ቁጥሮች !
ባጠናቀቅነው ነሀሴ ወር በይፋ የተገለፁ ህገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውሮች ፦
- መነሻውን ከጋምቤላ ያደረገ በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-15074 አ/አ በሆነ ዶልፊን ህዝብ ማመላለሻ ሲዘዋወር የነበረ ህገወጥ መሳሪያ ከነተጠርጣሪዎቹ በዚህ ወር ተይዟል፤ የተያዘው መሳሪያ በቁጥር 12 ክላሽንኮቭ እና 5 ጥይት መያዣ ነው።
- የሰሌዳ ቁጥር A76390 በሆነ ቪትዝ መኪና 5 ክላሽንኮቭ ከ132 ጥይት ጋር ሲዘዋወር በድንገተኛ ፍተሻ ተይዟል (እንደ ጎንደር ከተማ ፖሊስ መረጃ)
- በሀመር ወረዳ በዚህ እያጠናቀቅን ባለነው ወር ውስጥ በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 10 መሳሪያ፣ 14 ክላሽ ጥይት፣ 3 የክላሽ መጋዘን ተይዟል።
- በአዲስ አበባ ቦሌ ክ/ ከተማ ወረዳ 4 ልዩ ቦታው ውሃ ልማት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው አምባሳደር ፔንሲዮን ውስጥ 10 ባለሰደፍና 10 ታጣፊ ክላሽንኮቭ ጠብመንጃዎች እና 17 የክላሽንኮቭ ጥይት ካርታዎች ተይዘዋል። ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ 2 ግለሰቦች ተይዘዋል።
- በባህር ዳር ከተማ በአፄ ቴዎድሮስ ክ/ከተማ በአንድ ግለሰብ ቤት በተደረገ ፍተሻ 1 ሺህ 669 የብሬን ጥይት በዚህ ወር ተይዟል።
- ከከሚሴ ወደ አ/አ ሊዘዋወር የነበረ 53 ህገወጥ ጩቤ ፣ 30 የጥይት መያዣ ካርታ፣ 30 እንግብ፣ 30 የትጥቅ መያዣ ቀበቶ ሸዋ ሮቢት ላይ ተይዟል።
- በገንደውሃ ከተማ አንድ ግለሰብ 30 የክላሽ ካዝናዎችን በህገወጥ መንገድ በኩርሲ ወንበሮች ይዞ ሲንቀሳቀስ ተይዟል።
- በከፋ ዞን ጊምቦ ወረዳ በኬላ ላይ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ 634 ፍሬ የክላሽ ጥይትና 50,055 ብር ከነተጠርጣሪዎቹ ተይዟል።
NB : ከላይ የተጠቀሱት የህገወጥ መሳሪያ ዝውውሮች በዚህ ወር ከተሰሙት መካከል ጥቂቶቹ ናቸው ፤ ሌሎች ተዳራሽ ያልሆኑ ሊኖሩ ይችላሉ #ጥንቃቄ
@tikvahethiopia

6.7 ቢሊዮን ችግኝ ተተክሏል !
የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ሦስተኛውን ዙር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር መጠናቀቁን ዛሬ አሳውቀዋል።
የመርሀግብሩን መጠናቀቅ አስመልክቶ ባሰራጩት አጭር መልዕክት ፥ የሦስተኛው ዙር የአረንጓዴ ዐሻራ በስኬት በመጠናቀቁ እንኳን ደስ ያለን" ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዘንድሮው መርሀ ግብር 6.7 ቢሊየን ችግኞችን መተከላቸውን አሳውቀዋል፤ ይህም ከተቀመጠው ግብ ያለፈ መሆኑን ነው ያነሱት።
ከዚህ ከ2013 የአረንጓዴ ዐሻራ መርኃ ግብር መጠናቀቅ ጋር በተያያዘ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ የማጠቃለያ ስነስርዓት ዛሬ ተካሂዶ ነበር።
በዚህ ስነስርአት ላይ በሶስት ዓመታት ውስጥ ከ18 ቢሊየን የሚበልጡ ችግኞች መተከላቸው ተነግሯል ፤ በአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በአራት ዓመታት ውስጥ 20 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል ነበር የታሰበው።

#Ethiopia
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ #በጳጉሜ_ወር ለሀገር ሰላም እና አንድነት በመላው ዓለም በምትገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፀሎት እና ምህላ ወስኗል።
ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የሲዳማ፣ ጌዴኦ አማሮና ቡርጂ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ፥ ቋሚ ሲኖዶሱ 5ቱን የጳጉሜ ቀናት በፀሎትና ምህላ እንዲታሰብ መወሰኑን ገልፀዋል።
ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ፥ 2013 ዓ.ም ብዙ ችግሮችን ያሳየ መሆኑን ያነሱ ሲሆን "በፈተናው ውስጥም ቢሆን ግን ብዙ በረከቶችን ያሳየን ነገሮች አሉ" ብለዋል። እንደሀገር ፤ እንደዓለምም የተከሰቱ ችግሮች ወደቀጣይ ዓመት አብረው እንዳይተላለፉ እግዚአብሔርን በፀሎት መጠየቅ ስላለብን ይህ ውሳኔ ተላልፏል ሲሉ አስረድተዋል።
አክለውም፥ "ቤተክርስቲያን በሀገራችን ውስጥ ያለው ጦርነቱ ፣ ረሃቡ ፣ ስደቱ ፣ መፈናቀሉ ፣ ከቦታ ቦታ ያለው ህዝባችን በስጋት እንዳይኖር ይሄን ሁሉ ጉዳዬ ነው ብላ ወደእግዚአብሔር ማቅረብ አለብን በሚል ቀናቱን በፀሎት እና በምህላ በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እንዲታሰብ ወስናለች" ብለዋል።
"ወደሰዎች ሳይሆን ወደእግዚአብሔር በመፀለይ ለውጥ ይመጣል ፤ ያጣነው ሰላማችን ይመለሳል ፤ ወደእግዚአብሔር መፀለይ ሀገራችን ኢትዮጵያ ያለው ብሩህ ተስፋ፤ ጨለማ ውስጥ ነን ብሎ ለሚያስብ ህዝብ ብርሃን የሆነ ህይወት እንዲኖረው የሀገራችንም ከፍታ እንዲኖር ያደርጋል" ብለዋል።
"በዚህች ሰዓት ይሄ ፀሎት ወሳኝ በመሆኑ ትንሹም ትልቁም በሀገር ውስጥም በውጭም ያለው ቢፆም ቢፀልይ መፍትሄ ይመጣል ፤ አምስቱን ቀን በፀሎት እና በምህላ ማሳለፍ ይገባል" ሲሉ አክለዋል።

TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ #በጳጉሜ_ወር ለሀገር ሰላም እና አንድነት በመላው ዓለም በምትገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፀሎት እና ምህላ ወስኗል። ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የሲዳማ፣ ጌዴኦ አማሮና ቡርጂ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ፥ ቋሚ ሲኖዶሱ 5ቱን የጳጉሜ ቀናት በፀሎትና ምህላ እንዲታሰብ መወሰኑን ገልፀዋል።…
"...ቋሚ ሲኖዶስ በወሰነው መሰረት ህዝበ ክርስቲያኑ #በአንድነት እና #በፍቅር ሊፀልይ ይገባል" - ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር)
የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ፅ/ቤት የውጭ ጉዳይ መምሪያ የበላይ ኃላፊና የድሬዳዋና ጅቡቲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶክተር) ፥ ቋሚ ሲኖዶስ በወሰነው ውሳኔ መሰረት ከጳጉሜ 1 እስከ 5 ድረስ ባሉት ቀናት በአንድነት እና በፍቅር መፀለይ እንደሚገባ ገልፀዋል።
"ምዕመናኑ በአምስቱ ዕለታት #ስለሀገር ሰላም፣ #ፍቅር እና #አንድነት፣ በፀሎት እና በምዕላ በትጋት ጊዜውን እንዲያሳልፍ ጥብቅ መመሪያ የተላለፈ መሆኑን በቋሚ ሲኖዶስ በኩል ለየአብያተክርስቲያናቱ እና ገዳማቱ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ላሉ ሁሉ እነዚህን ዕለታት በፀሎት እና በምዕላ እንዲያሳልፍ ተወስኗል" ሲሉ ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶክተር) ለEOTC ቴሌቪዥን ጣቢያ ተናግረዋል።

በሐበሻ ቪው አዘጋጅነት የኢትዮጵያ ፊልም ሳምንት በለንደን / Ethiopian Film Week 2021 ከአምስት ቀናት በኃላ ይካሄዳል።
ከዓርብ ጳግሜን 5/2013 እስከ መስከረም 4/2014 in Europe that would be 10-14 September 2021 በሚዘልቀው በዚህ የፊልም ሳምንት ተወዳጅ እና የተመረጡ ፊልሞች ለእይታ ይቀርባሉ።
በለንደን ከተማ የምትገኙና በፊልም ሳምንቱ ላይ ለመካፈል የምትፈልጉ ዝርዝር መረጃ በዚህ ማግኘት ትችላላችሁ : t.me/myhabeshaview/173
ተጨማሪ መረጃ @habeshaview

የአፍጋኒስታን ሴቶች ተቋውሞ !
ታሊባን በአፍጋኒስታን ካቡል ከተማ ስለመብታቸው ለመጠየቅ ተቃውሞ የወጡ ሴቶች መበተነ ታውቋል።
ሰልኞቹ ወደ ቤተመንግስት በመሄድ ላይ እያሉ ታሊባን አስለቃሽ ጭስና አይን የሚያቃጥል ሌላ ፈሳሽ ጭምር በመጠቀም ሰልፉን ለመበተን ጥረት አድርጓል።
አንዳንድ የአፍጋኒስታን ሚዲያዎች እንዳሉት ከሆነ ታሊባን ተቃውሞውን ሙሉ በሙሉ መበተን አቅቶት እንደነበርና ነገሮች ከቁጥጥር ውጭ ሆነው እንደነበር ዘግበዋል።
ከዚህ በፊት በተለያዩ አጋጣሚዎች የካቡል ሴቶች ተቃውሟቸውን አደባባይ ወጥተው ሲገልጹ ነበር።
ሰልፈኞቹ ሴቶች ስራ የመስራት እንዲሁም በመንግስት መዋቅር ውስጥ የመካተት መብታቸውን በመጠየቅ ነው የተቃወሙት። በተጨማሪ የሴቶች መብት እንዲከበር ፣ ሴቶች በፖለቲካ ውስጥ ያላቸው ተሳትፎ ሳይረጋገጥ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለታሊባን እውቅና እንዳይሰጥ ጠይቀዋል።
ታሊባን አፍጋኒስታንን የሚያስተዳድረውን መንግስት በቅርብ ቀን ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል። ምንም እንኳን ታሊባን ሴቶች በመንግስት መዋቅር ውስጥ እንደሚካተቱ የገለጸ ቢሆንም በሚኒስትር ደረጃ ግን ማገልገል አይችሉም ብሏል።
ይህን ተከትሎም በርካታ ሴቶች ታሊባን በአውሮፓውያኑ ከ1996 እስከ 2001 ስልጣን ላይ በነበረበት ይከተለው የነበረውን ሴቶች ላይ ያለው አቋም መልሶ እንዳኣመጣ ስጋታቸው እየገለጹ መሆናቸውን ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ተራዝሟል ?
የ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበት ግዜ አለመራዘሙን ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ ገልጿል።
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር) ሐምሌ 06/2013 ዓ.ም በሰጡት መግለጫ፤ ፈተናው በጥቅምት አጋማሽ ይሰጣል ማለታቸው አይዘነጋም።
ሰሞኑን ፈተናው የሚሰጥበት ቀን እንደተራዘመ በማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን የተሰራጨው መረጃ ሐሰት መሆኑን የኤጀንሲው የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ረዲ ሽፋ ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ገልጸዋል።
"የተቀየረ ነገር የለም" ያሉት ዳይሬክተሩ፤ "እስካሁን ያለው መረጃ ፈተናው በጥቅምት ወር አጋማሽ እንደሚሰጥ ነው" ብለዋል።
ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ መረጃ ሰኞ የሚያደርሳችሁ ይሆናል።
የትግራይ ክልል ተማሪዎችን ሳይጨምር፤ 620 ሺህ ተማሪዎች ለብሔራዊ ፈተናው እንደሚቀመጡ መገለጹ ይታወሳል።
More : @tikvahuniversity

የጊኒው መፈንቅለ መንግስት ...
በምዕራብ አፍሪካዊቷ አገር ጊኒ ውስጥ ወታደሮች መፈንቅለ መንግሥት አካሂደው ባለፈው ዓመት በምርጫ ያሸነፉትን ፕሬዝዳንት ከመንበራቸው ማስወገዳቸውን ገለጹ።
ወታደሮቹ መፈንቅለ መንግሥት አካሂደው ሥልጣን መቆጣጠራቸውን የሚያሳይ ቪዲዮ በቴሌቪዥን ከታየ በኋላ ፕሬዝዳንቱ አልፋ ኮንዴ የት እንዳሉ አልታወቀም።
ወታደሮቹ በአገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ላይ ቀርበው የአገሪቱን መንግሥት መበተናቸውን ገልጸዋል።
ነገር ግን የአገሪቱ የመከላከያ ሚኒስቴር እንዳለው በወታደሮቹ የተሞከረው መፈንቅለ መንግሥት በፕሬዝንዳንቱ ጠባቂዎች አማካይነት ከሽፏል ብሏል።
እሁድ ጠዋት በዋና ከተማዋ ኮናክሪ ውስጥ በሚገኘው የፕሬዝዳንቱ ቤተ መንግሥት አቅራቢያ ለሰዓታት የቆየ ከባድ የተኩስ ልውውጥ በኋላ መፈንቅለ መንግሥት መሞከሩ የታወቀው።
በቴሌቪዠን ላይ ቀርበው የመንግሥት ግልበጣ መካሄዱን ያስታወቁት ስማቸው ያልተገለጸና የአገሪቱን ሰንደቅ አላማ በለበሱ በርካታ ወታደሮች የታጀቡ ዘጠኝ ወታደሮች ናቸው።
ወታደሮቹ ለወሰዱት እርምጃ እንደምክንያት የጠቀሱት በአገሪቱ ተንሰራፍቷል ያሉት ሙስና፣ የመልካም አስተዳደር ችግርና ድህነት መሆኑን ገልጸዋል።
እራሳቸውን የእርቅና ልማት ብሔራዊ ኮሚቴ ብለው የጠሩት ወታደሮቹ የአገሪቱ ሕገ መንግሥት መታገዱንና ሁሉን አቀፍ አዲስ ሕገመንግሥት ለማቀርቅ ምክክር እንደሚዘጋጅ ገልጸዋል።
በርካታ ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት የጊኒው መፈንቅለ መንግሥት የተመራው የቀድሞ የአገሪቱ ዋነኛ ወታደራዊ ኃይል መሪ በነበሩት ሌ/ኮሎኔል ማማዲ ዱምቡያ ሲል ቢቢሲ /BBC/ ዘግቧል።

#ETHIOPIA😷
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1,516 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ14 ሰዎች ህይወት አልፏል።
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 7,659 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 1,516 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል። በተመሳሳይ በ24 ሰዓት ውስጥ 14 ዜጎች ህይወታቸው አልፏል።
የፅኑ ታማሚዎችን በተመለከተም የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 727 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።
ትላንት 840 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።