#Mogadishu | በሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ የሚገኘው አውሮፕላን ማረፊያ ትናንትና ማለዳ በመድፍ በመደብደቡ በርካታ ሰዎች መቁሰላቸውን በተባበሩት መንግሥታት የሶማሊያ ልዑክ አስታወቀ። የመድፍ ጥይቶቹ ያረፉት በአየር ማረፊያው ውስጥ በሚገኙ የተባበሩት መንግሥታት እና የአፍሪካ ኅብረት ቅጥር ግቢዎች ውስጥ ነው።
Via DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Mogadishu
በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ አንድ ሆቴል በአልሸባብ ታጣቂዎችና በመንግሥት የፀጥታ ሃይሎች መካከል በተከፈተ የተኩስ ልውጥጥ 10 ሰዎች ተገድለዋል። በሶማሊያ ወጣቶች ሊግ ሆቴል በነበረው ተኩስ አምስት የአልሸባብ አባለት፣ ሁለት የመንግሥት የፀጥታ ሃይሎች እና ሦስት ንፁሃን ዜጐች ተገድለዋል። ሆቴሉ ለመንግሥት ባለስልጣናት እና ለባለሃብቶች አገለግሎት የሚሰጥ ነው ተብሏል። ፖሊስ ባወጣው መግለጫ ለሰባት ሰዓታት የቆየው የተኩስ ልውውጥ አሁን የቆመ ሲሆን፥ ቢያንስ 82 ሰዎች ከሆቴሉ እንዲወጡ ተደርገዋል። የተኩስ ልውውጡ የተጀመረው የአልሸባብ ታጣቂዎች ጥቃት መክፈታቸውን ተከትሎ ነው ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

በሞቃዲሾ በመኪና በተጠመደ የቦምብ ጥቃት ከ61 ሰዎች በላይ መሞታቸውና 100 ሰዎች ገደማ መቁሰላቸውን የሀገሪቱን ፖሊስ ዋቢ በማድረግ አልጀዚራ አስነብቧል፡፡ በጥቃቱ የቆሰሉት 100 ሰዎች ሆስፒታል የገቡ ሲሆን በአውቶብስ የሚጓዙ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንደሚገኙበት የሀገሪቱ ፖሊስ ሃላፊ መሃመድ ሃሰን ተናግረዋል፡፡ የሟቾች ቁጥርም ከፍ ሊል እንደሚችል ተገልጿል፡፡
(አልጀዚራ)

በሞቃዲሾ የመኪና ላይ የአጥፎ ጠፊ የቦንብ ጥቃት በትንሹ 8 ሰዎች ሲገደሉ 17 ሰዎች ቆስለዋል።
ፖሊስ ኢላማውን ያደረገው፤ “የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን (UN) የሚጠብቅ” በአካባቢው የሚገኝ የግል የደህንነት ኮንቮይ ላይ መሆኑንም አረጋግጧል።
ፖሊስ በፍንዳታው የተጎዱ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ሰራተኞች ስለመኖራቸው ግን ያለው ነገር የለም።
አልሸባብ ለጥቃቱ ኃላፊነት የወሰደ ሲሆን ፥ ጥቃቱ ያነጣጠረው ከጄኔራል ጎርደን ማሰልጠኛ ካምፕ "ነጭ መኮንኖች"ን በማጀብ ሲጓዝ በነበረ ኮንቮይ ላይ ነው ብሏል።
የመኪናው ላይ የቦንብ ፍንዳታ በቅራቢያው በነበረ የሞካሲር ትምህርት ቤት ሕንፃ ላይም ጉዳት ያደረሰ ሲሆን ቢያንስ 11 ተማሪዎች መቁሰላቸው ተመላክቷል።
Photo Credit : Harun Maruf
@tikvahethiopia