TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር...

በኮሮና ቫይረስ ስጋት ውስጥ እንደሆኑ የተነገረላቸው ተማሪዎችን ለማስመጣት ግብረኃይል መቋቋሙን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ አርብ የካቲት 6/2012 በወቅታዊ ጉዳይ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አስታውቋል፡፡

በቻይና ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች መንግስት የገንዘብ ድጋፍ መላኩን የገለጹት የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ነብያት ጌታቸው ተማሪዎቹ በቫይረስ እንዳይጠቁ ክትትል እየተደረገ ነው ብለዋል።

ምንጭ ፦ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በዲላ ማረሚያ ተቋም የተነሳው የእሳት ቃጠሎ...

በዲላ ማረሚያ ተቋም ዛሬ [የካቲት 06 / 2012 ዓ/ም] ረፋዱ ላይ በተነሳ የእሳት ቃጠሎ ከአምስት ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው ንብረት ማጥፋቱን የማረሚያ ተቋም  አስታውቋል። በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ ተገልጿል።

የዲና ማረሚያ ተቋም ኃላፊ ሳጅን ትግስት ሮቤ እንደገለጹት መንስኤው ለጊዜው ባልታወቀ ሁኔታ የተነሳው የእሳት ቃጠሎው የታራሚዎች መመገቢያ አዳራሽና የንብረት ክፍልን አውድሟል።

#ኢዜአ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"አባሎቼና ደጋፊዎቼ በጅምላ እየታሰሩብኝ ነው" - ኦነግ

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አባሎቼና ደጋፊዎቼ በጅምላ እየታሰሩብኝ ነው ብሏል፡፡ እስሩ እየተፈፀመ ያለው በኦሮሚያ ፖሊስ እንደሆነም ግንባሩ ዛሬ በፅህፈት ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አሳውቋል፡፡

እስከ ዛሬዋ ዕለት ድረስም በኦሮሚያ ክልል 7 ዞኖች እና 26 ከተሞች 350 አባሎቹ፣ ደጋፊዎቹና ሌሎች ወጣቶች መታሰራቸውን በመግለጫው ገልጿል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ የ174ቱ ስም ደርሶኛል ሲልም ዘርዝሯቸዋል፡፡

የምዕራብና ደቡብ ኦሮሚያ አካባቢዎች ህጋዊ መሰረት በሌለው እና ቀነገደብ ባልተቀመጠለት ኮማንድ ፖስት እየተዳደሩ ይገኛሉም ብሏል፡፡ የአካባቢዎቹ በኮማንድ ፖስት መተዳደር ነዋሪዎቹን ለግድያ፣ ዝርፊያ፣ አስገድዶ መድፈርና ሌሎች ወንጀሎች አጋልጧቸዋል ሲልም አክሏል፡፡

በምዕራብና ቄለም ወለጋ አካባቢዎች የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎቶች ከተቋረጡ ከ1 ወር ተኩል በላይ እንደሆነ የግንባሩ ባለስልጣናት በመግለጫው ላይ ተናግረዋል፡፡

በአገሪቱ አጠቃላይ ምርጫ ለማድረግ ዝግጅት እየተካሄደ ባለበት በአሁኑ ወቅት የነገሮች መክፋት አሳስቦኛል ሲልም ኦነግ በመግለጫው ጠቅሷል፡፡

መንግስት ለችግሩ አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጥ፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ደግሞ በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች እየተፈፀሙ ያሉ የመብት ጥሰቶችን አጣርቶ መረጃውን ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርግ ጠይቋል፡፡

ምንጭ፦ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የውጭ አገር ሥራ ስምሪት ተጠናክሮ ቀጥሏል!

የኢትዮጵያ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ከተጀመረ በጥቂት ወራት ውስጥ መንግሥት የሥራ ስምምነት ወዳደረገባቸው አገራት የሥራ ዕድል አግኝተው ወደ ሣውዲ ዓረቢያ 8,804፣ ኳታር 1,233፣ ጆርዳን 1,709፣ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ 1,262 በድምሩ 11,981 ዜጎች ለሥራ ተሰማርተዋል፡፡

እነዚህ ዜጎች በህጋዊ መንገድ መጓዛቸው ክብራቸው መብታቸውና ደህንነታቸው ተጠብቆ ምንም ዓይነት የጉዞ ወጪ ሳያወጡ በነፃ በውጭ ሀገር ለሥራ የተሰማሩ ናቸው ተብሏል፡፡

ህብረተሰቡ በህጋዊ መንገድ የውጭ አገር የሥራ ሥምሪት ተጀምሮ ዜጎች ተጠቃሚ እየሆኑ መሆኑን ተረድቶና ተገንዝቦ ልጆቹን ከህገ - ወጥ ደላላና ከህገ - ወጥ የሰዎች ዝውውር እንዲሁም ከህገ - ወጥ የበረሃ ጉዞ እንዲታቀብ ማሳስቢያ ተሰጥቷል።

[Ministry of Labor and Social Affairs]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የሰላም ዋጋ ስንት ደረሰ?

