TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ እየተሳተፉ የሚገኝበት የቶኪዮ አለም አቀፍ ኮንፈረንስ ቲካድ የመሪዎች ስብሰባ ተጀምሯል፡፡ በመክፈቻው ላይ የጃፓኑ ጠቅላይ ሚንስትር ሽንዞ አቤ ጃፓን ለአፍሪካ በጤና እና በትምህርት መሰረት ልማት እያደረገች ያለውን #ድጋፍ ትቀጥላለች ብለዋል፡፡ በአፍሪካ ልማት ዙሪያ ምክክር የሚያደርገው የቶኪዮ አለም አቀፍ ኮንፈረንስ ቲካድ አፍሪካ ከድህነትና ኃላቀርነት ለመውጣት የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ በጃፓን ጠንሳሽነትና አመራር ለአፍሪካ ልማት የሚካሄድ ኮንፈረንስ ነው፡፡

Via #EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ቢሮ ስር የሚገኘው የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ከዩኒቨርሲቲው ኢንፎርማቲክስ ኮሌጅ ጋር በመተባበር የዲጅታል ሊትሬሲ (መሰረታዊ የኮምፒዩተር እውቀትና ክህሎት) ስልጠና ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና ሙያተኞች ለ4ኛ ዙር በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡

Via Gondar University
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ ለአካባቢው ማህበረሰብ ከሁሉም የደ/ጎን/አስ/ዞን/ ሴክተር መስሪያ ቤቶች እና ከዩኒቨርስቲው ለተወጣጡ 1500(አንድ ሺህ አምስት መቶ) ሠራተኞች ከነሐሴ 17/2011 ዓ/ም ጀምሮ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀም (Digital Literacy) ሥልጠና እየሰጠ ነው፡፡ ሥልጠናው በሁለት ዙር የሚሰጥ ሲሆን በመጀመሪያው ዙር ስልጠና ከ620 በላይ ሠልጣኞች ሥልጠናውን ለ15 ቀናት በመውሰድ ላይ ናቸው፡፡

Via Debre Tabor University
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አሸንዳ2011

የአሸንዳ በዓል የፊታችን ነሃሴ 26 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ በሚሌኒየም አዳራሽ ይከበራል። ከሀገራችን በርካታ የባህል መገለጫ እሴቶች መካከል ተጠቃሽ የሆነው የአሸንዳ በዓል በሁሉም ኢትዮጵያዊያን መዲና አዲስ አበባ በልዩ ልዩ ዝግጅቶችና በድምቀትና ለማክበር የሚያስችል መርሃ-ግብር መውጣቱም የከተማ አስተዳድሩ ከንቲባ ፅሕፈት ቤት አስታውቋል። እንደ ኤፍ ቢ ሲ ዘገባ በበዓሉ ላይም የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራልና የከተማው መስተዳድር ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በእነ ጀነራል ተፈራ ማሞ መዝገብ የተጠየቀው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ይሰጠኝ ይግባኝ በባሕር ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውድቅ ተደርጓል፡፡ ዐቃቤ ህግ በአራት እና አምስት ጊዜ ቀጠሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ባለማቅረቡ ነው የተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ ይሰጠኝ ይግበኙ ውድቅ የተደረገው፡፡ ዐቃቤ ህግ ይግባኝ የማለት መብቱ የተጠበቀ መሆኑን ፍርድ ቤቱ አስታውቋል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለሀገራችን ለመስራት ምክንያት አንሻም!!

በደብረ ብርሀን ከተማ ቀበሌ 03 በተለምዶ ማዕከል ተብሎ በሚጠራው የከተማው መንገድ ያጋጠመውን የመንገድ ብልሽት በማየት በከተማው የሚገኙ የቅን - ድል ኢትዮጲያ ቤተሰቦች እና ብሩሀን የወጣቶች በጎ ፍቃደኛ ማህበር አባላት ይህን ችግር ለመቅረፍ እና ተሽከርካሪዎች አደጋ እንዳያጋጥማቸው በመጠገን ላይ ይገኛሉ፡፡

በከተማው የምትገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች እና ባለሀብቶች #የማቴሪያል ድጋፍ እንድታረጉላቸው ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ለሀገራችን ለመስራት ምክንያት አንሻም!!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዋሽ ወይን አክሲዮን ማኅበር በ2 ሚሊዮን ዶላር የማስፋፊያ ፕሮጀክት ሰርቶ አጠናቀቀ!

የአዋሽ ወይን አክሲዮን ማኅበር የምርት አቅሙን በሦስት እጥፍ ያሳድጋል የተባለለትን የማስፋፊያ ፕሮጀክት በ2 ሚሊዮን ዶላር ገንብቶ አጠናቀቀ። በአዲስ አበባ መካኒሳ አካባቢ በሚገኘው የመጥመቂያ ፋብሪካ የተገነባው የማስፋፊያ ፕሮጀክት ከዚህ ቀደም ፋብሪካው በአመት ሲመርተው የነበረውን የ6 ሚሊየን ሊትር ወደ 30 ሚሊዮን ሊትር የሚያሳድግ ሲሆን ከቻይና፤ ጀርመን እና ጣሊያን በተገኙ ቴክኖሎጂዎች የተደራጀ መሆኑ ተገጾል። በቀጣዩ ዓመት ተጨማሪ የማስፋፊያ ስራዎችን ለመስራት 1 ሚሊየን ዶላር በጀት መያዙን በተጨማሪም ለማህበራዊ ስራዎች ከ 15 ሚሊየን ብር መመደቡን አሳዉቀዋል፡፡የአልኮል መጠኑ ዝቅተኛ የሆነ ዳንኪራ የተሰኘ አዲስ ምርት ለገበያ አቅርቧል፡፡

Via #AddisMaleda
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የከተሞች ተቋማዊና የመሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም (UIIDP) የክልሎች በጀት ይፋ ሆኗል።
የከተሞች ተቋማዊና የመሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም (UIIDP) የክልሎች በጀት ይፋ ሆነ!

በአዳማ ከተማ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የ3ኛው ዙር የከተሞች መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም አሀድ የመጀመሪያው አመታዊ አፈፃፀም ግምገማ በዛሬው እለት ተጠናቋል።

በፕሮግራሙም የከተሞች ተቋማዊና የመሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም (UIIDP) የ2012 በጀት ዓመት የዘጠኝ ክልሎች እና የአንድ ከተማ አስተዳደር በጀት ይፋ ሆኗል። የተመደበው በጀት አጠቃላይ 104,125,856 የአሜሪካን ዶላር ሲሆን ድሬዳዋን ጨምሮ በዘጠኙ ክልሎች ለሚገኙና በፕሮግራሙ ለታቀፉ 117 ከተሞች የሚከፋፈል ነው። በበጀት ድልድሉም፦

-ኦሮሚያ ክልል 30, 466,320
-አማራ ክልል 25,778,179
-ደቡብ ክልል 19,592,230
-ትግራይ ክልል 14,353,457
-አፋር ክልል 1,622,409
-ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 720,546
-ጋምቤላ ክልል 764,041
-ሐረሪ ክልል 1,935,145
-ሶማሌ ክልል 4,149,867
-ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር 4,743,657 የአሜሪካን ዶላር ተመድቧል።

በመድረኩም በፕሮግራሙ ከታቀፋ የተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የመጡ ከንቲባዎች፣ የአለም ባንክ አመራሮች እና ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ነበሩ። በበጀት አጠቃቀም፣ በፕሮግራሙ መመሪያዎች፣ በነጥብ አሰጣጥ መስፈርቶች፣ በአፈፃፀምና ተዛማጅ ጉዳዮችም ሰፊ ውይይት ተደርጓል። በዘርፋ ላይ ያተኮሩ ስልጠናዎችም ተሰጥተዋል።

እንዲሁም የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር የከተማ ፕላንና መሬት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታዜር ገ/ እግዚያብሄር እንደተናገሩት ፕሮግራሙን ውጤታማ ለማድረግ የዜጎችን የእለት ተእለት ችግርሮች መፍታት እና የከተሞችን መሠረታዊ ፍላጎቶች ማሟላት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥቶ መንቀሳቀስ ይጠይቃል ብለዋል። ሚኒስትር ዲኤታው አክለውም በቀጣይም አነስተኛ አፈፃፀም ያሳዩ ከተሞች የተሻለ አፈፃፀም ካላቸው ከተሞች ልምድ እንዲቀስሙ በማድረግና በመደገፍ ውጤት ማስመዝገብ እንዲችሉ ማድረግ ይጠበቅብናል ብለዋል።

የከተማ ልማትና ቤቶች ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ መስፍን አሰፋ በበኩላቸው በያዝነው በጀት ዓመት ሶስት ሚሊዮን ለሚጠጉ ዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር መታቀዱን ጠቁመው ለፕሮግራሙ የተመደበውን በጀት በአግባቡ ስራ ላይ በማዋልና ሰፊ የስራ እድል በመፍጠር ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

via Negede
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አዲሱን የሥራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን ደንብ ማስፈጸሚያ መመርያ አስተያየት እንዲሰጥበት ለተቋማት ላከ!

ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በቅርቡ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያፀደቀውን የመንግሥት ሠራተኞች የሥራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን ደንብ ማስፈጸሚያ መመርያ አርቅቆ፣ ለክልሎችና ለተለያዩ ተቋማት አስተያየት እንዲሰጡበት አሠራጨ፡፡

ከአሁን ቀደም ከ40 ዓመታት በላይ ሲሠራበት የቆየውን የመንግሥት ሠራተኞች የሥራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን ከዘጠኝ ደረጃዎችና ከአሥራ ሁለት እርከኖች ወደ ሃያ ሁለት ደረጃዎች ብቻ በመወሰን፣ እያንዳንዱ ደረጃ ከአንድ እስከ 12 የሚደርሱ መደቦችን እንዲይዝ የሚያደርገውን ደንብ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የፀደቀው ከሳምንት በፊት ነበር፡፡

ከዚህ በተጨማሪም መመርያው ከአሁን ቀደም በመንግሥት ተወስነው ይሠራባቸው የነበሩ ከ70 በላይ የደመወዝ ስኬሎችን ወደ አንድ ስኬል የሚቀይር ሲሆን፣ ቀድሞ የነበረው ስኬል ይሠራበታል ቢባልም በተለያዩ መሥሪያ ቤቶች የተለያዩ ስኬሎች በመኖራቸው፣ ከ150 በላይ እንዲሆኑ ያደረገውን አሠራርም ይለውጣል፡፡

በዚህም መሠረት በተለያዩ መሥሪያ ቤቶች ለተመሳሳይ ሥራዎች የተለያዩ ክፍያዎች ይፈጸሙ ስለነበር፣ የክፍያ ኢፍትሐዊነት እንዲንሰራፋ በማድረጉና ለእኩል ሥራዎች እኩል ክፍያ የሚያጎናጽፈውን ሕጋዊ መብት ወደ ጎን ያለ አሠራር ነበር ተብሎ የቀድሞው ይተቻል፡፡ አዲሱ የሥራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን በአገር አቀፍ ደረጃ ሥራዎችን በመስፈርት በመመዘን፣ እኩል የሆኑ ሥራዎች እኩል ክፍያ እንዲያገኙ ያስችላልም ተብሏል፡፡

#ሪፖርተር_ጋዜጣ

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-08-28
ደቡብ ክልል ምክር ቤት አዲስ የክልል ፕሬዘዳንት ሊሾም ነው!

ደቡብ ክልል ምክር ቤት አርብ ነሐሴ 24/2011 በሚያካሒደው ስብሰባ ከሰኔ 19/2010 ጀምሮ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ሆነው በማገልገል ላይ የሚገኙትን ሚሊዮን ማቲዎስን ከስልጣናቸው በማንሳት በሌላ አዲስ ርዕሰ መስተዳደር እንደሚተካ ረቡዕ ነሐሴ 22/2011 የወጣው ሪፖርተር ጋዜጣ በፊት ገፁ አስነብቧል። ሚሊዮን ማቲዎስ ከርዕሰ መስተዳደርነታቸው በመነሳትም የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት የዲሞክራሲ ማዐእከል ምክትል አስተባባሪ ሆነው በሚንስትር ማዕረግ እንደሚያገለግሉ ተሰምቷል።

Via Reporter/addismaleda
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ሚሊዮን ማቴዎስ ከርዕሰ መስተዳድርነታቸው ተነስተው፣ በሚኒስትር ማዕረግ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ማዕከል ምክትል ዋና አስተባባሪ ሆነው እንደሚሾሙ ተሰምቷል። #Reporter

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ መለስ ዓለሙ የደቡብ ክልል ፕሬዘዳንት ሆነው ሊሾሙ ይችላሉ!

ከአሁን ቀደም የማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስትር በመሆን ያገለገሉት አቶ መለስ ዓለሙ፣ ለክልሉ ምክር ቤት በፕሬዚዳንትነት ሊሾሙ እንደሚችሉ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ አቶ መለስ በአሁኑ ወቅት በሚኒስትር ማዕረግ የኢሕአዴግ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ማዕከል ምክትል ዋና አስተባባሪ በመሆን በመሥራት ላይ ይገኛሉ፡፡

#ሪፖርተር_ጋዜጣ

ተጨማሪ የንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-08-28-2
በትግራይ ክልል በደረሰ የትራፊክ አደጋ በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ!

በትግራይ ማዕከላዊ ዞን በተለያዩ አካባቢዎች ትናንት በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች የሁለት ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል።

የዞኑ ትራፊክ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ኮማንደር ምሕረተአብ ገብረመድህን እንዳስታወቁት የመኪና አደጋው የደረሰው በዞኑ ታህታይ ማይጨው፣ ቆላተምቤን ወረዳዎች እና በአድዋ ከተማ ውስጥ ነው። በአደጋዎቹ የሁለት ሰዎች ሕይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ በሦስት ሰዎች ላይ ከባድ የመቁሰል አደጋ መድረሱን ኃላፊው ተናግረዋል።

በታህታይ ማይጨው ወረዳ በደረሰው የተሽከርካሪ አደጋ አንድ የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ ከሌላ ሚኒባስ ጋር ተጋጭቶ የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ ሦስት ሰዎች ከባድ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል።

በቆላተምቤን ወረዳም አንድ አይሱዙ መኪና የመገልበጥ አደጋ ደርሶበት የአንድ ሰው ህይወት ሲያጠፋ ለስድስት የቁም እንስሳት ሞት ምክንያት መሆኑንም ነው ኮማንደሩ የገለጹት። በአድዋ ከተማ ሲኖትራክ ተሽከርካሪ ከግዑዝ ነገር ጋር ተጋጭቶ በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱንም አመልክተዋል። ከባድ የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ሰዎች በአድዋ እና በአክሱም ሆስፒታሎች ውስጥ የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል።

የትራፊክ አደጋዎቹ ሊደርሱ የቻሉት በአሽከርካሪዎች የብቃት ማነስ፣ ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከርና የስነ ምግባር ጉድለት ምክንያት መሆኑንም ኮማንደር ምሕረተአብ ተናግረዋል። በደረሱ የተሽከርካሪ አደጋዎች በአጠቃላይ ከ206 ሺህ ብር በላይ ግምት ያለው ንብረት መውደሙንም ኃላፊው አስረድተዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የውድድር ማስታወቂያ!

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከአይቢኤ ኢትዮጲያና ከአፍሪካ ህብረት ጋር በመተባበር በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነ አህጉራዊ የኢኖቬሽንና የቴክኖሎጂ ንቅናቄ ‹‹አፍሪካ ኢኖቬሽን ሳምንት›› በሚል ርዕስ ከጥቅምት 17 እስከ ጥቅምት 22/2012 ድረስ በአዲስ አበባ ያካሂዳል፡፡

ስለሆነም ችግር ፈቺ፤ ሀብት ፈጣሪና ወደ ምርትና አገልግሎት ሊቀየር የሚችል የፈጠራ ስራ ያላችሁ በዚህ አህጉራዊ መድረክ ላይ ሀገራችሁን ወክላችሁ እንድትወዳደሩና የፈጠራ ውጤቶቻችሁን ለውጭና ለሀገር ውስጥ ባለሃብቶች፤ ለቬንቸር ካፒታል ተቋማት እና ለሌሎች የፋይናስ ምንጮች በማስተዋወቅ ወደ ምርትና አገልግሎት እንድትቀላቀሉ ይጋብዛል፡፡
 
ትኩረት የሚሰጣቸው ዘርፎች፡-

 ዘመናዊ  ከተሞች እና አዳዲስ የመኖሪያ ቴክኖሎጂዎች፤   ዲጂታላይዜሽን፤ የኢንተርኔት ንግድ ስርዓት፤ የግብርና፤  የጤናና የህክምና   ቴክኖሎጂ፤ መስተንግዶና ቱሪዝም፤  የማምረቻና እና የማዕድን ኢንደስትሪ ዘርፎች ተወዳድራችሁ ስራዎቻችሁን በኢኖቬሽን ሳምንቱ ማስተዋወቅ የምትፈልጉ አመልካቾች የፈጠራ ስራ ፕሮፖዛላችሁን በኢሜይል አድራሻችን [email protected]  ላይ በመላክ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን፤
 
ለማመልከቻ ቅፁና ለተጨማሪ መረጃ ድረ-ገፃችን www.mint.gov.et  ይመልከቱ፡፡
አልያም በስልክ ቁጥራችን +251-118-59-20-39 ይደውሉ፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  

#share #ሼር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ የምግብና የመድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ከ208 ሺህ ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ህገወጥ መድኃኒት፣ አደንዛዥ ዕፆችና አልሚ ምግቦች መያዙን አስታወቀ። ባለስልጣኑ ከኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልሎች ጤና ተቆጣጣሪዎች ጋር በመተባበር በሱቆችና መድኃኒት ቤቶች ላይ ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ መያዙን አስታውቋል።

ድንገተኛ ፍተሻው በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን በሞያሌ ወረዳ እና በሱማሌ ክልል ደግሞ ሊበን ዞን ዳዋ ወረዳ የተደረገ ሲሆን፥ ከ181 ሺህ 60 ብር በላይ የሚገመት ህገወጥ መድኃኒት፣ አደንዛዥ ዕፆችና አልሚ ምግቦች አገልግሎት ላይ ሳይወሉ መያዝ ተችሏል ነው ያለው። የተያዙት ህገወጥ መድኃኒት፣ አደንዛዥ ዕፆችና አልሚ ምግቦች በስምንት ሱቆች እና በሶስት መድኃኒት ቤቶች ውስጥ የተገኙ ሲሆን፥ በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ያልተመዘገቡና የቅዝቃዜ ሰንሰለታቸውን ሳይጠብቁ በኮንትሮባንድ መልክ የገቡ ናቸው ተብሏል። ባለስልጣኑ ህገወጥ መድኃኒቶቹንና ምግቦቹን ለአገልግሎት እንዳይቀርቡ በማድረግ ሱቆችና መድኃኒት ቤቶቹ እንዲታሸጉ ማድረጉንም ነው ያስታወቀው።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ድሬዳዋ

የኢትዮጵያ የምግብና የመድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን መስሪያ ቤት የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ከህብረተሰቡ በደረሰ #ጥቆማ መሰረት ከፖሊስ አካላት ጋር በመተባበር በድሬዳዋ ከተማ አባይ በሚባል መድኃኒት ቤት ውስጥ እንዲሁም በአንድ ግለሰብ ሲዘዋወሩ የነበሩ መድሃኒቶችን ይዟል።

መድሃኒቶቹ 27 ሺህ 470 ብር የሚገመት ዋጋ ያላቸው ሲሆን፥ የመድኃኒት ቤቱ ባለቤት በፖሊስ በቁጥጥር ስር እንዲውል በማድረግ ህጋዊ እርምጃ እንደተወሰደበት ከባለስልጣኑ የተገኘው መረጃ ያመላክታል። ባለስልጣኑ ህብረተሰቡ የቁጥጥሩ ባለቤት በመሆን ከማንኛውም ህገወጥ የምግብና የመድኃኒት ንግድና ዝውውር ራሱን በመጠበቅ የቁጥጥር ስራውን እዲያግዝም ጥሪውን አቅርቧል።

መሰል ህገወጥ የምግብና የመድኃኒት ንግድና ዝውውር ድርጊቶች ሲፈጸሙ ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በነጻ የስልክ መስመር በ8482 ወይም በአካባቢው ለሚገኙ የፍትህ አካላትና የጤና ተቆጣጣሪዎች እንዲጠቁም ጠይቋል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በህገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር ወንጀል የተሳተፈ አካል እስከ 10 አመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ሊቀጣ መሆኑ ተገለፀ!

ከህገወጥ ጦር መሳሪያ ዝውውር ጋር በተገናኘ የሚከሰቱ ወንጀሎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ያስችላል የተባለ ረቂቅ አዋጅ በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቢ ህግ አስታውቋል፡፡

በረቂቅ አዋጁ በህገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርና አያያዝ ወንጀል የተሳተፈ አካል እስከ 10 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ሊቀጣ እንደሚችል ተገልጿል፡፡

በአገሪቱ እየተስተዋለ የሚገኘውን ህገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርና አያያዝ በተመለከተ የጦር መሳሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅ እየተዘጋጀ እንደሆነ ይታወቃል፡፡

ረቂቅ አዋጁ ፀድቆ ስራ ላይ ሲውል በዋናነት ህጋዊ የጦር መሳሪያ አያያዝ ስርዓት በመፍጠር የአገርንና የህዝብን ሰላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ እንደሚጠቅም የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቢ ህግ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ጉዳይ ዳይሬክተር አቶ ዝናቡ ቱኑ በተለይ ለኢቲቪ ተናግረዋል፡፡

በወንጀሉ ዙሪያ ከዚህ በፊት በአገሪቱ የመቅጫ ህጎች የነበሩ ቢሆንም ህጎቹ በትክክል በጦር መሳሪያ አያያዝ፣ ፍቃድ፣ ቁጥጥርና አስተዳደር ዙሪያ በዝርዝር ያስቀመጡት ስርዓት እንዳልነበር ገልፀዋል፡፡

ከዚህም ባሻገር ከዚህ በፊት የነበሩት ህጎች በወንጀሉ ላይ የሚጥሉት የቅጣት መጠን ዝቅተኛ በመሆናቸው ዜጎች በወንጀል ድርጊቱ እንዳይሰማሩ የሚከለክሉ እንዳልነበሩም ተናግረዋል፡፡

አሁን ግን በባለድርሻ አካላት በውይይት እየዳበረ ያለው ረቂቅ አዋጅ በህገወጥ ጦር መሳሪያ ዝውውርና አያያዝ ላይ የሚጥለው ቅጣት ከበድ ያለ በመሆኑ ጥፋተኞችን ብሎም ህብረተሰቡን የሚያስተምር እንደሚሆን አመልክተዋል አቶ ዝናቡ፡፡

Via #EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በጋምቤላ ፈቃድ የሌላቸው 11 የውጭ ኮሌጆች ተገኙ!

ከየት እንደመጡ ያልታወቁ 11 ሕገወጥ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በጋምቤላ ክልል ሲያስተምሩ እንደተደረሰባቸው፣ የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

ኤጀንሲው ከተለያዩ ግለሰቦች በደረሰው ጥቆማ መሠረት ወደ ክልሉ ተንቀሳቅሶ የለያቸው እነዚህ 11 ተቋማት በድኅረ ምረቃና በተለያዩ የትምህርት ፕሮግራሞች ተማሪዎችን እየተቀበሉ እንደሚያስተምሩ ለሪፖርተር የገለጹት፣ የኤጀንሲው የኮሙዩኔኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ታረቀኝ ገረሱ ናቸው፡፡

ከኤጀንሲው ፈቃድ ሳያገኙ ሊያስተምሩ የተገኙት 11 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ በአገር ውስጥ የማይታወቁና እንግዳ መጠሪያ ያላቸውና ከውጭ የገቡ እንደሆኑ ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

‹‹በተደጋጋሚ በደረሰን ጥቆማ መሠረት ለማጣራት ወደ ክልሉ ስናመራ የጠበቅነው አንድ ተቋም ብቻ ነበር፡፡ ስንደርስ ግን 11 ሆነው አገኘናቸው፡፡ በወቅቱ ምንም ማድረግ ስላልቻልን ለክልሉ መንግሥት ስለሁኔታው በማስረዳት የክልሉን ነዋሪዎች ከሕገወጦች እንዲጠብቅ ደብዳቤ ጻፍን፤›› የሚሉት አቶ ታረቀኝ፣ ለክልሉ ደብዳቤ ከተጻፈ ስድስት ወራት የተቆጠረ ቢሆንም ምንም ዓይነት ምላሽ ለኤጀንሲው አለመድረሱን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

#ሪፖርተር_ጋዜጣ

ተጨማሪ የንብቡ👇
https://telegra.ph/eth-08-28-3
በቄለም ወለጋ ዞን የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሳታፊ ወጣቶች ለ4 ሺህ 360 መደበኛ ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ መሆኑን የዞኑ ትምህርት ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወደ ተባበሩት አረብ ኢምሬትስ የሄዱ 30ሺህ ዜጎች ህጋዊ ፍቃድ ተሰጣቸው!

ከዚህ ቀደም በህገ ወጥ መንገድ ወደ ተባበሩት አረብ ኢምሬትስ የሄዱ 30ሺህ ኢትዮጵያውያን ባሉበት ሀገር ላይ ህጋዊ የመኖሪያ ፍቃድ እንደተሰጣቸው የሰራተኛ ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴር መስርያቤቱ ዛሬ ከተባበሩት አረብ ኢምሬትስ የመጡ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ጋር ባደረገው የውይይት መድረክ ላይ የተገኙት የሰራተኛ ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ እንዳሉት ከሀገራቱ ባለስልጣናት ጋር በተደረገ ግንኙነት መሰረት በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ የሄዱ 30ሺህ ዜጎች ህጋዊ ፍቃድ ተሰጥቷቸዋል፡፡

እንደ ዶክተር ኤርጎጌ ገለፃ ከዚህ በፊት በሀገወጥ መንገድ ለሄዱት ዜጎች የተሰጠው ህጋዊ ፈቃድ ቢያስደስታቸውም ከዚህ በኋላ በሀገ ወጥ መንገድ ለሚሄዱ ዜጎች ምንም አይነት ምህረት እንደማይደረግና ሲያዙም ቀጥታ ወደ ሀገር ቤት እንደሚመለሱ ተናግረዋል፡፡

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia