TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#Tigray

የትግራይ ክልል ኃይሎች ከአማራ ክልል ጋር ወደሚያዋስነው የድንበር አካባቢ እየተንቀሳቀሱ ነው ተባለ።

በትግራይ የሚገኙ የዓይን እማኞችን ጠቅሶ 'ዘ ጋርዲያ' ጋዜጣ እንደዘገበው ከሆነ የህወሓት ኃይሎች በብዙ መኪኖች ተጭነው ወደ ምዕራብ አቅጣጫ አምርተዋል።

በሌላ መረጃ ፦ የአማራ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ አገኘሁ ተሻገር "የአማራ ክልልን ከማንኛውም ጥቃት ለመመከት አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል" ሲሉ ተናግረዋል።

ይህን ያሉት ዛሬ በሰጡት መግለጫ ነው።

የክልሉ ፕሬዜዳንት፥ "አሸባሪው ትህነግ እዚህ ግባ የሚባል ተፅዕኖ አያደርስም" ማለታቸውን አሚኮን ዋቢ በማድረግ ቢቢሲ ዘግቧል።

የፌደራል መንግሥት መቐላ ለወራት ተቆጣጥሮ ከቆየ በኋላ ከሳምንት በፊት በርካታ የትግራይ አካባቢዎችን ለቅቆ መውጣቱ ይታወሳል።

የትግራይ ኃይሎች መቐለን ጨምሮ በርካታ የትግራይ አካባቢዎችን በቁጥጥራቸው ሥር እንደሆኑ አስታውቀዋል።

የፌዴራል መንግስት ሰኞ ሰኔ 21 ሰብዓዊነት ላይ የተመሰረተ የተናጠል የተኩስ አቁም ቢያውጅም በትግራይ ኃይሎች በኩል የተኩስ አቁም ለማድረግ ባለ7 ነጥብ ቅድመ ሁኔታዎችን ማስቀመጣቸው አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#GERD ኢትዮጵያ የሁለተኛው ዙር የታላቁ ህዳሴ ግድብ የመሙላት ሂደት መጀመሩን እንዳሳወቀቻት ግብፅ ገለፀች። የግብፅ የውሃና መስኖ ሚኒስቴር የ2ኛው ዙር ሙሌት መጀመሩን "ኢትዮጵያ በይፋ ለግብፅ አሳውቃለች" ሲል ዛሬ መግለፁን ሮይተርስን ጨምሮ ሌሎች ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች እየዘገቡት ይገኛል። የህዳሴ ግድብ ሁለተኛው የውሃ ሙሌት ሂደት ስለመጀመሩ ኢትዮጵያ ለግብፅ በይፋዊ ደብዳቤ እንዳሳወቀቻት በግብፅ…
* Confirmed

ኢትዮጵያ የግድቡን 2ኛ ዙር ውሃ መሙላት መጀመሯን ለሱዳን እና ግብፅ በደብዳቤ ማሳወቋ ተረጋገጠ !

ኢትዮጵያ እአአ በ2015 በሶስቱ ሀገራት መካከል በተደረሰው የመርሆች ስምምነት መሰረት ግብፅና ሱዳን ለዝግጅት እንዲያመቻቸው ሲባል የግድቡን ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት መጀመሯን በይፋዊ ደብዳቤ እንዳስታወቀቻቸው የታላቁ ህዳሴ ግድብ የተደራዳሪ ከሚቴ አባል ፕሮፌሰር ይልማ ስለሺ #ለኢፕድ ገለፁ።

መሰረታዊ መረጃ ሳይት ድረስ ሂደው የማየት፣ አብረው መወያየት እና ባለሙያዎቹ አብረው እንዲነጋገሩ የማድረግ ስራዎች ባለፉት አስርት አመታት ከውሃ ባለሙያዎች፣ ከፖሊቲካኞች እንዲሁም ከዲፕሎማቶች ጀምሮ ስናደርገው የከረምነው ነው ብለዋል ፕሮፌሰር ይልማ።

ኢትዮጵያ ትናንት በይፋዊ ደብዳቤ የሰጠችው መረጃ በዚህ መርህ የተመርኮዘ እንደሆነና ይህም የመረጃ ልውውጥ አንዱ አካል ነው ሲሉ አብራርተዋል።

ሀገራቱም ይህን በመገንዘብ በእነሱ በኩል የሚያስተካክሉትን ጉዳዮች ሲያስተካክሉ ነበር ያሉት ፕሮፌሰር ይልማ፤ ሀገራቱ በስምምነታቸው መሰረት ግድቡ ቀስ በቀስ ሀምሌና ነሃሴ ላይ እንደሚሞላ ያውቁታል ግን ማረጋገጫ እንዲሆናቸው አሁን ተነግሯቸዋል ብለዋል፡፡

ሀገራቱ ሀምሌና ነሃሴ ይሞላል የሚለውን መረጃ አስቀድመው በተጨባጭ አውቀው በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴራቸው በኩል ሙሌቱ አይጎዳንም፤ ለዚህም እየተዘጋጀን ነው ሲሉ መደመጣቸውን ፕሮፌሰር ይልማ አስታውሰዋል።

የውሃ ሙሌቱ የማይካሄድ ቢሆን ኖሮ የቅድሚያ ዝግጅቱ ለወጪና ለኪሳራ ስለሚዳርጋቸው ዝግጅት ማድረግ አያስፈልጋቸውም ነበር ሲሉ ፕሮፌሰር ይልማ ለኢፕድ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
#Ethiopia

የ24 ሰዓት የኮቪድ ሪፖርት :

• የላብራቶሪ ምርመራ - 4,837
• ቫይረሱ የተገኘባቸው - 95
• ህይወታቸው ያለፈ - 3
• ከበሽታው ያገገሙ - 500

አጠቃላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች 276,598 የደረሱ ሲሆን ከእነዚህም መካከል 4,335 ህይወታቸው ሲያልፍ 261,656 ሰዎች አገግመዋል። ክትባት የተከተቡ ዜጎች 2,049,573 ደርሰዋል።

@tikvahethiopia
እነ አቶ ጃዋር መሐመድ ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት አልቀረቡም።

ተከሳሾቹ ከዚህ በኋላ ፍርድ ቤት አንቀርብም ክርክሩ የፖለቲካ ክርክር ነው ፤ የሚፈታውም በአስፈፃሚው አካል እንጂ በፍርድ ቤቱ አይደለም’’ ሲሉ አስታውቀዋል።

* እነ አቶ ጃዋር ፍርድ ቤት እንደማይቀርቡ በድጋሚ የገበፁበት ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል።

Credit : የኦሮሞ የፖለቲካ እስረኞች ጠበቆች ቡድን

@tikvahethiopia
#መቐለ_ዩኒቨርሲቲ

ሀምሳ ሁለት (52) ተማሪዎችና አንድ መምህር ከመቐለ ዩኒቨርሲቲ ኩሓ ካምፓስ በመውጣት በመኪና ወደ አባላ ከተማ (አፋር) መጓዛቸውንና ከዚያም ከአባላ ወደ አፍዴራ ሲጓዙ 'ስልሳ ስድስት' የሚባል የፍተሻ ጣቢያ ላይ ላይ በአፋር ክልል ፖሊስ አግኝቶ ተማሪ መሆናቸው ካረጋገጠ በኋላ ዛሬ ከሰዐት ለሠመራ ዩኒቨርሲቲ ማስረከቡን ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ሰምቷል።

በመጀመሪያ 19 ተማሪዎች እና አንድ መምህር በሠመራ ዩኒቨርሲቲ ድጋፍ ዛሬ ወደ አዲስ አበባ መመለሳቸው የተነገረ ሲሆን ቀሪ 33ቱን የሠመራ ዩኒቨርሲቲ ነገ ጠዋት ተማሪዎቹን በባስ አሽኛኝት እንደሚያደረግላቸው የህዝብ ግንኙነት ባለሙያው ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ አረጋግጠዋል።

ተማሪዎቹ በጉዟቸው ወቅይ ምንም የተለየ ችግር ባይገጥማቸውም ፤ ምግብ ባለማግኘታቸው አስከፊ ግዜ እንዳሳለፉ አልደበቁም። ከ52ቱ ተማሪዎች አንድ ሴት ተማሪ ያለች ሲሆኑ አብዛኛዎች የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ናቸው።

በተማሪዎቹ ጉዳይ አስተያየት የጠየቅነው የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር "አዲስ ነገር ሲኖር ጠቅለል አርገን" እናሳውቃለን ብሏል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መረጃዎች በ @tikvahuniversity በስፋት ማግኘት ይቻላል።

https://yangx.top/joinchat/RYD_4tbNBwRoKR2h

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ኢትዮ ቴሌኮም በደቡብ ሪጅን የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ አገልግሎትን አሰጀመረ ! በደቡብ ሪጅን የተጀመረው የ4ጂ አድቫንስድ አገልግሎት ሀዋሳ፣ ሻሸመኔ እና ቡሌ ሆራን ጨምሮ 12 ከተሞችን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሏል። አገልግሎቱ የኢንተርኔት እና ሌሎች በኩባንያው የሚቀርቡ አገልግሎቶች በተሻለ ፍጥነት ለማግኘት ያስችላልም ነው የተባለው። ኩባንያው ከፍተኛ የኢንተርኔት አጠቃቀም በሚታይባቸው 103 ከተሞች…
ዛሬ ኢትዮ ቴሌኮም የ4G LTE አገልግሎት ያስጀመረባቸው ከተሞች የትኞቹ ናቸው ?

በዛሬው ዕለት የ4G LTE የጀመረባቸው በደቡብ ሪጅን በሚገኙ 12 ከተሞች ሲሆን እነዚህም ፦
- ሀዋሳ፣
- ሻሸመኔ፣
- አርሲ ነገሌ፣
- ቡሌ ሆራ፣
- ዲላ፣
- ያቤሎ፣
- ይርጋለም፣
- አለታ ወንዶ፣
- ሞያሌ፣
- ሻኪሶ፣
- አዶላ እና ነገሌ ናቸው።

@tikvahethiopia
ዛሬ ምሽት በመረዋ ቀበሌ የትራፊክ አደጋ ደረሰ።

በጅሌ ጥሙጋ ወረዳ መረዋ ቀበሌ ውስጥ ልዩ ስሙ " ቆሮ " የሚባል አካባቢ ከደብረብረሃን ወደ ራያ የአካባቢ ሚሊሻ ይዞ ሲጓዝ የነበረ አይሱዚ ቅጥቅጥ የህዝብ ማመላለሻ መኪና ከምሽቱ 3:30 ገደማ የትራፊክ አደጋ እንደደረሰበት የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ሪፖርት አደረገ።

ከደብረ ብረሃን ከተማ ወደ ራያ ሲጓዝ የነበረው " ኮድ 3 ታርጋ ቁጥሩ 23588 " የሆነ የህዝብ ማመላለሻ አይሱዙ መኪና 46 ሚሊሻ አባላቶችን የጫነ ሲሆን ከሰንበቴ ከተማ ትንሽ ወጣ ብሎ ነው አደጋው የደረሰበት።

በአደጋው ቀላልና ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል። የአደጋው መንስኤ በፖሊስ ምርመራ እየተጣራ ይገኛል።

አደጋ የደረሰበት ቦታም የሀገር መከላከያ ሰራዊት ጨምሮ የፌደራልና የፖሊስ አባላት እንዲሁም ማህበረሰቡ በቦታው ላይ ተገኝተው አስፈላጊውን እርዳታ አድርገዋል።

መረጃው የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ነው።

@tikvahethiopia
#የጥንቃቄ_መልዕክት

በክረምት ወቅት የአየር ጸባዩ የሚፈጥረውን ከባድ ዝናብ ፣አደገኛ ጎርፍ ፣ጉም እና ጭጋግ ሳቢያ የትራፊክ አደጋ እንዳይከሰት አሽከርካሪዎች ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ አሽከርክሩ።

- የተሽከርካሪ ክፍሎችን ማለትም ሊሾ ጉማ ገጥሞ ማሽከርከር ፣
- የማይሰራ የዝናብ መጥረጊያ መግጠም ፣
- የማይሰራ መብራቶችን አለማስተካከል ፣
- በጭጋግ ወቅት ስቲከር ለጥፎ ማሽከርከር ፣
- ፍሬን እና ሌሎች የቴክኒክ ክፍሎችን ሳያስተካክሉ ማሽከርከር ለከፋ የትራፊክ አደጋ የሚዳርጉ በመሆኑ ጥንቃቄ ይደረግ።

Credit : DebrMarkos Police

@tikvahethiopia
#Update

በሁለት ቀን 5,048 ዜጎቻችን ከሳዑዲ አረቢያ ተመልሰዋል።

ኢትዮጵያ ከትላንት በስቲያ እንዲሁም በትላንትናው ዕለት በአጠቃላይ 5,048 ዜጎቿን ከሳዑዲ አረቢያ በማስወጣት ወደሀገራቸው መልሳለች።

ፎቶ : የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት የትግራይ ክልልን በጀት ለመልቀቅ ውሳኔ ላይ አልደረሰም !

የፌዴራል መንግስት ከሀሙስ ሃምሌ 1 ቀን 2013 ጀምሮ ስራ ላይ ከሚውለው የ2014 ዓመታዊ በጀት ለክልሎች ከሚደረገው የበጀት ድጋፍ ለትግራይ ክልል የሚደርሰውን ገንዘብ ለመልቀቅ ውሳኔ ላይ እንዳልደረሰ አሳውቋል።

የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጡት ቃል መንግስት የትግራይ ክልል በጀት እንዴት መለቀቅ አለበት የሚለው አዳስ ክስተት በመሆኑ አሁን ላይ ሁኔታውን ማንም መገመት አይችልም ብለዋል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኞ 28 ቀን 2013 ዓ/ም ባካሄደው 6ኛ ዓመት 4ማ ልዩ ስብሰባው ፣ ለ2014 በጀት እዲሆን የቀረበው 561.7 ቢሊዮን ብር የውሳኔ ሐሳብ በሙሉ ድምፅ ማፅደቁ አይዘነጋም።

ከፀደቀው የ2014 በጀት ለክልሎች ከሚሰጠው የበጀት ድጋፍ ትግራይ ክልል 12 ቢሊዮን ብር እንደሚያገኝ የቀረበው የበጀት ሰነድ ያመለክታል።

ይሁን እንጂ የገንዘብ ሚኒስትሩ የ2014 የትግራይ ክልል የበጀት አለቃቀቅ ሁኔታ ማንም ሊገምተው በማይችልበት ደረጃ እንደሚገኝ ፣ የህግ ማብራሪያና ትንታኔ እንደሚፈልግ አስረድተዋል።

የገንዘብ ሚኒስትሩ የበጀት አለቃቀቅና አፈፃፀሙ ገና ውይይት እንደሚፈልግና በሂደት እንደሚታወቅ ለሪፖርተር ጋዜጣ ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
የፌደሬሽን ምክር ቤትን ስልጣንና ተግባር ለመዘርዘር ተሻሽሎ የወጣውን አዋጅ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አጸደቀ።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 5ኛ ልዩ ስብሰባውን አካሂዷል።

በዚህም የፌደሬሽን ም/ቤትን ስልጣንና ተግባርን ለመዘርዘር ተሻሽሎ የወጣውን አዋጅ በሙሉ ድምጽ አፅድቋል።

በተጨማሪም ምክር ቤቱ በዓለም አቀፉ የልማት ማህበርና በኢትዮጵያ መካከል ለተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች እንዲውል የተፈረሙ አራት የብድር ስምምነቶችን አፅድቋል።

ምክር ቤቱ በዛሬ ስብሰባው ኢትዮጵያ ከአፍሪካ የመንገድ ደህንነት ቻርተርና ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጋር የተስማማችባቸውን ሁለት የመንገድ ደህንነት ቻርተሮችንም ማፅደቁን ኢዜአ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
ብሊንከን ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ጋር በስልክ መነጋገታቸውን ገለፁ።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ጋር በስልክ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መነጋገራቸውን ጁላይ 6 ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

አቶ ብሊንከን በግጭት ላይ ባሉ ሁሉም ወገኖች ዘንድ አስቸኳይና ዘላቂ ተኩስ የማቆሙን አስፈላጊነት አንስተው ማሳሰባቸውንና የተከዜ ድልድይ መፍረስንም አስመልክቶ ማውገዛቸውን ጠቅሰዋል። 

በተጨማሪ ፦
- የኤርትራ ጦርና የአማራ ሚሊሺያ ከትግራይ ሙሉ በሙሉ ለቅቀው እንዲወጡ
- ሰብዓዊ እርዳታን ለሚሹ ረድኤት ለመድረስ ሙሉ ተደራሽነት እንዲኖር
- በሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ተጠያቂ በሆኑት ላይ ግልፅ የሆነ ሂደት እንዲዘረጋ
- የኢትዮጵያን የውስጥ ወሰኖችንም ሆነ ዓለም አቀፍ ድንበር በኃይል ወይም ሕገ መንግሥቱን በመጣስ መለወጥ እንደሌለበት
- ኢትዮጵያ ውስጥ ሰፍኖ ያለውን የጎሳና ፖለቲካ ክፍፍሎች ሁሉን አቀፍ በሆነ ዘላቂ መፍትሔ የሚያስገኝ ፖለቲካዊ ውይይት እንዲካሔድ
- በተባበሩት መንግሥታት ፀጥታ ምክር ቤት የተመከረበትን ግብር ላይ እንሲያውሉ ያበረታቱ መሆኑን ጠቅሰዋል።

የስልክ ንግግሩን አስመልክቶ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ እስካሁን የተሰጠ መግለጫ የለም።

ምንጭ፦ SBS Amharic

@tikvahethiopia