ተጠርጣዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ...
በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በአንድ ተማሪ ሞት የተጠረጠሩ ተማሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ።
ዩኒቨርሲቲው ባወጣው መግለጫ ዓርብ ግንቦት 16/2011 ዓ.ም ከቀኑ 11 ሰዓት አካባቢ ምንጩ ያልታወቀ ጥቃት በተማሪዎች ላይ ደርሷል ብሏል።
ጥቃቱ ከተለመደው የተማሪ #ፀብና #ግርግር ለየት ያለ ባህሪ ያለው ሲሆን፥ ጩኸትና ግርግር የማይታይበት ተማሪዎችን #በአሰቃቂ ሁኔታ ጥቃት የሚያደርስ ነበርም ነው ያለው።
ጥቃት አድራሾችም ፊታቸውን በመሸፈናቸው በቀላሉ ለመለየት አስቸጋሪ ነበር ያለው ዩኒቨርሲቲው፥ ሆኖም ግን አርብ ጥቃቱን ካደረሱ በኋላ ከግቢ ወጥተው ወደ ጫካ ሲገቡ በማህበረሰቡ ጥቆማ የተወሰኑትን የፀጥታ ሃይሎች በቁጥጥር ሥር አውሏቸው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኝ ተጠቁሟል።
የደብረ ማርቆስ ከተማ ነዋሪዎች ስለ ችግሩ እና ስለ ቀጣይ የተማሪዎች ሰላም ተወያይተዋል። ድርጊቱን ያወገዙት ተወያዮቹ ችግር ፈጣሪዎቹን በማጋለጥ ለፀጥታ አካላት እንደሚሰጡም ቃል ገብተዋል። እስካሁን በድርጊቱ የተጠረጠሩ ተማሪዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውም ነው በውይይቱ ላይ የተገለፀው።
የአማራ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤትም የክልሉ መንግሥት እና ሕዝብ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በአንድ #ተመራቂ ተማሪ ላይ በደረሰዉ የሕይወት መጥፋት ከልብ ማዘኑን በመግለፅ ድርጊቱን አጥብቀው #እንደሚያወግዙት ገልጿል።
የክልሉ መንግሥት ከሕዝቡና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ጥቃት አድራሾችን ተከታትሎ ለሕግ እንደሚያቀርብ ማስታወቁንም ነው አብመድ የዘገበው።
የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ባወጣው የሀዘን መግለጫም በደብረማርቆስ ዩንቨርሲቲ ተማሪ በነበረው ወጣት ሰዓረ አብርሃ ህልፈተ ህይወት የተሰማዉ #ጥልቅ_ሃዘን ገልጿል።
ጉዳዩን በአፅንኦት እየተከታተለው እንደሚገኝ የገለፀው የክልሉ መንግስት፥ ወንጀለኞች ወደ ህግ እንዲቀርቡ እና አስፈላጊዉ ፍርድ እንዲያገኙ ከሚመለከተዉ አካል ሆኖ እንደሚሰራ በመግለፅ ለሟች ቤተሰብ፣ ወዳጅና ዘመድ መፅናናትን ተመኝቷል።
Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#UpdateSport ቅ/ጊዮርጊስ ከወላይታዲቻ የ15ሳምንት ጨዋታ ዲቻ ቅጣት ላይ ያለ ተጫዋች አስልፎአል በሚል ለቅ/ጊዮርጊስ ያልተጠበቀ 3ነጥብ አግኝቶ ቢያድርም ሲነጋ ቅጣትተገቢ አይደለም ተብሎ ውሳኔ ተገልብጦአል።
Via ታደለ አሰፋ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via ታደለ አሰፋ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ለእሳት አደጋ መቆጣጠሪያ ሄሊኮፕተር እንዲገዛ ለአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽህፈት ቤት ጥያቄ ቀርቧል፡፡ ጠያቂው የከተማዋ የእሳት አደጋ መከላከል ሥራ አመራር ኮሚሽን ነው፡፡ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ ለጥያቄው በሰጡት ምላሽ በዘንድሮው ወይም በመጭው በጀት ዐመት ሄሊኮፕተር ለመግዛት እንሞክራለን፤ ካልሆነም በእርዳታ አፈላልገን እናመጣለን ብለዋል ሲል ሸገር ዘግቧል፡፡
Via #ShegerFM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #ShegerFM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ድብረ ማርቆስ👆
#በደብረ_ማርቆስ_ዩኒቨርሲቲ ለአንድ ተማሪ ሞት ምክንያት የሆነውን ድርጊት የከተማው ነዋሪዎች እና የክልሉ መንግስት አወገዙ።
የደብረ ማርቆስ ከተማ ነዋሪዎች ስለ ችግሩ እና ስለ ቀጣይ የተማሪዎች #ሰላም ተወያይተዋል። ድርጊቱን ያወገዙት ተወያዮቹ ችግር ፈጣሪዎቹን በማጋለጥ ለጸጥታ አካላት እንደሚሰጡም ቃል ገብተዋል። እስካሁን በድርጊቱ የተጠረጠሩ ተማሪዎች #በቁጥጥር _ስር መዋላቸውም ነው በውይይቱ የተገለፀው።
ሌሎች የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የጸጥታ ስጋት እንዳይደርስባቸው ከጎናቸዉ እንደሚሆኑ ነዋሪዎቹ አረጋግጠዋል።
በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ እሁድ ግንቦት 18/2011 ዓ.ም የአንድ ተማሪ ህይወት ሲያልፋ ሶስት ተማሪዎች ቆስለዉ በህክምና ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል። የችግሩ መንስኤ እስካሁን እንዳልታወቀም ነው ማብራሪያ የተሰጠው።
የክልሉ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤትም የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እና ሕዝብ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪ ላይ በደረሰዉ የሕይወት መጥፋት ከልብ ከማዘን ባሻገር ድርጊቱን አጥብቀው እንደሚያወግዙት ገልጿል።
የክልሉ መንግሥት ከሕዝቡና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ጥቃት አድራሾችን ተከታትሎ ለሕግ እንደሚያቀርብም ነው ያስታወቀው። ለሟች ቤተሰቦች፣ ለጓደኞቹና ለዩኒቨርሲቲው ማሕበረሰብም መጽናናትን ተመኝቷል።
ምንጭ፦ አብመድ

ግንቦት 20, 1983 ዓ/ም👆
ከላይ ባለው ፎቶ የሕወሓት ሊቀመንበር #መለስ_ዜናዊ እና የደኅንነቱ ሹም #ክንፈ_ገብረ_መድኅን ወደ ግዮን ሆቴል ሲገቡ ይታያሉ።
የሚሊተሪ ለብሶ የሚታየው የቀድሞው ጦር (ደርግ) መኮንን የነበረው ኮሎኔል አስራት ነው። ኮሎኔል አስራት በሕወሓት ከተማረከ በኋላ ከኢህአዴግ ጋር ተሰልፎ በብሔራዊ መረጃና ደህንነት መምሪያ ሀላፊነት ደረጃ ድረስ ሲሰራ የነበረ፤ በኋላም የግርማዊ ዐፄ ኃይለሥላሴ አስከሬን ከኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ጽ/ቤት ለማውጣት የተዋቀረውን ግብረ ኃይል ያስተባበረ ነው።
አብዮት ልጇን ትበላለችና ኮሎኔል አስራት የቀይ ሽብር ተዋናይ ነበር ተብሎ ወደ ወህኒ ቤት የወረደ ሲሆን፤ በወህኒ ቤትም እያለ "በህመም" ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት የተለየ መሆኑ ታውቋል።
ግንቦት 20 ዛሬ 28ኛ አመቱ ሲታሰብ በፎቶው ላይ የምናያቸው ሶስቱም አመራሮች በሕይወት የሉም።
Via #PetrosAshenafi

የካርታው ነገር...
የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቅዳሜ እለት በድረ ገፁ ላይ የወጣውን ካርታ ማን እንዳተመው ለማወቅ ምርመራ እያደረገ መሆኑን ገለፀ።
የሚኒስትሩ ቃል አቀባይ፣ አቶ ነቢያት ጌታቸው፣ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንደገለፁት እንዴትና በማን ካርታው ድረ ገፃቸው ላይ እንደወጣ ይጣራል ብለዋል።
ቃል አቀባዩ አክለውም ማን እንዳተመው ከተለየ በኋላ አስፈላጊውን እርምጃ እንወስዳለን በማለት ተናግረዋል።
“ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራትም ሆነ ከሌሎች ጋር ላላት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ልዩ ትኩረት ትሰጣለች፤ ጉዳዩን በትኩረት እየተከታተልነው ነው’ ብለዋል።
ሶማሊያን የኢትዮጵያ አካል እንደሆነች የሚያሳይና ለሶማሌ ላንድን እውቅና የሚሰጠው ካርታ ባለፈው ቅዳሜ በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ድረ ገፅ ላይ ከታተመ ወዲህ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በርካቶች ሲቀባበሉት ነበር።
ሚኒስትር መሥሪያ ቤቱም ወዲያውኑ ካርታውን ከድረገፁ ላይ በማንሳት #ይቅርታ ጠይቋል።
Via #bbc

‹‹በአሁኑ ወቅት #በኦነግ ትዕዛዝ የሚተዳደር ወታደራዊ ኃይል የለም›› – የኦነግ ቃል አቀባይ አቶ #ቶሌራ_አደባ
.
.
