#Mekelle
መቐለ ከተማ የቀድሞው የክልሉ ገዢ (ህወሓት) ታጣቂዎች መግባት ጀምረዋል የሚል መረጃ ከተሰራጨ በኋላ ነዋሪዎች ደስታቸውን እየገለፁ መሆኑ ተሰምቷል።
ነዋሪዎች የሞተር ሳይክሎች እና የመኪኖች ጥሩምባ እያሰሙ በመቐለ ጎዳናዎች ሲዘዋወሩ ታይተዋል።
በመቐለ ርችት እየተተኮሰ መሆኑን እንዲሁም የትግራይ ክልል ሰንደቅ ዓላማ የሚያውለበልቡ የከተማዋ ነዋሪዎች በጎዳናዎች ሲዘዋወሩ መታየታቸውን ተገልጿል።
ከዚህ ቀደም ብሎ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና የፌድራል ፖሊስ አባላት ከተማዋን ለቀው መውጣት መጀመራቸው ተሰምቷል።
የከተማዋ መደበኛ እንቅስቃሴ ከቀኑ ስድስት ሰዓት በኋላ ነው መቀዛቀዝ የጀመረው።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት ከመቐለ ወደ ኲሃ አቅጣጫ ሲጓዙ መታየታቸውን ተሰምቷል።
የትግራይ ቴሌቭዥን ከዛሬ ጀምሮ ሥርጭቱ የተቋረጠ ሲሆን በትግራይ ክልል ሌሎች አካባቢዎች የቴሌኮም ግልጋሎት አይሰራም።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ከተማው የሚያደርገው ጉዞ ተቋርጧል።
የክልሉ መንግሥት ዋና መቀመጫ የሆነችው መቐለ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቁጥጥር ሥር የሆነችው ሕዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም. ነበር።
ዘገባው የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ (ከመቐለ) ነው።
@tikvahethiopia

#Update
አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ከደቂቃዎች በፊት በሰበር ዜና አማፅያን ወደፊት እየገፉ መምጣታቸውን ተከትሎ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደሮች ለቀው ወጥተዋል ብሏል።
እስካሁን እየወጡ ስላሉት መረጃዎች በኢትዮጵያ የፌዴራል መንግስት በኩል የተባለ ነገር የለም።

TIKVAH-ETHIOPIA
#BREAKING የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የፌዴራል መንግስት ሰብዓዊነትን መሰረት ባደረገና ተጨማሪ ጉዳት በማያስከትል መልኩ #የተኩስ_አቁም_ስምምነት እንዲያደርግ ጥያቄ ማቅረቡን አስታወቀ። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር አብርሃም በላይ እንዳስታወቁት፥ ክረምት እየገባ በመሆኑ የትግራይ ክልል አርሶ አደር ተረጋግቶ የእርሻ ስራውን እንዲያከናውን፣ የሰብዓዊ ድጋፍ ለተረጂዎች…
#BREAKING
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን የተኩስ አቁም ስምምነት ጥያቄ የፌዴራል መንግሥት በአዎንታዊነት እንደተቀበለው ባወጣው መግለጫ አስታወቀ !
* ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል።
@tikvahethiopia
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን የተኩስ አቁም ስምምነት ጥያቄ የፌዴራል መንግሥት በአዎንታዊነት እንደተቀበለው ባወጣው መግለጫ አስታወቀ !
* ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል።
@tikvahethiopia
#Update
በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀው የቀድሞው የትግራይ ክልል ገዢ ፓርቲ ህወሓት መቐለ ከተማን መቆጣጠሩን ማምሻውን አስታውቋል።
የህወሓት ከፍተኛ አመራር አቶ ጌታቸው ረዳ ፥ "የትግራይ ዋና ከተማ መቐለ በቁጥጥራችን ሥር ነች" ሲሉ #ለሬውተርስ ተናግረዋል።
የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ከመቐለ እንደዘገበው ደግሞ በከተማው የሚገኘው ኤፍ.ኤም መቐለ ራዲዮ ጣቢያ ተቋርጦ የነበረ ሥርጭቱን ጀምሯል።
የራዲዮ ጣቢያው ከዚህ ቀደም ይደመጡ ያልነበሩ፣ የትግራይ ኃይሎችን የሚያወድሱ ሙዚቃዎች በማሰማት ላይ እንደሚገኝ ተነግሯል።
" የትግራይ መከላከያ ኃይል (TDF) " ተብሎ የሚጠራው ታጣቂ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ወደ መቐለ ከተማ መግባቱን የከተማዋ ነዋሪዎች አረጋግጠዋል።
የመቐለ አስተዳደር በሚገኝበት አካባቢ እንዲሁም "አዋሽ ካምፕ" ተብሎ የሚጠራው የቀድሞ የሰሜን ዕዝ የጦር ሰፈር አካባቢ ታጣቂዎቹ ታይተዋል።
ሁለት የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች እንዳሉት በመቐለ የተለያዩ ቦታዎች ማምሻውን አልፎ አልፎ የተኩስ ይሰማ ነበር።
የተሽከርካሪዎች ጥሩምባ እንዲሁም የርችት ተኩስ አሁንም እየተሰማ እንደሚገኝ የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ከመቐለ ዘግቧል።

#Ethiopia
ኢትዮጵያ ውስጥ የኮቪድ-19 ክትባት የተከተቡ ዜጎች ቁጥር ከሁለት ሚሊዮን አለፈ።
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ጤና ሚኒስቴር ዛሬ ይፋ ያደረገው ሪፖርት እንደሚያሳየው ከሆነ አጠቃላይ የኮቪድ-19 ክትባት የተከተቡ ዜጎች ቁጥር 2,003,226 ደርሰዋል።
በሌላ መረጃ ፦ ባለፉት 24 ሰዓታት 3,144 የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 39 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
በተመሳሳይ በ24 ሰዓት የአንድ ሰው ህይወት አልፏል፤ 573 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

አንቶኒዮ ጉተሬዝ ከጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጋር መነጋገራቸውን አሳወቁ።
የተመድ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል የተፈጠረው ክስተት እጅግ አሳሳቢ መሆኑን ገልፀዋል።
ጉተሬዝ አሁንም ቀውሱን መፍቻ ምንም የወታደራዊ መፍትሄ እንደሌለ አሳውቀዋል።
ጉተሬዝ ፥ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር ተነጋግሬያለሁ ያሉ ሲሆን ውጤታማ የሆነ የተኩስ አቁም ተግባራዊ ይደረጋል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ ብለዋል።
የሲቪል ዜጎችን ደህንነት መጠበቅ፣ በችግር ላይ ላሉ ዜጎች የሰብዓዊ እርዳታ ማድረስ እና ለችግሩ ፖለቲካዊ መፍትሄ አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል።

#FDREDefenseForce
የመከላከያ ሚኒስቴር የ33ኛ ዙር ምልምል ወታደሮችን በአሁኑ ሰዓት በማስመረቅ ላይ ይገኛል።
በብርሸለቆ መሠረታዊ ውትድርና ማሠልጠኛ ት/ቤት ሲሰለጥኑ የነበሩ ወታደሮች የተሰጣቸውን ስልጠና አጠናቀዋል።
ተመራቂዎቹ ከመደበኛው ሠራዊቱ ጋር በመቀላቀልከ ውስጥ እና ከውጭ የሚቃጣን ወረራ በመመከት እንዲሁም የኢትዮጵያን አንድነት አጠናክው ያስቀጥላሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲል የሀገር መከላከያ ሰራዊት አሳውቋል።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሰራዊት

28 ታዳጊ ኢትዮጵያውያን ከታንዛኒያ ተመለሱ።
በህገወጥ ስደት ወደ ደቡብ አፍሪካ ለሚደረግ ጉዞ ከአገር ወጥተው የታንዛኒያን ድንበር ጥሰው ሲገቡ በአገሪቱ ፖሊስ ተይዘው የነበሩ 28 ታዳጊዎች በትላንትናው እለት ወደ አገር ቤት እንዲመለሱ መደረጉን በታንዛኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አሳውቋል።
ታዳጊዎቹቹ ከሌሎች 36 እድሜያቸው ከ18 አመት በላይ ከሆኑ ስደተኞች ጋር በአንድነት ተይዘው የነበሩ ሲሆኑ፤ የታንዛኒያ መንግስት እድሜያቸው አነስተኛ የሆኑትን ለማሰር የማይችል በመሆኑ በአፋጣኝ ወደ አገር ቤት እንዲመለሱ ኤምባሲው ሁኔታውን እንዲያመቻች ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ቅድሚያ ተሰጥቷቸው የተመለሱ ናቸው ተብሏል።
በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የአገራችን ዜጎች በታንዛኒያ እስር ቤቶች ውስጥ ታስረው ያሉ በመሆኑ ሁሉንም ዜጎች ወደ አገር ቤት ለመመለስ ከፍተኛ ጥረት በመደረግ ላይ መሆኑን ኤምባሲው ገልጿል።

ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን እያስመረቀ ነው።
ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ለ13ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ከ3 ሽህ በላይ ተማሪዎችን እያስመረቀ ይገኛል።
ዩኒቨርስቲው በ9 የትምህርት ኮሌጆች በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በሁለተኛና በሦስተኛ ዲግሪ ከሚያስመርቃቸው ተማሪዎች ውስጥ 40 በመቶ ሴቶች ናቸው፡፡
ምንጭ፦ አሚኮ

''...ሀጫሉ የእኔ ብቻ ሳይሆን የመላው ኦሮሞ ህዝብ ልጅ ነው'' - አቶ ሁንዴሳ ቦንሳ
የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ሶስተኛ የዘፈን አልበም ምርቃትና የአንደኛ ዓመት ሙት ዓመት መታሰቢያ ፕሮግራም ትላንት በአዲስ አበባ ተካሂዷል። በመርሃ-ግብሩ ላይ የአርቲስቱ ቤተሰቦች፣ ወዳጆችና በርካታ የጥበብ አፍቃሪያን ተገኝተው ነበር።
አርቲስቱ በህይወት እያለ ያዘጋጀው ሶስተኛው የዘፈን አልበም፤ 'ማል መሊሳ' በሚል ርዕስ ታትሞ ለአድማጮች ቀርቧል። የዘፈኑ 300 ሺህ ቅጂ በመጀመሪያ ዙር የተዘጋጀ ሲሆን አልበሙም 14 ዘፈኖችን ያካተተ እንደሆነ ተገልጿል።
ትናንት ምሽት በተካሄደ ፕሮግራም ለአርቲስቱ ሙት ዓመት መታሰቢያ የሻማ ማብራት ስነ-ስርዓት ተካሂዷል። በመርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የአርቲስቱ ባለቤት ወይዘሮ ፋንቱ ደምሴ ''ሀጫሉ በህይወት ቢለይም ትውስታውና ስራዎቹ ህያው ናቸው'' ብለዋል።
ከአርቲስቱ ህልፈት ቦኃላ ከቤተሰቡ ጎን ሆነው በተለያየ መልኩ ድጋፍ ላደረጉላቸው ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።
በቀጣይም የአርቲስቱን ስም ባልተገባ መንገድ ለመጠቀም የሚፈልጉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም አሳስበዋል።
የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ወላጅ አባት አቶ ሁንዴሳ ቦንሳ ''ሀጫሉ የእኔ ብቻ ሳይሆን የመላው ኦሮሞ ህዝብ ልጅ ነው'' ብለዋል። ''የልጄ ገዳዮች ህግ ፊት ቀርበው ፍትህ እንዲያገኙ ሁሉም እንደየ ሀይማኖቱ ጸሎት ያድርግልኝ'' ሲሉም ጥ አቅርበዋል።
በመርሃ-ግበሩ የጥበብ ስራዎችን የሚያግዝና በአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ስም የተሰየመ ፋውንዴሽን ተቋቁሟል።
አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ባለፈው ዓመት ሰኔ 22 በአዲስ አበባ በሰው እጅ በጥይት ተመቶ መገደሉ አይረሳም።
#ENA

ጃኮብ ዙማ የ15 ወራት እስር ተፈረደባቸው።
የደቡብ አፍሪካ የቀድሞ ፕሬዘዳንት ጃኮብ ዙማ የ15 ወራት እስር ተፈርዶባቸዋል።
የ79 ዓመቱ ጃኮብ ዙማ በአገሪቱ እርቀ ሰላም ኮሚሽን ፍ/ቤት መገኘት ሲኖርባቸው ባለመገኘታቸው ከህግ ተቋማት ትችቶች ሲቀርብባቸው ነበር።
ይህ እውነትን አፈላላጊ ኮሚሽን አቋቁሞ የዙማን ጉዳይ እየተመለከተ የነበረ ሲሆን ጃኮብ ዙማ ግን በዚህ ፍርድ ቤት አልቀርብም ሲሉ በይፋ ተቃውመው ነበር።
ዙማ በዚህ የኮሚሽኑ ፍርድ ቤት ለመቅረብ ፍቃደኛነት ባለመሆናቸው ባለፈ ፈርድ ቤቱ ገለልተኛ አይደለም በማለታቸው ፍርድ ቤት ተዳፍረዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል።
የዙማ ድርጊት ፍርድ ቤቱን መናቅና መድፈር በመሆኑ ሕግ አለማክበርን ያበረታታል፤ ሌሎችን ለህግ ተገዢ እንዳይሆኑ ያደርጋል የሚሉ ሀሳቦች ሲነሱ ቆይቷል።
የአገሪቱ ከፍተኛው ፍርድ ቤትም በቀድሞው ፕሬዘዳንት ድርጊት ጃኮብ ዙማ የ15 ወራት እስር ተፈርዶባቸዋል።
ዙማ እስሩ የተላለፈባቸው በተከሰሱበት የሙስና ወንጀል ቀጣይ የፍርድ ክርክር ላይ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ አላከበሩም በሚል ነው።
ምንጭ፦ አል ዓይን