TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#Ethiopia🇪🇹

በቶኪዮ ኦሎምፒክ ላይ ተሳታፊ የሆነው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልኡካን ቡድን አባላት ልምምዳቸውን አጠናክረው በመስራት ላይ ይገኛሉ። የመጀመሪያው ተጓዥ የኦሎምፒክ ልኡካን ቡድን ከ17 ቀናት በኋላ ውድድሩ ወደ ሚካሄድበት ቶኪዮ የሚያቀኑ ይሆናል።

• የአትሌቶቻችን ዝግጅት ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዟል ።

@tikvahethsport
የሀይቲ ፕሬዝዳንት ተገደሉ።

የሀይቲው ፕሬዝዳንት ጆቭኔል ሞይስ ማክሰኞ ለረቡዕ አጥቢያ በግል መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ መገደላቸው ተሰማ። የፕሬዜዳንቱ ባለቤት ጉዳት ደርሶባቸዋል።

- ፕሬዚዳንቱ የተገደሉት መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ነው።
- የፕሬዜዳንቱን ግድያ ያሳወቁት የሀገሪቱ ጊዜያዊ ጠ/ሚ ናቸው።
- በሀገሪቱ የፖለቲካ አለመረጋጋት ፣ ከ2018 ጀምሮ ደግሞ በሙስና መበራከት ስልጣናቸውን እንዲለቁ የሚጠይቅ ተቃውሞ ተነስቶ ነበር።

የሀይቲ ጊዜያዊ ጠ/ሚኒስትር የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ከተገደሉ በኋላ ፥ 'የመንግስት ቀጣይነት' ለማረጋገጥ ሁሉም እርምጃዎች ተወስደዋል ብለዋል።

* ይህ መረጃ ተጨማሪ ያታከልበታል !

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን (MSF) ሶስት ባልደረቦቹ ትግራይ ክልል ውስጥ መገደላቸውን ሪፖርት አደረገ። MSF የባልደረቦቹን ሞት ማረጋገጫ ከሰማ በኃላ ሃዘን ላይ መሆኑ ገልጿል። የደንገተኛ ጊዜ አስተባባሪ ማሪያ ኸርናዴዝ ፤ ረዳት አስተባባሪ ዮሀንስ ሃለፎም ረዳ፣ ሹፌር ቴድሮስ ገብረማርያም ገ/ሚካኤል ትላንት ከሰዓት ጉዞ እያደረጉ እያለ ግንኙነታቸው ተቋርጦ ነበር። ዛሬ ጥዋት ባዶ መኪናቸው ተገኝቷል፤…
MSF በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች እንቅስቃሴ አቆመ።

ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን (MSF) በአቢይ አዲ፣ አክሱም፣ ዓዲግራት (በማዕከላዊ እና ምስራቃዊ ትግራይ) እንቅስቃሴ ማድረግ አቋረጠ።

MSF እአአ ጁን 24 በትግራይ ክልል በ3 ባልደረቦቹ ላይ በተፈፀመው አሰቃቂ ግድያ ምክንያት ነው ከላይ በተገለፁት ቦታዎች የሰብዓዊ ድጋፍ እንቅስቃሴውን ያቆመው።

MSF በሌሎች የትግራይ ክልል አባቢዎች አቸኳይ ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች የሚያደረገውን እገዛ እጅግ ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ እንደሚቀጥል አሳውቋል።

በተጨማሪም በትግራይ ክልል ውስጥ ስለተገደሉት ሶስቱ ባልደረቦቹ አስቸኳይ ምርመራ እንዲደረግ እና የእርዳታ ሰጪ ሰራተኞች ስራቸውን ደህንነታቸው በተጠበቀበት ሁኔታ እንዲሰሩ እንዲደረግ አጥብቆ ጠይቋል።

የMSF የኦፕሬሽን ዳይሬክተር ተሬሳ ሳንክሪስቶቫል ፥ "የባልደረቦቻችን ግድያ ከተፈፀመ ወደ ሁለት ሳምንት ገደማ ሆኖታል እስካሁ ሃላፊነቱን የወሰደ አካል የለም እንዲሁም በአሟሟታቸው ሁኔታ ላይ ያሉ ሁኔታዎች አሁንም ግልፅ አይደሉም" ብለዋል።

ዳይሬክተሯ አክለውም ፥ "በባልደረቦቻችን አሟሟት ላይ ስለተፈጠረው ክስተት እውነታዎች ለማጣራት እና ተጠያቂው ማን እንደሆነ ዝርዝር እንዲቀርብልን በሚመለከታቸው አካላት አፋጣኝ ምርመራ እንዲደረግ የምንጠይቀው ለዚህ ነው ፤ በዚህ አስከፊ ወቅት በበርካታ የትግራይ አካባቢዎች እንቅስቃሴያችን ለማቆም መወሰናችን በጣም አሳዛኝ ነው ነገር ግን አስፈላጊ ውሳኔ ውስነናል።" ብለዋል።

MSF በአቢይ አዲ ፣ በአክሱም እንዲሁም በአዲግራት እንቅስቃሴውን ማቆሙ እየተሰጠ ባለው የሕይወት አድን ዕርዳታ ስራ ላይ ከፍተኛ የሆነ ክፍተት ይፈጥራል ተብሏል።

@tikvahethiopia
የሰኔ ወር የዋጋ ግሽበት ...

የ2013 የሰኔ ወር የዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ24.5 ከመቶ ጭማሬ አሳይቷል፡፡

የምግብ ዋጋ ግሽበት የሰኔ ወር ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ28.7 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

በዳቦና እህሎች ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ በያዝነው ወርም የቀጠለ ሲሆን ፥ በተለይ የበቆሎና የገብስ ዋጋ በፍጥነት #ጨምሯል፡፡ በተጨማሪ ፦
- ሥጋ፣
- የምግብ ዘይት፣
- ቅቤ፣
- ቅመማ ቅመም፣
- በርበሬና ቡና የዋጋ ጭማሪ በዚህም ወር በመቀጠላቸው ለዋጋ ግሽበት ምጣኔ በፍጥነት መጨመር አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡

ያለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ዋጋ ከአሁኑ ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር በንጽጽር ዝቅተኛ ስለነበር የዋጋ ግሽበቱ በያዝነው ወርም ከፍ ብሎ ታይቷል፡፡

በሌላ በኩል " ምግብ ነክ " ያልሆኑ የኢንዴክሱ ክፍሎች የዋጋ ግሽበት የሰኔ ወር 2013 ዓ.ም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ19 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

ከምግብ ነክ ያልሆኑ የኢንዴክሱ ክፍሎች የዋጋ ግሽበት ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከፍ እንዲል ካደረጉት ዋና ምክንያቶች ውስጥ በተለይም
- በአልኮል፣
- ልብስና ጫማ፣
- የቤት እንክብካቤና ኢነርጂ (ማገዶና ከሰል)፣
- የቤት መስሪያ እቃዎች (የቤት ኪራይ፣ ሲሚንቶና የቤት ኪዳን ቆርቆሮ) ፣
- ህክምና እና ጌጣጌጥ (ወርቅ) ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ ነው፡፡

አጠቃላይ ዋጋ ግሽበት ካለፈው ወር ጋር ሲነፃፀር 7 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጄንሲ አመልክቷል፡፡

#ኢፕድ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ዛሬ ምሽት በመረዋ ቀበሌ የትራፊክ አደጋ ደረሰ። በጅሌ ጥሙጋ ወረዳ መረዋ ቀበሌ ውስጥ ልዩ ስሙ " ቆሮ " የሚባል አካባቢ ከደብረብረሃን ወደ ራያ የአካባቢ ሚሊሻ ይዞ ሲጓዝ የነበረ አይሱዚ ቅጥቅጥ የህዝብ ማመላለሻ መኪና ከምሽቱ 3:30 ገደማ የትራፊክ አደጋ እንደደረሰበት የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ሪፖርት አደረገ። ከደብረ ብረሃን ከተማ ወደ ራያ ሲጓዝ የነበረው " ኮድ 3 ታርጋ ቁጥሩ 23588 " የሆነ…
#Update

'በትላንት ምሽቱ አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት አልፏል'

ትላትና ምሽት በጅሌ ጥሙጋ ወረዳ በመረዋ ቀበሌ ስለደረሰው የትራፊክ አደጋ የወረዳው ፖሊስ ፅህፈት ቤት በዛሬው ዕለት ዝርዝር መረጃ ሪፖርት አድርጓል።

አደጋው የደረሰበት ቦታ እና ሰዓት :

- መረዋ ቀበሌ ልዩ ስሙ "ቆሮ" የሚባል አካባቢ። ከምሽቱ 3:30 ገደማ።

አደጋው የደረሰበት መኪና ዝርዝር መረጃ :

- ከደብረ ብረሃን ከተማ ወደ ራያ የአካባቢ 48 የሚሊሻ አባላትን ይዞ ሲጓዝ የነበረ FSR ቅጥቅጥ የህዝብ ማመላለሻ መኪና። ኮድ 3 ታርጋ ቁጥሩ 23588 ነው።

የደረሰ ጉዳት ዝርዝር :

- ሹፌሩን ጨምሮ የ3 ሰው ህይወት አልፏል።
-13 ሰዎች ከባድ አካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።
- 32 ሰዎች ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

በአደጋው ስለተጎዱ ሰዎች ዝርዝር ሁኔታ :

- 2 አስክሬን ለምርመራ ሚኒልክ ሆስፒታል ተልኳል።
- በአደጋው ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ወደ አጣዬ ድስትሪክ ሆስፒታል ገንተው የህክምና ተከታትለው ከሆስፒታል ወጥተዋል።
- በከባድ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ግለሰቦች ወደ ደብረብረሃን ሪፈራል ሆስፒታል ተልከዋል።

የአደጋው መንስኤ ይታወቃል ?

እንደ ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ፖሊስ ፅህፈት ቤት ሪፖርት እስካሁን ድረስ የአደጋው መንስኤ አይታወቅም፤ በምርመራ እየተጣራ ነው።

NB : ትላንት ምሽት በትራፊክ አደጋ የደረሰባቸው ገለሰቦች በሰንበቴ ከተማ ጤና ጣቢያ የህክምና አገልግሎእ እያገኙ ነው ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ስህተት መሆኑንና ሁሉም ታካሚዎች በአጣዬ ድስትሪክ ሆስፒታል እና በደብረ ብረሃን ሪፈራል ሆስፒታል ህክምና እያገኙ መሆኑን የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ኮሚኒኬሽን አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#Ethiopia

የ24 ሰዓት የኮቪድ ሪፖርት :

• የላብራቶሪ ምርመራ - 4,772
• ቫይረሱ የተገኘባቸው - 85
• ህይወታቸው ያለፈ - 3
• ከበሽታው ያገገሙ - 93

አጠቃላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች 276,683 የደረሱ ሲሆን ከእነዚህም መካከል 4,335 ህይወታቸው ሲያልፍ 261,749 ሰዎች አገግመዋል። ክትባት የተከተቡ ዜጎች 2,053,298 ደርሰዋል።

@tikvahethiopia
#Tigray

በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ የተሰባሰቡ ጥቅል መረጃዎች ፦

• የሰላም ሚኒስቴር በትግራይ እየተከናወነ ስላለው የሰብዓዊ እንቅስቃሴ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ገለፃ ማድረጉ።

• ወደትግራይ ለሰብዓዊ ድጋፍ የበረራ ፍቃድ መስጠቱ።

• እስካሁን በአየር እርዳታ ለማድረስ የጠየቀ ዓለም አቀፍ ተቋም አለመኖሩ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን መግለፁ።

• የሴናተር ቦብ ሜንዴዝ ደብዳቤ።

• የአውሮፓ ህብረት ስብሰባ እና የኢትዮጵያ ምላሽ።

• በትግራይ ክልል ከሚገኙ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጋር በተያያዘ መግለጫ ሊሰጥ መሆኑ።

(ዛሬ በትግራይ ክልል ጉዳይ የተነገሩ የተጠቃለለ ሪፖርት)
[ ለቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የቀረበ - ከሚዲያዎች የተሰባሰብ ]

ያንብቡ👇
https://telegra.ph/Tigray-Update-07-07
"... የ2ኛው ዓመት የውሃ ሙሌት #ነሃሴ መጨረሻ ላይ ይጠናቀቃል" -ኢንጅነር ጌዲዮን አስፋው

የህዳሴ ግድብ ተደራዳሪና የባለሙያዎች ቡድን ሰብሳቢ ኢ/ር ጌዲዮን አስፋው ለኢዜአ በሰጡት ቃል የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 2ኛው ዙር የውሃ ሙሌት እየተከናወነ ያለው ሶስቱ አገሮች በፈረሙት የመርህ ስምምነት መሰረት መሆኑን አሳውቀዋል።

ኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን እ.ኤ.አ. በ2015 በመሪዎቻቸው አማካኝነት በሱዳን ካርቱም የህዳሴ ግድቡን ድርድር አስመልክቶ የመርሆች ስምምነት ተፈራርመዋል።

የመርህ ስምምነቱ አስር አንቀጾችን ያካተተ ሲሆን የሶስቱንም አገሮች ፍትሃዊና ምክንያታዊ የውሃ አጠቃቀም ለማረጋገጥ ያለመ መሆኑ ይታወቃል።

በዚህም ኢትዮጵያ ፣ ግብጽ እና ሱዳን በተስማሙት የመርህ ስምምነት መሰረት ሁለተኛው ዙር የግድቡ የውሃ ሙሌት እየተከናወነ ኢንጅነር ጌዲዮን አስፋው ገልፀዋል።

በታላቁ ህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት ላይ የሶስቱ አገሮች ባለሙያዎች የተስማሙባቸው ነጥቦች የተቀመጡ መሆኑን አስታውሰው አገሮቹ በዚሁ መሰረት መስማማታቸውን አስረድተዋል።

ግብጽና ሱዳን በመርሆች ስምምነት ውስጥ ሁለት ጥናቶች እንዲካሄዱ የሚያስቀምጥ ቢሆንም ግብጽ እና ሱዳን ጥናቱ እንዳይካሄድ ሲያስተጓጉሉ ነበር ብለዋል።

አገሮቹ ስምምነቱን ከተፈራረሙ በ15 ወር ውስጥ ሁለት (2) ጥናቶችን ማከናወን እንዳለባቸው ቢያስቀምጥም ጥናቶቹ እንዳይካሄዱ ግብጽና ሱዳን በያዙት ግትር አቋም ሳይሳካ ቀርቷል ነው ያሉት።

አለም አቀፉ ማህበረሰብ ግብጽ እንዲሁም ሱዳን የግድቡን ውሃ ሙሌት በተመለከተ የሚሰጡትን የተዛባ መረጃ ሊመረምር እንደሚገባም ገልጸዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/ENA-07-07

#ኢዜአ

@tikvahethiopia
የኢፌዴሪ አየር ሃይል ያሰለጠናቸውን ምልምል ወታደሮች በማስመረቅ ላይ ይገኛል ፡፡

ተመራቂ ምልምል ወታደሮቹ ከነገ ጀምሮ የበረራ ፣ የጥገና እና የቴክኒሻን ትምህርቶች ወደሚያገኙባቸው ተቋማት እንደሚገቡ የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሰራዊት አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#Attention

የልዩ ሀይል ደንብ ልብስና ሹጉጥ ታጥቀው የፀጥታ አካል በመምሰል ዝርፊያ ከምፍጽሙ ግለሰቦች ህ/ተሰቡ እንዲጠነቀቅ ተባለ።

ይህን ያለው የሀላባ ቁሊቶ ከተማ ሠላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ነው።

በቀን 27/10/2013 ዓ/ም ከምሽቱ 5:00 ሰዓት አከባቢ በሀላባ ዞን ሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር በሙራሳ ቀበሌ መንደር 7 ሁለት ግለሰቦች የደቡብ ልዩ ሀይል ደንብ ልብስ በመልበስ እና ሹጉጥ ታጥቀው በመሸታ ቤት ለወንጀል ተግባር በዝግጅት ላይ እያሉ በደረሰ ጥቆማ በሀለባ ቁሊቶ ፖሊስና በልዩ ሀይል አመራር አካለት ትብብር በቁጥጥር ስር ውሏል።

ህብረተሰቡ መሰል የማተለል ተግባር ከምፈጽሙ አካለት እራሱን በመጠበቅ አጠራጠሪ ሁኔታዎችን በምመለከትበት ወቅት ለፖሊስ ጥቆማ በመስጠት ትብብር እንዲያደርግ ተጠይቋል።

Photo Credit : የሀላባ ቁሊቶ ከተማ ሠላምና ፀጥታ ጽ/ቤት

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ጃኮብ ዙማ የ15 ወራት እስር ተፈረደባቸው። የደቡብ አፍሪካ የቀድሞ ፕሬዘዳንት ጃኮብ ዙማ የ15 ወራት እስር ተፈርዶባቸዋል። የ79 ዓመቱ ጃኮብ ዙማ በአገሪቱ እርቀ ሰላም ኮሚሽን ፍ/ቤት መገኘት ሲኖርባቸው ባለመገኘታቸው ከህግ ተቋማት ትችቶች ሲቀርብባቸው ነበር። ይህ እውነትን አፈላላጊ ኮሚሽን አቋቁሞ የዙማን ጉዳይ እየተመለከተ የነበረ ሲሆን ጃኮብ ዙማ ግን በዚህ ፍርድ ቤት አልቀርብም ሲሉ በይፋ ተቃውመው…
እጃቸውን ለፖሊስ የሰጡት ጃኮብ ዙማ ...

የቀድሞ የደ/አፍሪካ ፕሬዝዳንት የሆኑት #ጃኮብ_ዙማ በፍርድ የተበየነባቸውን የእስር ቅጣት ለመጀመር ራሳቸውን ለፖሊስ አስረክበዋል።

ትላንት [ረቡዕ] ረፋድ ላይ ከመኖሪያ ቤታቸው አቅራቢያ ወደሚገኝ አንድ እስር ቤት እንዳመሩ ተገልጿል።

የ79 ዓመቱ ዙማ ይህንን ባያደርጉ ፖሊስ አመሻሹ ላይ በቁጥጥር ስር ለማዋል እንደሚገደድ አስጠንቅቆ ነበር።

ዙማ አንድ የሙስና ምርመራ ላይ ላለመሳተፍ አሻፈረኝ በማለታቸው ነው የ15 ወራት እስር የተፈረደባቸው።

ይህ ፍርድ በደቡብ አፍሪካ ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ የሕግ ጥያቄ ያስነሳ ሲሆን ፣የቀድሞ ፕሬዝዳንት በተሰጠ የቀን እና የሰዓት ገደብ እስከ ረቡዕ እኩለ ለሊት በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ውሳኔን ያሳለፈ መሆኑን #ቢቢሲ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
ተመድ የኢትዮጵያን ወታደሮችን ሸለመ።

643 #የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪዎች በደ/ሱዳን ላደረጉት የሰላም ማስከበር አገልግሎት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሜዳሊያ ተቀብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪዎች ወደ ደቡብ ሱዳን ከተሰማሩ ወዲህ ግጭቶች እንዲቀንሱ ፣ የሰብአዊ ድጋፍ ለድጋፍ ፈላጊዎች በፍጥነት እንዲደርስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡

ለኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪዎች የተደረገው የእውቅና ስነ ስርዓት ላይ የተመድ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተው እንደነበር #UNMISS ን ዋቢ አድርጎ ኢብኮ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013

በዛሬው ዕለት በነገሌ ምርጫ ክልል ለህዝብ ተወካዮች እና ለክልል ምክር ቤቶች የሚወዳደሩ ዕጩዎች ምርጫ እየተካሄደ ነው።

ምርጫው ከጠዋት 12 ሰዓት ጀምሮ ነው እየተካሄደ ሚገኘው።

ለምርጫው ከ150 በላይ ታዛቢዎችና የምርጫ አስፈጻሚዎች መመደባቸውን ተገልጿል።

በምርጫ ክልሉ ለሁለቱም ምክር ቤቶች ሁለት በግል፣ አንድ ከኢዜማ እንዲሁም አራት ከብልጽግና ፓርቲ ዕጩዎች ለውድድር ቀርበዋል። #ENA

@tikvahethiopia