TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
ቁጥሮች ! ባጠናቀቅነው ነሀሴ ወር በይፋ የተገለፁ ህገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውሮች ፦ - መነሻውን ከጋምቤላ ያደረገ በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-15074 አ/አ በሆነ ዶልፊን ህዝብ ማመላለሻ ሲዘዋወር የነበረ ህገወጥ መሳሪያ ከነተጠርጣሪዎቹ በዚህ ወር ተይዟል፤ የተያዘው መሳሪያ በቁጥር 12 ክላሽንኮቭ እና 5 ጥይት መያዣ ነው። - የሰሌዳ ቁጥር A76390 በሆነ ቪትዝ መኪና 5 ክላሽንኮቭ ከ132 ጥይት ጋር…
ተጨማሪ...

ዛሬ ጥዋት በዚህ ባጠናቀቅነው ነሃሴ ወር በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የነበሩ ህገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውሮችን የተመለከተ ጥቂት መረጃ ተለዋውጠን ነበር።

ዛሬ በወሩ የመጨረሻ ቀን ላይ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ነጆ ከተማ ላይ 25,335 የክላሽ እና የብሬን ጥይት መያዙን ለኢዜአ ገልጿል።

ይህን ጥይት ከአ/አ ከተማ በ ኮድ 3 A 32684 አይሱዙ መኪና ተጭኖ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሽብርተኛ ብሎ ለፈረጀው ሸኔ ቡድን እንዲደረሰው የታቀደ ሲሆን ነጆ ከተማ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ ሪፖርት አድርጓል።

ከዚህ በተጨማሪ የክልሉ ፖሊስ አምቦ ባቢቻ ላይ 3 ሺህ የክላሽ ጥይት ተይዟል፤ ይህም በተመሳሳይ ለሸኔ ሊሰጥ ነበር የተባለ ሲሆን ጥይቱን ለማድረስ የሞከሩ ግለሰቦችም በፖሊስ ተይዘዋል።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Mekelle

3,500 ሜትሪክ ቶን ምግብና ሌሎችም ህይወት አድን የሰብዓዊ ድጋፍ የጫኑ ከ100 በላይ ተሽከርካሪዎች መቐለ በሰላም መግባታቸውን የዓለም ምግብ ፕሮግራም - ኢትዮጵያ (WFP) በሰበር ዜና አሳውቋል።

WFP እና አጋሮቹ በመላው ሰሜን ኢትዮጵያ አስቸኳይ ፍላጎቶችን ለማሟላት፤ አቅርቦቶችም መጠነ ሰፊ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ጥረት ማድረጋችንን እንቀጥላለልን ብለዋል።

@tikvahethiopia
ነገ የሚዘጉ መንገዶች !

"የኢትዮጵያዊነት ቀን"

ነገ ሰኞ ጳጉሜ 1 "ለኢትዮጵያ ክብር እቆማለሁ፤ እዘምራለሁ" በሚል መሪ ቃል በመስቀል አደባባይ ዝግጅት ይኖራል።

ይህን ዝግጅት አስመልክቶ ከጠዋቱ 11:30 ጀምሮ መርሃ ግብሩ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል።

- ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ አሽከርካሪዎች ኡራኤል ቤ/ክ
- ከቦሌ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ኦሎምፒያ
- ከሸራተን ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ ሀራምቤ ትራፊክ መብራት
- ከሜክሲኮ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ለገሃር ትራፊክ መብራት ላይ
- ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ ብሄራዊ ቤተ መንግስት
- ከተክለሀይማኖት ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ አሽከርካሪዎች
ብሔራዊ ቲያትር
- ከቼርቸል ጎዳና ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ አሽከርካሪዎች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መስሪያ ቤት
- ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ጥላሁን አደባባይ ዝግ የሚሆን ሲሆን ለከባድ ተሽከርካሪ ከጎተራ ወደ መስቀልአደባባይ ለሚመጡ መንገዱ አጎና ሲኒማ ላይ የሚዘጋ ይሆናል።

ከዚህም በተጨማሪ በነዚህ መንገዶች ላይ ተሽከርካሪን ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓት አቁሞ መሄድ ተከልክሏል።

አሽከርካሪዎች ከላይ የተዘረዘሩት መንገዶች ዝግ መሆናቸውን አውቀው አማራጭ መንገዶችን በመጠቀም ትብብር እንዲያደርጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክት አስተላልፏል።

@tikvahethiopia
ተቋርጦ የነበረው የንግድ ባንክ የስራ ቅጥር ዳግም ጀመረ።

ከሶስት ወር በፊት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አውጥቶት የነበረው የጀማሪ የባንክ ባለሙያ ክፍት የስራ ቦታ ምዝገባ ዳግም ጀመረ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሶስት (3) ወር በፊት የጀማሪ የባንክ ባለሙያ (Bank Trainee) ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ ምዝገባ አውጥቶ በሲስተም ችግር ምከንያት መቋረጡ ይታወሳል።

ባንኩ አሁን ዳግም ምዝገባ መጀመሩን ዛሬ የገለፀ ሲሆን ክፍት የሥራ ቦታውን መስፈርት የሚያሟል ነገር ግን ምዝገባውን ያላካሄዱ ሥራ ፈላጊዎች ማመልከት እንደሚችሉ አስታውቋል።

ምዝገባው የሚካሄደው በአመልካቾች የስም መጀመሪያ ፊደል መሠረት እንደሆነ የተገለፀ ሢሆን የፕሮግራሙን ዝርዝር ከላይ ተገልጿል።

ከዚህ ቀደም ያመለከቱ ሥራ ፈላጊዎች ድጋሜ ማመልከት አይኖርባቸውም የተባለ ሲሆን የሥም ዝርዝራቸውን ከሥር ባለው ማስፈንጠሪያ (Link) ማየት እንደሚችሉ ተጠቁሟል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለማመልከት፣ ክፍት የሥራ ቦታውን መሥፈርት እና ተጨማሪ መረጃዎች ለመመልከት ከዚህ በታች ያሉትን ማስፈንጠሪያዎች (Links) መጠቀም እንደሚቻል ጠቁሟል።

https://combanketh.et/cbeapi/uploads/List_of_Active_Applicants_for_the_post_of_Bank_Trainee_21a4ee8f9f.pdf

https://combanketh.et/cbeapi/uploads/External_Vacancy_9653676836.pdf

https://jobs.cbe.com.et:4453/OA_HTML/IrcVisitor.jsp

@tikvahethiopia
' የሰዓት እላፊ ገደብ ማሻሻያ - በሞጣ '

በምስራቅ ጎጃም አስተዳደር ዞን ሞጣ ከተማ አስተዳደር ተጥሎ የነበረው የሰዓት ዕላፊ ገደብ ከትላንት ጀምሮ ማሻሻያ ተደርጎበታል።

በሀገራዊ የፀጥታ ችግር ምክንያት የሞጣ ከተማ ሰላም እና ደህንነት ለመጠበቅ የሰዓት ዕላፊ ገደብን ጨምሮ በከተማዋ የተቋቋመው የፀጥታ ግብረ-ሃይል የተለያዩ ውሳኔዎች ማሳለፉ ይታወሳል።

ከተላፋት ውሳኔዎች መካከል የሰዓት ዕላፊ ገደብ አንዱ ነው።

ሌሎች የተላለፉ ውሳኔዎች እንደተጠበቁ ሆነው የሰዓት ዕላፊ ገደቡ ማሻሻያ ተደርጎበታል።

በዚህም መሰረት ጠዋት ከ12 ሰዓት በፊት መንቀሳቀስ የተከለከለ ሲሆን ምሽት 2 ሰዓት የነበረው የሰዓት ዕላፊ ገደብ ግን ወደ ምሽት 3 ሰዓት የተሻሻለ መሆኑን የፀጥታ ግብረ ሃይል ኮሚቴው አስታውቋል።

የከተማዋ ማህበረሰብ ለሰላሙ ሲል የተጣለውን ገደብ አክብሮ መንቀሳቀሱን ያመሰገነው ግብረ ሃይሉ ይህን ገደብ አሁንም ለራሱና ለከተማዋ ደህንነት ሲል አጠናክሮ መቀጠል አለበት ተብሏል።

@tikvahethiopia
የነዳጅ ምርቶች ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በመስከረም ወር ባለበት ይቀጥላል::

የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የመስከረም ወር የነዳጅ ምርቶች ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት እንደሚቀጥል አስታወቀ::

በዚህም ከጳጉሜን 1 ቀን 2013 ዓ.ም እስከ መስከረም 30 ቀን 2014 ዓ.ም የሁሉም ነዳጅ ምርቶች ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነሐሴ ወር በነበረበት ይቀጥላል::

ምንጭ: የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
#EthiopianAirlines

የሱዳን መንግሥት የዜና ወኪል ‘ሱና‘ ዛሬ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ተጓጉዘው ሱዳን ስለገቡ ጦር መሳሪያዎች የተዛባ ዘገባ ሰርቶ ነበር::

ሱና መሳሪያው "[በሱዳን] መንግሥት ላይ ወንጀል ለመፈጸም" ጥቅም ላይ ሊውል ነበር የሚል ጥርጣሬ አለ ሲል ገልጽዋል::

የሱዳን መንግስት በኢትዮጵያ አየር መንገድ በኩል ካርቱም ከገቡ በኋላ ተይዘዋል ስላለው የጦር መሳሪዎች ምርመራ እያደረኩ ነው ማለቱንም ሱና አክላል::

በሱዳን የዜና ወኪል የወጣውን የተዛባ መረጃ አስመልክቶ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የተሰጠ ምላሽ እንደሚከተለው ይቀርባል :

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሱዳን ያጓጓዘውን ለአደን አገልግሎት የሚውል መሳሪያ በተመለከተ አየር መንገዱ የሰጠው የማጓጓዝ አገልግሎት በአየር መንገዱ እና በደንበኛው ሙሉ ህጋዊ ማስረጃ የተደገፈ ህጋዊ የንግድ አሰራር መሆኑን ልናረጋግጥ እንወዳለን።

የአደን መሳሪያዎቹ በአዲስ አበባ በጸጥታ አካላት አስፈላጊው ህጋዊ የማጣራት ስራ እስኪሰራ ረዘም ያለ ግዜ የወሰደ በመሆኑ በተፈጠረው መዘግየት ምክንያት የአደን መሳሪያዎቹ ባለቤት መሳሪያዎቹን እንድናስረክብ አለበለዚያ 250 ሺህ የአሜሪካን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ እንድንቀጣ የሚያስገድድ ክስ በሱዳን ፍርድ ቤት መስርቷል።

በአደን መሳሪያዎቹ ላይ የተካሄደው ህጋዊ ማጣራት ከተከናወነ በኋላ ከኢትዮጵያ የፀጥታ አካላት የይለፍ ፍቃድ እንዳገኘን ጭነቱን ወደሱዳን አጓጉዘናል።

ከሱዳን የውጪ ጉዳይ መ/ቤት ያገኘነውን ህጋዊ ማረጋገጫ ጨምሮ የሰጠነውን አገልግሎት ህጋዊነት በተጨባጭ የሚያረጋግጡ በርካታ ማስረጃዎች በእጃችን የሚገኙ መሆኑን እንገልጻለን።

ስለጭነቱ ምንነት የሚገልፅ መረጃ ከላይ አያይዘናል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ
(ጳጉሜ 1/2013 ዓ/ም)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE ትምህርት ሚኒስቴር በዓለም ዐቀፍ ደረጃ በተከሰተው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት በፈረቃ ሲሰጥ የቆየው ትምህርት በ2014 የትምህርት ዘመን ወደ መደበኛው እንደሚመለስ አስታወቀ። ሚኒስቴሩ ይህን ያሳወቀው ለ "አዲስ ማለዳ ጋዜጣ" ነው። የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል እንዲረዳ በማሰብ በ2013 የትምህርት ዘመን ትምህርት በፈረቃ ሲሰጥ ነበር። በተጨማሪ ተማሪዎች ሲማሩበት የነበረው የቀናት…
#MoE

የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ ይፋ ባደረግው መረጃ የ2014 ዓ.ም የትምህርት አሰጣጥ ሂደት ላይ ውይይት ሊካሄድ መሆኑን አሳውቋል::

ሚኒስቴሩ በ2014 ዓ.ም በሚኖረው የመደበኛ ትምህርት አሰጣጥ ሂደት ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እቀመጣለሁ ነው ያለው::

በ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባስቀመጠው የኮቪድ-19 ፕሮቶኮል መሰረት ትምህርት በቀንና ፈረቃ ሲሰጥ መቆየቱ አስታውሳል::

በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የትምህርት አሰጣጡ እንዴት መሆን እንዳለበት ትምህርት ሚኒስቴር ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የኮቪድ 19 ፕሮቶኮል መዘጋጀቱን ገልጸዋል::

በቀጣይ የሚኖረው የትምህርት አሰጣጥ ሂደት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ተደርጎበት ወደ ፊት ዝርዝር የአፈፃፀም መመሪያ የሚወጣለትና ለህዝብ የሚገለፅ ይሆናል ሲል ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል::

ከቀናት በፊት 'አዲስ ማለዳ ጋዜጣ' ትምህርት ሚንስቴርን ዋቢ አድርጎ ባወጣው ፅሁፍ ሚኒስቴሩ የ2014 ትምህርት አሰጣጥ ከዚህ በፊት ወደነበረበት ለመመለስ ማቀዱን ገልጾ ነበር: ዛሬ ሚኒስቴሩ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፁ ባወጣው ፅሁፍ ስለጉዳዩ ያለው ነገር የለም : የ2014 ትምህርት አሰጣጥ እንዴት ይሁን የሚለውን ከባለድርሻ አካላት ጋር መክሬ ወደፊት ገልጻለሁ ሲል ነው የጠቆመው::

@tikvahethiopia
እጅግ ከፍተኛ ጥበቃ ከሚደረግበት እስር ቤት ያመለጡት ፍልስጥኤማውያን …

6 ፍልስጤማውያን እስረኞች ጠንካራ ጥበቃ ከሚደረግለት እስር ቤት ካመለጡ በኋላ እስረኞቹን አድኖ ለመያዝ እስራኤል ኦፕሬሽን ጀመረች።

ከ6ቱ 5ቱ የእድሜ ልክ እስር የተፈረደባቸው ናቸው::

ከእስር ቤቱ ያመለጡት እስረኞች ለወራት ያህል የእስር ቤት ክፍላቸውን ውጪ ካለ መንገድ ጋር የሚያገናኝ ዋሻ ለመሥራት ሲቆፍሩ ቆይተዋል ተብሏል።

እስረኞቹ ትናንት ለሊት ላይ ማምለጣቸው የተገለጸ ሲሆን፤ እስረኞቹ በእርሻ ስፍራ ሲሯሯጡ የተመለከቱ አርሶ አደሮች ለእስራኤል ባለሥልጣናት ጥቆማ አድርሰዋል።

ፍልስጤማውያኑ እስረኞች ተረዳድተው ከመጸዳጃ ክፍላቸው ጀምረው የቆፈሩት ዋሻ ከእስር ቤቱ ውጪ ካለ መንገድ ጋር የሚያገናኝ ነው።

ጄሩሳሌም ፖስት እንደዘገበው ከሆነ እስረኞቹ ዋሻውን ለመቆፈር ያረጀ ማንኪያ ተጠቅመዋል። የእስራኤል ደኅንነት ኤጀንሲ በበኩሉ እስረኞቹ ከእስር ቤቱ ውጪ ካለ አካል ድጋፍ ሳያገኙ አይቀርም ብሏል።

የእስራኤል ማረሚያ ቤት አገልግሎት ኃላፊዎች የእስረኞቹን ማምለጥ፤ "ከፍተኛ የደኅንነት ውድቀት ነው" ሲሉት የፍልስጤም ታጣቂ ቡድኖች ደግሞ፤ "ጀግንነት" ሲሉ አወድሰዋል።

ከእስር ቤቱ ያመለጡት እስረኞች ዌስት ባንክ አልያም ጆርዳን እንዳይገቡ የእስራኤል ፖሊስ መንገዶችን በመዝጋት ፍተሻ እያካሄደ ነው ተብሏል። ይሁን እንጂ ዌስት ባንክ እና ጆርዳን ከእስር ቤቱ 14 ኪሎ ሜትሮች ብቻ እንደሚርቁ ተመልክቷል።

ምንጭ ፦ ቢቢሲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EthiopianAirlines የሱዳን መንግሥት የዜና ወኪል ‘ሱና‘ ዛሬ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ተጓጉዘው ሱዳን ስለገቡ ጦር መሳሪያዎች የተዛባ ዘገባ ሰርቶ ነበር:: ሱና መሳሪያው "[በሱዳን] መንግሥት ላይ ወንጀል ለመፈጸም" ጥቅም ላይ ሊውል ነበር የሚል ጥርጣሬ አለ ሲል ገልጽዋል:: የሱዳን መንግስት በኢትዮጵያ አየር መንገድ በኩል ካርቱም ከገቡ በኋላ ተይዘዋል ስላለው የጦር መሳሪዎች ምርመራ…
#Update

“በኢትዮጵያ አየር መንገድ ተጭነው ወደ ካርቱም የገቡ “ጦር መሳሪያዎች ተያዙ” መባሉ ከእውነት የራቀ ነው" - የሱዳን የሃገር ግዛት ሚኒስቴር

የሱዳን የሃገር ግዛት ሚኒስቴር በኢትዮጵያ አየር መንገድ ተጭነው ወደ ካርቱም የገቡ “ጦር መሳሪያዎች ተያዙ” መባሉ “ከእውነት የራቀ” ነው ያለስ ሲሆን የጦር መሳሪያው ተገቢው የጉምሩክ ክሊራንስ ሂደት መጀመሩንም ገልጸዋል::

ሚኒስቴሩ የሱዳን ጉሙሩክ ባለስልጣናት ያዝን ያሉት “ጦር መሳሪያ” ምንም ዐይነት የህግ ግድፈት እንደሌለበት አስታውቋል::

ባለስልጣናቱ ያዝን ያሉት “ጦር መሳሪያ” ራሳቸው በሰጡት ህጋዊ ፈቃድ ተጓጉዞ ወደ ካርቱም የገባ እንደሆነ የጦር መሳሪያዎቹ ባለቤት የሆነውና ‘ዋዒል ሸምሰዲን’ የተባለው የንግድ ተቋም ገልጸዋል::

የተቋሙ ጠበቃ የሆኑት ሲራጁዲን ሃሚድ ተያዙ የተባሉትን ጦር መሳሪያዎች በህጋዊ መንገድ እንደገቡ መግለጻቸውን የአል ዐይን ኒውስ ዘግቧል::

‘ዋዒል ሸምሰዲን’ ለሲቪል ግልጋሎት የሚውሉ ጦር መሳሪያዎችን ከውጭ የማስገባት እና የመነገድ ፈቃድ ያለው ድርጅት ነው፡፡

በዝርዝር ያንብቡ : telegra.ph/Al-Ain-News-09-06

Credit : AL AIN NEWS (አል ዓይን ኒውስ)

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA😷

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1,190 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ22 ሰዎች ህይወት አልፏል።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 6,679 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 1,190 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል። በተመሳሳይ በ24 ሰዓት ውስጥ 22 ዜጎች ህይወታቸው አልፏል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 727 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

