TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
ቬራክሩዝ ውስጥ በተፈጸመ ጥቃት 8 ሴቶች እና 15 ወንዶች መሞቱ!

በሜክሲኮ በምሽት መዝናኛ ክለብ በተፈጸመ ጥቃት 23 ሰዎች መሞታቸው ተነገረ። በወደብ ከተማዋ ቬራክሩዝ በተፈጸመው ጥቃት 8 ሴቶች እና 15 ወንዶች መሞታቸው ነው የተነገረው። በወቅቱ በምሽት መዝናኛ ክለቡ ውስጥ እሳት መነሳቱንም ፖሊስ አስታውቋል።

እንደ ፖሊስ ገለጻ ከእሳቱ መነሳት ቀደም ብሎ መዝናኛ ክለቡ ላይ የተኩስ እሩምታ ተከፍቶ ነበር። ከተኩሱ በኋላም በጠርሙስ የተዘጋጁ ተቀጣጣይ ቁሶችን ወደ ክለቡ በመወርወር እሳት እንዲነሳ መደረጉንም ገልጿል።

ጥቃቱ የተፈጸመባት ከተማ ዋነኛ የእጽ አዘዋዋሪዎች መናኸሪያና በቡድን የሚንቀሳቀሱ ወንጀለኞች መገኛ መሆኗ ይነገራል። የአሁኑ ጥቃትም በእፅ አዘዋዋሪዎች አማካኝነት ሳይፈጸም አልቀረም ነው የተባለው።

ምንጭ፦ ቢቢሲ/fbc/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update እጅግ የተከበሩ የአለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ ስቱዲዮና መኖሪያ ቤት የሆነው “ቪላ አልፋ” እድሳት መጀመሩን የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን አስታውቋል።

Via #EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ደብቆ የተገኘ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ!

በምዕራብ ሸዋ ዞን ጮቢ ወረዳ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ደብቆ የተገኘ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ አስታወቀ። የወረዳው ፖሊስ ፅህፈት ቤት የወንጀል መከላከል ኃላፊ ሳጅን ወርቅነህ ዲነግዴ እንደገለፁት ግለሰቡ በቁጥጥር ስር የዋለው ዛሬ ጧት አራት ሰዓት አካባቢ ነው።

ግለሰቡ በወረዳው ቆርጬ ጨቢ ቀበሌ በሚገኝ በአንድ በእድሜ የገፉ አዛውንት መኖሪያ ቤት ውስጥ ሶስት ቦምቦች፣ ሁለት ክላሽንኮቭ ጠመንጃዎችና 198 ጥይቶች ከስድስት የጥይት መያዣ ካዝናዎች ጋር ደብቆ በመገኘቱ በቁጥጥር ስር መዋሉን ተናግረዋል። ህብረተሰቡ ለፖሊስ በሰጠው ጥቆማ መሰረት ግለሰቡ መያዙን የገለፁት  ሳጅን ወርቅነህ ጉዳዩ እየተጣራ መሆኑን ገለፀዋል። ህብረተሰቡ አጠራጣሪ የሆኑ ድርጊቶች ሲከሰቱ በአፋጣኝ ለፖሊስ በማሳወቅ ወንጀልን ለመከላከል እያሳየ ያለውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥል ሳጅን ወርቅነህ  አስገንዝበዋል።

Via ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#SayNoToRacism

ዉድ የቲኪቫህ ኢትዮጵያ ስፖርት ቤተሰቦች በዛሬው የቲኪቫህ ስፖርት አምዳችን አሳሳቢ እየሆነ በመጣው የዘረኝነት ጉዳይ ያዘጋጀንላችሁ ፅሁፍ አለ። በአንድ ወቅት ላይ የዚህ ድርጊት ሰላባ የነበረው የናፖሊ እና የሴኔጋል ብሐራዊ ቡድን የመሀል ተከላካይ ካሊዱ ኩሊባሊ ካሰፈረው ማስታወሻ ላይ የተናገረውን ባማረ አቀራረብ አመሻሹ ላይ ይዘንላችሁ እንቀርባለን።

ቲኪቫህ ኢትዮጵያ እና ቲኪቫህ ኢትዮጵያ ስፖርት ዘረኝነትን ያወግዛል።

#SayNoToRacism #TikvahEthiopiaAgainstRacism
#TikvahEthiopiaSportAgainstRacism
#WeAreAgainstRacism

Join TIKVAH-ETH SPORT👇
https://yangx.top/joinchat/AAAAAFb8M0pNEZTiGM68rg

@tikvahethsport
@kidusyoftahe
@yidaaa
ኢትዮጵያዊ ቦምብ የሚል ቃል ተጠቅሞ ቀልድ በመቀለዱ የ4 ወራት እስራት ቅጣት ተጣለበት!

ባለፈው ሚያዚያ በኬንያ አየር መንገድ የተሳፈረ አንድ ኢትዮጵያዊ ቦምብ የሚል ቃል ተጠቅሞ ቀልድ በመቀለዱ የ4 ወራት እስራት ወይም የ100 ሺህ የኬንያ ሽልንግ ቅጣት እንደተጣለበት ዴይሊ ኔሽን ጋዜጣ አስነብቧል፡፡ ፍርድ ቤት ቅጣቱን የጣለበት፣ የበረራ አስተናጋጇ የዕቃ ማስቀመጫዎችን ስትፈትሽ፣ “ምነው ፈራሽ? ቦምብ መሰለሽ?” ብሎ በመቀለዱ ነው፡፡ በቀልዱ ሳቢያ ባለፈው ሚያዚያ ወደ ጁሃንስበርግ ሊደረግ የነበረ በረራ እንዲሰረዝ እና የናይሮቢው ጆሞ ኬንያታ አውሮፕላን ማረፊያም ለ3 ሰዓታት እንዲዘጋ ምክንያት ሆኖ ነበር፡፡

Via #wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የተሻለ አፈፃፀም ያስመዘገቡ ከተሞች ተሸላሚ ሆኑ!

በአዳማ ከተማ ለሁለት ቀናት በቆየው የሶስተኛው ዙር የከተሞች መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም አሀድ የመጀመረያው ዓመት አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ላይ በዘርፉ የተከናወኑ ተግባራት የተገመገሙ ሲሆን የተሻለ አፈፃፀም ያስመዘገቡ ከተሞች ተሸላሚ ሆነዋል።

በሽልማት ፕሮግራሙም በተቋማዊ አፈፃፀም ውቅሮ ከተማ 93 ነጥብ በማምጣት በአንደኛ ደረጃ ተሸላሚ ስትሆን፤ ጎንደር፣ ፍኖተሰላም እና ሞጣ የሁለተኛ ደረጃ እንዲሁም አላማጣ እና አክሱም ከተሞች የሶስተኛ ደረጃን አግኝተዋል።

እንዲሁም በመሰረተ ልማትና አገልግሎት አቅርቦት ዘርፍ እንዲሁ ውቅሮ ከ99 ነጥብ በላይ በማምጣት ቀዳሚ ስትሆን፤ አዲግራት እና አላማጣ የሁለተኛ እና የሶስተኛ ደረጃን ማግኘት ችለዋል። በጀት አጠቃቀምና ኦዲት በተመለከተም ይርጋለም፣ ሀዋሳ እና አዳማ ከተሞች እንደ ቅደም ተከተላቸው ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ያለውን ደረጃ በማግኘት ተሸላሚ ሆነዋል።

