በአማራ እና በአፋር የሚገኙ የአሜሪካ ዜጎች የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃንን መከታተል እንዳለባቸው ፤ ግጭት በሚፈጠርባቸው አካባቢዎች ካሉም ለመጠለል መዘጋጀት እንዳለባቸውና እነዚህን አካባቢዎች መልቀቅ ሊያስቡበት እንደሚገባ አብቆ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
ዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት #Ethiopia

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 8 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 5,296 የላብራቶሪ ምርመራ 205 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 414 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

@tikvahethiopia