ሠላም ዋጋው ምን ያህል ነው? እንገምት እንበል። ማልዶ ወጥቶ፣ አምሽቶ ገብቶ ያለአንዳች እንከን ተግባርን ከውኖ መመለስ በምን ያህል ይለካል ? በምን ይመዘናል ? ልጅ ወልዶ ፣ አሳድጎ ፣ አስተምሮና ለወግ ማዕረግ አብቅቶ ተመስገን ብሎ አምላክን ለማመስገን መታደል ዋጋው ስንት ይሆን? የሰላም ዋጋ ስንት ደረሰ? 

ክፉ አይንካችሁ፤ ሰላም እደሩ!
#የቲክቫህቤተሰቦች

#ከአባ_መላኩ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#BREAKING

ኮሮና ቫይረስ አፍሪካ ገብቷል!

በአፍሪካዊቷ ሀገር #ግብፅ ውስጥ በኮሮና ቫይረስ የተጠቃ ግለሰብ መኖሩ ተረጋገጠ። ግብፅ የመጀመሪያዋ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ የተገኘባት አፍሪካዊ ሀገርም ሆናለች። ከግብፅ የጤና ሚኒስትር እንደተሰማው ከሆነ በኮሮና ቫይረስ የተጠቃው ግለሰብ የውጭ ሀገር ዜጋ ነው፤ ግለሰቡ የምን ሀገር ዜጋ እንደሆነ ግን አልተገለፀም።

#COVID19
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የወረታ ደረቅ ወደብና ተርሚናል ተመረቀ!

ከ100 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የወረታ ደረቅ ወደብና ተርሚናል የመጀመሪያ ምዕራፍ ተመረቀ።

በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ እንዲሁም የፌደራልና የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃለፊዎች ተገኝተዋል።

ከዚህ ባለፈም በገዳሪፍ ዋና አስተዳዳሪ ሜጀር ጀኔራል ነስረዲን አብዲ የተመራ ልዑክም በስነ ስርዓቱ ላይ ተገኝቷል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE - የሟቾች ቁጥር 1,491 ደርሷል - በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 65,247 በኮሮና ቫይረስ [2019-nCoV] የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1,491 የደረሰ ሲሆን 65,247 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል። ከበሽታው አገግመው ከሆስፒታል የወጡ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 7,099 መድረሳቸውን ተመልክተናል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

- የሟቾች ቁጥር 1,526 ደርሷል
- በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 67,110

በኮሮና ቫይረስ [#COVID19] የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1,526 የደረሰ ሲሆን 67,110 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል። ከበሽታው አገግመው ከሆስፒታል የወጡ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 8,365 መድረሳቸውን ተመልክተናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ምርጫ ቦርድ ዛሬ ከሲቪል ማህበራት ጋር እየመከረ ይገኛል!

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በያዝነው አመት በሀገራችን ለሚከናወነው ብሔራዊ ምርጫ የተለያዩ ዝግጅቶች እያደረገ ይገኛል፡፡ ላለፉት ቀናት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ሰፊ ውይይቶችን ማድረጉ ይታወሳል፡፡ ዛሬም ምርጫ ቦርድ ከ ሲቪል ማህበራት ጋር በመራጮች ትምህርት ፈቃድ አሰጣጥና ስነምግባር ዙሪያ፣ እንዲሁም የሀገር ውስጥ የምርጫ ታዛቢዎች ፈቃድ አሰጣጥና ስነምግባር ጉዳዮች ላይ እየመከረ ይገኛል፡፡

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ውሃን የሚገኙ ተማሪዎች የላኩት መልዕክት፦

- የኢትዮጵያ መንግስት እያደረኩ ነው የሚለው እገዛ የጠበቅነው ያህል አይደለም። አሁንም ችግር ላይ እንደሆነን መታወቅና አስቸኳይ መፍትሄ ሊሰጠን ይገባል።

- ትላንት ኤምባሲዉ ደብዳቤ በተወካዮች በኩል ልኮልን ነበር በጣም የማይጠበቅ መልዕክት ነው። እኛ የፈለግነው ደህንነታችን ተጠብቆ የሌላ ሀገር መንግስታት ዜጎቻቸውን እንዳሶጡ እኛንም እንዲያሶጡን ነው የነሱ ግን መልስ ጉዳዩ ዝግጅትን የሚጠይቅ እንደሆነ ነው የሚገልፁት።

- መንግስት ላለፉት 3 ሳምንታት ሙሉ ግን ምንም መልስ እየሰጠን አይደለም። በተለያዩ ወቅቶች የተለያዩ ምክንያቶችን ነው እየደረደሩ ያሉት። ሌሎች ሀገራት ተማሪዎቻቸን ካስወጡ ቆይተዋል። እኛ ግን አሁንም እዛው ነን!

ተማሪዎቹ ተላከልን ከኤምባሲው ተላከልን የሚሉትን ድብዳቤ ለቲክቫህ ኢትዮጵያም ልከዋል!

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ልጆቻቸውን ቻይና ልከው የሚያስተምሩ ወላጆች የኢትዮጵያ መንግስት ልጆቻቸውን ወደ ሀገራቸው እንዲመልስ ለመጠይቅ እንዲሁም ያደረባቸውን ቅሬታ ለመግለፅ ፋና ቴሌቪዥንና የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ይገኛሉ።

#TikvahFamily
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአቡዳቢ ውይይት አድርገዋል!

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው ዕለት በተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች በልዩ ልዩ ምክንያት በችግር ውስጥ ከሚገኙ፣ ጥቃት ከደረሰባቸው እና በመጠለያ ውስጥ ከሚገኙ ሴት ኢትዮጵያውያን ጋር መክረዋል። ምክክሩም በችግሮቻቸው እና በመፍትሄዎች ላይ ትኩረትን ያደረገ ነበር። በውይይቱ ችግር ከገጠማቸው ሴቶች በተጨማሪ በልዩ ልዩ ሥራዎች ላይ ተሰማርተው ስኬትን ያስመዘገቡ ሴቶችም በመድረኩ ላይ ልምዳቸውን አጋርተዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ልጆቻቸው ውሃን የሚገኙ ተማሪ ወላጆች ጥያቄ፦

- የኢትዮጵያ መንግስት በአስቸኳይ ልጆቻቸውን ወደሀገራቸው እንዲመልስላቸው ጠይቄ አቅርበዋል።

- የሌሎች ሀገር ዜጎች በራሳቸው መንግስት በአስቸኳይ ሲወጡ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ግን እስካሁን ድረስ ባለመውጣታቸው ያደረባቸውን ቅሬታ አሰምተዋል።

- በምግብ እጥረት ልጆቻቸው ክፉኛ እየተጎዱባቸው እንደሆነም ተናግረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በያዮ ወረዳ የተያዘው ህገወጥ የጦር መሳሪያ...

በኢሉአባቦር ዞን ያዮ ወረዳ ህገወጥ የጦር መሳሪያ ሲያዘዋውሩ ተደርሶባቸዋል ያላቸውን ሶሰት ግለሰቦች መያዙን ፖሊስ አስታውቋል።

የወረዳውፖሊስ አዛዥ ዋና ሳጅን ከድር አባፎጊ እንደገለፁት ግለሰቦቹ  የተያዙት ኮድ 3 -22454 አ.አ. በሆነ አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ የጦር መሳሪያዎቹን ሲያጓጉዙ ተደርሶባቸው ነው።

ግለሰቦቹ ከጋምቤላ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ እንደነበሩ አመልክተው ያዮ ወረዳ እንደደረሱ  በተደረገው ፍተሻ 40 ክላሽንኮቭ ጠብመንጃዎች በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን አስታውቀዋል።

#ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE የኮሮና ቫይረስ በሽታን (CoViD-19) አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዛሬ የካቲት 6/2012 የተሰጠ መግለጫ፡፡ @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፦

"ቀደም ብሎ ኢንስቲትዩቱ አንድ የኮሮና ቫይረስ [COVID19] በሽታ ምልክቶችን ያሳየ ሰው በለይቶ ማቆያ ማዕከሉ ውስጥ እንደሚገኝና ናሙናው ለቦራቶሪ ምርመራ መላኩን መግለጹ ይታወሳል። የምርመራው ውጤት የደረሰ ሲሆን ከበሽታው ነጻ መሆኑም ተረጋግጧል፡፡"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

በ4 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ወጪ በመቐለ ከተማ አስተዳደር እየተገነቡ ካሉ በድምሩ 93 ኪሎ ሜትር ከሚሸፍኑ መንገዶች መካከል 32 ኪሎ ሜትር የሚሸፍኑት 11 መንገዶች ዛሬ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል። መንገዶቹን የመረቁት የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ናቸው። የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም፣ የክልሉ ካቢኔ አባላት እንዲሁም የመቀሌ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ ኢንጅነር ኣርአያ ግርማይም በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተገኝተዋል።

#ኢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የባልደራስ አመራሮች በባህርዳር ከተማ...

በቅርቡ የተመሰረተው የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ አመራሮች ባህርዳር ይገኛሉ። አመራሮቹ ዛሬ ጠዋቱ በጣና ግዮን የማሕበራዊ የበጎ ፈቃድ ማሕበር አስተባባሪነት በባህር ዳር የጣና ሐይቅ ዳርቻን የፅዳት ዘመቻ ከወጣቱ ጋር መሳተፋቸውንም ተመልክተናል። የፓርቲው ፕሬዝደንት አቶ እስክንድር ነጋ በአካባቢው ለሚገኙ ወጣቶች መልዕክት ማስተላለፋቸውንም ሰምተናል።

[Sintayehu Chekol]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE በ4 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ወጪ በመቐለ ከተማ አስተዳደር እየተገነቡ ካሉ በድምሩ 93 ኪሎ ሜትር ከሚሸፍኑ መንገዶች መካከል 32 ኪሎ ሜትር የሚሸፍኑት 11 መንገዶች ዛሬ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል። መንገዶቹን የመረቁት የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ናቸው። የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም፣ የክልሉ ካቢኔ አባላት…
#Mekelle

ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል፦

"መቐለ የክልሉ ርዕሰ መዲና ብቻ ሳይትሆን ዓለም አቀፍ ይዘት ያላት የሁሉም ዜጎች ከተማ ለማድረግ እንሰራለን።

የመቐለ ከተማ ም/ከንቲባ ኢንጅነር ኣርአያ ግርማይ፦

"መንገድ ለአንድ ከተማ ዕድገት ወሳኝ ነው። በከተማዋ በየደረጃው እየተገነቡ ያሉት የመንገድ ፕሮጀክቶች ከህብረተሰቡ በሚሰበሰበው ግብር የሚሰሩ በመሆናቸው ህብረተሰቡ ተገቢውን ጥበቃ ሊያደርግላቸው ይገባል።"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ቤጂንግ ወደ ከተማዋ የሚመለስ ማንኛውም ሰው ለ14 ቀናት በለይቶ ማቆያ እንዲሰነብት ትዕዛዝ ማስተላለፏ ተሰምቷል። ከተማዋ ይህን ያደረገችው ገዳዩን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመቆጣጠር በማሰብ ነው።

በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በዓል ካከበሩ በኋላ ወደ ቤጂንግ የተመለሱ ነዋሪዎች በያሉበት አሊያም በየአቅራቢያቸው ወደሚገኙ ለይቶ ማቆያ ማዕከላት በማምራት ለ14 ቀናት ያህል ከኅብረተሰቡ ተገልለው እንዲቆዩ ከተማዋ አሳስባለች፡፡ ትዕዛዙን በማይተገብሩ ላይ ቅጣት እንደምትጥል ቤጂንግ አስጠንቅቃለች፡፡

#BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአውሮፓ በኮሮናቫይረስ የመጀመሪያ ሰው ሞተ!

አውሮፓ ውስጥ በኮሮናቫይረስ የመጀመሪያው ሰው ሞተ። ሟች ቻይናዊ ቱሪስት መሆናቸው የተነገረ ሲሆን ይህ ሞት ከእስያ አህጉር ውጪ የተመዘገበ የመጀመሪያው ነው ተብሏል። ቱሪስት የ80 ዓመት ወንድ ሲሆኑ ከቻይናዋ ሁቤይ ግዛት የመጡ መሆናቸውን የፈረንሳይ ጤና ሚኒስትር ተናግረዋል።

#BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia