#ግድቡ_የእኔ_ነው
ትላንት ለሊት እንቅልፍ አሸንፏችሁ የUN ፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባን መከታተል ያልቻላችሁ በUN የዩትዩብ ቻናል ላይ ይገኛል ገብታችሁ መመልከት ትችላላችሁ።
ጥቂት ትላንት ለሊቱን ስለነበረው ሁኔታ ...
- ኢትዮጵያውን በታላቁ የህዳሴ ግድብ የተጠራውን ስብሰባ በመቃወም ኒው ዮርክ በሚገኘው የተመድ መስሪያ ቤት ሰልፍ አድርገዋል።
- የትላንት ለሊቱን ስብሰባ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የመንግስት ሆነ የግል ሚዲያዎች በንቃት ተከታትለው በፍጥነት የተነሱ ያሳቦችን ለህዝብ ሲያደርሱ ነበር።
- ስብሰባው በቀጥታ በUN ቻናል እንደሚሰራጭ የሰሙ ኢትዮጵያውያን ሙሉ በሙሉ የአስተያየት መስጫውን ተቆጣጥረውት ነበር። አስተያየት መስጫው በኢትዮጵያ ባንዲራ፣ ግንድቡ የእኔ ነው፣ የግድቡን ጉዳይ ወደፀጥታው ም/ቤት ይዞ መሄድ አያስፈልግም በሚሉ መልዕክቶች ተጥለቅልቆ ነበር።
- በርካታ ሀገራት አሜሪካ፣ ቻይና፣ ሩስያ፣ ኬንያ፣ ሜክሲኮ፣ አይርላንድ፣ ህንድ እንዲሁም ሌሎች ሀገራት የድግቡ ድርድር በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር እንዲካሄድ ሃሳብ አቅርበዋል።
- የግብፅ እና ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ንግግር አድርገዋል ፤ በንግግራቸው ያነሷቸው ያሳቦች እንደሁል ጊዜው ከእውነታ የራቁ እና ሀገራችንን ተወቃሽ ለማድረግ የሞከሩበት ነበር።
- የኢትዮጵያ ተወካይ ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ በምክር ቤቱ የኢትዮጵያን አቋም አንፀባርቀዋል፤ እጅግ በሚያስድምም ሁኔታ በግድቡ ዙሪያ ስላለው ሁኔታ እና እውነታ አስረድተዋል።
- ኢትዮጵያውያን ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ባቀረቡት ንግግር ከልባቸው ተደስተው ፣ ኮርተውም ካሰሙት ንግግር በወሰዱት አረፍተነገሮች እና በእሳቸው እና አብረዋቸው በስብሰባው በነበሩ የኢትዮጵያ ተወካዮች ፎቶ ማህበራዊ ሚዲያውን ተቆጣጥረውት አንግተዋል።
@tikvahethiopia

"...ወደ ትግራይ የሚደረጉ በረራዎች ላይ ጠንካራ ፍተሻ እና ጥብቅ ምርመራ ይደረጋል" - አምባሳደር ዲና ሙፍቲ
የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለሰብአዊ እርዳታ ድጋፍ ወደትግራይ ክልል የሚደረጉ በረራዎች ላይ ጠንካራ ፍተሻ እና ምርመራ እንደሚደረግ አስታወቀ።
የሚኒስቴር መ/ ቤቱ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ሳምንታዊ መግለጫ በመስጠት ላይ ይገኛሉ።
አምባሳደሩ ለትግራይ ክልል ለሚደረገው የሰብአዊ እርዳታ የአለም አቀፍ ተቋማት የበረራ ፍቃድ ቢሰጥም፤ እያንዳንዱ በረራ ግን መነሻው ከአዲስ አበባ እንደሆነ ገልፀዋል።
ለሰብዓዊ እርዳታ በሚል ወደትግራይ ክልል የሚደረጉ በረራዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚገደርግ አስረድተዋል።
እያንዳንዱ በረራ አዲስ አበባ ካለፈ በኋላ ወደ ትግራይ ክልል እንደሚሄድ እና ሲመለሱም አዲስ አበባ አርፈው መሄድ እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።
መረጃው የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ ጣቢያ ነው።

እሁድ ጁላይ 11 ቀኑን ሙሉ በዳውንታውን ሲልቨር ስፕሪንግ
ማዲንጎ አፈወርቅ | Madingo
ብርሃኑ ተዘራ | Bere
ማሪቱ ለገሠ | Maritu
ሻምበል በላይነህ | Shambel
Featuring Peace Band
ሙዚቃ፤ ፋሺን ትርኢት ፤ ኮሜዲ ፤ ዲጄ ... ምን እበላ ብለው እንዳይጨነቁ የተለያዩ ባህላዊና ዘመናዊ ምግቦችና መጠጦች ተሰናድተዋል
Interested Vendors can apply on
[email protected] or call on 202 200 4997
- - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - -
#Ethiofest2021 #oneethiopianfest #ethiopia #dtss21 #dtss #djphatsu #djew #digistvshow #digis

የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ትላንት ድምፅ ሰጥቶ ነበር ?
ቱኒዝያ ሀገራችን #ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ የምትገነባውን ግድብ ውሃ መሙላት እንድታቆም ለተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ረቂቅ የውሳኔ ሐሳብ አቅርባ ነበር።
ይህ ረቂቅ የውሳኔ ሐሳብ ግብፅ፣ ኢትዮጵያ እና ሱዳን የአፍሪካ ሕብረት ሊቀ መንበር እና የተመድ ዋና ጸሐፊ በጋራ በሚገኙበት ድርድሩን እንደገና እንዲጀምሩ ይጠይቃል።
በግድቡ ሙሌትና አሠራር ላይ አስገዳጅ የሆነ ስምምነት በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ እንዲደረስም ጥሪ ያቀርባል።
የውሳኔ ሐሳቡ ስምምነቱ "በታችኛው የተፋሰሱ አገራት የውሃ ደኅንነት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንዳይደርስ በመከላከል ኢትዮጵያ ከግድቡ ኃይል የማመንጨት አቅሟን ማረጋገጥ አለበት" ይላል።
ሦስቱም አገራት ማንኛውንም መግለጫ ከመስጠት ወይም የድርድር ሂደቱን አደጋ ላይ ከሚጥል ማንኛውም አይነት እርምጃ እንዲቆጠቡ ያሳስባል።
ኢትዮጵያ በተናጠል ግድቡን እንዳትሞላ ይጠይቃል።
በግብፅ እና ሱዳን ጥሪ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ትላንት ለሊት ስብሰባ ተቀምጦ ነበር።
በስብሰባው ላይ አብኛው የምክር ቤቱ አባላት የታላቁ የህዳሴ ግድብ ድርድር በአፍሪካ ህብረት ማዕቀፍ እንዲከናወን ሃሳባቸውን አቅርበዋል።
ነገርን ግን የፀጥታው ምክር ቤት #በቱኒዝያ አማካኝነት በቀረበው ረቂቅ ውሳኔ ሀሳብ ላይ ድምፅ አልሰጠም። በምክር ቤቱ ይህ ነው የተባለ ውሳኔም አልተላለፈም፤ ነገር ግን የምክር ቤቱ አባላት በግድቡ ውዝግብ ዙሪያ ያላቸውን አቋም ገልፀዋል።
በቀረበው ረቂቅ የውሣኔ ሃሳብ ላይ እስካሁን ድረስ ትክክለኛው ድምፅ መስጫ ቀን ባይታወቅም እንደ አንዳንድ ዲፕሎማቶች ምንጭ ምናልባት በቀጣይ ሳምንት ድምፅ ሊሰጥ ይችላል ተብሎ ተገምቷል።

#GERD🇪🇹
"...የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የምትገነባው ሙሌት አካሂዳ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት ነው" - ፕ/ር ያዕቆብ አርሳኖ
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር እና የዓባይ ውሃ ጉዳይ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ያዕቆብ አርሳኖ ፥ ኢትዮጵያ ታላቁን የህዳሴ ግድብ የምትገነባው ሙሌት አካሂዳ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት በመሆኑ የሙሌት ጉዳይ ብዙ የሚያነጋግር እንዳልሆነ ገለፁ።
ፕሮፌሰር ያዕቆብ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ በሰጡት ቃል፤ ሁለተኛው ዙር የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት ጉዳይ ኢትዮጵያውያን እና የዓለምን ፖለቲከኞች ቀልብ በእጅጉ የሳበ ክስተት ነው ብለዋል።
በተለይ ግብጽና ወደግብጽ ተለጥፋ ያልተገባ ጭቅጭቅ ውስጥ የምትገኘው #ሱዳን በተነዙ የሐሰት ፕሮፓጋንዳዎችና እና አሳሳች መግለጫዎች የተነሳ የህዳሴው ግድብ ሁለተኛው እርከን ሙሌት በተጋነነ ወሬ ውስጥ ነበር ሲሉ ገልፀዋል።
መታወቅ የነበረበትም ሆነ አሁንም መታወቅ ያለበት ጉዳይ #ኢትዮጵያ ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የምትገነባው ሙሌት አካሂዳ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት መሆኑ ነው ሲሉ አስገንዝበዌ።
ይህ እንደሚሆን ደግሞ በኢትዮጵያ መንግስት ጥናት እና ዲዛይን ፣ በድርድሩ ሂደት ፣ በግድቡ ግንባታ ስራና በየጊዜው በሚወጡ በኢትዮጵያ መንግስት መግለጫዎች መገለጹን አስታውሰዋል።
#ኢፕድ

ኢትዮጵያ እስካሁን የዘጋችው ኤምባሲ አለ ?
የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የሆኑት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ “ኢትዮጵያ እስካሁን በይፋ የዘጋችው ኤምባሲ የለም” ሲሉ ዛሬ በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በተለያዩ ሀገራት የሚገኙት ኤምባሲዎቿን እንደዘጋች የሚናፈሰው መረጃ #ሀሰት መሆኑን አስገንዝበዋል።
“ነገር ግን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንደማንኛውም ተቋም ሪፎርም ላይ ይገኛል ” ያሉ ሲሆን የኤምባሲ እና ቆንስላ ፅህፈት ቤት ሰራተኞች መጥራት የተለመደ የስራ ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል።
ወደፊት የሚቀነሱና የሚዘጉ ኤምባሲዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ ግን ሳይጠቁሙ አላለፉም። #ENA

መረጃ ማጣሪያው የስም ቅያሪ አድርጓል።
ከዚህ ቀደም #በትግራይ ጉዳይ ላይ መረጃዎችን እያጣራ ሲያቀርብ የነበረው በፌዴራል መንግስት ስር የሚገኘው "የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማጣሪያ" ስሙን ቀይሯል።
ይህንንም በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ያሳወቀ ሲሆን አዲሱ ስያሜው "የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ ገፅ/Ethiopia Current Issues Fact Check" እንደሆነ ተገልጿል።
ከዚህ በኃላ ገፁ የትግራይን ጨምሮ #በመላው_ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያተኮሩ መረጃዎችን እንደሚያጣራ ገልጿል።

#OCHA
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት(ኦቻ) የተዛቡ መግለጫዎች ከመስጠት እንዲቆጠብ የኢትዮጵያ መንግስት ጠየቀ፡፡
መንግስት ኦቻ በትግራይ ሁኔታ የተዛቡ መግለጫዎች ሲያወጣ ነበር ብሏል፡፡
መንግስት ኦቻ የሚያከናውናቸውን ገንቢ ያልሆኑ ተግባራት ኢትዮጵያ ከተቋሙ ጋር በፈረንጆቹ ከ1984 አንስቶ የገነባቸውን ግንኙነት የሚሸረሽር በመሆኑ ድርጊቱን በመቃወም ለተ.መ.ድ. ዋና ጸሃፊ ድበዳቤ መፃፉን አስታውቋል።
የፌዴራል መንግስት የትግራይን ሁኔታ በተመለከተ የህግ ማስከበሩ ዘመቻ ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ “OCHA የነበረው ሚና እና የሚያወጣቸው የተዛቡ ሪፖርቶች ገንቢ አልነበሩም” ብሎ እንደሚያምንም መንግስት አስታውቋል፡፡
የኦቻ ሪፖርቶች የህወሐትን የተሳሳተ አስተሳሰብን የሚያጠናክር ፣የሚበራታታ እና ለማወደስ የተቀየሰ እንዲሁም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በክልሉ ያለውን ሁኔታ በተሳሳተ መንገድ እንዲረዳ የሚያደርግ ይመስላል ብሏል።
“OCHA ፓርላማ በአሸባሪነት የፈረጀውን ህገ-ወጥ ቡድን የትግራይ መከላከያ ሰራዊት /TDF/ እያለ የሚጠራ ተቋም ነው” ያለው መንግስት ከመስል ድርጊቱ እንዲቆጠብ እንዲሁም ለተቋሙ እና ኢትዮጵያ የቆየ ግንኙነት ሲባል የእርምት እርምጃዎች እንዲወስድ ሲል ጠይቋል፡፡
ያንብቡ : telegra.ph/Tigray-07-09
ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ

#Tigray
📞9167 👉 ICRC የአጭር የስልክ መስመር
📞0115527110 👉 የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ስልክ ቁጥር
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ፥ እስካሁ ከ300 ያላነሱ የመቐለ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከቤተሰቦቻቸው ጋር መረጃ እንዲለዋወጡ መደረጉን አስታውቋል።
የማህበሩ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ዶክተር ሰለሞን አሊ በክልሉ ከሚገኙ አለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ጋር በመተባበር በትግራይ ክልል የሚገኙ ተማሪዎችን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለማገናኘት እየተሰራ ያለው ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል።
እስካሁን ድረስ መቐለ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ከ300 በላይ ተማሪዎችን ደህንነት የሚገልፅ የሰላምታ መልክቶች በመቀበል ለቤተሰቦቻቸው ማስተላለፍ መቻሉን ዶ/ር ሰለሞን ጠቁመዋል፡፡
በሚቀጥሉት ጊዚያት በክልሉ ውስጥ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ተማሪዎች ያሉበትን ሁኔታ በተመለከተና የሰላምታ መልክቶችን በመቀበል ለቤተሰቦቻቸው የማድረስ ሂደቱ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
ዶ/ር ሰለሞን የተማሪ ወላጆች ተረጋግተው በፅናትና በትዕግስት እንዲጠብቁ አሳስበዋል፡፡
በ9167 የአለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) የአጭር የስልክ መስመር ላይ የተማሪ ወላጆች ተጨማሪ ማብራሪያ መረጃ ማግኘት ይችላሉ ብለዋል። በተጨማሪ በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ስልክ ቁጥር 0115 52 71 10 እና በ 9167 መረጃ መጠየቅ ይችላሉ ሲሉ #ለአሃዱ_ኤፍ_ኤም 94.3 ሬድዮ ተናግረዋል።

TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ የተሰባሰቡ ጥቅል መረጃዎች ፦ • የሰላም ሚኒስቴር በትግራይ እየተከናወነ ስላለው የሰብዓዊ እንቅስቃሴ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ገለፃ ማድረጉ። • ወደትግራይ ለሰብዓዊ ድጋፍ የበረራ ፍቃድ መስጠቱ። • እስካሁን በአየር እርዳታ ለማድረስ የጠየቀ ዓለም አቀፍ ተቋም አለመኖሩ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን መግለፁ። • የሴናተር ቦብ ሜንዴዝ ደብዳቤ። …
#Update
ከቀናት በፊት የትግራይ ተወላጅ የሆኑ እና በተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ ዜጎች ደረሰብን ስላሉት እንግልትና አጋጥሞናል ስላሉት ማዋከብ ሪፖርት አደርገው ነበር።
አሁንም ይህ ሁኔታ እንዳልተሻሻለ ከተለያዩ የሀገራችን ከተሞች የሚላኩት ሪፖርቶች እያስረዱ ነው።
ከአሸባሪው ህወሓት ጋር ግኝኑነት አላችሁ በሚል ብቻ ያለንም በቂ ማስረጃ ፤ አንድም ቀን ወደትግይ እንኳን ሳንሄድ በጥርጣሬ ተይዘን የተለቀቅን አለን ብለዋል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ የትግራይ ተወላጅ ነኝ ያለ ስሙ እንዲገለፅ ያልወደደ ዜጋ በላከው መልዕክት ፥ "እኔ ሃገሬ ናት ብዬ በመንኳት ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ውስጥ ነው የምኖረው፤ ግን ሀገሬ መሆኑን እስክጠራጠር ድረስ ትግራዋይ በምሆኔ ብቻ በነጻነት መኖር አልቻልኩም፤ ያጠፋውት ጥፋት ሳይኖር እራሴን እንደ ጥፋተኛ እንድቆጥር እሚያስገድደኝ ሁኔታ ውስጥ ነው ያለውት" ብሏል።
ከሽብረተኛው ድርጅት ጋር ግንኙነት አላችሁ በሚል የታሰሩ እና ማሸማቀቅ የሚደርስባቸው ግለሠቦች እንዳሉ መልዕክታቸውን የላኩ ዜጎች ገልፀዋል።
ይህ ሁኔታ ፍፁም ተገቢነት ስለሌለው የሚመለከተው አካል በአስቸኳይ የእርምት እርምጃ ሊወስድ ፣ ሰዎች ያለምንም ወንጀል በዚህ ደረጃ እንዲገላቱ ማድረግም ሊቆም እንደሚገባ አሳስበዋል።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ከሰሞኑ በአዲስ አበባ የትግራይ ክልል ተወላጅ የሆኑ ነዋሪዎችና የሚዲያ ሰዎች እንዲሁም ሌሎች ከትግራዩ ጉዳዩ ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል ተጠርጥረው የታሰሩ ሰዎችን ሁኔታን እየተከታተለ እንደሚገኝ አሳውቆ ነበር።
ሁኔታው በነዋሪዎች ላይ ማንነትን መሰረት ባደረገ ለጥርጣሬ እና መድልዎ የሚያጋልጥ ተግባር እንዳይሆንም ስጋት እንዳሳደረበት ኮሚሽኑ አስገንዝቧል።
ያንብቡ ፦ telegra.ph/TIGRAWAY-07-09

#Ethiopia
የ24 ሰዓት የኮቪድ ሪፖርት :
• የላብራቶሪ ምርመራ - ,6357
• ቫይረሱ የተገኘባቸው - 72
• ህይወታቸው ያለፈ - 1
• ከበሽታው ያገገሙ - 116
አጠቃላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች 276,871 የደረሱ ሲሆን ከእነዚህም መካከል 4,342 ህይወታቸው ሲያልፍ 261,933 ሰዎች አገግመዋል። ክትባት የተከተቡ ዜጎች 2,055,593 ደርሰዋል።

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አትሌት ለሜቻ ግርማ ድል ቀንቶታል!
ዛሬ ሞናኮ ላይ የዳይመንድ ሊግ ውድድር እየተካሄደ ነው።
በ3 ሺ ሜትር መሰናክል እልህ አስጨራሽ የነበረ ፉክክር የተካሄደበት ውድድር የተካሄደ ሲሆን የሀገራችን ልጅ ኢትዮጵያዊው አትሌት ለሜቻ ግርማ 8:07.75 በመግባት የአለም ፈጣኑን ሰዓት አስመዝግቧል።
Via @tikvahethsport

#AddisAbaba
አዲስ አበባ ከተማ የካ ክ/ከተማ በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ሃገር ውስጥ የገቡ ሽጉጦች የክላሽ ጥይቶችና ለሃሰተኛ የገንዘብ ህትመት የሚውሉ በኬሚካል የተነከሩ ወረቀቶች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያዎቹ የተገኙት ሰኔ 21/ 2013 ዓ.ም በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ልዩ ቦታው ኮተቤ መምህራን ኮሌጅ አካባቢ ከሚገኝው መኖሪያ ቤት ውስጥ ነው።
ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ሀለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ተጠርጣሪዎቹ በህገ-ወጥ መንገድ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሊያስገቡ የነበረው 30 ኢኮሊፒ የተባለ ቱርክ ሰራሽ ሽጉጥ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ ፖሊስ ባደረገው ፍተሻ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል።
በሌላ በኩል ሰኔ 12 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 12፡30 ሰዓት በየካ ክ /ከተማ ወረዳ 13 ልዩ ቦታው ካራ ልዩ ቦታዉ "ለምለም አምባ" በተባለዉ አካባቢ ፖሊስ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ በአንድ ተጠርጣሪ ላይ ባደረገው ክትትል መኖሪያ ቤት ውስጥ በህገ-ወጥ መንገድ የተከማቸ አንድ ሺ አንድ መቶ የክላሽን-ኮቭ ጥይት ይዟል።
በተጨማሪም ከመኖሪያ ቤቱ ውስጥ ሃሰተኛ የገንዘብ ኖቶችን ለማተም የሚረዱ በኬሚካል የተነከሩ አንድ መቶ አርባ ወረቀቶችና እና የተለያዩ ስምንት የባንክ ደብተሮች ሊያዝ ችሏል።
መረጃው የአ/አ ፖሊስ ኮሚሽን ነው።

ከሰኔ 30 - ሀምሌ 2/2013 ድረስ 6,944 ዜጎቻችን ከሳዑዲ አረቢያ ተመልሰዋል።
ኢትዮጵያ በሳዐዲ አረቢያ በችግር ላይ የሚገኙ ዜጎቿን በተጠናከረ ዘመቻ እያስወጣች ትገኛለች።
በ3 ቀናት ውስጥ ማለትም ከሰኔ ሰላሳ እስከ ሃምሌ ሁለት ድረስ በአጠቃላይ 6,944 ዜጎች ወደሀገራቸው መመለሳቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
ትላንት ወደሀገር እንዲመለሱ የተደረጉት 2,536 ዜጎች ሲሆኑ ከነዚህ መካከል 161 ህፃናት እና 333 ሴቶች ይገኙበታል።
ሃምሌ አንድ የተመለሱት 2,212 ዜጎች ሲሆኑ 381 ሴቶች እና 183 ህፃናት ይገኙበታል። እንዲሁም ሰኔ 30 የተመለሱት 2,196 ዜጎቻችን ሲሆኑ 196ቱ ሴቶች 88ቱ ህፃናት ናቸው።