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ‹‹በአሁኑ ወቅት በኦነግ ትዕዛዝ የሚተዳደር ወታደራዊ ኃይል የለም›› ሲል አረጋገጠ።
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ቃል አቀባይ አቶ ቶሌራ አደባ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደተናገሩት፤ ግንባሩ ቀደም ሲል ታጣቂ ኃይል የነበረው ቢሆንም ፣ወታደሮቹን ለአባገዳ እና ለኦሮሞ ህዝብ ካስረከበ ወዲህ ወታደሮች የሉትም።
መሠረታዊ የሆነና መታወቅ ያለበት ጉዳይ ኦነግ የመንግሥትን ጥሪ ተከትሎ ወደ አገር ቤት የገባው በሰላማዊ መንገድ ለመታገል መሆኑ ነው ያሉት አቶ ቶሌራ፣ይህም በመሆኑ ‹‹ግንባሩ በአሁኑ ወቅት የትጥቅ ትግሉን አቁሟል።›› ብለዋል። ‹በኦነግ ትዕዛዝ ስር የሚተዳደር ወታደራዊ ኃይል አሁን እንደሌለም አስታውቀዋል።
እንደ አቶ ቶሌራ ገለፃ፤ ኦነግ ወታደር አያደራጅም፤ ትግሉን የሚያካሄደው በሰላማዊ መንገድ በመታገል ነው። ዓላማውም ይኸው ነው። በአሁኑ ወቅትም የሚያደራጀው ሲቪልን ሲሆን፣ አባሎቹም ሲቪሎች ናቸው።
ቃል አቀባዩ እንደተናገሩት፤ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ኦነግን መወንጀል በመንግሥትም በድርጅቶችም ሆነ በግለሰቦች ተለምዷል። ኦነግ ባልሰራቸው ጥፋቶች ስሙን መጥቀስ በየጊዜው የተለመደ ጉዳይ ሆኗል። በኦሮሚያ ክልልም ሆነ በአንዳንድ አካባቢዎች ከሚከሰቱ ችግሮች ጋር ኦነግን ማያያዝ በርከቷል።
በኦነግ ስም የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ ቡድኖች እንዳሉ የጠቀሱት አቶ ቶሌራ፣ ቡድኖቹ ተደራጅተው የሚንቀሳቀሱ እንጂ በድርጅት መልክ የሚንቀሳቀሱ እንዳልሆኑ ተናግረዋል። ቡድኖቹ በዝርፊያ፣ በስርቆትና በመሰል ነገሮች የተሰማሩ መሆናቸውንም ጠቁመዋል።
የኦነግን መለያ ምልክት አሊያም ባንዲራ ይዘው መንገድ ላይ ተሽከርካሪ አስቁመው የሚዘርፉ እንዲሁም በኦነግ ስም በየመንደሩ እየተዘዋወሩ በሬ፣ ገንዘብ አምጣ የሚሉ ለዝርፊያ ብቻ ተሰባስበው የሚበተኑ ቡድኖች መኖራቸውንም ጠቅሰዋል። ይህን አይነቱን አካሄድ ግን የሚያጣራ አለመኖሩንም ገልጸው፤ ጉዳዩን አጣርቶ እውነተኛው ላይ መድረስ የሚችለው መንግሥት እንደሆነ አመልክተዋል።
አቶ ቶሌራ፣ በየትኛውም የሽግግር ወቅት ችግሮች ሊኖሩ እንደሚችሉ ጠቅሰው፣ በተከሰቱ ችግሮች ላይ ሙሉ በሙሉ ኦነግን ተጠያቂ ማድረግ አይቻልም ማለት ነው።›› ሲሉም አስረድተዋል።
Via #EPA

#update ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ገዱ አንዳርጋቸው ለይፋዊ ሥራ ጉብኝት ወደ ጅቡቲ አቅንተዋል፡፡ በዚሁ የመጀመሪያ የጅቡቲ ጉብኝታቸው ከጅቡቲው ፕሬዝዳንት እስማዔል ኡመር ጌሌ ጋር መወያየታቸውን ፋና ብሮድካስት አውስቷል፡፡ ስለ ሁለትዮሽ ግንኙነቱም ከሌሎች የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ጋር ይመካከራሉ፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአዲስ አበባ ከተማ 204 ማዳበሪያ ጀሶ፣ገለባና ሰጋቱራ የተቀላቀለበት ዱቄት በቁጥጥር ስር ዋለ።
204 ማዳበሪያ ጀሶ፣ገለባና ሰጋቱራ የተቀላቀለበት ዱቄት በትናንትናው ዕለት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 እህል በረንዳ በሚገኙ ሁለት የገበያ አደራሾች ውስጥ በቁጥጥር ስር ውሏል።
ዱቄቱ በቁጥጥር ስር የዋለውም በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 እህል በረንዳ ምዕራብ እና ግንባታ የገበያ አዳራሽ አከሲዮን ማህበር ሱቆች ውስጥ መሆኑን የክፍለ ከተማው ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል።
ድርጊቱን የተመለከቱት የአካባቢው ነዋሪዎች የከተማዋን ቆሻሻ እናፅዳ እያልን ባለንበት ባሁኑ ወቅት አፀያፊ ተግባር ላይ የተሰማራውን የቆሸሸ አዕምሮ ማፅዳት እንደሚገባ ተናግረዋል።
የተፈፀመው ድርጊት በየትኛውም እምነት አፀያፊ መሆኑን የተናገሩት የእህል በረንዳ ነጋዴዎች፣ ሸማቾች እና ነዋሪዎች፥ ድርጊቱን የፈፀሙ ግለሰቦች ለህግ ቀርበው አስተማሪ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ጠይቀዋል።
Via #fbc