ኮሮና ቫይረስ በጣልያን ሴርያው !
የጣልያን ጠቅላይ ሚንስትር ጁሴፔ ኮንቴ በሀገሪቷ ላይ 79 የቫይረሱ ተጠቂ መኖራቸውን እና በቫይረሱ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን መግለፃቸውን ተከትሎ በሴርያው ሊካሄዱ በነበሩ ሶስት ጨዋታዎች ላይ የቀን ለውጥ መደረጉ ተሰምቷል።
የቀን ለውጥ ከተደረገባቸው ጨዋታዎች መካከልም ኢንተር ሚላ ከ ሳምፕዶርያ ፤ ቬሮና ከ ካግላሪ እንዲሁም አትላንታ ከ ሳሱሎ የሚያደርጉት ጨዋታዎች እንደሆኑ ተገልጿል።
ምንጭ፦ @tikvahethsport
@tikvahethsport @tikvahethiopia

በምዕራብ ኦሮሚያ ኢንተርኔትና ስልክ ከተቋረጠ አንድ ወር ከሶስት ሳምንት ሆኖታል!
ከትላንት በስቲያ ከቢቢሲ ጋር ቃለ መጠይቅ ያደረጉት የጦር ኃይሎች ምክትል ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ጁላ ስለ ምዕራብ ወለጋ የኢንተርኔት እና ስልክ መቋረጥ፤ ይህም ለሚያካሂዱት ኦፕሬሽን ምን እንደጠቀመ ተጠይቀው ተከያዩን ምላሽ ሰጥተው ነበር፦
"በጣም ነው የሚጠቅመው እንጂ [የኢንተርኔት እና ስልክ ማቋረጥ]፤ እኚ ሰዎች [ታጣቂዎቹ] እኮ የመገናኛ ሬድዮ እንኳን የላቸውም። ሞባይል ስልክ ነው የሚጠቀሙት ሞባይል በመጠቀም ነው የመንግስትን እንቅስቃሴ ለሁለት ዓመታት ሲያከሽፉ የቆዩት"
PHOTO : FILE
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#FakeNewsAlert ፕ/ሩን በሚመለከት የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው! የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት የሆኑት ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት 'ህወሓት ወንጀል ፈጥሮላቸው የፍርድ ቤት ክስ እና ማዘዣ ወጣባቸው' በሚል በፌስቡክ እየተሰራጨ የሚገኘው መረጀ ሀሰተኛ ነው። መረጀው የፈጠራ ወሬ እንደሆንም ሰምተናል። ፕሮፌሰር ክንደያም መረጃውን 'ውሸት' ሲሉ ገልፀውታል። @tikvahethiopiaBot…
"ስራ ላይ ነን!" - ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት
የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት የሆኑት ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት ከስሙኑ በእሳቸው ዙርያ እየተነሱ ያሉ ጉዳዮች በሬ ወለደ ናቸው ብለዋል። ፕሮፌሰሩ 'በእኔ ላይ ጫና ያደረገ አካል የለም፤ ሊኖርም አይችልም' ሲሉ ገልፀዋል።
'የማደርገውም የምሳተፍበትም ሁሉ በሙሉ እምነትና ፍላጎት ነው ሲሉም አክለዋል። 'ተጨማሪ ማብራሪያ የሚፈልግ ካለ ለመስጠት ፍቃደኛ ነኝ፤ ስራ ላይ ነን!' ሲሉም በይፋዊ የትዊተር ገፃቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።
ከሰሞኑን ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት ላይ 'ህወሓት ወንጀል ፈጥሮላቸው፤ የፍርድ ቤት ክስና ማዘዣ ወጣባቸው' እየተባለ በማህበራዊ ሚዲያ ሀሰተኛ መረጃ ሲሰራጭ ነበር። ለዚህም ነው ፕሮፌሰር ክንደያ በትዊተር ገፃቸው ምላሽ የሰጡት።

ሌላ ተጨማሪ መረጃ ከመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፦
በትላንትናው ዕለት የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ ለሁለት ምሁራን የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል። ዩኒቨርሲቲው የፕሮፌሰርነት ማዕረግ የሰጠው ለዶክተር አበበ እጅጉ እና ለዶክተር አብርሃ ገ/ኪዳን መሆኑን ከዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት ሰምተናል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በትላንትናው ዕለት የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ ለሁለት ምሁራን የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል። ዩኒቨርሲቲው የፕሮፌሰርነት ማዕረግ የሰጠው ለዶክተር አበበ እጅጉ እና ለዶክተር አብርሃ ገ/ኪዳን መሆኑን ከዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት ሰምተናል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"ጾሙ ምዕመናን ከጥላቻ፣ ፍትህን ከማጉደል፣ ከበደልና ከዛቻ የሚቆጠቡበት ሊሆን ይገባል" - ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ
በመጪው ወርሃ ጾም ምዕመናን ከጥላቻ ፣ ፍትህን ከማጉደል፣ ሰውን ከመበደልና ከዛቻ እንዲቆጠቡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አሳሰበች።
ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ነገ በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚጀመረውን የአብይ ጾም አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ፓትርያርኩ በመልዕክታቸው ህዝበ ክርስቲያኑ ወርሃ ጾሙን ከቂምና ከበቀል ርቆ በመልካም ስነ ምግባርና በመንፈሳዊ ሕይወት አሸብርቆ ሊያሳልፍ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በዚህ ወቅት ማዳመጥ ያለብን የፈጣሪን ድምጽ ብቻ ነው ያሉት አቡነ ማትያስ፥ የፈጣሪ ድምጽ ደግሞ ፍቅርና ሰላም፣ አንድነትና ስምምነት፣ እርቅና ይቅርታ ምሕረትና ቸርነት፣ ርሕራሔና ሀዘኔታ፣ ጸሎትና ምጽዋት፣ ፍትሕና እውነት እንዲሁም እኩልነትና ሕብረት መሆናቸውን አውስተዋል።
ኢትዮጵያ አሁን የገጠማትን ችግር በጾም እና በጸሎት ከመትጋት የተሻለ አማራጭ እንደሌለም ነው ያመለከቱት።
#ENA

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ፦
ጾም ሲባል ወደ ሰዎች አእምሮ የሚመጣው የእንስሳት ውጤት ከሆኑ ምግቦች መከልከልና ሰዓት ጠብቆ መመገብ መሆኑን አንስተዋል፤ ጾም በንስሐ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ መሆኑን መገንዘብ እንደሚያስፈልግ አቡነ ማቲያስ አስረድተዋል።
ወደ ፈጣሪ ስንቀርብ በፍጹም ሃሳባችን፣ በፍጹም ልባችን በፍጹም ነፍሳችን ነውና በአካላችንና በመንፈሳችን ሁሉ ለእግዚአብሔር ሙሉ በሙሉ ለመታዘዝ ዝግጁ በመሆን ነው ሲሉም አስገንዝበዋል።
ምዕመናን ጾም ለእግዚአብሔር እንዲታዘዙ የሚያደርግ ፍቱን መሳሪያ በመሆኑ ወደ ፈጣሪ ቀርበው ለመለመንና ለመስማት እንዲሁም ንስሐ እንዲገቡ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን፦
ዐቢይ ፆም የእግዚአብሔርን ፈቃድ የምንፈፅምበትና ለወገናችን ፍፁም የሆነ ቅንነትን የምናሳይበት መሆን አለበት ሲሉ ብፅዕ ካርዲናል ብርሀነ-ኢየሱስ ሱራፌል የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀጳጳስ ገልፀዋል፡፡
ብፅዕ ካርዲናል ብርሀነ-ኢየሱስ ለምዕመናን ባስተላለፉት መልዕክት "ፆሙ ለተቸገሩ ወገኖች የምናደርገውን ድጋፍ አጠናክረን የምንቀጥልበት ሊሆን ይገባል" ብለዋል፡፡
"ጊዜው ስለኢትዮጵያና ስለዓለም ደህንነትና ሰላም ፈጣሪን አጥብቀን የምንማፅንበት ሊሆን ይገባል" ማለታቸውን ከኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ አመላክቷል።
ምንጭ፦ ኢቢሲ

ዛሬም የድጋፍ ሰልፎች ቀጥለዋል፦
የዶ/ር አብይ የለውጥ አመራርን የሚደግፍ የድጋፍ ሰልፍ ዛሬም በተለያዩ ከተሞች እንደተደረጉ ተመልክተናል። በዛሬው ዕለት የድግፍ ሰልፍ ከተደረገባቸው ከተሞች እና አካባቢዎች መካከል አዳማ፣ አምቦ፣ ገላን፣ ባሌ፣ ባቱ ይገኙበታል።
በሰልፎቹ ላይ የተገኙ ተሳታፊዎች እና የልወጥ አመራሩን የሚደግፉ ዜጎች የተለያዩ መልዕክቶችን ያስተላለፉ ሲሆን ለብልፅግና ፓርቲ የተለያዩ ድጋፎች ማድረጋቸው ተሰምቷል።
በሰልፎቹ ላይ ከተላለፉ መልዕክቶች የተወሰኑት፦
- በትግላችን ያመጣነውን ለውጥ እንጠብቃለን እንከባከባለን!
- ለለውጡ ውጤታማነት የድርሻችንን እንወጣለን !
- መነሻችን መደመር መድረሻችን ደግሞ ብልፅግና ነው!
- ህብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በመጠበቅ ለውጡን ከዳር እናደርሳለን !
- ስድብ እና ጥላቻ ሀገር አይገነባም!
PHOTO : Prosperity Party

የአብን ህዝባዊ ውይይት... የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የአዲስ አበባ ማስተበባበሪያ ፅ/ቤት በመጪው እሁድ የካቲት 15 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ከሚገኙ አባላቱና ደጋፊዎቹ ጋር አልማዝዬ ሜዳ አጠገብ በሚገኘው በቄራ ወረዳ 5 ሸማቾች ማኅበር አዳራሽ በንቅናቄው የማታግያ አጀንዳዎች እና በኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ ዙሪያ ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ሕዝባዊ ውይይት…
#Election2012
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የአዲስ አበባ ማስተባበሪያ ፅሕፈት ቤት ዛሬ የካቲት 15 ቀን 2012 ዓ.ም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ከሚገኙ አባላቱና ደጋፊዎቹ ጋር አልማዝዬ ሜዳ አጠገብ በሚገኘው በቄራ ወረዳ 5 ሸማቾች ማኅበር አዳራሽ ውይይት አድርጓል።
ውይይቱን የመሩት የአብን የኢኮኖሚ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ካሱ ኃይሉ የአማራ ሕዝብን ውስጣዊ አንድነቱን በማጠናከር ለመብቶቹ መከበር ሊታገል እንደሚገባ ገልፀዋል።
ኃላፊው አክለውም አብን በቀጣይ አገራዊ ምርጫ በማሸነፍ በአማራ ሕዝብ ላይ የተጋረጠውን የሕልውና አደጋ በዘላቂነት ለመቅረፍ የሚረዳ አደረጃጀትና መዋቅር በመላ አገሪቱ እየዘረጋ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
የንቅናቄውን የማታግያ አጀንዳዎች እና በኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ ዙሪያ በንቅናቄው ከፍተኛ አመራሮች ቀርቦ በተሳታፊዎች ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።
ምንጭ፦ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ

#ATTENTION
በአሁኑ ሰዓት በይርጋጨፌ እና አካባቢዋ የአንበጣ መንጋ በስፋት እየታየ እንደሆነ የቲክቫህ ይርጋጨፌ ቤተሰቦቻችን ገልፀዋል። መንጋው ጉዳት እንዳያደርስም ሁሉም ርብርብ እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል።
በተመሳሳይ፦
የአንበጣ መንጋ በባሌ ሮቤ ከትናንት ማምሻውን ጀምሮ ዛሬም እየታየ ነው እንደሆነ የባሌ ሮቤ ቲክቫህ ቤተሰቦች ጠቁመዋል ጥንቃቄ እንዲደርገም አሳስበዋል።
PHOTO : Tikvah Family [ይርጋጨፌ]

"የምር ለውጥ እዚህ ነው ያለው!" - ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል
የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር እና የህወሓት ሊቀ መንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ከሰሞኑን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተከታዩን ሲሉ ተደምጠዋል፦
...ዝም ብሎ የትግራይ የበላይነት ይባላል፤ የትግራይ የበላይነት የሚባል ነገር የለም። አቶ ለማ ሲናገረው የነበረው በግልፅ፣ ግለሰቦችም ይኖራሉ እኔም ገልጫለሁ የትግራይ የበላይነት የሚባል ነገር ግን የለም። የተደመደመ ነው። እስከ ቅርቡ ግን የትግራይ የበላይነት ይባላል።
ወረሩን ከየት ሀገር የመጣ ወራሪ እንደሆነ ማይገባን፤ ወረሩን፣ አባረርናቸው፤ እንዴት እንዲህ ይባላል? እኛ እያልን ያለነው ለውጡ መንገድ ስቷል! ለዚህም ነው ይህቺ ሀገር ሰላም ያጣችው።
... ትግራይ ዝም ብለን ተዘጋጅ ስላልነው አይደለም ሰላም የሆነው። እየሰራን ነው። ገምግመን ለውጥ ማሳየት አለብን። የገመገምነውን እየቆጠርን ነው እየሰራን ያለነው። የምር ለውጥ እዚህ ትግራይ ነው ያለው።
PHOTO : AWLO MEDIA

በመቅደላ ወረዳ የተገነቡ መሰረተ ልማቶች ተመረቁ!
በደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ የተገነቡ መሰረተ ልማቶች ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ተመስገን ጥሩነህና ከፍተኛ ሃላፊዎች በተገኙበት ዛሬ ተመረቁ። የመቅደላ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ተፈራ ሞላ እንዳስታወቁት የመሰረተ ልማቶቹ ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ በ87 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነቡ ናቸው።
#ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ የተገነቡ መሰረተ ልማቶች ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ተመስገን ጥሩነህና ከፍተኛ ሃላፊዎች በተገኙበት ዛሬ ተመረቁ። የመቅደላ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ተፈራ ሞላ እንዳስታወቁት የመሰረተ ልማቶቹ ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ በ87 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነቡ ናቸው።
#ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በህገ ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ 14 ክላሽ ጠብመንጃ ተያዘ!
በኢሉ አባቦር ዞን ቡሬ ወረዳ በህገ ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ 14 ክላሽኮቭ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ ገለፀ።
የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ታረቀኝ አሰፋ እንደገለፁት፥ የጦር መሳሪያው የተያዘው በሚኒባስ ተሽከርካሪ ከጋምቤላ ወደ አዲስ አበባ በመጓጓዝ ላይ እንዳለ ነው።
መሳሪያዎቹ ዛሬ ጠዋት 2 ሰዓት ተኩል አካባቢ በቡሬ ከተማ በተደረገው ፍተሻ በተሽከርካሪው ውስጠኛው አካል በላሜራ በተበየደ ቦታ ውስጥ ተደብቀው ተገኝተዋል።
የሚኒባሱ አሽከርካሪ ለጊዜው መሰወሩን ገልፀው ሌሎች በውስጥ የነበሩ ሁለት ሰዎች ግን በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል።
አሽከርካሪውን ለመያዝ ክትትል እየተደረገ መሆኑን የጠቆሙት ኮማንደሩ፥ በቁጥጥር ስር በዋሉት ግለሰቦች ላይ ማጣራት እንደሚካሄድ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በአምቦ የተፈፀመው የቦምብ ጥቃት...
ዛሬ እሁድ፣ ጠዋት ለጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ እና ለፓርቲያቸው ድጋፋቸውን ለመስጠት ሠልፍ በወጡ ሠልፈኞች ላይ በተወረወረ ቦምብ ቢያንስ 29 ሠዎች መቁሰላቸውን የአምቦ ከተማ አስተዳደር እና ጸጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ ለቢቢሲ ተናገሩ።
ኃላፊው አቶ ሂንሰርሙ ደለሳ እንዳሉት ቦንቡ የተወረወረው ለድጋፍ ሰልፍ በወጡ ፈረሰኞች ላይ ነው።
ጉዳት ካጋጠማቸው መካከል የህክምና እርዳታ ተደርጎላቸው ከሆሰፒታል የወጡ እንዳሉ ሁሉ የተለያዩ የጉዳት መጠን ያስተናገዱ መኖራቸውን አቶ ሂንሰርሙ ተናግረዋል።
ከወንጀሉ ጋር ተያይዞ ተጠርጥረው የተያዙ ሰዎች መኖራቸውን የተናገሩት ኃላፊው "በጫካ ውስጥ ታጥቆ የሚንቀሳቀስው ኃይል ወንጀሉን ሳይፈፅም እንደማይቀር እንጠረጥራለን" ብለዋል።
በጥቃቱ በርካታ ፈረሶችም መጎዳታቸውን ቢቢሲ ከአምቦ ከተማ ነዋሪዎች ባገኘው መረጃ ለማወቅ ችሏል።
#BBC

#AMBO
በዛሬው የአምቦ የድጋፍ ሰልፍ ላይ በደረሰው የቦምብ ጥቃት ከተጎዱት 29 ሰዎች መካከል 28ቱ ህክምና አግኝተው ወደ መጡበት ተመልሰዋል። የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በጉዳዩ የተጠረጠሩ 6 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቋል።
[የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን፣ኢቢሲ]

#COVID19
ደቡብ ኮርያ የኮሮና ተዋሃሲ ተጠቂዎች ቁጥር እጅጉን ማሻቀቡን ተከትሎ የተዋሃሲውን ስርጭት ለማቆም ባለስልጣኖቿ ማንኛውንም እርምጃ እንዲወስዱ ፈቅዳለች።
በሃገሪቱ በአንድ ቀን ከ150 ሰዎች በላይ በተዋሐሲው መያዛቸውን ተከትሎ የቀይ ደረጃ የተሰጠውን የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ለመስጠት መገደዷን ፕሬዚዳንት ሙን ጃኤ ኢን አስታውቀዋል።
በደቡብ ኮሪያ ዛሬ የተመዘገበውን የሁለት ሰዎች ሞት ጨምሮ 602 ሰዎች በተዋሐሲው መያዛቸውን የሃገሪቱን የበሽታ መቆጣጠሪያ ማዕከልን ጠቅሶ የደቡብ ኮሮያ የዜና ምንጭ ዮን ሃፕ ዘግቧል።
በአንድ ቀን በተወሐሲው የተጠቁ ሰዎች ቁጥር በእጥፍ የተገኙባት ደቡብ ኮርያ ወረርሽኙ እንዳይንሰራፋ ጠንካራ እና ፈጣን የተባለለትን እርምጃ ተግባራዊ ማድረግ መጀመራቸውን ጠቅላይ ሚንስትር ቹንግ ስዬ ክዩን አርብ ዕለት አስታውቀው ነበር።
ለዚህም ዳኤጉ እና ቼኦንግዶ የተሰኙ አካባቢዎችን የልዩ እንክብካቤ ማዕከላት ተደርገዋል። ከ 2.5 ሚልዮን በላይ ነዋሪዎች የሚገኙባት ዳኤጉ ነዋሪዎች ከቤታቸው እንዳይወጡ መደረጉም ታውቋል።
#DW

#UPDATE
በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የሚኖሩ መኖሪያ ፈቃድ የሌላቸውን ኢትዮጵያውያን ህጋዊ ለማድረግ የምዝገባ ሥራ መጀመሩን በዱባይ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት አስታወቀ።
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከየካቲት 5-7 ቀን 2012 ዓ.ም በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ጉብኝት በማድረግ በመካከለኛው ምሥራቅ አገራት ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር በመገናኘት ውይይት ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡
በጉብኝቱ በተለይ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የሚኖሩ ዜጎቻችን ያለባቸውን ችግሮች ለማቅረብ ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በተደረገ ውይይት ስምምነት ከተደረሰባቸው ጉዳዮች መካከል በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ያለመኖሪያ ፈቃድ የሚኖሩ ዜጎቻችንን ህጋዊ ለማድረግ ስምምነት ተደርሶ እየተሰራበት ይገኛል፡፡
በዚሁ መሠረት ከዛሬ ጀምሮ ለአንድ ወር የሚቆይ የዜጎች የመረጃ የማሰባሰብ ሥራ በአቡዳቢ ኤምባሲ እና በዱባይ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት በይፋ ተጀምሯል፡፡
[ዱባይ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaBot