TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
ለቲክቫህ አውሮፓ እና አሜሪካ ቤተሰቦች፦

በሀገራችን ኢትዮጵያ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተመርቀው ወጥተው ለረጅም ዓመታት ስራ ማግኘት ያልቻሉ እጅግ በርካታ ወጣቶች እንደሚገኙ ይታወቃል። ከዓመት ወደ ዓመትም ስራ ማግኘት የማይችሉ ወጣቶች ቁጥር ከመቀነስ ይልቅ እየጨመረ ነው።

ያለ ስራ መቀመጥ ምን ያህል ሀገሪቷን አንገዳግዶ ወደገደል እንደሚጨምራት እያወቁ እንኳ የሀገሪቱ ፖለቲከኞች ስለኢኮኖሚው፣ ስለወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ፣ የወጣቶች ህይወት በሚቀየርበት መፍትሄ ዙሪያ ዘመቻ ሲያካሂዱ አይታዩም፤ ሁሉም አካላት ግን ለፖለቲካ ግባቸው ወጣቶችን መጠቀማቸው እሙን ነው።

እኛ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች ሀገራዊ፣ እንዲሁም ዜግነታዊ ግዴታችንን ለመወጣት 24 ሰዓት እየሰራን ነው። ይህ አስቸጋሪ ወቅትም አልፎ ሁሉም መልካም እንደሚሆን ስለምናምን በቻልነው አቅም ችግሮችን ለማቃለል እንዲሁም የቤተሰባችን አባላት የሆኑ ስራ ማግኘት የልቻሉ ወጣቶችን ለማገዝ እቅዶችን አውጥተን እየተንቀሳቀስን ነው።

በመሆኑም የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ የሆናችሁ እና ኑሯችሁን በአሜሪካ እና አውሮፓ ያደረጋችሁ አባለቶቻችን በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ሀሰቦችን ለመጋራት፣ ለመነጋገር እቅድ ስለያዝን የምትኖሩበትን ከተማና ስልካችሁን ከዚህ በታች ባሉት አድራሻዎች ታስመዘግቡ ዘንድ እንጠይቃለን።

@tsegabwolde
@tsegabtikvah
[email protected]
[email protected]

#TikvahFamily!
#TheSilentMajority

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሽያጭ የናፈቃቸው የመኪና ነጋዴዎች!

[በአዲስ ዘመን ጋዜጣ]

በተለምዶ እንቁላል ፋብሪካ ተብሎ የሚጠራው አካባቢ በመኪና ገበያነት ይታወቃል። ሰሞኑን ግን “ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው” እንዲሉ፤ የአካባቢው የመኪና ነጋዴዎች አዲሱ የኤክሳይዝ አዋጅ ረቂቅ ለተወካዮች ምክር ቤት ከቀረበ ጀምሮ “ባልተረጋገጠ እሳቤ ምክንያት ሽያጭ ከቆመ ወራት አስቆጥረናል::” ይላሉ።

ከመሸጫዎቹ በአንዱ የአንዲት ቶዮታ ቪትስ የኋላ በር ተከፍቶ በዕቃ ማስቀመጫው ውሃ ተቀምጦበታል። አራት ወጣቶች እና ሁለት ጎልማሶች ክፍት ከተተወው የኋላ በር ፊት ለፊት ከብበው ተቀምጠው የያዙትን ውሃ እየተጎነጩ ያወራሉ። ስለገበያው ሁኔታ ሲጠየቁ ቀደም ሲል በሃዘን ስሜት ሲነጋገሩ የነበሩት ሁሉም አንድ ላይ በቁጣ ይናገራሉ:: “ገበያው ሞቷል፤ በፊት አንድ መኪና ይሸጥ ከነበረበት በ40 እና በ50 ሺህ ብር ቅናሽ ለመሸጥ ብንሞክርም እንኳን ደፍሮ የሚገዛ የለም” ይላሉ።

የመኪና አስመጪው አቶ መሃመድ አወል እንደሚናገሩት፤ መኪና ሻጭ ብዙ ቢሆንም መኪና ገዢ ጠፍቷል። ቀድሞ የመኪና ማስገቢያ ግብር ጨመረ ተብሎ ሲወራ፤ እነርሱም በመኪና ዋጋ ላይ ጨምረው ነበር። አሁን ደግሞ “አዲስ ያልተነዳ መኪና የማስገቢያ ቀረጥ ቀንሷል” መባሉ ገበያውን አበላሽቶታል። በተጨማሪ ገዢው ህዝብም ሆነ የመኪና ነጋዴው ግብሩ በምን ያህል ቀነሰ ወይም ጨመረ የሚለው በትክክል አልገባውም፤ በዚህ ሳቢያ ገበያው ተበላሽቷል።

More https://telegra.ph/EPA-02-24

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE - የሟቾች ቁጥር 2,464 ደርሷል - በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 78,823 ዛሬ ባገኘነው ሪፖርት በኮሮና ቫይረስ [#COVID19] የሞቱ ሰዎች ቁጥር 2,464 የደረሰ ሲሆን 78,823 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል። ከበሽታው አገግመው ከሆስፒታል የወጡ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 23,317 ደርሰዋል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

- የሟቾች ቁጥር 2,619 ከፍ ብሏል
- በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 79,565

ዛሬ ባገኘነው ሪፖርት በኮሮና ቫይረስ [#COVID19] የሞቱ ሰዎች ቁጥር 2,619 የደረሰ ሲሆን 79,565 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል። ከበሽታው አገግመው ከሆስፒታል የወጡ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 25,084 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

የአዲስ አበባ ቃሊቲ ገሙሩክ ኮሚሽን ቅዳሜ የካቲት 14,2012 ባስተላለፈው ውሳኔ የታሰሩትን መኪኖች ጨምሮ ለህዝብ አገልግሎት ስም ገብተው ለግል አገልግሎት የዋሉት መኪኖች በመጪው አንድ ወር ውስጥ ታርጋቸውን ወደ ኮድ 3 ወይም 1 ካልቀየሩ ህጋዊ እርምጃ እወስዳለው ብሏል። ይህም ማለት መኪኖቹ ታርጋቸውን ካልቀየሩ እንደ መኪናቸው አይነት ሆኖ ከ 700,000 አስከ አንድ ሚልየን ብር ታክስ ሊከፍሉ ይገደዳሉ ማለት ነው።

ባለፈው ሳምንት መጀመርያ በመንግስት የፀጥታ ሀይሎች ተይዘው በጉምሩክ ኮሚሽን የአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉሙሩክ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የታሰሩትና በአዲሰ አበባ ፣ በኦሮሚያ ፣ በአማራ እና በደቡብ ክልል በ2 ቁጥር ታርጋ መሀል ሸገር ላይ ሲንቀሳቀሱ የነበሩት D4D ፣ ዳማስ እና ዶልፊን መኪኖች ባለቤት የታሰሩት መኪኖቻቸው እንዲፈቱላቸው አራሱ የጉሙሩክ ኮሚሽን ያዘጋጀውን የግዴታ ውል ማመልከቻ አየፈረሙ ይገኛሉ።

ምንጭ፦ ፊደል ፖስት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#MoSHE

በዘንድሮው ዓመት በበርካታ ዩኒቨርሲቲዎች ተቀስቅሶ የነበረውን ረብሻ ተከትሎ በዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች ላይ የተለያዩ ዛቻና ማስፈራሪያዎች እየደረሰ መሆኑ ተጠቆመ።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ደቻሳ ጉርሙ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት በአሁኑ ወቅት የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ሆኖ መስራት ፈታኝ እየሆነ የመጣና በተለይም የፀጥታ ስጋት ባለባቸው አካባቢዎች ፕሬዚዳንቶቹ የተለያዩ ማስፈራሪያዎችና ዛቻ ስለሚደርስባቸው በስጋት ውስጥ ሆነው እየሰሩ ነው ሲሉ ገልፀዋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተማሪዎችን በሐይማኖትና በብሔር በማጋጨት የዩኒቨርሲቲ አስተዳደሮችን ለማጥቃት የሚደረግ ሙከራ መኖሩን የገለፁት ዳይሬክተሩ፤ በዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች ላይም በየጊዜው ዛቻና ማስፈራሪያዎች ይደርሳል ብለዋል።

More : https://telegra.ph/EPA-02-24-3

[ኢፕድ]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

ሰሜን ኮሪያ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን በመስጋት 380 የተለያዩ ሃገራት ዜጎችን ወደ ማቆያ ስፍራ ማስገባቷ ተነገረ።

ወደ ማቆያ ስፍራ የተወሰዱት አብዛኛዎቹ የውጭ ሃገር ዜጎች ዲፕሎማቶች ሲሆኑ በዋና ከተማዋ ፒዮንግያንግ በሚገኝ ጣቢያ ውስጥ እንዲቆዩ ይደረጋል ተብሏል።

200 አካባቢ የሚሆኑ የውጭ ዜጎች በቫይረሱ ምክንያት ለአንድ ወር ያክል ከመኖሪያ ቤታቸው እንዳይወጡ ተደርገው እንደነበር ይታወሳል።

ከቤት የመውጣት ክልከላው ከተጠናቀቀ በኋላም ወደ ማቆያ ስፍራዎች እንዲገቡ ተደርጓል ነው የተባለው።

ሰዎቹ ለምን ያክል ጊዜ በማቆያ ጣቢያው እንደሚቆዩ ግን የተባለ ነገር የለም። በሰሜን ኮሪያ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሰው መኖሩን የሚያመላክት መረጃ እስካሁን አልተገኘም።

[BBC,FBC]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ሆኖ መስራት ፈታኝ እየሆነ ነው...

"በዓመቱ መጀመሪያ አካባቢ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በተፈጠረው ግጭት በተማሪዎች ላይ ርምጃ ሲወሰድ፤ “የእገሌ ብሔር ስለሆነ ነው እርምጃ የተወሰደበት” በማለት የብሔሩ አክቲቪስትና እምባ ጠባቂ ነን ባዮች ይዝታሉ ያስፈራራሉ። ይህም ፕሬዚዳንቶቹ በነፃነት ስራቸውን እንዳይሰሩ ከማድረጉም በላይ ተማሪዎች ከትምህርታቸው ውጭ በሆነ አጀንዳ እንዲዋጡ አድርጓል።" - አቶ ደቻሳ ግሩሙ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"እስካሁን የምችለውን አድርጊያለሁ፤ አሁን ደግሞ ሌላ ሰው ኃላፊነቱን ይውሰድ። እኔ ደጋፊ ሁኜ እቀጥላለሁ።" - ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ

#MulgetaAnberber
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የካቲት 14 እና 15 ቀን 2012 ዓ.ም ያካሄደውን 1ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ የንቅናቄውን የሥራ አስፈፃሚ አባላት በመምረጥ ተጠናቋል!

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የካቲት 14 እና 15 ቀን 2012 ዓ.ም 1ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔውን የምርጫ ቦርድ ታዛቢ በተገኘበት በደብረ ብርሃን ከተማ አካሂዷል።

ጉባዔውን በንግግር የከፈቱት የንቅናቄው ሊቀመንበር ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ አብን የአማራን ሕዝብ ጥያቄ መመለሥ በሚያስችለውና ወቅቱ በሚፈልገው ልክ ይገኝ ዘንድ ላለፉት ጊዜያት የመጣበትን መንገድ መርምሮ በጥናት ላይ የተመሰረተ መዋቅራዊ ማሻሽያ መዘጋጀቱን ገለፀው በዚህ ላይ ጠቅላላ ጉባዔው በደንብ ተወያይቶ አቋም እንዲይዝበት ጠይቀዋል።

ጉባዔው በመጀመረያ ቀን ውሎው የአብን መዋቅራዊ ማሻሽያ(ሪፎርም) አስፈላጊነትና አላማ፣ የንቅናቄው ጥቅል የሥራ ክንውን ሪፖርት፣ የፋይናንስ ኦዲትና ኢንስፔክሽን ሪፖርት፣ የብሔራዊ ም/ቤቱ ሪፖርት፣ የተሻሻለው የንቅናቄው መተዳደሪያ ደንብና ቀርቦ በጠቅላላ ጉባዔው አባላት ሰፊ ውይይት ካደረገ በኃላ አፅድቋል።

More https://telegra.ph/NAMA-02-24

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
9ኙ የአብን ሥራ አስፈፃሚ አመራሮች፦

1. አቶ በለጠ ሞላ  - ሊቀመንበር
2. አቶ የሱፍ ኢብራሂም  - ም/ሊቀመንበር
3. አቶ አዲስ ኃረገወይን - የፖሊሲ ስትራቴጂ ኃላፊ
4. አቶ ጣሂር ሞሐመድ - የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ
5. ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃ/ማርያም - የውጭ ጉዳይና ዓለማቀፍ ግንኙነት
6. አቶ ጋሻው መርሻ - የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ
7. አቶ መልካሙ ፀጋዬ - የፅሕፈት ቤት ኃላፊ
8. አቶ ጥበበ ሰይፈ - የሕግና ስነምግባር ኃላፊ
9. አቶ ክርስቲያን ታደለ - የፓለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ ናቸው።

ምንጭ፦ አብን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

በቅርቡ ወደ ኢራን ማርካዚ ግዛት በገባው ኮሮና ቫይረስ ስምንት የሚሆኑ የሀገሪቱ ዜጎች ለህልፈት መዳረጋቸውን የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥርም 43 መድረሱ ነው የተገለጸው።

ይህን ተከትሎም ሀገሪቱ ቫይረሱ በተከሰተባቸው ግዛቶች የሚገኙ ትምህርት ቤቶች እና የተለያዩ ባህላዊ ማዕከሎች እንዲዘጉ መወሰኗ ተሰምቷል።

ከዚህ ባለፈም የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሃሰን ሩሃኒ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ብሄራዊ የመቆጣጠሪያ ማዕከል እንዲቋቋም ትዕዛዝ መስጠታቸው ተገልጿል።

የሚቋቋመው ማዕከልም በሀገሪቱ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል የሚደረገውን ዘመቻ የሚያስተባብር ይሆናል።

#አልጀዚራ #ኤፍቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

በኢራን በኮሮና ቫይረስ [#COVID19] የተጠቁ ዜጎች ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ ቱርክ፣  አፍጋኒስታን እና ፓኪስታን ከሀገሪቱ የሚያዋስናቸውን ደንበር መዝጋታቸውን አልጀዚራ ዘግቧል።

#ኤፍቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

በኮሮና ቫይረስ ስጋት ያየለ ይመስላል...

ከ13 በላይ የሚሆኑ ሀገራት በኮሮናቫይረስ ስጋት የተነሳ ከደቡብ ኮሪያ የሚመጡ ሰዎች እንዳይገቡ ገደብ መጣላቸው ተገልጿል፡፡

እንደ ሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ገለፃ ከሆነ እስራኤልን ጨምሮ ፤ ባህሬን ፤ አሜሪካና እንግሊዝ ይህን እርምጃዎች ከወሰዱ ሀገራት መካከል ይገኙበታል ተብሏል፡፡

እስራኤል እንዳስታወቀችው ከደቡብ ኮሪያና ከጃፓን ለጉብኝት የሚመጡ ዜጎች ወደ ሀገሪቱ እንዳይገቡ ከሰኞ ጀምሮ የጉዞ እቀባ ተግባራዊ ማድረጓን የአገሪቱ ዜና አውታሮች ዘግበዋል፡፡

ባህሬንም ከአርብ ጀምሮ ተመሳሳይ እርምጃ መውሰዷ ታውቋል፡፡ የእስራኤል ውሳኔ የተላለፈው ባለፈው ቅዳሜ የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ወደ ደቡብ ኮሪያና ጃፓን የሚያደርጉትን በረራዎች እንደሚያግዱ ከተገለፀ በኋላ ነው፡፡

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የገቢዎች ሚኒስቴር በኤክሳይስ ታክስ አዋጅ አፈፃም ዙሪያ ከአስፈፃሚ አካላት ጋር ተወያየ!

የገቢዎች ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት ከፌዴራል፣ ከክልል እና ከከተማ አስተዳደር የገቢው ዘርፍ አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር ውይይት አካሂዷዳ። የውይይቱ ዋና አላማ አዋጁን የሚያስፈጽሙ አካላት ጋር የጋራ መግባባት ለመፍጠር ያለመ ነው ተብሏል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎች ከአፈፃፀም ጋር በተያያዘ ግልጸነት የሚያስፈልጉ ጉዳዮችን በማንሳት ከመድረክ ላይ ሰፊ ማብራራያ ተሰጠዋል፡፡

አዋጁን ለማስፈጸም የገቢዎች ሚኒስቴር በሚያደርጋቸው ዝግጅቶች፣ ኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸው ምርቶች ለማምረት የፈቃድ አሰጣጥ ሂደት፣ ከማምረቻዎች ጋር ተያይዞ የታክስ ግዴታ የሚጀምርበት ጊዜ፣ ቀድሞ ስለተከፈ ታክስ ተመላሽ የሚደረግበት ስርዓት በተመለከተ በገንዘብ ሚኒስቴር የታክስ አማካሪ አቶ ዋሲሁን አባተ የውይይት መነሻ ፅሁፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

እንዲሁም የአክሳይስ ታክስ የተጣለበት ያልተጣለበት ዕቃዎች፣ የኤክሳይስ ታክስ አዋጅ ለማስፈጸም በገቢዎች ሚኒስቴር ስር አዲስ አደረጃጀት እንደሚያፈልግ እንዲሁም በአዋጁ ውስጥ የተካተቱት ውሳኔዎች ለወደ ፊት መሻሻል ሲያስፈልግ በምን መልኩ መሆን እንዳለበት ከአስፈፃሚ አካላት ጋር ውይይት ተደርጓል፡፡

ምንጭ፦ የገቢዎች ሚኒስቴር
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ቻይና የዱር እንስሳት ንግድን ልታግድ ነው!

የቻይና ከፍተኛው የህግ አውጪ ኮሚቴ እንዳስታወቀው የዱር እንስሳት መነገድም ሆነ መመገብ ለአዲሱ የኮሮና ቫይረስ በሽታ መነሻ ናቸው በሚል ድርጊቱን ለመቆጣጠር ረቂቅ አዋጅ አዘጋጀ፡፡

ለብሄራዊ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ (NPC). የተመራው ረቂቅ ህግ የትኛውንም የዱር እንስሳት መመገብም ሆነ መነገድን የሚከለክል ሲሆን ይህም የህብረተሰቡን ጤና ከመጠበቅ አልፎ ብዝሀ-ህይወትን ለመታደግ ያስችላል ነው የተባለው፡፡

ቋሚ ኮሚቴው 3ሺ የብሄራዊ የህዝብ ምክር ቤት አባላትን ሲወክል ኮሚቴው በመጪው ወር በሚያደርገው ስብሰባ አዋጁን እንደሚያጸድቀው ቢጠበቅም በሀገሪቱ የተከሰተው የጤና ቀውስ እንደሚያዘገየው ከወዲሁ ተገምቷል፡፡

የቻይና የጤና ባለሞያዎች የኮሮና ቫይረስ በውሀን ግዛት የመከሰቱ መነሻ የዱር እንስሳት ገበያ እንደሆነ ግምታቸውን አስቀመጠዋል፡፡

የቻይና ወግ አጥባቂዎች ጤንነታቸው ያልተረጋገጠ የዱር እንስሳት ሲሸጡ ቻይና ዝም በማለቷ ለተከሰተው የጤናና ኢኮኖሚዊ ቀውስ ሀላፊነቷን አልተወጣችም በማለትም ሲወቅሷት ሰንብተዋል፡፡

#AFP #ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አቶ ንዋይ ገብረዓብ ማረፋቸው ተሰማ!

የቀድሞዎቹ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትሮች መለስ ዜናዊ እና ሃይለማርያም ደሳለኝ የኢኮኖሚ አማካሪ የነበሩት አቶ ንዋይ ገብረዓብ አረፉ።

የትግራይ ክልል የመንግስት ኮሙንኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው የቀድሞዎቹን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትሮች የኢኮኖሚ አማካሪ የነበሩት አቶ ንዋይ ገብረዓብ ዛሬ ረፋድ ባደረባቸው ህመም ምክንያት አርፈዋል።

አቶ ንዋይ ኢትዮጵያ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ጋር ጥሩ ግንኙነት አንዲኖራት፣ኢትዮጵያ ከአገራት ጋር የምታደርጋቸውን ኢኮኖሚያዊ ስምምነቶችን እና ሌሎች አገራዊ ጉዳዮች ላይ መሪዎቹን ሲያማክሩ ቆይተዋል።

አቶ ንዋይ ከሁለት ዓመት በፊት የአፍሪካ ህብረት የኢኮኖሚ ኮሚሽነር ለመሆን የኢትዮጵያ እጩ ተወዳዳሪ ሆነው ቢቀርቡም በመጨረሻው ዙር በካሜሩን እጩ መሸነፋቸው አይዘነጋም።

#ኢትዮኤፍኤም107.8 #ሳሙኤልአባተ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Election2012

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሟሟላት የሚገባቸውን ዝርዝር ጉዳዮች እስከ መጋቢት 3 ቀን 2012 ዓ/ም እንዲያሟሉ አሳስቧል።

በፓለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና ምርጫ አዋጅ ቁጥር 1162 / 2011 መሰረት በቦርዱ ሀገር አቀፍ እና የክልል ፓርቲዎች ማሟላት ያለባቸውን ግዴታዎች ለማስፈጸም የወጣው መመሪያ ቁጥር 3/2012 መሰረት የፓለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ ማሟላት የሚገባቸውን ዝርዝር ሁኔታ የሚያስረዱ ሰነዶች ማዘጋጀቱ እና ለፓርቲዎች እንዲደርሳቸው ማድረጉ አስታውሷል፡፡

ለእያንዳንዱ ፓርቲም በደብዳቤ ማሟላት የሚገባቸውን ሁኔታዎች ሁሉ እስከ መጋቢት 3 ቀን 2012 ዓ/ም ድረስ አሟልተው እንዲያቀርቡ ቦርዱ አስታውቋል። ቦርዱ እስካሁን ሰነዶቻቸውን ያስገቡ ፓርቲዎች ቁጥር ዝቅተኛ መሆኑን በዛሬው ዕለት ገልጿል።

በመሆኑም ማሟላት የሚጠበቅባቸው ዝርዝር ሁኔታዎችን የሚያስረዱ ሰነዶች የደረሳቸው የፓለቲካ ፓርቲዎች በሙሉ መጋቢት 3 ቀን 2012 ከመድረሱ በፊት ማሟላት የሚገባቸውን በሙሉ አሟልተው የምዝገባ ስርአቱን እንዲጀምሩ አሳስቧል።

ምንጭ፡-የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

በሶማሌ ብ/ክ/ መንግስት በውጫሊ መግቢያና መውጫ ድንበር ላይ የኮሮና COVID -19 ን ለመከላከል እየተደረገ ያለው ቅድመ ጥንቃቄ ስራ ተጎበኘ።

ከኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር እና ከክልሉ ጤና ቢሮ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች በተገኙበት በሶማሌ ብ/ክ/ መንግስት የውጫሊ መግቢያና መውጫ ድንበር ላይ የኮሮና COVID -19 ን ለመከላከል እየተደረገ ያለው ቅድመ ጥንቃቄ ስራ የተጎበኘ ስሆን እስካሁን ከበሽታው ጋር የተያያዘ ያጋጠመ ምልክት የለም።

በሽታው ወደ አገር ውስጥ እንዳይገባ በአከባቢው ላይ የተጀመረው የልይታ ስራ አበረታች ቢሆንም ጊዜያዊ የመለያ ጣቢያን ከማዘጋጀት ጀምሮ አስፈላጊው የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎች ትኩረት አግኝተው ሊሰሩ እንደሚገባ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሰሃረላ አብዱላሂ አሳስበዋል።

ምንጭ፦ ጤና ሚኒስቴር
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚያግዙ የህክምና ቁሳቁሶችን ከተለያዩ ሀገራት ወደ ቻይና እያጓጓዘ እንደሚገኝ ገልጿል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia