TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#ከደኢህዴን_መግለጫ ~የክልል ጉዳይ

በክልል የመደራጀት ጥያቄን በተመለከተ የህዝቦች ህገ መንግስታዊ መብት መሆኑን ድርጅታችን ይገነዘባል። በክልል የመደራጀት ጥያቄ ሲነሳ የነበረው ከአንድ አካባቢ ብቻ ባይሆንም ጥያቄውን በጥናት ላይ ተመስርቶ ምላሽ ማግኘት እንዳለበት ድርጅቱ በ10ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ በወሰደው አቋም መሰረት በዝርዝር ህዝቡን ያሳተፈ ጥናት ሲያደርግ ቆይቷል። በጥናቱ የቀረቡ አማራጮችን በጥልቀት በመመርመር የህዝቡን የጋራና ዘላቂ ጥቅም የሚያረጋግጥ አማራጭ በመውሰድ የክልል አደረጃጀት ጥያቄዎች በሚመለሱበት አግባብ ላይ አቋም ተወስዷል። በክልላችን መላው ህዝብ ምክክርና ውይይት የሚደረግበት ሆኖ በአንድ በኩል በጥናቱ የተገኘውን የክልሉ ህዝቦች አብሮ የመቀጠል ፍላጎትን ባከበረ፤ በሌላ ጎኑ ደግሞ የጉባኤውን ውሳኔ ተግባራዊ ባደረገ መንገድና ሃላፊነት በተሞላበት ሁኔታ የመምራት ሃላፊነት ለመወጣት ማዕከላዊ ኮሚቴው ተስማምቷል። #TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia