TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#Ethiopia

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ #በጳጉሜ_ወር ለሀገር ሰላም እና አንድነት በመላው ዓለም በምትገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፀሎት እና ምህላ ወስኗል።

ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የሲዳማ፣ ጌዴኦ አማሮና ቡርጂ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ፥ ቋሚ ሲኖዶሱ 5ቱን የጳጉሜ ቀናት በፀሎትና ምህላ እንዲታሰብ መወሰኑን ገልፀዋል።

ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ፥ 2013 ዓ.ም ብዙ ችግሮችን ያሳየ መሆኑን ያነሱ ሲሆን "በፈተናው ውስጥም ቢሆን ግን ብዙ በረከቶችን ያሳየን ነገሮች አሉ" ብለዋል። እንደሀገር ፤ እንደዓለምም የተከሰቱ ችግሮች ወደቀጣይ ዓመት አብረው እንዳይተላለፉ እግዚአብሔርን በፀሎት መጠየቅ ስላለብን ይህ ውሳኔ ተላልፏል ሲሉ አስረድተዋል።

አክለውም፥ "ቤተክርስቲያን በሀገራችን ውስጥ ያለው ጦርነቱ ፣ ረሃቡ ፣ ስደቱ ፣ መፈናቀሉ ፣ ከቦታ ቦታ ያለው ህዝባችን በስጋት እንዳይኖር ይሄን ሁሉ ጉዳዬ ነው ብላ ወደእግዚአብሔር ማቅረብ አለብን በሚል ቀናቱን በፀሎት እና በምህላ በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እንዲታሰብ ወስናለች" ብለዋል።

"ወደሰዎች ሳይሆን ወደእግዚአብሔር በመፀለይ ለውጥ ይመጣል ፤ ያጣነው ሰላማችን ይመለሳል ፤ ወደእግዚአብሔር መፀለይ ሀገራችን ኢትዮጵያ ያለው ብሩህ ተስፋ፤ ጨለማ ውስጥ ነን ብሎ ለሚያስብ ህዝብ ብርሃን የሆነ ህይወት እንዲኖረው የሀገራችንም ከፍታ እንዲኖር ያደርጋል" ብለዋል።

"በዚህች ሰዓት ይሄ ፀሎት ወሳኝ በመሆኑ ትንሹም ትልቁም በሀገር ውስጥም በውጭም ያለው ቢፆም ቢፀልይ መፍትሄ ይመጣል ፤ አምስቱን ቀን በፀሎት እና በምህላ ማሳለፍ ይገባል" ሲሉ አክለዋል።

@tikvahethiopia