TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
Audio
#DrDebretsionGebremichael

የኢትዮጵያና የኤርትራ የድንበር ይገባኛልና ሌሎች ውዝግቦች በሕግና ስርዓት  የመጨረሻ መፍትሔ ሊሰጣቸዉ እንደሚገባ የሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ሕወሓት) ሊቀመንበርና የትግራይ ምክትል ርዕሠ መስተዳድር ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል አስታወቁ።

ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን በቅርቡ የኤርትራዉ ፕሬዝደንት ለሰጡት አስተያየት አፀፋ በመሰለ መግለጫቸው ለየውዝግቡ አብነቱ ሕጋዊ መፍትሔ ማግኘት ነው ብለዋል።

የኤርትራ ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ኢትዮጵያና ኤርትራ ሰላም ለማውረድ ከተስማሙ በኋላ የሁለቱ ሐገራት የድንበር  ሁኔታን «የከፋ» ብለዉታል። ፕሬዝደንት ኢሳያስ ለሁኔታው መክፋት የትግራዩን ገዢ ፓርቲ ሕወሓትን ተጠያቂ አድርገዋልም።

[የጀርመን ድምፅ ሬድዮ]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ATTENTION

ከነገ መጋቢት 19/2012 ዓ/ም ጀምሮ በትግራይ ክልል ውስጥ ከከተማ ወደ ከተማ መንቀሳቀስ አይፈቀድም። ከገጠር ወደ ገጠር፣ እንዲሁም ከገጠር ወደ ከተማ ወይም ከከተማ ወደ ገጠር መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው። ከነገ ጀምሮ ባለንበት ቦታ ነው የምንቀመጠው።

#DrDebretsionGebremichael #TigraiTV
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ATTENTION

ወደ ትግራይ የሚያስገቡ ዋና መንገዶች አይዘጉም። ነገር ግን ክትትል እና ቁጥጥር ይደረግባቸዋል። አንድ ሰው መቐለ ገብቶ ወደ አዲግራት ወደ አድዋ ወይም ወደ ሽሬ መሄድ የሚባል ጉዳይ አይኖርም። በአንድ መስመር ሰው ከገባ እዛው ቦታ ብቻ ነው መቀመጥ ያለበት። መንቀሳቀስ አይፈቀድም። ይህንን አዎቆ ነው ወደ ትግራይ መግባት የሚቻለው።

#DrDebretsionGebremichael #TigraiTV
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrDebretsionGebremichael

በትግራይ ክልል የኮሮና ቫይረስ በሽታ ባልታወቀ ምክንያት እንዳይገባ የክልሉ መንግስት በቅርቡ የሞቱ ሰዎች በምን ምክንያት እንደሞቱ ምርመራ የማድረግ ስራን እየሰራ ይገኛል።

ከሰሞኑን በትግራይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በተራዘመበት ዕለት የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ይህን ሲናገሩ ተደምጠዋል ፦

በሽታው የለም ብለን መደምደም ባንችልም ፤ እስካሁን ባለው ሁኔታ አልተገኘም። ሌላው ቀርቶ በየአካባቢው የሚሞቱ ሰዎች በምን እንደሞቱ መታወቅ አለበት ብለን እየመረመርን ነው የምንገኘው።

ምክንያቱም ብዙ ሰው ከረገፈ በኃላ አይደለም ወረርሽኝ ነው ብለን የምንለው። እናም ባልታወቀ መንገድ እንዳይገባ ፍተሻ እያደረግን ነው።

ስለዚህ በቅርቡ በሞቱ ሰዎች ላይ ባደረግነው ምርመራም በሽታው ወይም ቫይረሱ ሊገኝ አልቻለም።

በዚህም ሁኔታ ምርመራውን በማጠናከር የኮሮና ቫይረስ አለመግባቱን ካረጋገጥን በኃላ ከክልሉ ውጪ በሚመጡ ሰዎች ላይ ብቻ ትኩረት አድርገን የምንሰራ ይሆናል። ነገር ግን እስካሁን እዛ ላይ አልደረስንም።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrDebretsionGebremichael

እስካሁን በተደረገው ዳሰሳና ምርመራ በትግራይ ክልል ውስጥ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሰው እንዳልተገኘ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ገልፀዋል። በቀጣይ ግን የሚታወቅ ነገር የለም ብለዋል ምክትል ፕሬዘዳንቱ።

ዶክተር ደብረፅዮን በተወሰኑ የንግድ ተቋማት ላይ ተጥሎ የነበረው ክልከላ እንደሚነሳም አሳውቀዋል። ይሁን እንጂ የቫይረሱን ወረርሽኝ ለመከላከል የሚደረጉ ሁሉም ዘዴዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

ኮፊ ሀውስ፣ ካፌ፣ ጭማቂ ቤት፣ ጸጉር ቤቶች ስራ መቀጠል ይችላሉ ተብሏል፤ ጠላ ቤቶች (take away - ገዝቶ ለሚሄድ)፣ መጠጥ ቤቶችና አከፋፋዮች በመጋዘን የያዙትን ብቻ መሸጥ ይችላሉ (take away) ፤ በትራንስፖርት በኩል ደግሞ በገጠር ወረዳ ውስጥ ከቀበሌ ቀበሌ የሚሄዱ መኪኖች ብቻ አገልግሎት እንዲቀጥሉ ተብሏል።

ምንጭ፦ ትግራይ ቲቪ፣ ዳንኤል ብርሃኔ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia