UAE ወደ ትግራይ ክልል እርዳታ ላከች።
UAE ከዓለም የምግብ ፕሮግራም ጋር በመተባበር ለትግራይ ክልል የሚሆኑ የምግብ እርዳታዎችን የጫነ አውሮፕላን ላከች፡፡
እርዳታዎቹን የጫነው አውሮፕላን ከዩኤኢ ለትግራይ ክልል የተላኩ ሰብዓዊ ድጋፎችን የጫነ የመጀመሪያው አውሮፕላን ሲሆን ድጋፉን በሚያስተባብሩ የኤመራት የሰብዓዊ ቡድን አባላት ታጅቧል፡፡
UAE 200 ሜትሪክ ቶን የምግብ እርዳታዎችን ነው ወደ ትግራይ የላከችው፡፡
ይህ የትኛውም ሰብዓዊ ችግር በገጠመ ጊዜ ዩኤኢ ከኢትዮጵያ እና ከዓለም ህዝብ ጎን እንደምትቆም የሚያሳይ ነው ተብሏል፡፡
በኢትዮጵያ የዩኤኢ አምባሳደር መሃመድ ሳሊም አህመድ ሙሳድ አል ረሺድ እንደተናገሩት ዩኤኢ በትግራይ ሰብዓዊ ድጋፎችን ለማድረግ እና የምግብ እርዳታዎችን ለማቅረብ ፍላጎት አላት፡፡
አሁን የተላከው እርዳታም ዩኤኢ ለድጋፍ በተፈለገችበት ቦታ ሁሉ ለመገኘት ላላት ቆርጠኝነት ማሳያ ነው እንደ አምባሳደሩ ገለጻ፡፡
የዓለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) የምስራቅ አፍሪካ አስተባባሪ ሚሼል ዳንፎርድ በበኩሉ ወቅቱን ለጠበቀው እርዳታ ዩኤኢን አመስግኖ ድጋፉን በቶሎ ትግራይ ለማድረስ እንደሚሰሩ አስታውቋል፡፡
UAE ከአሁን ቀደምም ለኢትዮጵያ የተለያዩ የኮሮና ክትባቶችን ድጋፍ አድርጋለች፡፡
የመረጃ ባለቤት ፦ አል ዓይን ኒውስ
@tikvahethiopia

#COVID19
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 985 የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ10 ሰዎች ህይወት ደግሞ ጠፍቷል።
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 7,686 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 985 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።
በተመሳሳይ በ24 ሰዓታት ውስጥ 10 ዜጎች ህይወታቸው አልፏል።

TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ : የቱርክ ፕሬዜዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ በዛሬው ዕለት አቀባበል አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በቱርክ የስራ ጉብኝት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ Photo Credit : በቱርክ የኢትዮጵያ ኤምባሲ @tikvhethiopia
#Update
ኢትዮጵያ እና ቱርክበወታደራዊ ዘርፎች በትብብር ለመስራት ተስማሙ።
ኢትዮጵያ እና ቱርክ በወታደራዊና ውሃ ዘርፎች ዙሪያ በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል።
የወታደራዊ ዘርፍ ስምምነቱን የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር ቀነአ ያደታ ከቱርክ አቻቸው ጋር ተፈራርመውታል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት በዛሬው እለት ወደ ቱርክ ማቅናታቸው ይታወሳል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቱርኩ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይፕ ኤርዶኻን ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በቱርክ ፕሬዜዳንት ለተደረገላቸው አቀባበል ምስጋና አቅርበዋል።
መረጃው ፦ ኤፍ ቢ ሲ

#ማሳሰቢያ
"ርችት መተኮስ በጥብቅ የተከለከለ ነው" - ፖሊስ
የቡሔ በዓልን ምክንያት በማድረግ ርችቶችን መተኮስ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
የቡሔ በዓልን ምክንያት በማድረግ የሚተኮሱ ርችቶችን ሽፋን በማድረግ ሰላምን የመደፍረስ ፍላጎት ያላቸው ግለሰቦች በህገ-ወጥ መንገድ የገዙትን የጦር መሣሪያ እንደሚፈትሹና የተለያዩ ለፀጥታ ስጋት የሆኑ ሁኔታዎች እንደሚፈጥሩ ፖሊስ በተለያዩ ጊዚያት ባደረጋቸው ጥናቶችና በደረሰው መረጃ ያረጋገጠ መሆኑን ገልጾ ማንኛውም ግለሰብ ሆነ ተቋም ከሚመለከተው አካል ፍቃድ ሳያገኝ ርችቶችን መተኮስ እንደማይችል ተገንዝቦ ተገቢውን ትብብር እንዲያደርግ ፖሊስ አሳስቧል፡፡
ሁኔታው ለህገ-ወጦች ምቹ ሁኔታ ፈጥሮ የከተማዋ ፀጥታ ስጋት እንዳይሆን ህብረተሰቡ አካባቢውን በመጠበቅ ለፖሊስ አባላት መረጃዎችን እንዲሰጥ ፖሊስ ጥሪውን እያስተላለፈ ከሚመለከተው አካል ተገቢውን ፍቃድ ሣይሰጥበት ርችቶችን በሚተኩሱ ግለሠቦች ሆኑ ተቋማት ላይ ህጋዊ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቋል፡፡
(አዲስ አበባ ፖሊስ)

Photo
#Update
የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ የቱርክ የስራ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደሀገር ተመለሱ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በይፋዊ ማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባሰራጩት መልዕክት ፥ "ከተከበሩ የቱርክ ፕሬዝደንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶጋን ጋር የነበረንን ውድ ጊዜ አጠናቀን ወደ ሀገር ተመልሰናል።" ብለዋል።
አክለውም ፥ "የቱርክ መንግስት እና ህዝብ ያደረገልንን የወሳኝ ጊዜ ትብብር ሀገራችን #ኢትዮጵያ መቼም አትረሳውም" ሲሉ ፅፈዋል።

#ጥንቃቄ ከ #አዲስአበባ ወደ #ጎጃም በሚወስደው መንገድ ዓባይ በረሃ በመባል በሚታወቀው አካባቢ ልዩ ስሙ #ፍልቅልቅ በሚባለው ስፍራ ላይ ዛሬ ሌሊቱን ባጋጠመ የድንጋይ መንሸራተት ናዳ የትራንስፖርት አገልግሎት መስተጓጓል አጋጥሟል። ችግሩን በቶሎ ለመቅረፍ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን (ኢመባ) በስፍራው አሰቸኳይ ጥገና የሚያደርግ ግብረ ሃይል በመላክ በስፍራው ከሚገኘው አሰቸኳይ ጥገና ቡድን ጋር…
#ጥንቃቄ
ከአዲስ አበባ ወደ ጎጃም በሚወስደው መንገድ ዓባይ በረሃ በመባል በሚታወቀው አካባቢ ልዩ ስሙ ፍልቅልቅ በሚባለው ስፍራ ላይ ያጋጠመውን ከባድ የድንጋይ መንሸራተት ናዳ ክፍት ለማድረግ ርብርቡ እየተደረገ ነው።
በዛሬው ዕለት ይህን መስመሩን ለመክፈት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ከኢትዮጵየ መንገዶች ባለስልጣን የተገኘው መረጃ ያሳያል።
የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን አስቸኳይ ጥገናው ተጠናቆ መንገዱ ክፍት መሆኑን የሚያሳውቅ ይሆናል።
በመሆኑም አሽከርካሪዎች እና የመንገዱ ተጠቃሚዎች ይህን የባለስልጣን መስሪያቤቱን መረጃ ሳታረጋግጡ እንቅስቃሴ እንዳታደርጉ ማሳሰቢያ ተላልፏል።
ከቀናት በፊት በስፍራው የሚንሸራተት ጠመዝማዛና ናዳ በሚበዛበት በዚሁ ስፍራ ከወትሮ የተለየ ግዙፍ ናዳ መከሰቱ የሚታወስ ነው።
ይህን ተከትሎ ኢመባ ችግሩን ለመፍታት በስፍራው አሰቸኳይ ጥገና የሚያደርግ ግብረ ሃይል፣ በርካታ ማሽነሪና የሰው ሀይል በስፍራው ከሚገኘው አሰቸኳይ ጥገና ቡድን ጋር በጋራ በማሰማራት በተደረገው ጥረት መንገዱን የዘጋውን ቋጥኘ ድንጋይ በደማሚት እና በማሽነሪዎች በመታገዝ አብዛኛው የመንገዱን ክፍል ነጻ ለማድረግ ተችሏል።
ቀሪ ስራዎችን አጠናቆ መስመሩን ክፍት ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ነው ብሏል ኢመባ።

በዓለም ላይ ለረዥም አመታት በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ...
(ቢቢሲ)
20 አመታት ያህል ያለ ፍርድ የታሰረው ኤርትራዊ ጋዜጠኛ ዳዊት ይስሃቅ በአስቸኳይ እንዲፈታ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለሙያዎች ጠይቀዋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተ.መ.ድ) የሰብዓዊ መብት አጣሪ ሜሪ ሎውሎር እንዳሉት ዳዊት ይስሃቅ በባለፉት ሁለት አስርት አመታት ክስ አልተመሰረተበትም እንዲሁም ጠበቃውን አግኝቶ አያውቅም።
የሰብዓዊ መብት አጣሪዋ ሌውሎር ፥ ጋዜጠኛ ዳዊት ይስሃቅ በህይወት አለ የሚለው ጉዳይ ላይ ፍራቻ እንዳለ ገልፀው የኤርትራ ባለስልጣናት የጋዜጠኛውን በህይወት መኖር ማስረጃ እንዲያቀርቡም አሳስበዋል።
ጋዜጠኛ ዳዊት ማነው?
ጋዜጠኛና ገጣሚው ዳዊት ይስሃቅ ነፃ ኤርትራን አገለግላሁ በማለት ወደ ትውልድ አገሩ ተመልሶም የለውጥ ደጋፊ የሆነ ጋዜጣም አቋቁሞም ነበር።
የስዊድንና ኤርትራዊ ዜግነት ያለው ዳዊት በአውሮፓውያኑ 1990ዎቹ በአገሪቱ ውስጥ ከመጀመሪያዎቹ ነፃ ጋዜጦች ውስጥ አንዱን አቋቋመ።
ኤርትራም የግል ጋዜጦችን ዘጋች እንዲሁም የሚቀርቡበትን ትችት ዝም ለማሰኘት የኤርትራ መንግሥት በጀመረው ዘመቻም ፖለቲከኞችን፣ ጋዜጠኞችንና ተማሪዎችን ለእስር ዳርጓል።
ጋዜጠኛው የፖለቲካ ተሃድሶን ከሚሹ ፖለቲከኞች የተላከ ግልፅ ደብዳቤ ካሳተመ በኋላም ነው ለእስር የተዳረገው።
ዳዊትን ጨምሮ በርካታ የግል ጋዜጣ አዘጋጆችም እኤአ 2001 ለእስር ተዳርገዋል።
ጋዜጠኛው ቤተሰቡን፣ ጠበቃውን እንዲሁም በተደጋጋሚ ከተባበሩት መንግሥታትም ሆነ የስዊድን ተወካዮች እንዲያገኙት ጥያቄ ቢቀርብም ማንም ጎብኝቶት አያውቅም።
በህይወት እንዳለ የተጠረጠረው በጎሮጎሳውያኑ 2005 ሲሆን በእስር ላይ በፈታኝ ሁኔታ እንደሚገኝም ተጠቁሟል።
ያንብቡ: telegra.ph/BBC-08-19-5

#Update የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ የቱርክ የስራ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደሀገር ተመለሱ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በይፋዊ ማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባሰራጩት መልዕክት ፥ "ከተከበሩ የቱርክ ፕሬዝደንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶጋን ጋር የነበረንን ውድ ጊዜ አጠናቀን ወደ ሀገር ተመልሰናል።" ብለዋል። አክለውም ፥ "የቱርክ መንግስት እና ህዝብ ያደረገልንን የወሳኝ ጊዜ ትብብር ሀገራችን…
#Turkey #Ethiopia #Sudan
የቱርክ ፕሬዝዳንት ረጂብ ጣይብ ኤርዶጋን በኢትዮ - ሱዳን ድንበር ጉዳን ኢትዮጵያ እና ሱዳን ለሸማገላችሁ ሲሉ ሀሳብ አቅርበዋል።
ኤርዶሃን ሃሳቡን ያቀረቡት፤ ከጠ/ሚ አብይ አህመድ ጋር ትላንት በአንካራ በሰጡት መግለጫ ነው።
በትላትናው የዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ሪሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን መግለጫ ወቅት የትግራይ እና የኢትዮ-ሱዳን የድንበር ጉዳዮች ተነስተዋል።
ኤርዶጋን ሀገራቸው ቱርክ ኢትዮጵያ እና ሱዳን የሚወዛገቡበትን የድንበር ጉዳይ ለማደራደር ፍላጎት እንዳላት ገልፀዋል።
ኤርዶጋን “ውዝግቡ በ2ቱ አገሮች መካከል በሚደረግ ውይይት በመልካም ጉርብትና ላይ በመመስረት እንዲፈታ የልብ ፍላጎቴ መሆኑን ገልጫለሁ ፤ ቱርክ ጉዳዩ በሰላም እልባት እንዲያገኝ ሽምግልናን ጨምሮ ማናቸውንም አስተዋጽኦ ለማድረግ ዝግጁ ናት" ብለዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ኤርዶጋን በሰሜን ኢትዮጵያ ስለተፈጠረው ጦርነት ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ አላት ያሉትን ስትራቴጂካዊ አቀማመጥ እና ጠቀሜታ ጠቅሰው ለሀገሪቱ ሰላም፣ ጸጥታ እና አንድነት ትኩረት እንደሚሰጡ ገልጸዋል።
“የቀጠናውን ሰላም እና መረጋጋት ከመጠበቅ አኳያ ለወቅታዊው ችግር በለዘብተኛ አካሄድ መፍትሔ ማበጀት ያስፈልጋል ብለን እናምናለን” ብለዋል።
አክለውም 9 ወራት በላይ ያስቆጠረው ውጊያ ከተባባሰ ዳፋው በአካባቢው አገራት ሊዳረስ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።
#EthiopiaInsider #Anadolu

#Agamsa
ከሰሞኑን በእንግሊዙ የቴሌግራፍ ጋዜጣ የወጣው የምርመራ ሪፖርት መነጋገሪያ ሆኗል።
ሪፖርቱ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ አከባቢ አጋምሳ ተብላ የምትጠራ ከአፋር ክልል የጥቂት ኪሎሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ መንደር ሙሉ በሙሉ መውደሙን በሳተላይት ምስል በታገዘ ሁኔታ ቀርቧል።
ሪፖርቱን ያዘጋጀው ጋዜጠኛ ዘካሪያስ ዘላለም ፥ በተደረገው የምርመራ ስራና ከአከባቢው ወደ ደሴ የተፈናቀሉት ንጹዓኖች በማነጋገር የጦር ወንጀል የተፈጸመው በአከባቢው ይንቀሳቀሱ የነበሩት የ "ትግራይ ሃይሎች" መሆኑን ደርሰንበታል ብሏል።
በተጠቃው አከባቢ ላይ አብዛኛው ነዋሪ በግብርና ስራ የሚተዳደሩ ሲሆኑ ከሳተላይት ምስሎችን በመመልከት ከ50 በላይ ጎጆ ቤቶች መቃጠላቸውንና ቃጠሎዉ ከሃምሌ 26 እለት ጀምሮ መፈጸሙንም ማረጋገጥ መቻሉን የጋዜጣው ሪፖርት ያስረዳል።
ጋዜጠኛው ፥ የሳተላይት ምስል ሪሰርች ባለሙያዎች ሪፖርቱ ላይ አብረው መስራታቸውን የገለፀ ሲሆን ተቀማጭነቱ በእንግሊዝ የደረገው የDX Open Network ተቋም ባለሙያዎች ምስሎቹን በማጥናት በንጹዓኖች ንብረት የደረሰው ጉዳት በቅርብ ርቀት እንጂ በአየር ሃይል ድብደባ የተፈጸመ አለመሆኑ አረጋገጠዋል።
የአከባቢ ነዋሪዎች ስለ ወድመቱ ሲጠየቁ በቆቦ ሮቢት እና ዙሪያው በአጠቃላይ 3 መንደሮች ቤት ለቤት በመዞር ወይ ደግሞ በከባድ ብረት ድብደባ መውደማቸው የተናገሩ ሲሆን ለግዜው አንዲት መንደር ሙሉ ለሙሉ መጥፋቱንና ቢያንስ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሲቪል መኖሪያ የነበረ ንብረት ወደ አመድ መቀየሩን ተረጋግጧል።
ይህንን ሪፖርት ተከትሎ ለህወሃት ቃል አቀባይ የሆኑት አምባሳደር ፍሰሃ ተመስገን የ "ትግራይ ሃይሎች" በነጹዓኖች መኖሪያ እርምጃ ወስደዋል የሚለው "ሙሉ ለሙሉ ሃሰት ነው" በማለት ምላሽ ሰጥተዋል።