#update ቻይና የዩናይትድ ስቴትሱ ግዙፉ ቦይንግ ኩባንያ ካሳ ሊከፍለኝ ይገባል ስትል ዛሬ ጠየቀች። ካሳው የሚከፈለኝም ከበረራ ውጪ የኾኑ ቦይንግ አውሮፕላኖቼ ማግኘት የሚገባኝን ገቢ እንዳላገኝ ሰበብ በመኾናቸው ነው ብላለች።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ የአውሮፕላን አደጋ መጋቢት 1 ቀን፤ 2011 ዓ.ም ከተከሰተ በኋላ ቻይና አጠቃላይ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖቿን አገልግሎት እንዳይሰጡ በማድረግ የመጀመሪያዋ ሀገር ናት።
የቻይና የበረራ አገልግሎት ባለሞያ ሊ ዢያዎጂን ለሮይተርስ የዜና ምንጭ፦ «ቻይና እንዳይበሩ ያደረገቻቸው 96 አውሮፕላኖቿ ከአጠቃላይ አውሮፕላኖቿ 4 በመቶ የሚሸፍኑ» መኾናቸውን ተናግረዋል። «እናም አውሮፕላኖቹ እንዳይበሩ በመደረጉ ለቻይና አየር መንገዶች ግዙፍ ኪሳራ አስከትሏል» ሲሉ አክለዋል። ኪሳራውም በቀን የቻይና 100,000 ዩዋን ወይም ($14,469.90) ዶላር እንደሚገመት ባለሞያው አብራርተዋል።
ከቻይና ውጪ የቱርክ አየር መንገድ፤ የዩናይትድ አየር መንገድ፤ ርያን ኤር እና ፍላይ ዱባይ አየር መንገዶችም ካሣ መጠየቃቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። በኢትዮጵያ እና በኢንዶኔዢያ አየር መንገዶች የቦይንግ አውሮፕላኖች መከስከስ አደጋ 346 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።
Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#update በየወሩ እስከ 18 ሺህ ብር እያወጡ የኩላሊት እጥበት ወይንም ዲያሊስስ ህክምና ሲወስዱ የቆዩ 29 ህሙማን ህክምናቸው በነፃ ሊሆንላቸው ነው፡፡
በዘውዲቱ ሆስፒታል የኩላሊት እጥበት ህክምና ሲያገኙ የነበሩ 20 ታካሚዎችና በየመንገዱ እርዳታ እየለመኑ በግል የሕክምና ተቋማት ሲታከሙ የቆዩ 9 የኩላሊት ህመምተኞች ህክምናቸውን ከነገ ጀምሮ በነፃ ያገኛሉ ተብሏል፡፡ ይህን ያለው የኩላሊት ህመመተኞች እጥበት በጎ አድራጎት ድርጅት ነው፡፡
29ኙ ህሙማን በዘውዲቱ ሆስፒታል በነፃ የኩላሊት እጥበት ህክምናውን እንዲያገኙ የተደረገው የተለያዩ 5 ባንኮች በሰጡት የገንዘብ ድጋፍ ነው ብለዋል ዋና ስራ አስኪያጁ አቶ ሰለሞን አሰፋ፡፡
ባንኮቹ ከበጎ ፈቃደኛ ሰራተኞቻቸውና ከደንበኞቻቸው በሚሰበስቡት ገንዘብ ህሙማኑ የሚታከሙበትን በአመት ከ1.3 ሚሊዮን ብር በላይ ይከፍላሉ ብለዋል አቶ ሰለሞን፡፡
ዋና ስራ አስኪያጁ ለሸገር እንደተናገሩት ማህበሩ ህሙማኑ የዲያሊስስ ህክምና እንዲያገኙ በወር እስከ 4 ሺህ ብር ወጭ ያደርጋል፡፡
ህክምናው በመንግስት በወር 4 ሺህ ብር በግል የህክምና ተቋማት ደግሞ እስከ 18 ሺህ ብር ይጠይቃል ብለዋል፡፡
በግላቸው የሚታከሙት በህክምናው ውድነት ምክንያት ጥሪታቸውን አሟጥጠው በሕይወት ለመቆየት በየመንገዱ የሚለምኑም እንደነበሩ አስታውሰው አሁን ሁሉም ጎዳና ላይ ሲለምኑ የነበሩ 9 ሰዎች በነፃ ሊታከሙ ቃል ገብቷል ብለዋል፡፡
Via #ShegerFM

#update በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዘጠኝ ልዩ ቦታው ጎሮ ፖሊስ ጣቢያ አካባቢ በቡድን በመደራጀት የውንብድና ወንጀል ሲፈጽሙ የነበሩ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡
ከተጠርጣሪዎች አንዷ የግል ተበዳይን ብዙ የሚመነዘር ዶላር እንዳላት በመንገር ካግባባችው በኋላ ብሩን ከባንክ አውጥቶ በስምምነታቸው መሰረት ወደሚመነዘርበት ስፍራ እንደደረሱ የያዘውን ሁለት ሚሊየን ብር በመቀማት ደብድበው ካደከሙት በኋላ በያዙት መኪና ውስጥ በማስገባት ጥቂት ተጉዘው አውጥተው ይጥሉታል፡፡ ፖሊስ ወንጀል ስለመፈጸሙ ጥቆማ ይደርሰውና የማጣራት ስራውን ይጀምራል፡፡
ፖሊስ የውንብድና ወንጀሉን የፈጸሙ አካላትን በመለየት በቁጥጥር ስር ካዋላቸው በኋላ የምርመራ ስራውን ይጀምራል፡፡ ግለሰቦቹ ወንጀሉን ስለመፈጸማቸው ማረጋገጫ ማስረጃዎችን ያሰባሰበው ፖሊስ ምርመራውን አጠናቆ የምርመራ መዝገቡን ለአቃቤህግ ይልካል፡፡
በሰውና በሰነድ ማስረጃ የተደገፈውን መዝገብ የተመለከተው አቃቤ ህግ በግለሰቦቹ ላይ በከባድ የውንብድና ወንጀል ክስ የመሰረተባቸው መሆኑን የቦሌ ክፍለ ከትማ ፖሊስ መምሪያ መርማሪ ዋ/ሳጅን አበራ ፍቃዱ ተናግረዋል፡፡
Via አ/አ ፖሊስ ኮሚሽን

አድናቂዎቼ!!! ተጋብዛችኋል
ቅዳሜ ግንቦት 17 ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ የመጀመሪያውን "የአስራ አንዱ ገፆች" ሲዲ ምርቃት "ሙዚቃ መብቴ ነው" በሚል አርዕስት ስለናት የበጎ አድራጎት ድርጅት ስር ለሚገኙ ህፃናት አዘጋጅተናል፡፡
አድናቂዎቼ!!! ተጋብዛችኋል፡፡
ስትመጡ ግን ለህፃናቱ ምትችሉትን ነገር ሸክፋችሁ ኑ!!!!
" በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ያሉ ህፃናት ሙዚቃን የመስማት ፣ የማየት ፣ የመጫወት እንዲሁም ሙዚቀኛም የመሆን መብት አላቸው፡፡ "
እስካሁን ቃል የገቡልን አጋሮች
EBS TV - የሚዲያ ሽፋን
ንጉስ ማልት - የሚሸጡ መጠጦችን በማቅረብ
ሞናርክ ሆቴል - የሙዚቃ እስፒከሮችን እና ውሀ ለታዳሚዎች በማቅረብ
ኢንዲያና እስበር ሬስቶራንት - ለታዳሚዎች እስናኮችን በማቅረብ
ሌሎችንም በቀጣይ እንገልፃለን፡፡
ለመሳተፍ ለምትፈልጉ ድርጅቶችም ሆነ ግለሰቦች
ስልክ ቁጥር - +251910978192
- +251911468214
- +251923986652

#update ኤርትራዊያን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለ ሥራ ፍቃድ ሥራ መስራት አይችሉም- ብሏል የኢምግሬሽንና ዜግነት ጉዳዮች መምሪያ፡፡. ሸገር አንድ የመስሪያ ቤቱን ሃላፊ ጠቅሶ እንደዘገበው ኤርትራዊያኑ በዘፈቀደ እየገቡ ቢሆንም በቅርቡ ግን መንግስት እንደማንኛውም የውጭ ሀገር ዜጋ እንዲስተናገዱ የሚያስችል ሕግ ለማዘጋጀት ሃሳብ አለ፡፡ በዚሁ ጉዳይ ላይ ከኤርትራ መንግስት ጋር ገና ንግግር ላይ ነን ብለዋል፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢ/ር ታከለ ኡማ በአዲስ አበባ ባህል ኪነ-ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ስር የሚገኙ የኪነ ጥበብ ተቋማት ላይ ምልከታ አድርገዋል፡፡
-
ኢ/ር ታከለ ኡማ ለረዥም ጊዜያት ተቋማዊ ችግር ያለባቸውን ፣ ከይዞታ ጋር የተያያዘ ችግር መፍትሄ ያልተሰጣቸውን እና ፈፅመው በመረሳት እድሳት ሳይደረግላቸው የቆዩ ቴአትር ቤቶችን ከከተማ አስተዳደሩ የካቢኔ አባላት እና አንጋፋ የዘርፉ ባለሞያዎች ጋር በመሆን ጎብኝተዋል፡፡
በመጀመርያ ከስምንት ዓመት በፊት የድሮ ህንፃው የፈረሰውን የራስ ቴአትር ቤትን ጎብኝተዋል፡፡
የቀድሞ ይዞታው በመንገድ ግንባታ ምክንያት የተጣበበው የራስ ቴአትር የከተማ አስተዳደሩ ደረጃውን የበጠበቀ መልኩ እንዲገነባ በመልሶ ማልማት ወደ መሬት ባንክ ገቢ የተደረገው እና በተለምዶ አሜሪካ ጊቢ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ 4500 ካ/ሜ ቦታ ለዚሁ ማዕከል ግንባታ እንዲውል ወስኗል፡፡
ጉብኝታቸውን በመቀጠልም ለአፍሪካ የመጀመርያ የሆነው እና በርካታ የቴአትር ባለሞያዎችን ያፈራውን የሃገር ፍቅር ቴአትር ቤትን ጎብኝተዋል፡፡
በዚህም የቴአትር ቤቱን ይዞታዎች በማሻሻል ታሪካዊ ቅርፁን ሳይቀይር ተጨማሪ አዳዲስ የማስፋፍያ ግንባታዎች እንዲደረጉም ተወስኗል፡፡
በመቀጠልም የግንባታ ሂደቱ በውል ወሳጅ ተቋራጭ ምክንያት የተጓተተውን የህፃናት እና ወጣቶች ቴአትር ቤትን ጎብኝተዋል፡፡
ቴአትር ቤቱ በፍጥነት ግንባታው እንዲጠናቀቅ እና አገልግሎት መስጠት እንዲጀምር አሁን ያለውን ተቋራጭ ውል በማፍረስ ከሌላ ተቋራጭ ጋር አዲስ ውል እንዲፈራረም ተወስኗል፡፡
በመጨረሻም ኢ/ር ታከለ ኡማ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጥበባት ኮሌጅን ጎብኝተዋል፡፡
በዚህ ጉብኝታቸውም በቴአትር እና የስነ ጥበብ ዲፓርትመንቶች ላይ ያለውን የመማርያ ህንፃ እና የመሠረተ ልማት ችግር በሚቅረፍበት ሁኔታ ላይ ከባለሞያዎች እና የዩኒቨርሲቲው አመራሮች ጋር ተወያይተው አቅጣጫም ሰጥተዋል፡፡
Via #MayorOfficeAA

ፎቶ👆በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ባለው የአብሮነትና የምስጋና የአፍጥር ምሽት ላይ ኢ/ር ታከለ ኡማ በክብር እንግድነት ተገኝተዋል፡፡
Via @mayorofficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via @mayorofficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጋዜጠኛ ምስጋናው ጌታቸው❓
/በኤልያስ መሰረት/
"ጋዜጠኛችን በሁለት ዙር ድብደባ ተፈጽሞበታል። እንደሰማሁት ደብዳቢ ፖሊሶቹ 'እስክንድር ይመጣል ብለን ነበር' እያሉ እኔን ሲጠባበቁ ነበር"--- #እስክንድር_ነጋ
"በተባለው ግለሰብ ላይ ምንም ድብደባ አልተፈፀመም። የጋዜጠኛ መታወቂያ እና ደብዳቤ ሳይዝ በድብቅ ካሜራ ሲቀርፅ ተይዞ መጣራት እያረግን ነው"--- የአራዳ ፖሊስ ባልደረባ ኮማንደር የኔወርቅ
እስክንድር እንደሚለው "ቤታቸው የፈረሰባቸው ግለሰቦች ኢትዮጲስ ጋዜጣን 'ጉዳያችንን ዘግቡልን' ባሉት መሰረት ጋዜጠኛ ምስጋናው ጌታቸው በድብቅ የሚቀርፅ ሪኮርደር ይዞ ዛሬ ወደ ስፍራው አመራ። መነፅር ላይ ያለው ይህ ድብቅ ካሜራን ለመጠቀም የፈለግነው ፖሊሶች ተደራጅተው እንደሚጠብቁን ስላወቅን ነው። ጋዜጠኛው ስፍራው ላይ እንደደረሰ ካሜራውን ተቀብለው ደበደቡት። እንደገና በሁለተኛ ዙር ከ45 ደቂቃ በሁዋላ ድብደባ አደረሱበት። ከዛም 4 ኪሎ ብርሀን እና ሰላም አካባቢ ወዳለ ፖሊስ ጣብያ ወስደውታል። ፖሊስ አሁን እያለ ያለው ጋዜጠኛው ቃሉን ከሰጠ በሁዋላ አቃቤ ህግ ይወስናል ነው። ድብደባ ሲፈፀምበት ምስክር አለ ብንላቸውም ክስ መመስረት አትችሉም ተብለናል።"
በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡት ኮማንደር የኔወርቅ ደሞ "ጋዜጠኛ ለመሆኑ መታወቂያ ይዟል እንዴ?" ብለው እኔኑ ጠይቀውኝ ከዛ እንዲህ ብለዋል። "የተደበደበ የለም። ፍቃድም መታወቂያም አልነበረውም። እኛ ገና ጋዜጠኛ መሆኑን እያጣራን ነው። ተደብቆ ሲቀርፅ የእኛ ፖሊሶች ይዘውታል። ፈቃድ የሌለው ሰው በድብቅ ሰው መቅረፅ አይችልም። ግን ጫፉን የነካው ሰው የለም።"
እስክንድር አክሎም "የጋዜጠኝነት ስራ ለመስራት ልዩ ፈቃድ አያስፈልገውም። አስፈላጊነት መስዋትነት እንከፍላለን እንጂ ሁሌ ደብዳቤ እያፃፍን ስራ አንሰራም" ብሏል።

#update የለገጣፎ ተፈናቃዮች አቤቱታቸውን ለፌደሬሽን ምክር ቤት ህገ መንግስት አጣሪ ጉባኤ ማቅረባቸውን ሪፖርተር አስነብቧል፡፡ 183 ያህሉ ተፈናቃዮች ያቀረቡት አቤቱታ ኦሮሚያ ክልል የሊዝ አዋጁን መሠረት አድርጎ ያወጣቸው ደንቦችና መመርያዎች መኖሪያ ቤታችን ስላፈረሰ የእኩልነትና ሰብዓዊ መብታችን ተነክቷል፤ እናም የሕገ መንግሥት ትርጓሜ ይሰጥልን የሚል ነው፡፡ ሕገ መንግሥቱ በአንቀጽ 37 ፍትሕ የማግኘት መብት በሰጠበት ሁኔታ በፌዴራል የሊዝ አዋጁ ለባለንብረቶቹ ምንም ዓይነት ካሳ ሳይከፈል የማስለቀቅ ሥልጣኑን ለአስፈጻሚ አካል ብቻ መስጠቱ ከሕገ መንግሥቱ ጋር ይቃረናል ይላል- ሰነዱ፡፡ 6 ነጥቦችን የያዘው አቤቱታ ለጉባኤው የቀረበው ግንቦት 2 ነው፡፡ በለገጣፎ ያለ ፕላን የተሠሩ ተብለው ከወራት በፊት በሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶች መፍረሳቸው ይታወሳል፡፡ ተፈናቃዮቹ የ70 ሚሊዮን ብር ጉዳት ካሳ ክስ ሊመሰርቱ መሆኑም ታውቋል፡፡
Via #ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ስጋት ያለበት አካባቢ የለም...
የ12ኛ እና 10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናዎች ስጋት በሌለበት ሁኔታ ለመስጠት እየተሰራ መሆኑን የሃገር አቀፍ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ ገለጸ። ኤጀንሲው እስካሁን ባለው ሁኔታ ስጋት ተብሎ የተለየ አካባቢ የለም ብሏል። ፈተናውንም ለመስጠት ዝግጅት መጠናቀቊን ዐስታውቋል።