TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#EthiopianAirlines🇪🇹

የኢትዮጵያ አየር መንገድ “SKYTRAX” በ2021ዓ.ም ባዘጋጀው ምርጥ የአለማችን አየር መንገዶች ውድድር በአራት ዘርፎች ሽልማቶችን ለመቀዳጀት በቃ።

"በአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ" ዘርፍ ለተከታታይ 4 አመት ፣ "በአፍሪካ ምርጥ ቢዝነስ ክላስ" ዘርፍ ለተከታታይ 3 አመት፣ "በአፍሪካ ምርጥ ኢኮኖሚ ክላስ" ዘርፍ ለተከታታይ 3 አመት እና "በአፍሪካ ምርጥ የበረራ መስተንግዶ ሰራተኞች" ዘርፍ አንደኛ ለመሆን ችሏል።

አየር መንገዱ በSKYTRAX ምርጥ የአለማችን 100 አየር መንገዶች ዝርዝር ውስጥም በ37ኛ ደረጃ ለመቀመጥ የቻለ ሲሆን ውድድሩ በአለማችን ላይ የሚገኙ ከ350 የሚልቁ አየር መንገዶችን ያሳተፈ ነው።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA😷

ሀገራችን ኢትዮጵያ 🇪🇹 ተጨማሪ 46 ዜጎችን በኮቪድ-19 ሳቢያ አጥታለች።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 46 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 9,750 የላብራቶሪ ምርመራ ደግሞ 1,218 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 806 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

@tikvahethiopia
#ማስጠንቀቂያ

የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ከሚመለከተው አካል ፈቃድ ሳያገኝ ድሮኖችን ሲያበር የተገኘ በሕግ እንደሚጠየቅ አስጠንቅቋል።

ለዜጎች ሰላም መረጋገጥ እንዲሁም የቁልፍ መሰረት ልማቶችን ደህንነት በቴክኖሎጂ በመታገዝ ለመጠበቅና ስጋቶችን ለመከላከል ሲባል ድሮኖችን ያለምንም ህጋዊ ፈቃድ ለቀረፃ መጠቀምም ሆነ ማብረር እንደማይቻል መስሪያ ቤቱ አሳስቧል።

አንዳንድ ግለሰቦችና ድርጅቶች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከሚመለከተው አካል ህጋዊ ፈቃድ ሳያገኙ ድሮኖችን በሀገሪቱ በሚካሄዱ ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊ እና ህዝባዊ ሁነቶች ላይ ለቀረፃ ሲጠቀሙ እና ሲያበሩ እየተስተዋለ መሆኑን የገለፀው የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እነዚህ ግለሰቦችና ድርጅቶች ጉዳዩ በህግ የሚያስጠይቅ መሆኑን አውቀው ከህገ ወጥ ድርጊታቸው ሊታቀቡ እንደሚገባ በጥብቅ አስጠንቅቋል።

ከሚመለከተው አካል ፈቃድ ሳያገኝ ድሮኖችን ለቀረፃ ሲጠቀምና ሲያበር የተገኘ ማንኛውም አካል ወይም ግለሰብ በህግ ይጠየቃልም ብሏል።

Credit : የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት

@tikvahethiopia
* ግብፅ እና አሜሪካ !

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የብሄራዊ ፀጥታ ጉዳዮች አማካሪ ጃክ ሱሊቫን እና የግብፁ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲ ሲ ዛሬ በአካባቢያዊ ውጥረቶች , በዋሽንግተን እና በመካከለኛው ምስራቅ ግንኙነቶች ላይ መወያየታቸው ተሰምቷል።

ዛሬ ካይሮ ውስጥ በተካሄደው በዚህ ውይይት ላይ ከተነጋገሩባቸው ጉዳዮች መካከል የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጉዳይ እንደሚገኝበት ኤፒ ዘግቧል።

ሁለቱ አካላት የተነጋገሩባቸውን ዝርዝር ጉዳዮች ዘገባው አልጠቀሰም።

የግብፅ መንግስት በዜጎች ላይ ያካሂዳል በተባለው ጥሰት ላይም መነጋገራቸው ተገልጿል።

አሜሪካ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በግብፅ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ አለኝ ባለችው ስጋት ለግብፅ የምትሰጠውን 130 ሚሊዮን ወታደራዊ እርዳታ እንደምትይዝ አስታውቃ ነበር።

የግብፁ ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት ባወጣው መግለጫ የዛሬው ንግግር በእስራኤል እና በፍልሥጤማውያን መካከል የሰላም ድርድር እንደገና እንዲጀመር የሚደረጉ ጥረቶች ላይ ያተኮረ እንደነበር አሳውቋል።

የባይደን አማካሪ ግብፅ ከመግባታቸው በፊት በሳዑዲ አረቢያ እና በዩኤኢ ቆይታ የነበራቸው ሲሆን በቆይታቸው የየመን ጦርነት የሚያበቃበት መንገድ ፍለጋ ላይ መነጋገራቸው ተዘግቧል።

መረጃው የኤፒ እና ዴቼቨለ ነው።

@tikvahethiopia
#Amhara : በአሁን ሰዓት የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ መስራች ጉባኤውን እያካሄደ ነው።

ወይዘሮ ፋንቱ ተስፋየ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ተሹመዋል ፤ አቶ አማረ ሰጤ ደግሞ ምክትል አፈ ጉባዔ ሆነው ተሹመዋል።

Photo Credit : አሚኮ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Amhara : በአሁን ሰዓት የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ መስራች ጉባኤውን እያካሄደ ነው። ወይዘሮ ፋንቱ ተስፋየ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ተሹመዋል ፤ አቶ አማረ ሰጤ ደግሞ ምክትል አፈ ጉባዔ ሆነው ተሹመዋል። Photo Credit : አሚኮ @tikvahethiopia
#Update

የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ዶክተር ይልቃል ከፋለ ለክልሉ ርእሰ መሥተዳድርነት በእጩነት አቅርቧል፡፡

በአሁን ሰዓት እየተካሄደ በሚገኘው የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ መሥራች ጉባኤ ፤ የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ዶክተር ይልቃል ከፋለ ለክልሉ ርእሰ መሥተዳድርነት በእጩነት አቅርቧል፡፡

Credit : አሚኮ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ዶክተር ይልቃል ከፋለ ለክልሉ ርእሰ መሥተዳድርነት በእጩነት አቅርቧል፡፡ በአሁን ሰዓት እየተካሄደ በሚገኘው የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ መሥራች ጉባኤ ፤ የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ዶክተር ይልቃል ከፋለ ለክልሉ ርእሰ መሥተዳድርነት በእጩነት አቅርቧል፡፡ Credit : አሚኮ @tikvahethiopia
#BREAKING

ዶክተር ይልቃል ከፋለ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ሆነው ተሾሙ።

የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ እያካሄደ በሚገኘው የመሥራች ጉባኤ ዶክተር ይልቃል ከፋለን የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አድርጎ ሾሟል።

ዶክተር ይልቃል ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።

ዶክተር ይልቃል ፥ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲን ፕሬዝዳንት የመሩ ሲሆን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮንም በኃላፊነት መርተዋል።

@tikvahethiopia
#Sidama : በአሁን ሰዓት አዲሱ የሲዳማ ክልል መንግስት ምስረታ ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል።

በዚህ ጉባኤ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳደር፣ የም/ቤት አፈ ጉባዔ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ይሾማሉ።

Photo Credit : Sidama Media Network

@tikvahethiopia
#Gambella : በአሁን ሰዓት የጋምቤላ ክልል አዲስ መንግስት መስራች ጉባኤ እየተካሄደ ነው።

የክልሉ ምክር ቤት 6ኛ ዙር የምርጫ ጊዜ 1ኛ የስራ ዘመን የምስረታ ጉባኤውን እያካሄደ ሲሆን ጉባኤው ለቀጣይ 5 ዓመታት ክልሉን የሚመራ አዲስ አስተዳደር ይመሰርታል፡፡

የምክር ቤቱን አፈጉባኤዎች እንዲሁም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ይሾማሉ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Gambella : በአሁን ሰዓት የጋምቤላ ክልል አዲስ መንግስት መስራች ጉባኤ እየተካሄደ ነው። የክልሉ ምክር ቤት 6ኛ ዙር የምርጫ ጊዜ 1ኛ የስራ ዘመን የምስረታ ጉባኤውን እያካሄደ ሲሆን ጉባኤው ለቀጣይ 5 ዓመታት ክልሉን የሚመራ አዲስ አስተዳደር ይመሰርታል፡፡ የምክር ቤቱን አፈጉባኤዎች እንዲሁም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ይሾማሉ። @tikvahethiopia
#Update

የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት ወይዘሮ ባንቺአየሁ ድንገታን የምክር ቤቱ አፈጉባኤ አድርጎ ሾሟል።

ወ/ሮ ባንቻየሁ ከዚህ ቀደም የክልሉ ሴቶች እና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ፣ የወጣቶች እና ስፖርት ኃላፊ፣ የጋህዴን ፅ/ቤት ኃላፊ፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የገቢዎች ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል።

@tikvahethiopia
በምዕራብ ምዕራብ ሪጅን የ4G LTE አገልግሎት ጀመረ።

ዛሬ በአሶሳ ከተማ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ፍሬሕይወት ታምሩ በተገኙበት የምዕራብ ምዕራብ ሪጅን 4G LTE አገልግሎት ማስጀመሪያ ስነስርዓት ተካሂዷል።

አገልግሎቱ በምዕራብ ምዕራብ ሪጅን የሚገኙ ፦
- ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አካባቢ ፣ ጉባ
- በመተከል ዞን ፥ ግልገል በለስ
- አሶሳ እና ባምባሲ ከተሞች ተጠቃሚ ያደርጋል።

በአገልግሎቱ ከ108 ሺህ በላይ ደንበኞች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ወ/ሪት ፍሬህይወት አሳውቀዋል።

ወ/ሪት ፍሬህይወት ፥ የአንደኛው ምዕራፍ የ4G LTE አድቫንስድ አገልግሎት መጠናቀቁን የገለፁ ሲሆን 106 ከተሞች ለማዳረስ ታቅዶ በ92 ከተሞች ስኬታማ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል።

ወደምዕራብ ሪጅን የተደረገው የአገልግሎቱ ማስፋፊያ ፈታኝ እንደነበር የጠቆሙ ሲሆን በባለድርሻ አካላት የተጠናከረ ድጋፍ ስራው መጠናቀቁን ገልፀዋል። የሁለተኛው ምዕራፍ ማስፋፊያ ስራ በተጓዳኝ እየተከናወነ መሆኑንም አሳውቀዋል።

Credit : ENA
Photo : CAPITAL

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Gambella : በአሁን ሰዓት የጋምቤላ ክልል አዲስ መንግስት መስራች ጉባኤ እየተካሄደ ነው። የክልሉ ምክር ቤት 6ኛ ዙር የምርጫ ጊዜ 1ኛ የስራ ዘመን የምስረታ ጉባኤውን እያካሄደ ሲሆን ጉባኤው ለቀጣይ 5 ዓመታት ክልሉን የሚመራ አዲስ አስተዳደር ይመሰርታል፡፡ የምክር ቤቱን አፈጉባኤዎች እንዲሁም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ይሾማሉ። @tikvahethiopia
#Update

አቶ ኡሞድ ኡጁሉ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ።

የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት አቶ ኡሞድ ኡጁሉን የክልሉ ርዕሠ-መስተዳድር አድርጎ ሾሟል።

አቶ ኡሞድ ኡጁሉ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት፣ የክልሉ ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር እንዲሁም ከህዳር 1/2011 ዓ.ም ጀምሮ የክልሉ ርእሠ መስተዳድር ሆነው አገልግለዋል።

አሁንም ለቀጣይ 5 አመታት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሆነው እንዲያገለግሉ በምክር ቤቱ ተሹመዋል።

Credit : የጋምቤላ ክልል ፕሬስ ሴክሬተሪያት

@tikvahethiopia
#Update

አቶ ጌታቸው ጀምበር (እጩ ዶክተር) የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ሆነው ተሹመዋል።

Credit : AMC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የአማራ ክልል ፕሬዜዳንት ዶክተር ይልቃል ከፋለ ያቀረቧቸው እጩ የስራ ኃላፊዎች ከላይ በምስሉ የምትመለከቷቸው ናቸው። ከቀረቡት እጩዎች መካከል 75 በመቶ አዲስ የሥራ ኃላፊዎች መሆናቸው ተገልጿል። @tikvahethiopia
* TAHIR MOHAMMED

የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት ዶክተር ይልቃል ከፋለ ካቀረቧቸው እጩዎች መካከል አቶ ጣሂር ሙሃመድ ይገኙበታል።

አቶ ጣሂር ከአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) አመራሮች መካከል ሲሆኑ በአማራ ክልል የቱሪዝም ቢሮን በኃላፊነት እንዲመሩ ነው የቀረቡት።

@tikvahethiopia