ትላንት 904 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

@tikvahethiopia
#ባህርዳር

ነገ ባህር ዳር ከተማ የኢትዮጵያ እና የዚምባቡዌ የእግር ኳስ ፍልሚያን ታስተናግዳለች።

ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ወደጋና አቅንታ 1 ለ 0 በሆነ ጠባብ ውጤት መሸነፏ ይታወሳል፤ የነገው ጨዋታ ሁለተኛው የማጣሪያ ጨዋታ ነው።

ይህን ጨዋታ የምታስተናድገው ደግሞ ውቢቷ ባህር ዳር ከተማ ናት።

የነገው ጨዋታ ኮሚሽነር ከኤርትራ ፤ የዳኞች ገምጋሚ ከኮትዲቫር ፤ አራቱም የጨዋታ አመራሮች ከሲሼልስ ናቸው።

በነገው ፍልሚያ ብሄራዊ ቡድናችን የተለመደውን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ የሚለብስ ይሆናል።

የኢትዮጵያና የዚምባቡዌ ብሄራዊ ቡድኖች በነገው እለት የሚያደርጉት ጨዋታ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለካፍ ጥያቄ ቢያቀርብም የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ፍቃደኛ ባለመሆኑ ጨዋታው ያለተመልካች እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዛሬ ምሽት አሳውቋል።

@tikvahethiopia
በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሀሳብ ልዩነት ሊኖር ይችላል ሀገር ግን እስከመጨረሻው ድረስ ሀገር ናት ፤ እናት ናት 🇪🇹 !

የኢትዮጵያ ስም በክፉ ሲነሳ ሮጠው ቀድመው ለብዙሃን ለማሰራጨት የሚጥሩ በእግጥም ለኢትዮጵያ ክፉ የሚመኙ አካላት እንዳሉ በተለያየ ጊዜ መመልከት ተችሏል።

እንደማሳያ ትላንት SUNA/ሱና የሰራውን ፍፁም ከእውነት የራቀ፣ ሀሰተኛ፣ የተዛባ እና እጅግ በጣም አደገኛ ዘገባ አንድ እና ሁለቴ ሳያጣሩ የኢትዮጵያ ስም በክፉ መነሳቱን አንድም በጥላቻ፣ በሌላ መልኩ ለራሳቸው የተቃውሞ ሀሳብ ማጠናከሪያ ለመጠቀም ሲሯሯጡ የነበሩ ሰዎች ታይተዋል።

መረጃው ሱና ባወጣበት ቅፅበት የኢትዮጵያ አየር መንገድን አንዳች ምላሽ ሳይጠይቁ/የአየር መንገዱን መግለጫም ሳይጠብቁ የአንዱን ወገን እጅግ አደገኛ ዘገባ በድስታ ሲያሰራጩ የተዩ ብዙ ናቸው።

ይህንን ካደረጉት መካከል የተለያዩ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች፣ በኢትዮጵያ ጉዳይ የሚፅፉ የውጭ አክቲቪስቶች ፣የሀገር ውስጥ አክቲቪስቶች ፣ ማህበራዊ ሚዲያን መሰረት ያደረጉ ሚዲያዎች ይገኙበታል።

አንዳዴ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ተከታይ ለማፍራት እና የራሳቸውን ስሜት ለማጋራት፣ የሚፈልጉትን አጀንዳ ለማራመድ ሲሉ በአግባቡ መጣራት ያለባቸውን የተለያዩ ዘገባዎች አንድ ጊዜም መለስ ብለው ሳያዩ ለህዝብ የሚያጋሩ ሀገር ከሌለ እነሱም እንደሌሉ አውቀው መጠንቀቅ አለባቸው።

መንግስትን ፣ ፓርቲን መደገፍ አለመደገፍ ፣ የመንግስት ተቃዋሚዎችን ፓርቲዎችን መደገፍ አለመደገፍ ምንም ችግር የለውም ሚሊዮኖች ለሚኖሩበት ሀገር ፣ ላሳደች ሀገር፣ ክፋ ማሰብ እጅግ አሳፋሪና አደገኛ ድርጊት ነው።

@tikvahethiopia