TIKVAH-ETHIOPIA
ነዋሪዎችን ያማረረው ህገወጥ ተኩስ... በጎንደር ከተማ በተለይም ማራኪ ክፍለ ከተማ ሰሞኑን የተለያዩ ምክኒያቶች ስበብ በማድረግ ህገ ወጥ ተኩስ እየተፈጸመ ይገኛል። ይህን ምክኒያት በማድረግ የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች ትላንትናው ውይይት አድርገዋል። የውይይቱ ተሳታፊዎች በአካባቢያቸው የሚፈፀመውን ህገወጥ ተኩሱን አውግዘዋል። የጦር መሳሪያ የያዙ ግለሰቦች የወታደራዊ የጦር መሳሪያው አያያዝ ህግና…
#GONDAR : በጎንደር ከህገወጥ ተኩስ ጋር በተያያዘ የከተማው ፖሊስ መሳሪያ የማስወረድ ስራ እና ሰዎችን የማሰር እርምጃ እየወሰደ ነው።
ከትንላት ጀምሮ እስከ አሁን ሰአት ድረስ የጎንደር ከተማ ፖሊስ ከ50 የሚበልጥ የጦር መሳሪያ ያስወረደ ሲሆን ከህገወጥ ተኩስ ጋር በተያያዘ ከ30 በላይ ሰዎችን ማሰሩንና ፍ/ቤት በማቅረብ ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑን ለጎንደር ከተማ ኮሚኒኬሽን አሳውቋል።
ስራው እየተሰራ የሚገኘው ከፖሊስ፣ ሚሊሻ፣ አድማ ብተና፣ ፌደራል ፖሊስና ልዩ ሃይል እንዲሁም ከከተማው የክፍለ ከተማ እና የቀበሌ አመራሮችን ባካተት ቡድን ነው ተብሏል።
የጎንደር ከተማ ፓሊስ መምሪያ ኃላፊ የሆኑት ኮማንደር አየልኝ ታክሎ ማምሻውን ለጎንደር ኮሚኒኬሽን በሰጡት ቃል፤ " ያለአግባብ መሳሪያ ሲተኩሱ የነበሩና ከህግ ለማምለጥ የተደበቁ ግለሰቦችንም የገቡበት ገብተን በቁጥጥር ስር ለማዋል ስራ እየተሰራ ነው" ብለዋል።
ኮማንደሩ አክለው ፥ "ህብረተሰቡ የሚሰጠውን ማንኛውም ጥቆማ በመቀበል ቦታው ድረስ የፀጥታ አካላትን በመላክ ህግ የማስከበር ስራችንን አጠናክረን እንቀጥላለን" ያሉ ሲሆን "ህብረተሰቡ ይህን ተረድቶ ትብብሩን ሊቀጥል ይገባል" ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የህገ ወጥ ተኩስ ጉዳይ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎችን በእጅጉ ሰላም የነሳቸው እና ያማረራቸው ጉዳይ መሆኑ በተደጋጋሚ ሲገለፅ እንደነበር ይታወቃል ፤ ከጊዜ ወደጊዜ ይህ ድርጊት ይቆማል ተብሎ ቢታሰብም አሁንም ድረስ ቀጥሏል። ለችግሩ መፍትሄ ለመስጠት በተለያየ ጊዜ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት መደረጉ የሚዘነጋ አይደለም።
@tikvahethiopia

" ደም ይለግሱ "
ከመስከረም 19 - መስከረም 21/2014 የሚቆም የደም ልገሳ መርሃ ግብር በልብ ማዕከል-ኢትዮጵያ እየተካሄደ ነው።
" ነገሮችን በተረጋጋ ሁኔታ እና በፍቅር ለማየት የልብ ሚና ከፍተኛ መሆኑ አያጠራጥርም፤ ልብ ደግሞ ያለ ደም ባዶ ነው ስለዚህም ሁላችሁም በኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ እየመጣችሁ ከመስከረም 19 እስከ 21 ድረስ አብራችሁን ሆናችሁ ደም ለግሱ ፤ እንዳትቀሩብን።"
ቦታ ፦ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በር ቁጥር 4 ሲሆን ምናልባት ተጨማሪ መረጃ ከፈለጋችሁ በ 0977909090 ላይ መደወል ትችላላችሁ።
ይህን መልዕክት ለወዳጆቻችሁ አጋሩ!

" ግሸን ደብረ ከርቤ ዓመታዊ ንግስ በዓል "
በየዓመቱ መስከረም 21 በደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ የግሸን ደብረ ከርቤ (ግሽን ማርያም) ዓመታዊ የንግስ በዓል ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝበ ክርስቲያን በሚገኝበት ይከበራል።
የዘንድሮውም የንግስ በዓል በሠላም እንዲጠናቀቅ ፌዴራል ፖሊስ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን ገልጿል።
ፖሊስ የፀጥታው ሥራ አጠናክሮ እየሰራ በመሆኑ ከደብረ ብርሃን ጀምሮ እስከ ግሸን ማሪያም ድረስ ከፍተኛ የቅኝት (የፓትሮል ) ውጠራ ሥራ በመስራት ላይ ይገኛል።
በአሁኑ ወቅት በአካባቢው ላይ ምንም ዓይነት የፀጥታ ችግር አለመኖሩን ፌዴራል ፖሊስ ያሳወቀ ሲሆን በቀጠናው ላይ የሚገኙ ፦
- የአትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የሰሜን ፈጥኖ ደራሽ
- የአማራ ክልል ልዩ ኃይል
- የከተማው ፓሊስ ጋር በመቀናጀት ምንም አይነት የፀጥታ ችግር እንዳይፈጠር አካባቢውን በጥምረት እየጠበቁ እንደሆኑም አመልክቷል።
ህብረተሰቡ በአካባቢው ለፀጥታ ስጋት የሆኑ ተግባሮች ሲያጋጥሙት በፍጥነት አቅራቢያው ላሉ የፀጥታ አካላት ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቧል።
በሌላ በኩል ፥ የዘንድሮው የግሽን ደብረ ከርቤ ዓመታዊ በዓል ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅና እንግዶችን በወሎ የእንግዳ አቀባበል በማስተናገድ የተሳካ በዓል ማሳለፍ እንደሚገባ የደሴ ከንቲባ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ከንቲባው አቶ አበበ ገብረ መስቀል ትላንት ለኤፍ ቢ ሲ በሰጡት ቃል ÷ ደሴ ከተማ በርካታ የበዓሉ ተጓዦች የሚያርፍባት በመሆኑ በተለይ የከተማው ነዋሪ እንግዶችን ሊንከባብ ይገባል ብለዋል።
በዓሉን ተከትሎ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ምንም አይነት የዋጋ ጭማሬ እንዳያደርጉ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል።
ያንብቡ : telegra.ph/Meskerm-21-09-29

በድሬዳዋ ዛሬ አዲስ መንግስት ይመሰረታል።
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ዛሬ የምስረታ ጉባኤ ያካሂዳል።
በምስረታ ጉባኤው ለቀጣይ 5 ዓመታት ከተማዋን የሚመራ አዲስ አስተዳደር ይመሰርታል፡፡ ጉባኤው የምክር ቤቱን አፈጉባኤዎች የሚመርጥ ሲሆን የከተማዋን ከንቲባ ይሾማል።
በተጨማሪም ጉባኤው የካቢኔ አባላት ሹመትንም እንደ ሚያፀድቅ ይጠበቃል።

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#WFP : የዓለም ምግብ ፕሮግራም /WFP/ ባለፉት ጥቂት ቀናት 61 ተሽከርካሪዎች ከትግራይ ክልል መመለሳቸውን አሳውቋል ፤ በቀጣዮቹ ቀናት/ሳምንታት ተጨማሪ ተሽከርካሪዎች ይመለሳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጿል።
ድርጅቱ ፥ ተሽከርካሪዎቹ ጉዟቸውን መቀጠላቸውን ለማረጋገጥ ፣ የሰብአዊ ዕርዳታ አቅርቦትን ለማመቻቸት ማንኛውም የሎጅስቲክስ ችግር ለመቅረፍ ከአጓጓዦች ጋር መስራቱን እንደሚቀጥል አሳውቋል።
ባለፉት 3 ሳምንታት 6,150 ሜትሪክ ቶን ምግብ የጫኑ 5 ኮንቮዮች - 171 የጭነት ተሽከርካሪዎች ትግራይ መግባታቸውን የዓለም ምግብ ፕሮግራም የገለፀ ሲሆን ለአንድ ወር 350,000 ሰዎችን ለመመገብ በቂ መሆኑን ጠቅሷል።
አክሎም ፥ " ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ ለማድረስ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ነፃ የእርዳታ ፍሰት መኖሩ አስፈላጊ ነው" ብሏል።

" አንዳንድ የአሜሪካና የአውሮፓ የተራድኦ ድርጅቶች የተለያዩ ደባዎችን እየሰሩ ነው "- የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን
የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አንዳንድ የአሜሪካና የአውሮፓ የተራድኦ ድርጅቶች ለተፈናቃይ ወገኖች እርዳታ ለማቅረብ ተቀባይነት የሌላቸውን ምክንያቶች እያቀረቡ ነው ብሏል።
በኮሚሽኑ ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ደበበ ዘውዴ ለብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ-ኢብኮ በሰጡት ቃል፥ የተራድኦ ድርጅቶቹ "ጦርነት ባለበት እንዴት እንገባለን"፣ "የተረጋጋ ሠላም አምጡልን" እንዲሁም "ሃብት የለንም" የሚሉ ተቀባይነት የሌላቸውን ምክንያቶችን እንደሚያቀርቡ ተናግረዋል።
ዓለም አቀፍ መርሁ በሚያዘው መሰረት የተራድኦ ድርጅቶች ኢትዮጵያ ውስጥ እስከ ተንቀሳቀሱ ድረስ የኢትዮጵያን ህግ ጠብቀው የሰብዓዊ እርዳታ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው ያሉት አቶ ደበበ የተራድኦ ድርጅቶቹ ችግሮች ባሉባቸው አካባቢዎች ገብተው እርዳታ የማቅረብ የውል ግዴታ ቢቀበሉም ተግባራዊ አለመሆኑን ገልፀዋል።
መንግስት የተራድኦ ድርጅቶቹ ገበተው እርዳታ እንዲያቀርቡ ተደጋጋሚ ጥሪ ቢያቀርብም ጥቅሞቻቸውን ለማስጠበቅ የሚፈልጉ አንዳንድ የአሜርካና የአውሮፓ የተራድኦ ድርጅቶች የተለያዩ ደባዎችን እየሰሩ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
አቶ ደበበ፥ "ይህን ደባ ለማለፍ የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት ተደርጎ በወሮታና ኮምቦልቻ በቂ የእለት ደራሽ እርዳታ ክምችት አለ" ሲሉ አስረድተዋል። ችግሮችን በቅርበት ተረድቶ አፈጣኝ ምላሽ ለመስጠት እንዲያስችልም የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ማስተባበሪያ ማዕከለት በባህር ዳር፤ ኮምቦልቻና አፋር ተቋቁሞ እየተሰራ መሆኑንም ገልፀዋል።
ማዕከላቱ የጤና፣ ውኃ፣ ምግብና የስነ ልቦና እና የጸጥታ ችግሮችን በቅርበት ለመፍታት እንደሚያስችሉ ነው ለብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጡት ቃል የጠቆሙት።

የWHO ሰራተኞች በወሲባዊ ብዝበዛ ላይ መሳተፋቸው ተረጋገጠ።
አንድ በገለልተኛ ኮሚሽን የተዘጋጀ ሪፖርት በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ተቀስቅሶ የነበረውን የኢቦላ ወረርሽኝን ለመግታት ተሰማርተው በሴቶችና በልጃገረዶች ላይ ወሲባዊ ጥቃት ካደረሱ 83 የእርዳታ ሠራተኞች መካከል የዓለም ጤና ድርጅት ሠራተኞች እንደሚገኙበት ማመልከቱን ቢቢሲ ዘገበ።
9 የአስገድዶ መድፈር ክሶችን ያካተተው ይህ በደል እአአ ከ2018 እስከ 2020 ባለው ጊዜ የደረሰ ሲሆን በሀገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ሠራተኞች የተፈጸመ ነው።
ሪፖርቱ ይፋ የተደረገው ከ50 በላይ የአካባቢው ሴቶች የወሲብ ጥቃት እንደተፈጸማቸውን ሪፖርት ካደረጉ በኋላ ነው።
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ጉዳዩን "ይቅርታ የማያሰጥ" ሲሉ ገልጸውታል።
ባለ 35 ገጹ ይህ ሪፖርት ምርመራ ከተደረገ በኋላ በገለልተኛ ኮሚሽን የተዘጋጀ ነው።
ሥራ ለማግኘት በልዋጩ ወሲብ እንዲፈፅሙ እንደተገደዱ የገለጹ በርካታ ሴቶችን ቃለ መጠይቅ ያደረገው ኮሚሽኑ ወንጀሉን ፈጽመዋል ተብለው ከተጠረጠሩት 83 ሰዎች መካከል 21ዱ በዓለም ጤና ድርጅት ተቀጥረው እንደሚሠሩ አረጋግጧል።
የዓለም ጤና ድርጅት እስካሁን በድርጅቱ ተቀጥረው የሚሠሩ የ4 ሰዎችን ውል ያቋረጠ መሆኑን ገልጾ ተጨማሪ እርምጃዎች እንደሚወሰዱ ቃል ገብቷል።
ዶ/ር ቴድሮስ ለተጎጂዎችና ከጥቃቱ ለተረፉት በቀጥታ ይቅርታ ጠይቀዋል።
ዶ/ር ቴድሮስ ፥ "እናንተን ለማገልገል እና ለመጠበቅ በዓለም ጤና ድርጅት ተቀጥረው በሚሠሩ ሰዎች በደረሰባችሁ ነገር አዝናለሁ። ወንጀለኞቹ ይቅርታ እንዲደረግላቸው ሳይሆን ተጠያቂ እንዲሆኑ ማድረግ ቀዳሚ ተግባሬ ነው" ብለዋል።
ተጨማሪ ያንብቡ : https://telegra.ph/BBC-09-29-3

#Metekel በመተከል የፀጥታ ችግር 194 ትምህርት ቤቶች መጎዳታቸው ፤ ከ194ቱ ውስጥ 56 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ፤ 138 ትምህርት ቤቶች ደግሞ በከፊል መፍረሳቸው ተገለፀ።
ይህ የተገለፀው ዛሬ በአሶሳ በጀመረው 23ኛው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አቀፍ ትምህርት ጉባኤ ላይ ነው።፡
በዚሁ መድረክ ላይ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ቢንያም መንገሻ እንደተናገሩት ፤ በመተከል ግጭት ትምህርት ቤቶቹ የተጎዱት በ2013 ዓ.ም ሲሆን እነዚህም የመጀመሪያ፣ መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ናቸው ብለዋል።
በፀጥታ ችግር ከተጎዱ 194 ትምህርት ቤቶች ፥ 56 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን፤ 138 ትምህርት ቤቶች ደግሞ በከፊል መፈራረሳቸውን ኃላፊው ጠቁመዋል።
ትምህርት ቤቶቹ 69 ሺህ ተማሪዎች የሚማሩባቸው እንደነበሩ ገልፀዋል።
የትምህርት ቢሮ ኃላፊው ፥ የተጎዱ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት እንዲሁም የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የ10 ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ ተዘጋጅቶ እየተሠራ ነው ሲሉ ጠቁመዋል።
Credit : ENA

በድሬዳዋ ዛሬ አዲስ መንግስት ይመሰረታል። የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ዛሬ የምስረታ ጉባኤ ያካሂዳል። በምስረታ ጉባኤው ለቀጣይ 5 ዓመታት ከተማዋን የሚመራ አዲስ አስተዳደር ይመሰርታል፡፡ ጉባኤው የምክር ቤቱን አፈጉባኤዎች የሚመርጥ ሲሆን የከተማዋን ከንቲባ ይሾማል። በተጨማሪም ጉባኤው የካቢኔ አባላት ሹመትንም እንደ ሚያፀድቅ ይጠበቃል። @tikvahethiopia
* Update
አቶ ከድር ጁሀር የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ ሆነው ተሾሙ።
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት በሙሉ ድምፅ ነው ሹመታቸውን ያፀደቀው።
በድሬዳዋ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ሆነው ሲያገለግሉ የቆዪት አቶ ከድር ጁሀር የአስተዳደሩ ከንቲባ በመሆን ቃለ መሀላ ፈፀመዋል።
በሌላ በኩል ፥ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፈትህያ አደም ሆነው በሙሉ ድምፅ ተሹመዋል።
የአስተዳደሩ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ በመሆን ወ/ሮ ፈትያ አደም ቃለ መሀላ ፈፅመዋል።
Credit : የድሬዳዋ አስተዳደር ኮሚኒኬሽን

#Khartoum : 5 የሱዳን ደህንነት አባላት ካርቱም ውስጥ በታጣቂዎች ተገደሉ።
የደህንነት አባላቱ የተገደሉት ከታጣቂዎች ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ መሆኑን ኤፒን ዋቢ አድርጎ አል ዓይን በድረገፁ አስነብቧል።
ታጣቂዎች የISIS የሽብር ቡድን አባላት ሳይሆኑ እንዳልቀሩ ተገልጿል።
የሱዳን የብሔራዊ የደህንነት አገልግሎት ባወጣው መግለጫ 5 አባላቱ በተሰነዘረባቸው ጥቃት ህይወታቸው ማለፉን አረጋግጦ ፥ አባላቱ የተገደሉት የIS የሽበር ቡድን አባላት ናቸው በሚል የተጠረጠሩ ሰዎችን ለመያዝ ስምሪት ላይ እያሉ በተከፈተ የተኩስ ልውውጥ ነው ብሏል።
በዚህ አደጋ ተሳትፈዋል በሚል 11 የውጭ አገራት ዜግነት ያላቸው ተጠርጣሪዎች መያዛቸውንም መስሪያ ቤቱ አክሎ ገልጿል።
IS የተሰኘው የሽብር ቡድን እስካሁን በሱዳን ለተሰነዘረው ጥቃት ሃላፊነት መውሰዱን ያልገለጸ ሲሆን የሱዳን መንግስት ግን ጥቃቱ በዚህ የሽብር ቡድን እንደደረሰ ገልጿል።
አሜሪካ ከዚህ በፊት IS የሽብር ቡድን በሱዳን ሊንቀሳቀስ እና ጥቃት ሊሰነዝር ይችላል የሚል ስጋት እንዳላት ገልጻ ነበር።
የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ በደህንነት አባላቱ ሞት ማዘናቸውን ገልፀዋል።
Credit : አል ዓይን

" ስራ ዝግ ሆኖ ይውላል "
ነገ መስከረም 20 የሚካሄደው ምርጫን እንዲሁም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝበ ውሳኔ ተከትሎ ስራ ዝግ ሆኖ እንደሚውል ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አሳውቋል።
ስራ ዝግ ሆኖ የሚውለው ፦
- በሐረሪ ክልል፣
- በሶማሌ ክልል፣
- በደ/ብ/ብ/ህ ክልል ፦
• በምእራብ ኦሞ ዞን፣
• በደቡብ ኦሞ ዞን፣
• በቤንች ሸኮ ዞን፣
• በሸካ ዞን፣
• በጌዲዮ ዞን፣
• በሃድያ ዞን፣
• በጉራጌ ዞን፣
• በጋሞ ዞን፣
• በካፋ ዞን፣
• በወላይታ ዞን ፣
• በዳውሮ ዞን፣
• በባስኬቶ ልዩ ወረዳ እና በኮንታ ልዩ ወረዳ ነው።
ምርጫ ቦርድ ዜጎች እለቱን ለድምጽ መስጫ ብቻ መጠቀማቸው ስለሚያስፈልግ ከላይ በተጠቀሱት ክልሎች እና ዞኖች የሚገኙ የፌዴራል እና የክልል መንግስታዊ ተቋማት መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም ስራ ዝግ እንዲያደርጉ አሳውቋል።
ቦርዱ ፥ የአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት፣ ሆስፒታሎች፣ የእለት ተእለት አገልግሎት ሰጪዎች (ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች፣ የትራንስፓርት አገልግሎት …ወዘተ) በዝግ ቀናት የሚያደርጉትን አገልግሎት በተመሳሳይ ማከናወን እንደሚችሉ ገልጾ እነዚህ ተቋማት እንቅስቃሴ መዘጋት አይጠበቅባቸውም ብሏል።
የትራንስፓርት አገልግሎት በተለመደው መንገድ የሚቀጥል ቢሆንም በተጠቀሱት ክልሎች እና ዞኖች ዜጎች ድምጽ ከመስጠት ውጪ ከፍተኛ እንቅስቃሴን የሚፈልጉ ሁነቶችን እና እቅዶችን እንዳይዙ እና እንቅስቃሴያቸውን ድምጽ ለመስጠት ብቻ እንዲያደርጉም ቦርዱ አበረታቷል።

* Update አቶ ከድር ጁሀር የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ ሆነው ተሾሙ። የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት በሙሉ ድምፅ ነው ሹመታቸውን ያፀደቀው። በድሬዳዋ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ሆነው ሲያገለግሉ የቆዪት አቶ ከድር ጁሀር የአስተዳደሩ ከንቲባ በመሆን ቃለ መሀላ ፈፀመዋል። በሌላ በኩል ፥ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፈትህያ አደም ሆነው በሙሉ ድምፅ ተሹመዋል። የአስተዳደሩ…
#Diredawa : ድሬዳዋ ከተማ ዛሬ አዲስ መንግስት መስርታለች።
ዛሬ ከሰዓት በተካሃደው የድሬዳዋ ከተማ አዲስ መንግስት መስረታ የከተማው ምክር ቤት አቶ ከድር ጁሃርን በሙሉ ድምፅ ከንቲባ አድርጎ ሲሾም በከንቲባው የቀረቡትን የካቤኔ አባላትንም ሹመት አፅድቋል።
ሹመታቸው በምክር ቤት የፀደቀላቸው የካቢኔ አባላት የሚከተሉት ናቸው ፦
1. ም/ከንቲባና ንግድ ቢሮ - ሀርቢ ቡህ ወርሰሜ
2. የፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ/ የመንግስት ተጠሪ - ኢብራሂም ዩሱፍ
3. ፋይናንስ ቢሮ - ሱልጣን አሊይ
4. ቴክኒክና ሙያ ቢሮ - ሮቤል ጌታቸው
5. ግብርና ቢሮ - ኑረዲን አብደላ
6. ኮንስትራክሽን - ኢ/ር ጀማል ኢብራሂም
7. ጤና ጥበቃ ቢሮ - ለምለም በዛብህ
8. ፍትህ ቢሮ - አብዱሰላም አህመድ
9. መሬት ልማት ቢሮ - ሳጂድ አሊይ ሁሴን
10. ትምህርት ቢሮ - ሙሉካ መሀመድ ሁሴን
11. መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ - ኢስቂያስ ታፈሰ
12. ሴቶችና ህጻናት - ፈጡም ሙስጠፋ ሀቢብ
13. ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ - አቡበከር አዶሽ ኦልሀዬ
14. ዋናው ኦዲተር - ጫልቱ ሁሴን
15. ብዙሃን መገናኛ - አብዱሰላም መይደኔ
Credit : ድሬዳዋ ኮሚኒኬሽን