TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
ፎቶ📸በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን ደብረ ታቦር ከተማ ዛሬ ለወጣቶች የመልካም እሴቶችና የምክንያታዊነት ማጎልበቻ ሥልጠና ሲሰጥ ውሏል። #ETHIOPIA

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአፋር ክልል ከሚገኘው የማዕድን ሀብት ህብረተሰቡና ክልሉን የተሻለ ተጠቃሚ ለማድረግ የተለያዩ ድጋፎችን እንደሚያደርግ የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ገለጸ። በክልሉ ህገ-ወጥ የማዕድን ግብይትን መቆጣጠር ላይ ያተኮረና የወረዳና ክልል ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት የውይይት መድረክ ትላንት በሰመራ ከተማ ተካሄዷል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-08-20-7

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#SayNoToRacism በየትኛውም የምድር ክፍል በሰው ልጅ ላይ የሚፈፀምን የዘረኝነት ጥቃት አጥብቀን እናወግዛለን!! የቆዳ ቀለማችን ቢለያይም ውስጣችን አንድ ነው። #PaulLabilePogba #TIKVAH_ETHIOPIA
የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ፕ/ር ክንደያ ገብረህይወት በእስራኤላዊቷ ተማሪ አያ ናምኔህ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀዋል። #RIP

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ዛሬ #InnovationEducationInAfrica በቦትስዋና፣ ጋቦሮኒ ተከፍቷል፡፡ በዚህ ኤክስፖ ላይ የመቐለ ዩኒቨርሲቲው መምህር ኢንጂነር #ፊሊሞን_ግደይ /EIT/ ከተመረጡት 40 ፈጣሪዎች መካከል አንዱ በመሆን ተካፋይ ሆኗል።

የመምህር ፊሊሞ ፈጠራ AHADU MOBILE GSM የተሰኘ ሲሆን የትምህርት ቤት አስተዳደር ስርዓት ላይ ትኩረት ያደርገ ነው። ሲስተሙ መምህራን በሞባይላቸው ተጠቅመው ተማሪዎች በትምህርት ገበታቸውን ላይ ስለመገኘታቸው ለመቆጣጠርና መምህራን በስራ ገበታቸው ላይ እንደተገኙ ለመቆጣጠር፤ መምህራን ለወላጆች ስለተማሪዎቻቸው የትምህርት ሁኔታ ሪፖርት ለማድረግና ወላጆችም በልጆቻቸው የትምህርት ሁኔታ ላይ ተሳትፎ እንዲያደርጉ የሚረዳ ነው።

በኤክስፖው መክፈቻ ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ፅዮን ተክሉ በመምህሩ የፈጠራ ስራ መደሰታቸውን ገልፀው የሀገራችንን ስራዎች አጠንክረን ልናስተዋውቅ ይገባል ብለዋል። ለመምህር ፊሊሞንም እንኳን ደስ አለህ ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ #ፅዮን_ተክሉ በቦትስዋና፣ ጋቦሮኒ Innovation Education In Africa 2019🇪🇹

ፎቶ: የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ፅዮን ተክሉ
#TIKVAH_ETH

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ #ፅዮን_ተክሉና የመቐለ ዩኒቨርሲቲው መምህር ኢንጂነር ፊሊሞን ግደይ በቦትስዋና፣ ጋቦሮኒ Innovation Education In Africa 2019🇪🇹

ፎቶ: የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ፅዮን ተክሉ #TIKVAH_ETH

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሰላም ዋጋው ስንት ነው?
#PEACE

ሰላም የሁሉም ነገር መሰረት ነው፡፡ ለዚህም ነው ሰዎች ሲገናኙ ቅድሚያ ስለ ሰላማቸው ሁኔታ የሚጠያየቁት፡፡ ጠዋት ከእንቅላፋቸው ተነስተው “በሳላም አውለኝ”፤ ማታ ሲተኙም “በሰላም ያዋልከኝ በሰላም አሳድረኝ” ብለው ምስጋናቸውን የሚገልጹትም የሰላምን ትልቅ ዋጋ በመረዳት ነው፡፡ እናም ሁሉም ሰው ሊባል በሚችል መልኩ ሰላም በህይወቱ ላይ ትልቅ ውድ ዋጋ ያለው ነገር መሆኑን ይገነዘባል፤ ለሰላሙም ዘብ ይቆማል፡፡

ሆኖም ከብዙዎች #በተቃራኒ ሰላም ለማደፍረስ የሚተጉ ኃይሎችም አሉ፡፡ በእነዚህ አይነት ሰዎች የተነሳ በተለያዩ የዓለም ሀገራት የሚገኙ ህዝቦች ሰላምና መረጋጋት እንዲርቃቸውና በአንጻሩ ጦርነት፣ የእርስ በርስ ግጭት፣ ሽብርተኝነትና ወንጀል ተንሰራፍተው የሰዎችን ዕለታዊ ኑሮ እንዲታወክ ምክንያት ይሆናሉ፡፡

በሰላም እጦት ምክንያት የሚሊዮኖች ህይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት ተከስቷል፤ እየተከሰተም ነው፡፡ የ2017 Global Peace Index እንደሚያሳየው በአለም አቀፍ ደረጃ በሰላም እጦት ምክንያት በየዓመቱ 13 ነጥብ 6 ትሪሊየን ዶላር ኪሳራ እየተስተናገደ ነው፡፡ በግለሰብ ደረጃ በእያንዳንዱ ቀን አንድ ሰው ማግኘት ከሚገባው ውስጥ 5 ዶላር ያጣል ማለት ነው፡፡

ሶሪያ፣ የመን፣ ኢራቅና ደቡብ ሱዳን በሰላም #እጦት ምክንያት እየተናጡ ከሚገኙ ሀገራት ውስጥ ቀዳሚውን ስፍራ ይዘው ይገኛሉ፡፡ በተለይም ሶሪያና የመን በእርስ በርስ ጦርነት ምክንያት ወደ ፍርስራሽነት እየተቀየሩ ነው፡፡ የዓለም የስልጣኔ ቁንጮ የነበረችው ሀገረ ኢራቅም በአሸባሪ ቡድኖች ምክንያት ታላላቅ የስልጣኔ አሻራዎቿን ለመገበር ከመገደዷም በላይ ህዝቡ ለሞትና ለስደት ተዳርጓ፤ በከፍተኛ ስነ ልቦና ጫና ውስጥ ወድቋል፡፡

ተጨማሪ የንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-08-20-8
#update "ህብረ ብሄራዊ አንድነታችን ለጋራ እድገታችን እና ለተደማጭነታችን መሰረት ነው” በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀ የአመራሮች የግምገማ መድረክ ትላንት በወራቤ ከተማ ተጀመሯል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የጤና ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማን ከአለም የጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሀኖም ጋር ተወያዩ፡፡ በዚህ ወቅት የኢትዮጵያን የጤና ዘርፍ ለማጠናከር፣ የመረጃ አያያዝ እና አጠቃቀም ስርዓትን ለማጎልበት በጋራ ለመስራት ትኩረት አድርገው መክረዋል፡፡ በተለይም ክትባት፣ የመረጃ አብዮት እና የዘርፈ ብዙ የወረዳ ትራንስፎርሜሽን ስራዎች የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ እንደተወያዩ ዶክተር አሚር አስታውቀዋል፡፡

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከወላይታ ዞን፣ በዴሳ ከተማ!

"እኛ በወላይታ ዞን የበደሣ ከተማ በጎ ፍቃደኞች ነን ክረምቱን በከተማችንንበማፅዳት፣ ከ5 አሰከ 12 ክፍል ያሉትን ተማሪዎች በማስተማር፣ ችግኞችን በመትከል እያሳለፍን እንገኛለን!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከኮምቦልቻ...

"የኑሮ ውድነቱን ለምን ዝም እንደተባለ አልገባንም፤ ኮምቦልቻ ላይ 1 ኩንታል ጤፍ 3400 ብር፣ ሽንኩርት ከ35 እሥከ 40 ዘይት፣ በሊትር 90 ብር፣ ቲማቲም 20 ብር እየተሸጠ ነድ፤ ለአንድ የፋብሪካ ሠራተኛ የወር ደመወዝ 1100 ብር እየተከፈለው ሠው ወደት ይሒዲ!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የስኳር ኮርፖሬሽን ከ13 እስከ 14 ወራት ለምርት የሚደርሱ፣ በሽታና ተባዮችን መቋቋምም የሚችሉ አራት አገር በቀል የሸንኮራ አገዳ ዝርያዎችን በምርምር ማግኘቱን አስታውቋል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
ማት ብራይደን ከVOA ጋር!
ISIS አይኑን ኢትዮጵያ ላይ ጥሏል!

"...ISIS ብድግ ብሎ አካባቢውን #ያጥለቀልቃል የሚል እምነት የለኝም፤ ISIS የሚያስተዳድራቸው በኃይል የሚይዛቸው አካባቢዎች በቅርቡ ይኖራሉ ብዬ አላምንም ያ እራሳቸውን ለአደጋ ማጋለጥና ማጥፋት ይሆንባቸዋል። የኢትዮጵየ ጦርና ፌደራል ፖሊስን የመሳሰሉ ኃይሎች ናቸው የሚጠብቋቸው፤ ይሁን እንጂ ISIS ኃላፊነት የሚወስድባቸውን ጥቃቶች፣ አደጋዎችና ግድያዎችን የመሳሰሉ ሁኔታዎች ይኖራሉ ብዬ አስባለሁ" ማት ብራይደን
.
.
ሶማሊያ የሚገኘው የእሥላማዊ መንግሥት ክንፍ ኢትዮጵያ ውስጥ ጀሌዎችን ለመመልመል የሚያስችሉትን በአማርኛ በድምፅና በቪድዮ የተቀረፁ ጂሃዳዊ የቅስቀሳ ውጤቶችና ፅሁፎችን ሊያወጣና ሊያሠራጭ እንደሆነ ተገልጿል።

እሥላማዊ መንግሥት ቡድን ለአዲሱ ዘመቻው ኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየው የጎሣና የፖለቲካ አለመረጋጋት አመቺ ሁኔታ እንደፈጠረለት ኬንያ ውስጥ የሚገኘው የሳሃን ምርምር ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ማት ብራይደን ከአሜሪካ ድምፅ የሶማሊኛ አገልግሎት ባልደረባ ሃሩን ማሩፍ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ አስታውቀዋል።

Via VOA
ፎቶ:TRT/TIKVAH-ETH SC.SH/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጥላቻ ፓለቲካ ስነ ልቦናዊ ምክንያት፦

ደራሲ ጆርጅ ኦርዌል በስፔን ጦርነት ተሳትፎ ነበር። በአንድ ውጊያ በቅርብ ርቀት የጠላት ወታደር ቀበቶ የሌለውን ሱሪው እንዳይወልቅበት በሁለቱም እጆቹ ይዞ እንዳይተኮስበት ፈርቶ ይንቀጠቀጣል። ኦርዌል እንዲያመልጥ አመቻቸለት።

ለምን እንዳልተኮሰ ሲጠየቅ ‹‹እኔ ጦርነት ውስጥ የመጣሁት ፋሺስትን ልዋጋ ነው። ሱሪው እንዳይወልቅበት በሁለት እጆቹ የያዘ፤ ፈርቶ እየተንቀጠቀጠ ያለ ሰው፤ ሰው ነው እንጂ ፋሺስት አይደለም›› ብሎ መለሰ።

የጥላቻ ፓለቲካ ቅስቀሳ የሚያደርጉ ሰዎች ተቀናቃኞቻቸውን ፍፁም አረመኔና ማሰብ የማይችሉ አድርገው ይስሏቸዋል። አእምሮ እንደሌላቸው ተደርገው ሲሳሉ ከሰውነት ዝቅ ይላሉ። ሌላውን የተለየ/ተፃራሪ ሀሳብ፣ፍላጎት ወይም አመለካከት ያለው ‹‹ሰው ነው›› ብሎ በማየትና ማሰብ የማይችል አእምሮ የሌለው አድርጎ በመመልከት መካከል ከፍተኛ ልዩነት አለ። የሚያሰከትለው ውጤትም የዛኑ ያክል የተራራቀ ነው።

ከሰው ጋር ልዩነት ሲፈጠር በንግግርና በውይይት መፍታት ይቻላል። ነገር ግን ሌላውንን አእምሮ እንዳለው ሰው መረዳት ካልተቻለ ይህን ለማድረግ አስቸጋሪ ይሆናል።

የሁለተኛው የአለም ጦርነት ከመጀመሩ በፊት ጀርመኖች አይሁዶችን ከሰው በታች እንደሆኑ አድርገው ቀስቅሰዋል። በሩዋንዳ ወንድማማቾች የተጠፋፉት ሌላውን ከሰውነት ዝቅ አድርገው አእምሮ እንደሌለው አድርገው በመሳላቸው ነው።

በተለያየ ፓለቲካዊ ምክኒያትና በተለያየ ጊዜ አንድ ቡድን፣ ብሄር ወይም ፓርቲ በሌላው ማሰብ የማይችል አረመኔ ተደርጎ ተስሏል። ነገር ግን ደረጃው ይለያይ እንጂ ሁሉም መልካምነትና ክፋት፤ ትእግስትና ጭካኔ፤ ፍላጎትና ፍርሃት ተሰናስለው የሚገኙበት ሰው ነው።

ሰው - ሰውነት ይቀድማል!

መልካም ጊዜ!
ዶ/ር ዮናስ ላቀው

Via #GETU
@tikvahethiopia
ትምህርት ሚኒስቴር!

አዲሱ የትምህርት መዋቅር 6 ዓመት የአንደኛ ደረጃ፣ 2 ዓመት የመለስተኛ ትምህርት እንዲሁም 4 ዓመት የ2ኛ ደረጃ ትምህርት እንዲሆን መወሰኑን የትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

በዚህም መሰረት ተማሪዎች የ2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በ18 ዓመት የሚያጠናቅቁ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትሩ ዶ/ር ጥላዬ ጌጤ ገልጸዋል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ከዚህ በፊት በግል ዘርፍ ተይዞ የቆየው የቅድመ መደበኛ ትምህርት በግልና በመንግስት እንዲያዝ መደረጉም ተጠቅሷል፡፡

ተማሪዎች 6ኛ ክፍል #ሲያጠናቅቁ ክልላዊ ፈተናን እነደሚፈተኑና ከዚህ በፊት ክልላዊ ፈተና የነበረው 8ኛ ክፍል ሀገራዊ ፈተና እንደሚሆን ነው የተገለጸው፡፡ በዚህም የ10ኛ ክፍል ፈተና እንደማይኖርና የ12ኛ ክፍል ፈተናው ለዩኒቨርሲቲ መግቢያ ሊሆንም ላይሆንም እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡

Via EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia