TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
"ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ!" በሚል መሪ ሀሳብ 18 ዓመታትን በስኬት የተጓዘው ታላቁ ሩጫ በቅርቡ አለማቀፍ እውቅና ማግኘቱ የሚታወስ ሲሆን ዘንድሮም ህዳር 7 "ሴቶች ልጆች በእኩል ሚዛን መታየት መደመጥ እና ተቀባይነት ሊኖራቸው ይገባል" በሚል መሪ ቃል ይካሄዳል፡፡ በዚህ ታላቅ ሩጫ የሚገኘው ገቢ በተለያዩ አከባቢዎች ላሉ ማህበረሰቦች ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት እንደሚውል አዘጋጆቹ ያስታወቁ ሲሆን በእንግድነት የተገኙት የትምህርት ሚኒስትር ሚኒስተር ዴኤታ ወ/ሮ ጽዮን ተክሉ ታላቁ ሩጫ ሊገነባው ላሰበው ትምህርት ቤቶች ምስጋናቸውን አቅርበው የዘንድሮ መሪ ቃሉን ለአንድ ቀን ብቻ ሳይሆን አመቱን በሙሉ በልባችን ይዘን መንቀሳቀስ ይጠበቅብናል የሚል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-03-2

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ወንጀል ውርስ አይደለም በጋብቻ መተሳሰራቸው ብቻ እንዴት በሽብር ያስጠይቃቸዋል?" የወ/ሮ ደስታ (የብ/ጀ አሳምነው ጽጌ ባለቤት) ጠበቃ ዛሬ የተናገሩት!
.
.
"ፃፈ የተባለው #opinion ነው እሱ ደግሞ ወንጀል ሊሆን አይችልም የኤልያስን አስተሳሰብ ፖሊስ ጠላው ማለት ወንጀል ነው ማለት አይደለም" የኤልያስ ገብሩ ጠበቃ!
.
.
ዛሬ በችሎት በሽብር ወንጀል የተጠረጠሩት እነ ኤልያስ ገብሩ የቀረቡ ሲሆን ፖሊስ የሰራቸውን የምርመራ ስራዎች ለዳኛው ገልፆ ለቀሪ ምርመራዎች ተጨማሪ 28 ቀናት እንዲሰጠው ጠይቋል። ወ/ሮ ደስታን በተመለከተ በባንክ ገንዘብ ማግኘቱን፣ በእናታቸው ስም የተገዛ መኪና መገኘቱን፣ የጦር መሳርያ በቤታቸው መገኘቱን ገልፅዋል። ወንጀል ውርስ አይደለም ያሉት ጠበቃቸው ተጠርጣሪዋ 18 አመት ውጪ ሰርተው ነው የመጡት ንብረት ማፍራት እንዴት ሽብርን ያቋቁማል የጦር መሳርያውም ባለቤታቸው የመንግስት ባለስልጣን በመሆናቸው ቤታቸው የተቀመጠ ነው ብለዋል።

Via Samrawit
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን በአዲስ አበበ ከተማ መስከረም 24 ቀን እና በቢሾፍቱ ከተማ መስከረም 25 ቀን 2012 ዓ/ም የሚከበረውን የኢሬቻ በዓል ለማደናቀፍ ወደ አዲስ አበባ ሊገቡ ነበር ያላቸውን ቦምቦች ጭምሮ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች ከዘጠኝ ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታወቀ።

Ethiopian Federal Police Commission

@tsegabwolde @tikvahethiopia
⬆️ወደ አዲስ አበባ ከተማ ሊገቡ ሲሉ በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የተያዙት ቦንቦች! #AddisAbeba #ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የተሰጠ መግለጫ!

መስከረም 24 እና 25 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ እና በቢሾፍቱ ከተሞች የሚከበረውን የኢሬቻ በዓል አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የተሰጠ መግለጫ፦
👉https://telegra.ph/ETH-10-03-4

መስከረም 22 ቀን 2012 ዓ.ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Feyisa Lilesa 

አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ በ2016 በሪዮ ኦሎምፒክ ያገኘውን ሜዳሊያ በኢትዮጵያ ለውጥ ለማምጣት ለተሰዉ ሰማዓታት መታሰቢያነት እሰጣለሁ ባለው መሰረት ዛሬ በሚሊኒየም አዳራሽ የርክክብ ስነ ስርዓት ተካሒዷል፡፡ አትሌቱ በገባው ቃል መሰረት በሪዮ ኦሎምፒክ ያገኘውን ሜዳሊያውን ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ አስረክበዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-03-3

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በመስከረም ወር የተመዘገበው አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነጻጸር በ18 ነጥብ 6 ከመቶ ከፍ ብሏል። የምግብ ዋጋ ግሽበት የመስከረም ወር 2012 ዓ.ም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነፃፀር በ23 ነጥብ 3 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
•በጤፍ፣
•በገብስ፣
•በማሽላ፣
•በቆሎና
•የስንዴ ዱቄት ዋጋ ጭማሪው እንደቀጠለ ቢሆንም የአጨማመሩ ፍጥነት ግን ካለፉት ወራት ያነሰ መሆኑን የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ አመልክቷል።

ከዚህ በተጨማሪም በየቀኑ ለምግብነት ተፈላጊ የሆኑት አንዳንድ የአትክልት ዓይነቶች በተለይም ቲማቲም፣ ቀይ ሽንኩርትና ነጭ ሽንኩርት በአንድ ወር ውስጥ ጭማሪ በማሳየታቸው የዋጋ ግሽበት ከፍ እንዲል አስተዋፅኦ አድርጓል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሌላ በኩል...

ምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጦች የዋጋ ግሽበት የመስከረም ወር 2012 ዓ.ም ካለፈው ዓመት መስከረም ወር 2011 ዓ.ም ጋር ሲነፃፀርም የ13 ነጥብ 1 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

ካለፉት ጥቂት ወራት ጀምሮ ምግብ ነክ ያልሆኑ የሸቀጦች የዋጋ ግሽበት በተከታታይ ጭማሪ እያሳየ መሆኑን ተጠቁሟል።

ግሽበቱ ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከፍ እንዲል ያደረገው በተለይ ልብስና መጫሚያ፣ የቤት ኪራይ፣ የቤት እንክብካቤና ኢነርጂ (ማገዶና ከሰል)፣ የቤት ዕቃዎችና የቤት ማስጌጫዎች፣ የቤት መስሪያ ዕቃዎች፣ ህክምናና ትራንስፖርት (በተለይ የቤት መኪና) ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ እንደሆነ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ አመልክቷል።

Via ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሁሉም ውስጡ #ስጋና #ደም
ቀለም መልኩ ቢለያይም
ወላጁ #አንድ ነው አባቱ አንድ ነው
ዞሮ ዞሮ #አዳም
.
.
ሰውነት ይከበር!
ሰውነት ይቅደም!
#ETHOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢሬቻ2012

በኢሬቻ በዓል ወቅት የሚከናወኑ የባዕድ አምልኮዎች የኦሮሞን ባህል የማይወክሉ በመሆናቸው ሊቆሙ እንደሚገባ የአባገዳዎች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ጫላ ሶሪ ተናገሩ፡፡ የኢሬቻን በዓል በማስመልከት አፈ ጉባኤው በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ የኢሬቻ በዓል ሲከበር ባዕድ አምልኮ የሚመስሉ ኦሮሞ የማይፈፅማቸው ነገሮች ይከናወናሉ፡፡ በተለይ የኢሬቻበዓል ሲቃረብ በግ በማረድ ጭንቅላቱን ውሃ ውስጥ መጣል፣ ጥቁር ዶሮዎችን እራስ ላይ በማዞር ውሃ ውስጥ መክተት፣ አረቄና ውስኪ ውሃ ውስጥ መጣል እና ሽቶ ማርከፍከፍ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ እነዚህ ድርጊቶች ደግሞ የኢሬቻን በዓል ስለማይወክሉ ሊቆሙ ይገባል፡፡ ‹‹በእነዚህ ነገሮች ኦሮሞ ፈጣሪውን አይለምንም፤ ምስጋናም አያቀርብም›› የሚሉት አቶ ጫላ፣ እነዚህ ነገሮች ሰው ሰራሽ በመሆናቸው ምክንያት አይለመንባቸውም፤ ምስጋናም አይቀርብባቸውም ብለዋል፡፡

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማስታወሻ፦ የሚዘጉ መንገዶች!

በመስቀል አደባባይ የሚከናወኑ ልዩ ልዩ ስነ-ሥርአቶች ተጀምረው እስከሚጠናቀቁ ድረስ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ከበዓሉ ዋዜማ ጀምሮ፦


ጎተራ ሼል ዴፖ ፣ ጎፋ ማዞሪያ ፣ ቄራ 6 ቁጥር ማዞሪያ ፣ ሳር ቤቶች ፣ ካርል አደባባይ ፣ ጦር ኃይሎች አደባባይ ፣ ኮካኮላ ድልድይ ፣ ልደታ ከፍተኛ ፍ/ቤት ፣ ልደታ ፀበል ፣ አብነት አደባባይ ፣ ሞላ ማሩ መገንጠያ ፣ በርበሬ በረንዳ ፣ ተክለ ሃይማኖት ፣ ቴዎድሮስ አደባባይ ፣ ንግድ ማተሚያ ቤት ፣ አሮጌው ቄራ ፣ ባሻወልዴ ፣ፓርላማ መብራት ፣ ጥይት ቤት ፣ ጀርመን አደባባይ ፣ ሲግናል፣ እንግሊዝ ኤምባሲ መገንጠያ ፣ ለም ሆቴል ፣ ሾላ ገበያ መብራት ፣ ጎርጎሪዮስ አደባባይ ፣ መስቀል ፍላወር ፣ መገናኛ ላይና ታች ፣ ኤድናሞል አደባባይ ፣ ሰንሻይን መገንጠያ ፣ ቦሌ ቀለበት እና ቦሌ ሚካኤል ወደ ዝግጅቱ ስፍራ የሚወስዱ መንገዶች ለጊዜው ለተሽከርካሪ ዝግ ናቸው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትም ሆነ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥማችሁ መረጃ ለመስጠት እነዚህን ቁጥሮች ተጠቀሙ፦

•991 ወይም 816 ነፃ የስልክ መስመሮች
•01- 11 -11- 01 -11፣
•01- 11- 26- 43- 59፣
•01- 11- 01- 02- 97፣

Addis Abeba Police Commission
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ዐዴፓ

በትግራይ ክልል ዐሲምባ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ዐዴፓ) የሚባል አዲስ የፖለቲካ ድርጅት ተመስርቷል፡፡ የፓርቲው ዋና ማኅበራዊ መሠረት ኢሮብ ብሄረሰብ መሆኑ ተገልጧል፡፡ በኢትዮ-ኤርትራ ድንበር አካባቢ ነዋሪ ለሆኑ ሕዝቦች ጥቅም ለመታገል ነው የተቋቋመው፡፡ የፓርቲው ሊቀመንበር ዶ/ር ዶሪ አስገዶም እንዳሉት ፓርቲያቸው የአልጀርሱን ስምምነት እንደሚቃወም ለጀርመን ድምጽ ራዲዮ ገልጸዋል፡፡ ድንበሩ ከተካለለ፣ አብዛኛው የኢሮብ ወረዳ ለኤርትራ ሊካለል እንደሚችል ይጠበቃል፡፡

Via DW/wazema
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ASOSA|በአሶሳ ከተማና አካባቢው የመብራት አገልግሎት የተቋረጠው በመንዲና ነጆ መካከል ሁለት የመስመር ማስተላለፊያ ተሸካሚ ምሰሶዎች በመውደቃቸው መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡ የወደቁ የመስመር ማስተላለፊያ ተሸካሚ ምሰሶዎችን መልሶ ገንብቶ በአጭር ጊዜ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል እየተሰራ መሆኑም ተገልጿል። በአሶሳና አካባቢዋ ከመስከረም 17 ጀምሮ የመብራት አገልግሎት እንደተቋረጠ ነው።

Via #BGRS
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን የመገናኛ ብዙኃንን አስጠነቀቀ!

የዘገባ የይዘት ምንጭን ከአንድ ወገን ብቻ በማድረግና የዘገባ ትክክለኝነትን በመጣስ በሕዝቦች መካከል የእርስ በርስ ግጭት በመቀስቀስ ላይ የተጠመዱ የንግድና የመንግሥት የመገናኛ ብዙኃን ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጠን አሳሰበ፡፡

ባለስልጣኑ እነዚህን ተቋማት ከመደገፍና ከማስተማር ባለፈ የይዘት ትንተና ውጤትን መሠረት በማድረግ እስከ መዝጋት የሚደርስ እርምጃ እንደሚወስድም አስጠንቅቋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-04

@tsegabwolde @tikvahethiopia