TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
ጎንደር እና ደብረ ታቦርን ጨምሮ 12 ከተሞች የ4G LTE አገልግሎት ተጠቃሚ ሆኑ።

ኢትዮ ቴሌኮም በሰሜን ሰሜን ምዕራብ ሪጅን የ4G LTE አድቫንስድ አገልግሎትን በዛሬው ዕለት አስጀምሯል።

በሰሜን ሰሜን ምዕራብ ሪጅን የ4G LTE አድቫንስድ አገልግሎት #የጎንደር እና #ደብረታቦርን ጨምሮ 12 ከተሞችን ተጠቃሚ ያደርጋል።

በሰሜን ሰሜን ምዕራብ ሪጅን ብቻ 142 ሺህ ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ይገኛሉ።

ኢቲዮ ቴሌኮም ዲጅታል ኢትዮጵያን መገንባት እና በመረጃ የበለፀገ ማህበረሠብ መገንባትን ታላሚ በማድረግ የ4ጂ ኤል ቲኢ አገልግሎት በ67 ከተሞች አገልግሎት ማስጀመሩን ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ፍሬህይወት ታምሩ መግለፃቸውን etv ዘግቧል።

@tikvahethiopia