#Update
በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀው የቀድሞው የትግራይ ክልል ገዢ ፓርቲ ህወሓት መቐለ ከተማን መቆጣጠሩን ማምሻውን አስታውቋል።
የህወሓት ከፍተኛ አመራር አቶ ጌታቸው ረዳ ፥ "የትግራይ ዋና ከተማ መቐለ በቁጥጥራችን ሥር ነች" ሲሉ #ለሬውተርስ ተናግረዋል።
የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ከመቐለ እንደዘገበው ደግሞ በከተማው የሚገኘው ኤፍ.ኤም መቐለ ራዲዮ ጣቢያ ተቋርጦ የነበረ ሥርጭቱን ጀምሯል።
የራዲዮ ጣቢያው ከዚህ ቀደም ይደመጡ ያልነበሩ፣ የትግራይ ኃይሎችን የሚያወድሱ ሙዚቃዎች በማሰማት ላይ እንደሚገኝ ተነግሯል።
" የትግራይ መከላከያ ኃይል (TDF) " ተብሎ የሚጠራው ታጣቂ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ወደ መቐለ ከተማ መግባቱን የከተማዋ ነዋሪዎች አረጋግጠዋል።
የመቐለ አስተዳደር በሚገኝበት አካባቢ እንዲሁም "አዋሽ ካምፕ" ተብሎ የሚጠራው የቀድሞ የሰሜን ዕዝ የጦር ሰፈር አካባቢ ታጣቂዎቹ ታይተዋል።
ሁለት የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች እንዳሉት በመቐለ የተለያዩ ቦታዎች ማምሻውን አልፎ አልፎ የተኩስ ይሰማ ነበር።
የተሽከርካሪዎች ጥሩምባ እንዲሁም የርችት ተኩስ አሁንም እየተሰማ እንደሚገኝ የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ከመቐለ ዘግቧል።
@tikvahethiopia