TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
በመስከረም ወር የተመዘገበው አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነጻጸር በ18 ነጥብ 6 ከመቶ ከፍ ብሏል። የምግብ ዋጋ ግሽበት የመስከረም ወር 2012 ዓ.ም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነፃፀር በ23 ነጥብ 3 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
•በጤፍ፣
•በገብስ፣
•በማሽላ፣
•በቆሎና
•የስንዴ ዱቄት ዋጋ ጭማሪው እንደቀጠለ ቢሆንም የአጨማመሩ ፍጥነት ግን ካለፉት ወራት ያነሰ መሆኑን የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ አመልክቷል።

ከዚህ በተጨማሪም በየቀኑ ለምግብነት ተፈላጊ የሆኑት አንዳንድ የአትክልት ዓይነቶች በተለይም ቲማቲም፣ ቀይ ሽንኩርትና ነጭ ሽንኩርት በአንድ ወር ውስጥ ጭማሪ በማሳየታቸው የዋጋ ግሽበት ከፍ እንዲል አስተዋፅኦ አድርጓል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሌላ በኩል...

ምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጦች የዋጋ ግሽበት የመስከረም ወር 2012 ዓ.ም ካለፈው ዓመት መስከረም ወር 2011 ዓ.ም ጋር ሲነፃፀርም የ13 ነጥብ 1 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

ካለፉት ጥቂት ወራት ጀምሮ ምግብ ነክ ያልሆኑ የሸቀጦች የዋጋ ግሽበት በተከታታይ ጭማሪ እያሳየ መሆኑን ተጠቁሟል።

ግሽበቱ ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከፍ እንዲል ያደረገው በተለይ ልብስና መጫሚያ፣ የቤት ኪራይ፣ የቤት እንክብካቤና ኢነርጂ (ማገዶና ከሰል)፣ የቤት ዕቃዎችና የቤት ማስጌጫዎች፣ የቤት መስሪያ ዕቃዎች፣ ህክምናና ትራንስፖርት (በተለይ የቤት መኪና) ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ እንደሆነ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ አመልክቷል።

Via ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሁሉም ውስጡ #ስጋና #ደም
ቀለም መልኩ ቢለያይም
ወላጁ #አንድ ነው አባቱ አንድ ነው
ዞሮ ዞሮ #አዳም
.
.
ሰውነት ይከበር!
ሰውነት ይቅደም!
#ETHOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢሬቻ2012

በኢሬቻ በዓል ወቅት የሚከናወኑ የባዕድ አምልኮዎች የኦሮሞን ባህል የማይወክሉ በመሆናቸው ሊቆሙ እንደሚገባ የአባገዳዎች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ጫላ ሶሪ ተናገሩ፡፡ የኢሬቻን በዓል በማስመልከት አፈ ጉባኤው በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ የኢሬቻ በዓል ሲከበር ባዕድ አምልኮ የሚመስሉ ኦሮሞ የማይፈፅማቸው ነገሮች ይከናወናሉ፡፡ በተለይ የኢሬቻበዓል ሲቃረብ በግ በማረድ ጭንቅላቱን ውሃ ውስጥ መጣል፣ ጥቁር ዶሮዎችን እራስ ላይ በማዞር ውሃ ውስጥ መክተት፣ አረቄና ውስኪ ውሃ ውስጥ መጣል እና ሽቶ ማርከፍከፍ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ እነዚህ ድርጊቶች ደግሞ የኢሬቻን በዓል ስለማይወክሉ ሊቆሙ ይገባል፡፡ ‹‹በእነዚህ ነገሮች ኦሮሞ ፈጣሪውን አይለምንም፤ ምስጋናም አያቀርብም›› የሚሉት አቶ ጫላ፣ እነዚህ ነገሮች ሰው ሰራሽ በመሆናቸው ምክንያት አይለመንባቸውም፤ ምስጋናም አይቀርብባቸውም ብለዋል፡፡

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማስታወሻ፦ የሚዘጉ መንገዶች!

በመስቀል አደባባይ የሚከናወኑ ልዩ ልዩ ስነ-ሥርአቶች ተጀምረው እስከሚጠናቀቁ ድረስ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ከበዓሉ ዋዜማ ጀምሮ፦


ጎተራ ሼል ዴፖ ፣ ጎፋ ማዞሪያ ፣ ቄራ 6 ቁጥር ማዞሪያ ፣ ሳር ቤቶች ፣ ካርል አደባባይ ፣ ጦር ኃይሎች አደባባይ ፣ ኮካኮላ ድልድይ ፣ ልደታ ከፍተኛ ፍ/ቤት ፣ ልደታ ፀበል ፣ አብነት አደባባይ ፣ ሞላ ማሩ መገንጠያ ፣ በርበሬ በረንዳ ፣ ተክለ ሃይማኖት ፣ ቴዎድሮስ አደባባይ ፣ ንግድ ማተሚያ ቤት ፣ አሮጌው ቄራ ፣ ባሻወልዴ ፣ፓርላማ መብራት ፣ ጥይት ቤት ፣ ጀርመን አደባባይ ፣ ሲግናል፣ እንግሊዝ ኤምባሲ መገንጠያ ፣ ለም ሆቴል ፣ ሾላ ገበያ መብራት ፣ ጎርጎሪዮስ አደባባይ ፣ መስቀል ፍላወር ፣ መገናኛ ላይና ታች ፣ ኤድናሞል አደባባይ ፣ ሰንሻይን መገንጠያ ፣ ቦሌ ቀለበት እና ቦሌ ሚካኤል ወደ ዝግጅቱ ስፍራ የሚወስዱ መንገዶች ለጊዜው ለተሽከርካሪ ዝግ ናቸው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትም ሆነ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥማችሁ መረጃ ለመስጠት እነዚህን ቁጥሮች ተጠቀሙ፦

•991 ወይም 816 ነፃ የስልክ መስመሮች
•01- 11 -11- 01 -11፣
•01- 11- 26- 43- 59፣
•01- 11- 01- 02- 97፣

Addis Abeba Police Commission
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ዐዴፓ

በትግራይ ክልል ዐሲምባ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ዐዴፓ) የሚባል አዲስ የፖለቲካ ድርጅት ተመስርቷል፡፡ የፓርቲው ዋና ማኅበራዊ መሠረት ኢሮብ ብሄረሰብ መሆኑ ተገልጧል፡፡ በኢትዮ-ኤርትራ ድንበር አካባቢ ነዋሪ ለሆኑ ሕዝቦች ጥቅም ለመታገል ነው የተቋቋመው፡፡ የፓርቲው ሊቀመንበር ዶ/ር ዶሪ አስገዶም እንዳሉት ፓርቲያቸው የአልጀርሱን ስምምነት እንደሚቃወም ለጀርመን ድምጽ ራዲዮ ገልጸዋል፡፡ ድንበሩ ከተካለለ፣ አብዛኛው የኢሮብ ወረዳ ለኤርትራ ሊካለል እንደሚችል ይጠበቃል፡፡

Via DW/wazema
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ASOSA|በአሶሳ ከተማና አካባቢው የመብራት አገልግሎት የተቋረጠው በመንዲና ነጆ መካከል ሁለት የመስመር ማስተላለፊያ ተሸካሚ ምሰሶዎች በመውደቃቸው መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡ የወደቁ የመስመር ማስተላለፊያ ተሸካሚ ምሰሶዎችን መልሶ ገንብቶ በአጭር ጊዜ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል እየተሰራ መሆኑም ተገልጿል። በአሶሳና አካባቢዋ ከመስከረም 17 ጀምሮ የመብራት አገልግሎት እንደተቋረጠ ነው።

Via #BGRS
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን የመገናኛ ብዙኃንን አስጠነቀቀ!

የዘገባ የይዘት ምንጭን ከአንድ ወገን ብቻ በማድረግና የዘገባ ትክክለኝነትን በመጣስ በሕዝቦች መካከል የእርስ በርስ ግጭት በመቀስቀስ ላይ የተጠመዱ የንግድና የመንግሥት የመገናኛ ብዙኃን ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጠን አሳሰበ፡፡

ባለስልጣኑ እነዚህን ተቋማት ከመደገፍና ከማስተማር ባለፈ የይዘት ትንተና ውጤትን መሠረት በማድረግ እስከ መዝጋት የሚደርስ እርምጃ እንደሚወስድም አስጠንቅቋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-04

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbeba

በአዲስ አበባ ወጣቶች ፌደሬሽን አስተባባሪነት #ነገ መስከረም 24 በአዲስ አበባ ከተማ የሚከበረውን የእሬቻ በዓል ምክንያት በማድረግ ከከተማዋ የተለያዩ ክፍሎች የተሰባሰቡ ወጣቶች መስቀል አደባባይ እና አካባቢውን አፅድተዋል፡፡

ከ3 ሺህ በላይ ወጣቶች የተሳተፉበት የፅዳት ዘመቻ በዛሬው ዕለት ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ የተካሄደ ሲሆን በነገው ዕለትም በዓሉ ከተከበረ በኋላ ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ የፅዳት ዘመቻው ይካሄዳል ተብሏል፡፡

የፅዳት ዘመቻው ከ10ሩም ክፍለ ከተሞች ከሚገኙ የወጣት ፌደሬሽን አመራሮች ጋር በመሆን የአዲስ አበባ ወጣቶች ፌደሬሽን እያስተባበረው ይገኛል፡፡

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በ5ኛው ዓመት የTIKVHA-ETH የመፅሃፍት ማሰባሰብ ዘመቻ ከአ/አ እና ዙሪያዋ ብቻ ከ700 በላይ መፅሃፍ ተሰብስቧል!

በቅን-ድል ኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት ማህበር አስተባባሪነት ከነሀሴ 20 ጀምሮ ሲካሄድ የቆየው 5ተኛው ዙር የTIKVAH-ETH የመፅሐፍ ማሰባሰብ ዘመቻ የመጀመሪያው ምዕራፍ ከ700 በላይ መፅሐፍቶችን መስከረም 10 ቀን 2012 ለሰበታ ቤተ-መፅሐፍት ቤት በመለገስ ተጠናቋል፡፡

ልዩ ምስጋና፦ ለአዱስ አበባ ከተማና ዙሪያዋ ላሉ ነዋሪዎች፣ ተማሪዎች ወጣቶች በሙሉ!

በዚህ መልካም ስራ ላገዛችሁን:-

•ሰበታ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ
•የሰበታ ከተማ አስተዳደር
•የሰበታ ቤተ-መፅሐፍት ቤት ሰራተኞች
•ዮናስ ገ/መስቀል
•አብደላ ሁሴን ....ከካራ
•አልምብርሃን በለጠ ....ከላፍቶ
ቅን-ድል ኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት ማህበር አባላት እና ሁላችሁም በዚህ መልካም ስራ ላይ የበኩላችሁን አስተዋጽኦ ላደረጋችሁ መልካምነት መልሶ ይክፈላችሁ፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia