TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.5K photos
1.59K videos
216 files
4.33K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#update የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ህዝቦች ዴሞክራሲዊ ፓርቲ (ቤጉህዴፓ) ሊቀመንበር አቶ አበራ ባዬታ #መልቀቂያ አስገብተዋል:። ይህንኑ ተከትሎ የፖርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት #አስቸኳይ ጉባኤ ያካሄዳል፡፡የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ አበራ ባዬታ ዛሬ ለኢቢሲ እንዳስታወቁት ማዕከላዊ ኮሚቴው በሚያደርገው ጉባዔ የመልቀቂያ ጥያቄውን መርምሮ ውሳኔ መስጠት ዋነኛ አጀንዳው ይሆናል፡፡የአመራር እጦት ችግሮች በፓርቲው ውስጥ መኖራቸው ተደርሶበታል ነው ያሉት ሊቀመንበሩ፡፡ ለፓርቲው ተተኪ ሊቀመንበር መምረጥና በተጓደሉ ሥራ አስፈጻሚዎች አባላት ምትክ ምርጫ እንደሚካሄድም ገልጸዋል።

Via EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ዛሬ ወይም ነገ ከሰዓት ይለቀቃል!

የ12ኛ ክፍል #መልቀቂያ ወይም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና ውጤት ዛሬ ወይም ነገ ከሰዓት በኋላ ይፋ እንደሚሆን ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታውቋል። የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ገብረእግዚያብሄር ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ፈተናዎቹ ዓለም አቀፍ ተወዳሪነታቸው በተመሰከረላቸው ዘመናዊ አዳዲስ የማረሚያ ማሽኖችን በመጠቀም በጥራት የታረሙ መሆናቸውም ተነግሯል። ይሁንና በማህበራዊ ብዙሃን መገናኛዎች የ12ኛ ከፍል ውጤት ተለቋል ተብሎ የሚናፈሰው መረጃ ሃሰት ነው ብለዋል። የእርማቱ ስራ የተጠነቀቀቀ በመሆኑ ኤጀንሲው ዛሬ ወይም ነገ በኤጀንሲው ድረ-ገጽ በመግባት ተማሪዎች ውጤቶቻቸውን ማየት እንደሚችሉ ተገልጿል።

Via #ኢትዮኤፍኤም
@tsegabwolde @tikvahethiopia