TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
አጫጭር መረጃዎች ፦

- በዩናይትድ ኪንግደም የሟቾች ቁጥር 28,131 ደርሷል፤ ባለፉት 24 ሰዓት የ621 ሰዎች ሞት ሪፖርት ተደርጓል። በሌላ በኩል በአንድ ቀን 4,806 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- ባለፉት 24 ሰዓት በኳታር 776 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 14,872 ደርሰዋል።

- በጣልያን ባለፉት 24 ሰዓት 474 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል። በሌላ በኩል 1,900 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- በቱርክ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች 124,375 ደርሰዋል፤ በአንድ ቀን 1,983 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። የሟቾች ቁጥር በ78 ጨምሮ በአጠቃላይ 3,336 ሆኖ ተመዝግቧል።

- ግብፅ በዛሬው ዕለት 298 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 6,193 ደርሷል።

- በጋና በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 2,169 ደርሰዋል፤ ባለፉት 24 ሰዓት 95 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። #GHS 88% በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ግልፅ የሆነ የጉዞ ታሪክ የላቸውም ብሏል።

- በAfricaCDC መረጃ መሰረት በአፍሪካ 1,701 ሰዎች ሞተዋል፤ 41,330 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፤ 13,621 አገግመዋል።

- በዓለም አቀፍ ደረጃ የሟቾች ቁጥር ከ243,024 ደርሷል፤ 1,102,551 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል፤ 3,456,207 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia