TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ከቀናት በፊት የትግራይ ተወላጅ የሆኑ እና በተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ ዜጎች ደረሰብን ስላሉት እንግልትና አጋጥሞናል ስላሉት ማዋከብ ሪፖርት አደርገው ነበር። አሁንም ይህ ሁኔታ እንዳልተሻሻለ ከተለያዩ የሀገራችን ከተሞች የሚላኩት ሪፖርቶች እያስረዱ ነው። ከአሸባሪው ህወሓት ጋር ግኝኑነት አላችሁ በሚል ብቻ ያለንም በቂ ማስረጃ ፤ አንድም ቀን ወደትግይ እንኳን ሳንሄድ በጥርጣሬ ተይዘን የተለቀቅን…
"... ያለ አግባብ እንግልት እየደረሰብን ነው" - የትግራይ ተወላጆች
በአዲስ አበባ ከተማ ጎፋ መብራት ሃይል አካባቢ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ያለ አግባብ እንግልት እየደረሰብን ነው ሲሉ ተናገሩ፡፡
በጎፋ መብራት ሃይል የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች እንደተናገሩት በአካባቢው በሚደረጉ ፍተሻዎች በማንነታችን የትግራይ ተወላጆች በመሆናችን እየታሰርን እና ቤቶቻችን እየታሸጉ ነው ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።
ቅሬታ አቅራቢዎቹ እንዳሉት ለፍተሻ የሚመጡ የፀጥታ አካላት ምንም አይነት የመፈተሸ ፍቃድ ሳይዙ በተመረጡ የትግራይ ቤቶች ላይ ፍተሻ እያደረጉ መሆኑን ተናግረዋል።
በትግራይ ተወላጆች እየቀረበ ስላለው ቅሬታ የተጠየቁት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን የህዝብ ግንኙነት እና የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ "ስለተፈጠረው ችግር ግን እውቀቱ የለኝም" ብለዋል፡፡
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ጀላን አብዲ ጉዳዩን #እንደማያውቁት ተናግረዋል፡፡
በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሰላም ሚኒስቴር የወንጀል ክትትል እና ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ መንግስቱ አበራ ደግሞ ፥ "እስካሁን አዲስ የወረደ የአሰራር አቅጣጫም ሆነ የቀረበ ቅሬታ የለም፤ ሀገሪቱ ካለችበት ወቅታዊ ችግር አንፃር የተለመደ ሰላም የማሰጠበቅ ስራ እየተሰራ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
መረጃው የአሐዱ ኤፍ ኤም 94.3 ሬድዮ ጣቢያ ነው።
@tikvahethiopia