TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#Tigray

በመከላከያ የሰራዊት ግንባታ ስራዎች ዋና አስተባባሪ ሌ/ጄነራል ባጫ ደበሌ ዛሬ በቴሌቪዥን ቀርበው ባደረጉት ገለፃ የፌዴራሉ መንግስት በትግራይ ላይ ያወጀውን የተናጠል የተኩስ አቁም እርምጃ ህወሓት እንደአጋጣሚ ተጠቅሞ ትንኮሳ እየፈፀመ ነው ብለዋል።

ሌ/ጄነራል ባጫ ደበሌ ህወሓት የተኩስ አቁሙን እንደአጋጣሚ ተጠቅሞ ለጥበቃ፣ ለሳተላይት አሃዱዎች፣ የክልል የፀጥታ ኃይሎችን ለማጥቃት እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

"ኮረም እና አላማጣ ቀድሞውንም ሰራዊት አልነበረንም ... ነገር ግን በራያ አካባቢ አነስተኛ ኃይል ማስቀመጥ ነበረብን ፤ በተጨማሪ የአካባቢ ኃይሎችን ማስቀመጥ ነበረብን ህወሓት የተኩስ አቁሙን እንደአጋጣሚ ተጠቅሞ እኛ መቋቋም ሳናደርግ እናጠቃለን በሚል ኃይላችንን አጥቆት ለመደምሰስ ሞክሯል" ብለዋል።

የታወጀው የተናጠል ተኩስ አቁም ለሰብዓዊ ድጋፍ እና የትግራይ ገበሬዎች የግብርና ስራቸውን በነፃነት እንዲሰሩ ታሳቢ በማድረግ የታወጀ መኖሩን አስታውሰው "ህወሓት" ግጭትን መፍጠር መሰረታዊ ባህሪው በመሆኑ ውሳኔውን አልተቀበለም ሲሉ ገልፀዋል።

ሌተናል ጄኔራሉ ፤ ወታደራዊ ስራ በወታደሮች የሚሰራ እንጂ #በአክቲቪስቶች የሚሰራ አይደለም ያሉ ሲሆን አሁን የተፈፀመ ላለው ትንኮሳ መከላከያው የት መስፈር እና እንዴት በሙሉ አቅሙ ጥቃት መፈፀም እንዳለበት ውሳኔ ተወስኖ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

"እየተዋጋን ያለነው #ለኢትዮጵያ_ድንበር ነው ፤ የኛ ድንበር #መረብ ነው" ሲሉ የተደመጡት ሌ/ጄነራል ባጫ የመረብ ድንበር ድረስ ኢትዮጵያን ለመበጣጠስ የሚፈልገውን ኃይል የማይቻል መሆኑን ማሳየት ነው ሲሉ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia