TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.7K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
አዲስ አበባ‼️

የአዲስ አበባ አስተዳደር ምክር ቤት የከተማ አስተዳደሩን አስፈጻሚ አካላት እንደገና ለማቋቋም የወጣውን አዋጅ #አፀደቀ

አዋጁ መፅደቁ ለመዲናዋ ህብረተሰብ አስተዳደሩ የሚሰጠውን አገልግሎት የተሻለ #ቀልጣፋና ምቹ ከማድረግ ባለፈ ከዚህ በፊት ያለአግባብ ይባክን የነበረን ገንዘብ ለማስቀረት ያስችላል ተብሏል።

እንደ ኤፍ ቢ ሲ ዘገባ በቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ላይም የምክር ቤቱ አባላት የተለያዩ አስተያየቶች እና ጥያቄዎችን አንስተው ከተወያዩ በኋላ በሙሉ ድምፅ አዋጁን አፅድቆታል።

በአዋጅ መሰረት 18 ተቋማት ሲታጠፉ አምስት ተቋማት ደግሞ በአዲስ መልክ ተቋቁመዋል።

በዚህም መሰረት፦

1. የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ
2.የመዋቅርና አደረጃጀት ፕሮጀክት ፅህፈት ቤት
3. ዴሊቨሪ ዩኒት
4. ካይዘን ኢንስትቲዩት
5. ወንዞችና ዳርቻዎች ልማትና የአየር ንብረት ለውጥ ማጣጣም ፕሮጀክት ፅህፈት ቤት
6. እንጦጦና አካባቢው ቱሪስት መዳረሻ ፕሮጀክት ፅህፈት ቤት
7.የመስሪያ ቦታዎች ልማት አስተዳደር ኤጀንሲ
8.ትራንስፓርት ፈንድ ፅህፈት ቤት
9.ትራንስፖርት ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት
10.ህብረተሰብ ተሳትፎ ልማት ኤጀንሲ
11.ቤቶች አስተዳደር ኤጀንሲ
12. የተቀናጀ መሬት መረጃ ማዕከል
13.ማህበራዊ ጥበቃ ፈንድ እና ልማታዊ ሴተፍትኔት ኤጀንሲ
14.ደንብ ማስከበር አገልግሎት ፅህፈት ቤት
15.የውሃና ፍሳሽ ሳኒቴሽን ልማትና ማስፋፊ ፕሮጀክት ፅህፈት ቤት
16.የማዕከላትና ኮሪደር ልማት ኮርፖሬሽን
17.መለስ ዜናዊ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር፣ ሽግሽግና ኢንኩቤሽን ማዕከል
18. ሬዚሊየንስ ፕሮጀክት ፅህፈት ቤት

በአዲስ መልክ የተቋቋሙ ተቋማት፦

1. ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ
2. የመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን
3. የወጣቶችና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ
4. ግንባታ ኢንተርኘራይዝ
5. ግንባታ ዲዛይን ፅህፈት ቤት ናቸው።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት‼️

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መንግስት ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ጋር የተፈራረመውን የኢትዮጵያውያን የስራ ስምሪት መግባቢያ ሰነድ #አፀደቀ፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው ሶስተኛ ልዩ ስብሰባው መንግስት ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ጋር የተፈራረመውን የኢትዮጵያውያን የስራ ስምሪት መግባቢያ ሰነድ በአብላጫ ድምጽና በ26 ተቃውሞ አፅድቆታል፡፡

የመግባቢያ ሰነዱ 20 አንቀጾች ያሉት ሲሆን በኤምሬቶች ህግ መሰረት በቤት ውስጥ አገልግሎት ምድብ ውስጥ በሚገኙ ስራዎች እንዲሁም በግሉ ዘርፍ ለስራ የሚሰማሩ ሰራተኞችን ያካተተ ስምምነት ነው፡፡

በስምምነቱ መሰረት የሰራተኞች ምልመላና ስምሪት የሀገሪቱን ህግ ያከበረ እንዲሆን የማድረግ፣ የሰራተኞች መብትና ደህንነት እንዲጠበቅ እና ሰራተኞች ለጉልበት #ብዝበዛ እንዳይጋለጡ የማድረግ፣ ለስራ ውሎች የህግ እውቅና እና ተፈጻሚነት የመስጠት፣ ሰራተኞች ገቢያቸውን ወደ ሀገራቸው እንዲልኩ ማስቻል የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ግዴታ እንደተጣለበት በስምምነቱ ተጠቁሟል፡፡

ምንጭ፦ ኢፕድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ኮሚሽነር እና ምክትል ኮሚሽነር ሹመትን #አፀደቀ። ምክር ቤቱ በዛሬው ዕለት ባካሄደው 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 39ኛ መደበኛ ስብሰባ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የቀረበለት የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ኮሚሽነር እና ምክትል ኮሚሽነር ሹመትን አፅድቋል። በዚህ መሰረትም ዶክተር ጣሰው ገብሬ የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ከሚሽነር እንዲሁም ኡስታዝ አቡበክር አህመድ ደግሞ የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ሆነው ተሹመዋል። ምክር ቤቱ የኮሚሽኑን ኮሚሽነር እና ምክትል ኮሚሽነር በ25 ተቃውሞና በአብላጫ ድምፅ ማፅደቁም ታውቋል። በተመሳሳይ ምክር ቤቱ የእርቀ ሰላም ኮሚሽን ሰብሳቢ እና ምክትል ሰብሳቢ ሹመትንም አጽድቋል። በዚህም መሰረት ካርዲናል ብርሃነ እየሱስ ሱራፌል ሊቀ ጳጳሳት ዘካቶሊካውያን የኮሚሽኑ ሰብሳቢ፤ ወይዘሮ የትነበርሽ ንጉሴ ምክትል የኮሚሽኑ ሰብሳቢ ሆነው ተሹመዋል። ምክር ቤቱ የእርቀ ሰላም ኮሚሽን ሰብሳቢ እና ምክትል ሰብሳቢ ሹመትን በአብላጫ ድምፅ ያጸደቀው ሲሆን፥ 10 ድምፅ ተአቅቦና አራት ተቃውሞ ቀርቦበታል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia