TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#BREAKING

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በ24 ክለቦች ከጥቅምት ወር መጨረሻ ጀምሮ መደረግ ይጀምራል፡፡

•መከላከያ፣ ደቡብ ፓሊስ እና ደደቢት ተመልሰዋል፡፡

•አርባምንጭ ለገጣፎ እና መድን በከፍተኛ ሊግ ሁለተኛ ሆነው በመጨረሳቸው ወደ ፕሪሚየር ሊጉ አድገዋል።

•ሀድያ ሆሳዕና፣ ወልቂጤ እና ሰበታ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ማደጋቸው ይታወሳል፡፡

•ምርጥ የከፍተኛ ሊግ ሶስተኛ ክለቦች ኢኮስኮ እና ነቀምት ከተማም ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ገብተዋል፡፡

•ቅዱስ ጊዮርጊስ አይቀጣም በፕሪሚየር ሊጉ ይቀጥላል፡፡

•የሸገር ደርቢም የመደረጉ ነገር #አጠራጥሯል፡፡

•የአማራ እና ትግራይ ክለቦች በአንድ ላይ አይወዳደሩም፡፡

•ሲዳማ ቡና እና ወላይታ ድቻ አይገናኙም፡፡

via ቴዎድሮስ ታከለ (Teddy Soccer)

@tikvahethiopia @tikvahethsport
#ADDISABEBA

በአዲስ አበባ የሚኒባስ ታክሲዎችን ስምሪትና ተገቢ ያልሆነ የታሪፍ ክፍያዎችን በዘመናዊ መንገድ ለመቆጣጠር ነፃ የስልክ ጥሪና የሞባይል መተግበሪያ በቅርቡ ጥቅም ላይ ሊያውል መሆኑን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ባለስልጣን አስታወቀ፡፡ አዲሱ አሰራርም በከተማዋ ያለውን የትራንስፖርት ችግር ከማቃለል ባለፈ ሚኒባስ ታክሲዎች በተገቢው መንገድ ለከተማው ህዝብ አገልግሎት መስጠታቸውን ለመከታተል እንደሚረዳ የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ በድሉ ሌሊሳ በተለይ ለኢቲቪ ተናግረዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከETHIO-TELECOM TPO BRANCH⬆️

"ዛሬ ጳጉሜ 6 ፍሬ ”ethiotelecom TPO Branch” ቸርችር ጉዳና ከሊሴ ጉን ያለውን ብራንች ጎብኝታለች!" Dagim/TIKVAH-ETH/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ADDISABEBA የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን የአዲስ ዓመት በዓልን አስመልከቶ ደንበኞቼ የውሃ ችግር እንዳያጋጥማቸው እየሰራሁ ነው ብሏል፡፡ የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን በአሉን ተከትሎም ከጷጉሜ አንድ እስከ መስከረም አምስት የሚቆይ በማዕከል እና በስምንቱም ቅ/ጽ/ቤቶች ጊዜያዊ ኮሚቴ በማቋቋም እስከ ምሽቱ አምስት ሰዓት ድረስ እየሰራ ነው፡፡

የውሃ እጥረቱን ለመቀነስም ከለገዳዲ እና ገፈርሳ ግድቦች ከዚህ በፊት በሚያመርቱት ላይ በቀን 10 ሺህ ሜ.ኩ እንዲሁም በስድስት ቅ/ጽ/ቤቶች ሰር ከሚገኙ 31 ጉድጓዶች አጠቃላይ በቀን 4 ሺህ ሜ.ኩብ ተጨማሪ ውሃ እየተመረተ ይገኛል፡፡ ከዚህም በተጓዳኝ የኤሌትሪክ ሀይል መቆራረጥ ሲያጋጥም የጀኔረተር ቡድን በየቀኑ በሦስትና አራት ጣቢያዎች ላይ ነዳጅ ከመደበኛው እንቅስቃሴ በተለየ መልኩ በቀን እስከ አምስት ሺህ ሊትር እየተሞላ ነው፡፡

የከፋ ችግር ባለባቸው አካባቢ ውሃን ለማድረስ የባለሥልጣኑ 24 የውሃ ቦቲ ሁሉም ዝግጁ ሆነው እየተጠባበቁ ሲሆን ከእነዚህ አራቱ እየተዘዋዎሩ ችግር ያለባቸውን ቦታዎች በመለየት አፋጣኝ መልስ ለመስጠት የሚያስችል እንቅስቃሴ እያደረጉ እንደሚገኝ ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ #ዝናሽ_ታያቸው በግንባታ ላይ የሚገኘውን የቁስቋም የህፃናት ክብካቤ ማዕከል ጎበኙ፡፡ ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው በዛሬው ዕለት የቁስቋም የህፃናት ክብካቤ ማዕከል የግንባታ ሂደት የደረሰበትን ደረጃ ጎብኝተዋል፡፡ ማዕከሉ ግንባታ ሲጠናቀቅ ለወ/ሮ ዘውዴ የህፃናት ክብካቤ ማዕከል ተላልፎ እንደሚሰጥም ነው ከቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት የተገኝ መረጃ ያመላክታል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ዋቸሞ_ዩኒቨርሲቲ

የአዲስ ተማሪዎች መግቢያ ቀን ማስተካከያ⬆️

"በምትመለከቱት ማስታወቂያ ላይ ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች ጥቅምት 28 እና 29 የሚለው የፅሁፍ #ስህተት ስለሆነ መስከረም 28 እና 29 ተብሎ ይስተካከል። በተጨማሪም አዲስ በዱራሜ ካምፓስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመመዝገቢያ ቀን ጥቅምት 5 እና 6 መሆኑን እንገልፃለን።" ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ

#share #ሼር

የዩኒቨርሲቲ ጉዳዮችን በስፋት በTIKVAH-MAGAZINE ታገኛላችሁ👇
https://yangx.top/joinchat/AAAAAEcez-UrldBjOpa-qQ
የኦሮሚያ አባ ገዳዎች ህብረት የ2012 የኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ የእርቅ ሳምንት አውጇል!

የኦሮሚያ አባ ገዳዎች ህብረት የ2012 የኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ የእርቅ ሳምንት አወጀ። የእርቅ ሳምንቱ ከመስከረም 9 እስከ መስከረም 22 2012 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ መሆኑንም የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታውቋል።

የእርቅ ሳምንቱ የታወጀው በ2012 ዓ.ም መስከረም 24 እና 25 በተከታታይ በአዲስ አበባ ሆራ ፊንፊኔ እና በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዴ የሚከበሩ የኢሬቻ በዓላትን ምክንያት በማድረግ እንደሆነም ተገልጿል። አባ ገዳ ጎበና ሆላ እንዳስታወቁት፥ የእርቅ ሳምንቱ የታወጀው ሰማይና ምድሩን በማስታረቅ በሰላምና በፍቅር የኢሬቻ በዓልን ለማክበር ነው። የ2012 አዲስ ዓመትም የሰላምና አደስታ እንዲሆንም የኦሮሞ አባ ገዳዎች ምኞታቸውን ገልፀዋል።

የኦሮሞ ህዝብ የምስጋና ቀን የሆነው ኢሬቻ በዓል በተለያዩ የኦሮሚያ ክፍሎች በዓመት ሁለት ጊዜ ይከበራል። የመጀመሪያው የክረምት መውጣትን ተከትሎ በውሃማ አካባቢዎች የሚከበር ሲሆን፥ ሁለተኛው ደግሞ በበልግ ወቅት በተራራማ አካባቢዎች ይከበራል። ተቋርጦ የነበረውን “የሆራ ፊንፊኔ” ኢሬቻ በዓልንም በአዲስ አበባ ለማክበር አስፈላጊው ቅደመ ዝግጅት መጠናቀቁን የኦሮሚያ አባ ገዳዎች ህብረትና የኦሮሚያ ቱሪዝም ቢሮ በጋራ በሰጡት መግለጫ ማስታወቃቸው ይታወሳል።

ምንጭ፡-FBC
@tikvahethiopia @tsegabwolde
አዲሱ ዓመት 2012 ዓ.ም በሀገራችን በሁለንተናዊ መልኩ ስኬትን የምናስመዘግብበት እንዲሆን የኃይማኖት አባቶቹ ልባዊ ምኞታቸውን ገለጹ።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-11
ተጠንቀቁ!

የአዲሱን ዓመት በዓል አስታከው ከዚህ ቀደምም እየተደረገ እንዳለው አንዳንድ አጭበርባሪዎች "ከተለያዩ ሚዲያዎች ነው የምንደውለው፤ የበዓል ስጦት ደርሶታል ገንዘብ ይላኩ" እያሉ በርካቶች ጋር እየደወሉ ይገኛል ስለሆነም ጥንቃቄ አድርጉ። በተለይም ከፋና ነው የምንደውለው ነው የሚሉት!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወርቁ ተገኝቷል⬆️

“ዶሮው ከጆሮዬ ላይ በጥሶ የዋጠውን ወርቅ ቤት ገብቼ እንዳረድኩት አግኝቼዋለው” - ወይዘሮ ሃጫልቱ

የኢዜአ በትናንትናው ዕለት ይዞት በወጣው ልዩ ዘገባ ለሽያጭ ገበያ የወጣው ዶሮ 1 ነጥብ 75 ግራም የሚመዝን ወርቅ ከጆሮ ላይ በጥሶ እንደዋጠ ማስነበቡ ይታወሳል፡፡ " ከገበያ መልስ ቤት እንደደረስኩኝ ባለቤቴን ጠርቼ ዶሮውን ወዲያው እንዳረደው የጆሮ ጌጥ ወርቄን በዶሮው አንጀት ውስጥ አግኝቼዋለው " ስትልም የወርቋ ባለቤት ወይዘሮ ሃጫልቱ ለኦቢኤን ተናግራለች፡፡ ወርቁን ባለቤቷ ለሠርጋቸው ጥሎሽ እንደሰጣትም አክላላች ወይዘሮ ሃጫልቱ፡ የታረደውንም ዶሮ በመብላት እልሄን ተወጥቻለው ስትልም የወርቋ ባለቤት ተናግራለች፡፡

Via #OBN/ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FakeNews በጅማ ከተማ አንድ አባት ታርደው ወንዝ ዳር ተጥለው ተገኙ ተብሎ በፌስቡክ እና በቴሌግራም የሚሰራጨው መረጃ #ከእውነት_የራቀ ነው። ይህንን ያረጋገጡልንም የጅማ ከተማ ነዋሪ የሆኑ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ናቸው።

ሼር የምታደርጉትን መረጃ በቅድሚያ አጣሩ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NEW

ጅማ ዩኒቨርሲቲ -- የተማሪዎች መግቢያ ቀን ይፋ ተደርጓል!

የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀናትን እና ሌሎች መረጃዎችን በTIKVAH-MAGAZINE ታገኛላችሁ👇
https://yangx.top/joinchat/AAAAAEcez-UrldBjOpa-qQ
@tikvahethmagazine
ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተላለፈ መልዕክት!

ለጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ፦

#የጎንደር_ዩኒቨርሲቲ እንኳን ለ2012 የትምህርት ዘመን በሰላም አደረሳችሁ እያለ የ2012 የትምህርት ዘመን መግቢያ ጊዜ በዮኒቨርሲቲያችን ሬዲዮና ቴሌቪዥን ፕሮግራሞች፣ በፌስቡክ እና ሊንክድኢን ገጾቻችን በቅርቡ የምናሳውቃችሁ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የጎንደር ዩኒቨርስቲ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከፍተኛ ጥንቃቄ አድርጉ!

በአርባ ምንጭ ከተማ ቅቤን ከባዕድ ነገር ጋር ቀላቅለው ሲሸጡ የነበሩ ግለሰቦች ተያዙ፡፡ በጫንጮ ከተማም 456 ኪሎ ግራም ቅቤ ከባዕድ ነገር ጋር ቀላቅለው ለገበያ ሊያቀርቡ የነበሩ ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል። የአርባ ምንጭ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ዳንኤል አረጋ ለኢዜአ እንዳሉት ቅቤን ከባዕድ ነገር ጋር ቀላቅለው ሲሸጡ ነበሩ ሁለት ግለሰቦች የተያዙት በትናንትናው ዕለት ነው፡፡ ግለሰቦቹ የተያዙት በዓሉን ምክንያት በማድረግ የከተማው ፖሊስ ለነዋሪው አስቀድሞ በፈጠረው ግንዛቤ መሰረት ከነዋሪዎች ለፖሊስ በደረሰ ጥቆማ ነው። “ፖሊስ በአሁኑ ወቅት በግለሰቦቹ ላይ ምርመራ የጀመረ ሲሆን ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ ይደጋል” ብለዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-11-3

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሀገር መከላከያ ሠራዊት በኢትዮጵያና በአፍሪካ ቀንድ አስተማማኝ ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን በአገር መከላከያ ሚኒስቴር የሰላም ማስከበር ማዕከል ኃላፊ ሜጀር ጀነራል ድሪባ መኮንን ተናገሩ። ሜጀር ጄነራል ድሪባ ይህን ያሉት በሰላም  ማስከበር ማዕከል ሁርሶ የተጠባባቂ ኃይል ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት በሰላም ማስከበር ተልዕኮ ለዘጠነኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን የሠራዊት አባላት ባስመረቀበት ወቅት ነው፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የ10,000,000 ብር ባለዕድለኛ ማን ይሆን??

እንቁጣጣሽ ሎተሪ በዛሬው ዕለት /ጳጉሜ 6/ ይወጣል።/የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር/

ከሰዓታት በኃላ!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መከላከያ ሰራዊት የIS አባላትን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል!

የኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ሰሞኑን የተወሰኑ የአይኤስ አባላትን በቁጥጥር ስር ማዋሉንና ያልተያዙትም በጥብቅ ክትትል ውስጥ መሆናቸውን የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹምና የዘመቻ መምሪያ ኃላፊ ጀነራል ብርሀኑ ጁላ አስታወቁ፡፡

ሰራዊቱ በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት ሀገርና ሕዝብን ከአደጋ ለመጠበቅ እየሰራ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡ ጀነራሉ እንዳስታወቁት፤ አይ ኤስ ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች ለመንቀሳቀስ በተደጋጋሚ ጥረት አድርጎ ቢመክንበትም በአገሪቱ ከተለያዩ አካባቢዎች የመለመላቸው፣ ስልጠና የወሰዱና የተጠመቁ ሰዎች እንዳሉ መንግስት በሚገባ እንደሚያውቅ ተናግረዋል፡፡

‹‹በአሁኑ ወቅት የአይኤስ አባላት ምን እያደረጉ እንዳሉ፣ የት የት ቦታ በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኙ፣ ከእነማን ጋር ግንኙነት እንዳላቸው፣ በከተሞች ውስጥ ያሉት ሰዎቻቸው እነማን እንደሆኑ፣ ምን እየሰሩ እንዳሉ፣ እቅዳቸው ምን እንደሆነና ሌሎች መግለጽ የማያስፈልጉ ጉዳዮችም እጅግ ከፍተኛ ክትትል እየተደረገባቸው ነው››ብለዋል ጀነራሉ፡፡

‹‹ሀገራችንንና ሕዝባችንን ከየትኛውም አደጋ ለመጠበቅና ለመከላከል ባለብን አደራና ከባድ ኃላፊነት የተነሳ ቀን ከሌት አንተኛም›› ያሉት ምክትል ጠቅላይ ኢታማጆሩ፤ ‹‹ሰራዊቱ እረፍት የሚባል ነገር አያውቅም፤ ያረፍንበት ጊዜም የለም›› ሲሉ አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡

እንደ ጀነራሉ ማብራሪያ፤ አንዳንድ ጊዜ የሆነ ሰው እንደተገኘ ሄዶ መያዝና መቆጣጠር ተገቢ አይደለም፤ ምክንያቱም ለአንድ ሰው ተብሎ ብዙ ነገር እንዳይታጣና እንዳያመልጥ በማድረግ በጥንቃቄና በሕግ አግባብ መቆጣጠር ስለሚቻል ሁኔታው አስቸጋሪ አይሆንም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-11-2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከአሁን በኃላ ግን ዝም አንልም...

የጦር ኃይሎች ም/ኢ/ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላ፦

"የመከላከያ ሰራዊታችን እኩሪ ታሪክ ያለው ሰራዊት ነው። በህገ መንግስት ዙሪያ የተገነባ ነው። ከራስ በፊት ለህዝብ የሚል ነው። ከሀገሪቱ ዜጎች የተሻለ የማይከፈለው ነው። ራሱን አሳልፎ ለህዝብ የሰጠ ነው። ችግር መፍታት የሚችል ሰራዊት ነው። ሌሎች መፍታት ያቃታቸውን ችግሮች መፍታት የሚችል ነው። feedback ማግኘት አለበት። feedback ማለት ሰራዊታችን ገንዘብ ስጡኝ፤ ቁርበት አንጥፉልኝ አይልም። ክብሩ ግን መጠበቅ አለበት። መመስገን አለበት! ከተመሰገነ ይበቃዋል። ህዝቡ በሰራዊቱ "አመሰግናለሁ" ካለ የሰራዊታችን የሞራል ምንጭ እሱ ነው። "አንዲት ኢትዮጵያ" እያለ የሚዘምረው ከኛ በላይ የሚዘምረው፤ እኛማ ጦር ሜዳ ውለን ህይወታችንን ሰጥተን፤ ተቷክሰን፣ አሸንፈን ጓዶች ገብረን ፣ ሀገር ጠብቀን፣ እዚህ አድርሰናል። ለዚህች ሀገር ጠጠር ያልወረወረ መሸታ ቤት የሚውል እየወጣ ሰራዊቱን እያብጠለጠለ ነው። የዴሞክራሲ ምህዳር ይስፋ ስለተባለ እያብጠለጠለን ዝም ብለናል። ከአሁን በኃላ ግን ዝም አንልም።"

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia

የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር፦

1662862 --የ1ኛ የአሸናፊ እጣ ቁጥር ሆኗል
0022646--2ኛ እጣ ቁጥር ሆኗል
1231149--የ3ኛ አሸናፊ እጣ ቁጥር ሆኗል
0018527--የ4ኛ የአሸናፊ እጣ ቁጥር ሆኗል
1703425--የ6ኛ የአሸናፊ እጣ ቁጥር ሆኗል

ባለዕድለኞች እንኳን ደስ አላችሁ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
እንቁጣጣሽ ሎተሪ ወጣ!

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው እንቁጣጣሽ ሎተሪ ጳጉሜን 06/2011 ዓ.ም በብሔራዊ ሎተሪ ዕድል አዳራሽ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ላይ በህዝብ ፊት ወጥቷል፡፡ በዚህም መሰረት የወጡት የአሸናፊ ዕጣ ቁጥሮች እንደሚከተሉት ሆነዋል፡፡

1ኛ. 10,000,000 ብር የሚያስገኘው የ1ኛ ዕጣ ቁጥር-----1662862

2ኛ. 5,000,000 ብር የሚያስገኘው የ2ኛ ዕጣ ቁጥር------0022646

3ኛ. 2,500,000 ብር የሚያስገኘው የ3ኛ ዕጣ ቁጥር ----1231149

4ኛ. 1,500,000 ብር የሚያስገኘው የ4ኛ ዕጣ ቁጥር ----0018527

5ኛ. 1,000,000 ብር የሚያስገኘው የ5ኛ ዕጣ ቁጥር -----1774633

6ኛ. 500,000 ብር የሚያስገኘው የ6ኛ ዕጣ ቁጥር ------1703425

7ኛ. 20 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 20,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር ------- 36808

8ኛ. 20 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 10,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር-------- 89196

9ኛ. 200 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 5,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር--------7889

10ኛ. 200 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 1,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር-------3883

11ኛ. 2,000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 500 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር-------788

12ኛ. 2,000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 250 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር-- ----657

13ኛ. 20,000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 100 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር-----52

14ኛ. 20,000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 50 የሚያስገኘው (የማስተዛዘኛ) ዕጣ ቁጥር----1 በመሆን ወጥቷል፡፡

#ሼር #share
@tsegabwolde @tikvahethiopia