በዚሁ ወቅት የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ክብርት ኢንጂነር አይሻ መሀመድ እንደተናገሩት የተሻለ አፈፃፀም ያስመዘገቡ ከተሞች አሁንም ለላቀ ስራ ይበልጥ እንዲተጉ እና አነስተኛ አፈፃፀም ያሳዩ ከተሞች በአፋጣኝ ክፍተቶቻቸውን በመለየት እና ከሌሎች ከተሞች ልምድ በመውሰድ በያዝነው በጀት ዓመት የተሻለ አፈፃፀም ማስመዝገብ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል። ሚኒስትሯ አክለውም በቀደሙት ጊዜያት በነበሩ ፕሮግራሞች በፕሮግሪሙ ታቅፈው የነበሩ 44 ነባር ከተምች የተመደበላቸውን በጀት ለታለመለት አላማ በማዋል የተቀመጠውን ስርዓት ሙሉ በሙሉ በማጠናቀቅ በራሳቸው ገቢ መተዳደር መጀመር ቢኖርባቸውም ከተሞቹ ይህን አለማድረጋቸውን ጠቁመው በ2012 በጀት ዓመት ሁለተኛው የእድገት እና ትራንስፎርሜሽን እቅድ መርሃ-ግብር የሚጠናቀቅበት ዓመት በመሆኑ የተጀማመሩ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት በማጠናቀቅ በፕላን የተመሩ ከተሞችን መፍጠር እና የህዝብን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት በዘላቂነት ማረጋገጥ እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። በያዝነው በጀት ዓመትም በፕሮግራሙ የታቀፉ ሁሉም ከተሞች በሙሉ አቅማቸው ወደስራ እንዲገቡ ጥሪ አስተላልፈዋል። በመጨረሻም የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ከተሞች የተዘጋጀላቸውን ሽልማት ክብርት ሚኒስትሯ አበርክተዋል።

የከተሞቹን አፈፃፀም ነጥብ እና ሌሎች መረጃዎችን በዝርዝር በዚህ ድረገፅ www.mudc.gov.et/ መመልከት ይችላሉ!

Via Negede
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተሸላሚ ከተሞች!

በተቋማዊ አፈፃፀም፦

1ኛ ደረጃ - ውቅሮ ከተማ
2ኛ ደረጃ - ጎንደር፣ ፍኖተሰላም እና ሞጣ
3ኛ ደረጃ - አላማጣ እና አክሱም

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተሸላሚ ከተሞች!

በመሰረተ ልማትና አገልግሎት አቅርቦት ዘርፍ፦


1ኛ ደረጃ - ውቅሮ
2ኛ ደረጃ - አዲግራት
3ኛ ደረጃ - አላማጣ

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተሸላሚ ከተሞች!

በበጀት አጠቃቀምና ኦዲት፦

1ኛ ደረጃ - ይርጋለም
2ኛ ደረጃ - ሀዋሳ
3ኛ ደረጃ - አዳማ

የከተሞቹን አፈፃፀም ነጥብ እና ሌሎች መረጃዎችን በዝርዝር በዚህ ድረገፅ www.mudc.gov.et/ መመልከት ይችላሉ።

#TIKVAH_ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ETHIOPIA ምድረ ቀደምት!

በአፋር አዲስ የቅድመ ሰው ዝርያ ተገኘ!

ከቅድመ ሰው ዝርያ ጋር በተያያዘ አዲስ ግኝት መገኘቱ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለልስጣን አስታወቀ። በአፋር ክልል ወራንሶ ሚሌ በተባለ የአረኪኦሎጂ ጥናት ቦታ ላለፉት ሶስት ዓመታት ጥልቅ ጥናት ሲያካሂድ የቆየው ቡድን ከቅድመ ሰው ዝርያ ጋር በተያያዘ አዲስ ግኝት ማግኘቱን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አስታቋል።

የጥናትና ምርምር ግኝቱም እ.ኤ.አ. ኦገስት 28/2019 በߵߵNatureߴߴ በተባለው አለም አቀፍ መፅሄት ታትሞ እንደሚወጣ የገለፀው ባለስልጣን መስሪያቤቱ፤ ግኝቱ በዘርፉ ጥናት በርካታ ማስረጃዎች በመገኘታቸው ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ ደረጃ ߵߵNatureߴߴ የሰው ዘር መገኛߴߴ በሚል ለተሰጣት ስያሜ ተጨማሪ ምስክር ነው ብሏል።

ከዚሁ ግኝት ጋር በተያያዘ ባለስልጣን መስሪያቤቱ ከጥናት ቡዱኑ ጋር በመሆን ዛሬ (ነሐሴ 22 ቀን 2011 ዓ/ም) አምስት ኪሎ በሚገኘው የባለስልጣኑ አዳራሽ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በድሬዳዋ ከተማ በመብረቅ የሰው ህይወት አለፈ!

በድሬዳዋ ከተማ ትናንት የጣለው ከባድ ዝናብን ተከትሎ አንድ ሰው በመብረቅ ህይወቱ ሲያልፍ በሌሎች ሶስት ሰዎችና በመሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት መድረሱን የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ።

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ቡድን አስተባባሪ ረዳት ኢንስፔክተር ባንተአለም ግርማ እንደገለፁት በከተማው ትናንት የጣለውን ሃይለኛ ዝናብ ተከትሎ በወረደው መብረቅ ገንደ ጋራ በተባለ ሰፈር አንድ ሰው ጭንቅላቱን ተመትቶ ወዲያውኑ ህይወቱን አልፏል። በተጨማሪም አንድ ባለሦስት ጎማ ታክሲ መንገድ ሲያቋርጥ በደራሽ ጎርፍ ተገልብጦ በሶስት ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት አድርሷል። እንደረዳት ኢንስፔክተሩ ገለፃ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በድልጮራ ሆስፒታል ህክምና በመከታተል ላይ ይገኛሉ፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ  አገልግሎት የድሬዳዋ አስተዳደር አውቶሜሽንና ቴክኖሎጂ ዳይሬክተር አቶ ወንድወሰን ዘመድሁን እንደገለፁት ደግሞ ትናንት ማታ ንፋስ ቀላቅሎ የጣለው ከባድ ዝናብ በኤሌክትሪክ መስመሮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል። የኤሌክትሪክ መስመር ተሸካሚ የእንጨትና የኮንክሪት ምሰሶዎች ማፈራረሱንም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

በተለይ በከተማው ከዚራና ነምበርዋን አካባቢው የሚገኙ ትልልቅ የዛፍ ግንዶች በንፋስ በመገንጠላቸው የኤሌክትሪክ መስመሮች ተበጣጥሰው አገልግሎት ተቋርጦ እንደነበር ገልፀዋል፡፡ የኤክትሪክ ሰራተኞች ከትናንት ማታ ጀምሮ ባደረጉት ርብርብ አገልግሎቱእንዲጀምር መደረጉንም አቶ ወንድወሰን ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በ2011 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ የተሰጠው የብቃት ማረጋገጫ ፈተና ውጤት፦

"የጤና ሚኒስቴር የአገልግሎት ጥራትን ከማሻሻል አንጻር የተለያዩ ስራዎችን እየተገበረ ይገኛል ከነዚህም መካከል አንዱ የሆነው የጤና ባለሙያዎችን ከተመረቁ በኃላ ብቃታቸውን መዝኖ ወደ ስራ እንዲገቡ የሚያስችል ስርአት መዘርጋት ነው ይህንንም ለማከናወን እንዲያስችል ላለፉት አራት(4) አመታት የተለያዩ ዝግጅቶች ሲደረጉ ከቆዩ በኃላ በዚህ አመት ከሀምሌ 1-9 2011 ዓ.ም ለ10,480 የጤና ሙያ ዘርፍ ተመራቂዎች የብቃት ምዘና የተሰጠን ሲሆን #ወጤቱንም ነገ ነሐሴ 23 ቀን 2011ዓ.ም ለጤና ባለሙያዎችና ለሚመለከታቸው ተቋማት የምናሳውቅ ይሆናል፡፡ ተማሪዎች ውጤታቸውን በዌብ ሳይት hple.moh.gov.et በመግባት registration number፣ ስም እና የአባት ስም በማስገባት መመልከት ይችላሉ፡፡"

የጤና ሚኒስቴር

#ሼር #share

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ውጤታችሁን ነገ ማየት ትችላላችሁ!

የጤና ሙያ ዘርፍ ተመራቂዎች #የብቃት ምዘና የተሰጠን ሲሆን #ወጤቱንም ነገ ነሐሴ 23 ቀን 2011ዓ.ም ለጤና ባለሙያዎችና ለሚመለከታቸው ተቋማት የጤና ሚኒስቴር የሚያሳውቅ ይሆናል፡፡ ተማሪዎች ውጤታችሁን በዌብ ሳይት hple.moh.gov.et በመግባት registration number፣ ስም እና የአባት ስም በማስገባት መመልከት ትችላላችሁ።

#Share #ሼር

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የASTU/AASTU የመመዝገቢያ መስፈርት!

ለኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች የ2012 ዓ.ም መግቢያ ፈተና የምዝገባ ጥሪ!

የምዝገባ ጊዜ፡- ከነሐሴ 23 - ጳጉሜ 03

የምዝገባ ቦታ፦

የምዝገባ መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾች በማንኛውም ስፍራ በኢንተርኔት (online) በ www.aastu.edu.et,  www.astu.edu.et ድህረ ገፅ በመጠቀም መመዝገብ ይችላሉ፡፡

ፈተናው የሚሰጥበት ቀን፡-

በማስታወቂያ እና በዩኒቨርሲቲዎቹ ዌብሳይት የሚገለጽ ይሆናል፡፡

ፈተናው የሚሰጥበት ቦታ፡-

በምዝገባ ወቅት በመረጡት የፈተና ጣቢያ በአካል በመቅረብ ይሆናል፡፡

ማሳሰቢያ፡-

•ለምዝገባና ለፈተና ምንም አይነት ክፍያ አይጠየቅም፣

•ከሚመዘገቡት አመልካቾች ውስጥ ለፈተና የሚቀርቡት ስም ዝርዝራቸው በሚከተሉት ድረ-ገፆች፡-

www.aastu.edu.etwww.astu.edu.et
እንደአመቺነቱም በስልክ አጭር የጽሑፍ መልዕክት የሚገለፅ ይሆናል፡፡

•አመልካቾች ከወዲሁ ፈተናው በሚሰጥባቸው የትምህርት ዓይነቶች፣ ማለትም የመሰናዶ (11ኛ እና 12ኛ ክፍል) ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስ፣ ሂሳብና እንግሊዝኛ እንዲዘጋጁ ይመከራል፡፡

•ፈተና የሚሰጠው በቀጥታ (online) ስለሆነ አመልካቾች በፈተና ጊዜ ሊያጋጥም የሚችል ግራ መጋባትን ለማስቀረት በምዝገባ ጊዜ ከመመዝገቢያ ፎርማቱ ጋር ተያይዞ የቀረበውን የሙከራ ፈተና እንዲለማመዱ ይመከራል፡፡

•አመልካቾች ለፈተና ሲቀርቡ የ2011 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት፣ የሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና አድሚሽን ካርድ (ወይም መታወቂያ) እና የምዝገባ ማረጋገጫ ኮፒ መያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-08-28-4

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ድረገፅ በመግባት መመልከት ትችላላችሁ፦ http://www.astu.edu.et/announcements/2012
የጤና ሙያ ዘርፍ ተመራቂ ተማሪዎች የብቃት ምዘና ውጤት በዌብ ሳይት hple.moh.gov.et በመግባት registration number፣ ስም እና የአባት ስም በማስገባት መመልከት ትችላላችሁ።

#Share #ሼር

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፖሊስ 53 ተጠርጣሪዎች መያዙን አስታወቀ!

በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ፈዲስ ወረዳ ለህግ የበላይነት መከበር እንቅፋት ሆነዋል የተባሉ 53 ተጠርጣሪዎችን መያዙን ፖሊስ አስታወቀ።

የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ዲቭዥን ኃላፊ ኮማንደር ስዩም ደገፋ እንደገለጹት ተጠርጣሪዎቹ በወረዳው ቦኮ ከተማ ህብረተሰብን በመከፋፈል ለጸብ የሚያነሳሱ ተግባራትን  በተደጋጋሚ ሲፈጸሙ ቆይተዋል። እንዲሁም ለደን ጭፍጨፋ የሚዳርጉ ግለሰቦችን ከማበረታታት ባለፈ በግለሰብና የመንግስት ንብረቶች ላይ ውድመትና ዘረፋ እንደፈጸም ሲነሳሱ እንደነበርም አመልክተዋል።

በወረዳው የሚገኙ ፍርድ ቤቶችና የፖሊስ ጽህፈት ቤቶችን ጨምሮ ሌሎች አገልግሎት ሰጪ የመንግስት ተቋማት የሚጠበቅባቸውን አገልግሎት እንዳያከናውኑ እንቅፋት እንደሆኑም ተጠቅሷል።

እነዚህ 53 ተጠርጣሪዎች የተያዙት ከነሐሴ 18/2011ዓ.ም ጀምሮ ነው። እንደ ኮማንደር ስዩም ገለጻ በወረዳው የሚከከሰተውን የወንጀል ድርጊት ለመከላከል ነሐሴ 19 ቀን 2011 ዓ. ም በቦኮ ከተማ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር የሰላም ኮንፍረንስ የተካሄደ ሲሆን የተያዙት ተጠርጣሪዎቹ የፍርድ ውሳኔ እንዲያገኙም ተወስኗል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸በኢትዮጵያ 3.8 ሚሊዮን አመታት ዕድሜ ያለው የቅድመ-ሰው የተሟላ የራስ ቅል ማግኘታቸውን ሳይንቲስቶች በዛሬው ዕለት ይፋ አደረጉ። «በአስደናቂ ሁኔታ የተሟላ» ነው የተባለው የራስ ቅል ግኝት ዓለም ስለ ሰው ልጅ ዝግመተ-ለውጥ ያለውን አረዳድ የመለወጥ ዕድል አለው ተብሏል።

Via #DW
ፎቶ: የክሊቭላንድ የተፈጥሮ ታሪክ ቤተ-መዘክር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አክሱም

በአክሱም ከተማ ከነሀሴ 24 ቀን ጀምሮ የሚከበረውን የዓይኒዋሪ/አሸንዳ በዓል ምክንያት በማድረግ ባዛርና ዓውደርእይ ዛሬ ተከፈተ። በትግራይ ክልል የአሸንዳ በዓል በየዓመቱ ከነሀሴ 16 ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት እንደሚከበረው ሁሉ የዓይኒዋሪ በዓል ደግሞ ከነሀሴ 24 ቀን ጀምሮ በአክሱምና አካባቢው በተመሳሳይ መልኩ ይከበራል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአጭበርባሪዎች ራሳችሁን ጠብቁ!

"ዛሬ አንድ የቴሌግራም ግሩኘ ላይ ገብቼ አንድ የPhoto Effect የሚል app አውርጄ ስልኬ ላይ ከጫንኩት በኋላ ስከፍተው ወዲያውኑ ከስልኬ ላይ የ5ብር #ፖኬጅ ወደዚ ቁጥር 0984838733 ላከብኝ እና ለሌሎች መማሪያ ይሆናል ብዬ ነው።"

በነገራችን ላይ በርካታ በዚህ ስራ የተጠመዱ ሰዎች አሉ፤ በተለያዩ የማጭበርበሪያ መንገዶች የሚጠቀሙ ውድ ቤተሰቦቻችን ጥንቃቄ አድርጉ።

ጥንቃቄ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia