TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.52K videos
215 files
4.13K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
ወንጀል ነክ መረጃ‼️

ከባድ የአካል ጉዳት ያደረሰዉ #ተከሳሽ በእስራት ተቀጣ፡፡ ተከሳሽ #ሳሙኤል_ጎችል_ወልደመስቀል በ1996 ዓ.ም የወጣዉን የኢፌዴሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 555/ለ ስር የተመለከተዉን ድንጋጌ ተላልፎ በፈፀመዉ ከባድ የአካል ጉዳት ማድረስ ወንጀል ተከሷል፡፡

ተከሳሽ በሌላ ሰዉ አካል ላይ ጉዳት ለማድረስ በማሰብ ሰኔ 2 ቀን 2010 ዓ.ም በግምት ከምሽቱ 12፤30 ሲሆን በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ቦታዉ በግ ተራ ተብሎ ከሚጠራዉ አካባቢ የግል ተበዳይ አብርሀም ታፈረን በቦክስ በመምታት የላይኛዉ የፊት ለፊት አራት ጥርሶቹ እንዲወልቁ ያደረገ በመሆኑ በፈፀመዉ ከባድ የአካል ጉዳት ማድረስ ወንጀል ነዉ፡፡

ተከሳሽ ከላይ በክስ ዝርዝሩ አደረክ የተባልኩትን ድርጊት አልፈፀምኩም ሲል የእምነት ክህደት ቃሉን ቢሰጥም ዐቃቢ ህግ 4 የሰዉ ምስክሮችንና የሰነድ የማስረጃዎቹን አጠናቅሮ ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል፡፡

መዝገቡን የተመለከተዉ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የየካ ምድብ የወንጀል ችሎትም ተከሳሽ ጥፋተኛ ነዉ ሲል ታህሳስ 08 ቀን 2011 ዓ.ም በዋለዉ 3ተኛ ወንጀል ችሎት በቅጣት ዉሳኔው ተከሳሽን ያርማል ሌሎችንም ያስተምራል በማለት በ2 አመት ከ9 ወር እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡

ምንጭ፦ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UpdateSport የ20 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ #ሳሙኤል_ተፈራ በበርሚንግሐም የ1500 ሜትር የቤት ውስጥ የሩጫ ውድድር የዓለም ክብረ-ወሰን አሻሻለ። ሳሙኤል ውድድሩን በ3 ደቂቃ ከ31 ሰከንድ ከ04 ማይክሮ ሰከንድ ጨርሷል። ላለፉት 22 አመታት አይነኬ ሆኖ የቆየው እና በሞሮኳዊው ሒሻም ኤል ጎሩዥ ተይዞ የነበረው ክብረ-ወሰን 3 ደቂቃ ከ31 ሰከንድ ከ18 ማይክሮሰከንድ ነበር። ባለፈው ሳምንት ክብረ-ወሰኑን ለማሻሻል 0.01 ሰከንድ ብቻ ሲቀረው ውድድሩን ያጠናቀቀው ሌላው ኢትዮጵያዊ ዮሚፍ ቀጀልቻ ሁለተኛ ሆኖ አጠናቋል። ዮሚፍ በዚህ ውድድር የዓለም ክብረ-ወሰንን የማሻሻል ዕቅድ ነበረው። የአውስትራሊያው ስቴዋርት ማክስዌይን ውድድሩን በሶስተኛነት አጠናቋል። ሳሙኤል ውድድሩን ካሸነፈ በኋላ "ይኸን ማመን አልችልም። በውጤቱ ተደስቻለሁ። የዓለም ክብረ-ወሰን ባለቤት መሆን የተለየ ስሜት ይፈጥራል" ሲል ተናግሯል።

via dw
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ግሎባል ሆቴል🔝

በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም የህክምና ኮሌጅ ከአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር ለመምህራ የአእምሮ ጤና ስልጠና በግሎባል ሆቴል በመስጠት ላይ ይገኛል። ስልጠናውን የከፈቱት የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ምክትል ሀላፊ ዶክተር #ሳሙኤል_ዘመንፈስቅዱስ ናቸው።

ምንጭ፦ ዶክተር ምትኩ ጌቱ(በኢትዮጵያ የአንጎል ግንዛቤ ማስጨበጫ ሳምንት ዋና አስተባባሪና አዘጋጅ) - TIKVAH-ETH
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጥናት ሪፖርቱ ይፋ ሊደረግ ነው...

ከአካባቢ ብክለት ጋር በተያያዘ ከፍተኛ #ተቃውሞ የቀረበበት ንብረትነቱ የሚድሮክ ጎልድ የሆነው #የለገደምቢ ወርቅ ማውጫ ላይ ሲያካሂድ የነበረውን ጥናት ሪፖርት በመጪው ሳምንት ይፋ እንደሚያደርግ፣ የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የሚድሮክ ጎልድ ኩባንያ በለገደምቢ ወርቅ ለማምረት የሚጠቀምበት ኬሚካል በአካባቢውና በማኅበረሰቡ ጤና ላይ ቀውስ እንደፈጠረ በመግለጽ፣ የሻኪሶ ከተማና የአካባቢው ነዋሪዎች ከፍተኛ ተቃውሞ በማሰማታቸው የማዕድን ሚኒስቴር ጉዳዩ በገለልተኛ ወገን እስኪጣራ የኩባንያው የማዕድን ምርት ፈቃድ ከአንድ ዓመት በፊት ማገዱ ይታወሳል፡፡

ሚያዝያ 16 ቀን 2011 ዓ.ም. ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር አቶ #ሳሙኤል_ሁርቃቶ፣ በገለልተኛ ባለሙያዎች በሚድሮክ ጎልድ ኩባንያ አሠራር ላይ ሲካሄድ የነበረው ጥናት ሪፖርት #በመጪው ሳምንት ይፋ እንደሚደረግ አስታውቀዋል፡፡

የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር የአካባቢ ተፅዕኖ ጥናት ቀደም ሲል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስጠንቶ የነበረ ቢሆንም፣ ውጤቱ ለሕዝብ ይፋ ሳይደረግ ቆይቷል፡፡ ሚኒስቴሩ የሚድሮክ ጎልድን ፈቃድ #ካገደ በኋላ ከኩባንያው ኃላፊዎች፣ ከአካባቢው ኅብረተሰብ ተወካዮችና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ባዘጋጀው የምክክር መድረክ ተጨማሪ ጥናት በገለልተኛ ወገን እንዲከናወን ከስምምነት ላይ መድረሱ ይታወሳል፡፡

የካናዳ መንግሥት ለማዕድን ሚኒስቴር በሚሰጠው የድጋፍ ፕሮግራም፣ በለገደምቢ ወርቅ ማውጫ ላይ ለሚካሄደው ጥናት የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡ ጥናቱ በካናዳ ከፍተኛ ባለሙያዎች እንደተካሄደ ታውቋል፡፡ በጥናቱ ግኝት ላይ ተመርኩዞ ሚኒስቴሩ የውሳኔ ሐሳብ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል፡፡ ሚድሮክ ጎልድ ሥራው በመቋረጡ ለከፍተኛ ኪሳራ እንደተዳረገ በመግለጽ፣ ጥናቱ በአፋጣኝ እንዲሠራ ሲወተውት መቆየቱ ይታወሳል፡፡

በማዕድን ኩባንያዎችና በአካባቢ ማኅበረሰቦች ስለሚፈጠሩ ግጭቶች የተናገሩት አቶ ሳሙኤል፣ አንዳንድ ኩባንያዎች የማኅበረሰብ አቀፍ ሥራ እንደማያከናውኑ ከክልል መንግሥታት ጋርም ግንኙነት እንደሌላቸው ገልጸዋል፡፡ ‹‹ከፌዴራል መንግሥት የማዕድን ሥራ ፈቃድ የተሰጣቸው ኩባንያዎች በክልል ውስጥ ደሴት ሆነው የሚሠሩ ነበሩ፡፡ ከክልል መንግሥት ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት አያደርጉም፡፡ ክልሉም ምን እንደሚሠሩ አያውቅም፡፡ ልክ ችግር ሲፈጠር ኩባንያዎቹ የክልሉን መንግሥት ያናግራሉ፤›› ያሉት አቶ ሳሙኤል፣ ይህን አሠራር ለመለወጥ ሚኒስቴሩ በማዕድን ኩባንያዎችና በክልል መንግሥታት መካከል መልካም የሥራ ግንኙነት ለመፍጠር እየሠራ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ክልሎች የማዕድን ኩባንያዎች የሚያከናውኗቸውን ሥራዎች አውቀው አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው እየተሠራ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ በማኅበረሰብ ልማት ፕሮጀክቶች ላይ ሊነገሩ የሚገቡ መልካም ሥራዎች የሠሩ ኩባንያዎች እንዳሉም ጠቁመዋል፡፡

ሚድሮክ ጎልድ የለገደምቢ የወርቅ ማውጫን በ1989 ዓ.ም. ከፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ በጨረታ በ172 ሚሊዮን ዶላር መግዛቱ ይታወሳል፡፡ የወርቅ ማውጫው በዓመት አራት ቶን ወርቅ የማምረት አቅም አለው፡፡

ምንጭ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለ7 የማዕድን ምርመራና ለ3 የማዕድን አምራቾች ፍቃድ ተሰጠ!

የኢፌድሪ ማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር የፈቃድ መስፈርቶችን አሟልተዋል ላላቸው በማዕድን ፍለጋና ምርት ለማምረት ፈቃድ ለጠየቁ ኩባንያዎች ፈቃድ ሰጠ።

በዚህም መሰረት ዛሬ ለ7 በማዕድን ምርመራ ለተሰማሩና ሶስት ደግሞ የማዕድን ምርት ለማምረት ፍቃድ ለጠየቁ 6 ኩባንያዎች ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ፍቃድ ሰጥቷል።

ኩባንያዎቹ ለኢንቨስትመንት ወጪ በአጠቃላይ 258 ሚልዮን 500 ሺህ ብር በላይ የመደቡ ሲሆን፤ ለ281 ዜጎች የስራ ዕድል የሚፈጥሩ ይሆናሉ ተብሏል።

ኩባንያዎቹ የስራ ዕድል ከመፍጠር ባሻገርም የውጭ ምንዛሬ ያስገኛሉ ያሉት የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴሩ ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ ኩባንያዎቹ ስራቸውን የፌደራልና የክልሎችን የመዕድን አዋጆች፣ ደንቦችና መመርያዎችን መሰረት አድርገው ያከናውናሉ ብለዋል።

ዶክተር #ሳሙኤል አክለውም ኩባንያዎቹ ተግባራቸውን በጥንቃቄና ቅልጥፍና በተሞላበት ሁኔታ በማከናወን ለአካባቢ ጥበቃ ትኩረት እንዲያደርጉ ከስምምነት ተደርሷል ብለዋል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በ2012 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት እንዳይስተጓጎል ጠንካራ ሥራ ተሰርቷል!

መጪው የ2012 ዓ.ም በሀገሪቱ የተለያዩ ኩነቶች የሚከናወኑበት በመሆኑ ከዚያ ጋር ተያይዞ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ የትምህርት መስተጓጎል እንዲሁም አላስፈላጊ ሁከቶች እንዳይከሰት ጠንካራ ሥራ መሰራቱን የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ሰላማዊ እና የተረጋጋ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲኖር በተለየ ሁኔታ መዘጋጀታቸውን አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች ገልጸዋል፡፡

የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት፣ ከዚህ ቀደም የተከሰቱ ግጭቶች፣ሁከቶች እና ሞት ትልቅ ትምህርት ሰጥተው ስላለፉ ከዚህ በኋላ ተመሳሳይ ችግሮች እንዳይደገሙ ጠንካራ ሥራ ተሰርቷል፡፡ ዶክተር #ሳሙኤል እንዳሉት ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ የመማር ማስተማር ሂደቱን ሰላማዊ ያደርግልኛል ያለውን ሰነድ አዘጋጅቷል፡፡ ሰነዱ በአገሪቱ ከሚገኙ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች ጋር ውይይት የተደረገበት ሲሆን እያንዳንዱ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ኃላፊ ነት፣ መብትና ግዴታን የያዘ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia