TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
እንኳን አደረሳችሁ! እንኳን ደስ አላችሁ!!

ለሰው ልጅ ከወርቅ ከአልማዝ፤ ከገንዘብ እና ከሀብት በላይ ትልቁ የሚሰጠው እምነት ነውና በዚህ ገፅ እምነት ጥላችሁ፤ ገፁ የማንም ሳይሆን የኔ ነው ብላችሁ፤ ብዙ አስቸጋሪ እና ፈታኝ ጊዜዎችን አብራችሁ አልፋችሁ እዚህ ስለደረሳችሁ እንኳን ደስ አላችሁ።

የTIKVAH-ETH ቤተሰቦች ይህ ገፅ የናተ ነው የነገውም ቀን የናተው ነው እንዴት ብትሉ፦

√ ማንም ይህን ገፅ በሚዲያ እና በተለያዩ ቦታዎች ሳያስተዋውቅ ከ20 አባል አንስቶ 324,000 ያደረሳችሁት እናተ ናችሁ!

√ ድምፅ ያጡ ሰዎችን ድምፅ ስታሰሙ የነበራችሁት እናተ ናችሁ!

√ ሰው ሲታመም አንድም ቀን ሳትሰለቹ ስታሳክሙ፤ ስታግዙ የነበራችሁት እናተ ናችሁ!

√ ሰዎች ሲፈናቀሉ እኔ ለወገኔ ደራሽ ነኝ ብላችሁ የተጠየቃችሁትን ስታደርጉ የነበራችሁት እናተ ናችሁ!

√ ለተቸገሩት ስትደርሱ የነበራችሁት እናተው ናችሁ!

°በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ፃታዊ ጥቃቶች በቁርጠኝነት ስትቃወሙ እና ስታወግዙ የነበራችሁት እናተው ናችሁ!

√ እውነተኛ መረጃ በፎቶ እያስደገፋችሁ እየላካችሁ ገፃችሁን ታማኝ ያደረጋችሁት እናተ ናችሁ!!

√ ጥላቻ ሀገር ሊያጠፋ ነው ኑ ተነስተን #ግንዛቤ እንፍጠር ስትባሉ ከ7 ሺ ኪሎ ሜትሮች በላይ ትምህርታችሁን ጥላችሁ ስትጓዙ የነበራችሁት፤ በየሄዳችሁበትም ሌላ ቤተሰብ የፈጠራችሁት እናተው ናችሁ!

√ ሀገራችን መፅሀፍ ያስፈልጋታል ስትባሉ እጃችሁ እስኪገነጠል ድረስ መፅሃፍ ተሸክማችሁ በየላይብረሪው መፅሀፍትን የለገሳችሁት እናተው ናችሁ።

🏷እናስ ከናተ ውጪ ማን የዚህ ገፅ ባለቤት ሊሆን ይችላል? ማንም!! አዎን ነገ ልደታችሁ ነው። ነገ የናተ ቀን ነው!!

የምንፈልጋትን አምንከባበርባትን፣ የምንቻቻልባትን፣ የምንዋደድባትን ሁሉም በሰውነቱ የሚከበርባትን፣የሰው ቋንቋው፣ ባህሉ፣ እምነቱ፣ አመለካከቱ የሚከበርባትን #ኢትዮጵያ ለመገንባት ዛሬም ሳንደክም እንሰራለን!!

🏷ነገ 6:00 አበበች ጎበና የህፃናት እንክብካቤና ልማት ድርጅት ተገኝታችሁ ለሰራችሁት ስራ ከእናታችሁ ምርቃትን ተቀበሉ! ለቀጣዩም አብሮነት ቃል ግቡ!!

ለኢትዮጵያ እኛ ልጆቿ አለንላት!!
@tsegabwolde @tikvahethiopua