TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.7K photos
1.52K videos
215 files
4.15K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ🔝

በሀረማያ ዩኒቨርስቲ በተማሪዎችና በፖሊስ መካከል በተፈጠረ ግጭት ጉዳት መድረሱ ተሰምቷል። ግጭቱ የተፈጠረው የኦሮሞ ተማሪዎች የአዲስ አበባ ባለቤትነት እንዲሁም አፋን ኦሮሞ የፌደራል የስራ ቋንቋ እንዲሆን በመጠየቅ ተቃውሞ ማሰማት መጀራቸውን ተከትሎ ነው።

Via ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር 302 ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን አደጋ #ምርመራ የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት #በቅርቡ እንደሚለቀቅ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ #ነቢያት_ጌታቸው ለሮይተርስ ተናግረዋል፡፡ ሪፖርቱን ይፋ የሚያደርገው ትራንስፖርት ሚንስቴር ነው፡፡ ውጤቱ ለአውሮፕላኑ የተገጠመለት (MCAS) ሶፍትዌር #ከካፒቴኑ ቁጥጥር ውጭ አውሮፕላኑ አፍንጫውን ቁልቁል ዘቅዝቆ እንዲከሰከስ እንዳደረገው እንደሚገልጽ ይጠበቃል፡፡ #ቦይንግ ኩባንያ ሶፍትዌሩን አሻሽያለሁ ብሏል፤ በሚዲያ ዘመቻ ራሱን ለመከላከል እየሞከረ ነው፡፡

Via ሮይተርስ(በዋዜማ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሀረማያ ዩኒቨርሲቲ...

"በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ እየተወጣ ያለው ሰልፍ ማን እንደጠራው የማይታወቅ ነው እና ተማሪዎች እንዲጠነቀቁ መልዕክቴን አስተላልፍልኝ።" Abba Jifar

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ የፖሊስነት ስልጠና ሲከታተሉ የነበሩ ከ700 በላይ ፖሊሶችን በዛሬው እለት አስመርቋል። በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይም የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል አለማየሁ እጅጉን ጨምሮ የኦሮሚያ ክልል የፀጥታ እና አስተዳደር ቢሮ አመራሮችና ከፍተኛ የክልሉ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ተገኝተው ነበር።

Via fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መቶ በመቶ ፈተነዋል...

"የሃሳብ ልዩነት አልነበረንም አንልም። ይህ ደግሞ በተፈጥሮ፣ በግለሰብ ሌላው ቀርቶ በአንድ ቤተሰብ አባላት መካከል እንኳን በቴሌቭዥን ቻናል ምርጫ ልዩነት ላይ ይገጥማል። …በመካከላችን ያጋጠመው የሀሳብ ልዩነት ነበር። ይህን ደግሞ በመርህ ደረጃ እና በውይይት መቶ በመቶ ፈትተነዋል።" የሶማሌ ክልል ም/ ርዕሰ መስተዳድር አቶ #ሙስጠፌ_ሙህመድ እና የሶ.ህ.ዴ.ፓ ሊቀመንበር አቶ #አህመድ_ሽዴ በጅግጅጋ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው 10ኛው የሶ.ህ.ዴ.ፓ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ከተናገሩት።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥንቃቄ ይደረግ🔝

ወደሀዋሳ ጉዞ ላይ የምትገኙ #አሽከርካሪዎች ከመቂ በኃላ መንገዱ በከፊል በአቧራ በመሸፈኑ #ለእይታ እጅግ አስቸጋሪ ነው፤ እባካችሁ በጥንቃቄ አሽከርክሩ...

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት #የሰብዓዊ_መብት_ኮሚሽን እጩ ዋና ኮሚሽነር አቅራቢ ኮሚቴ 89 ግለሰቦች ለጥቆማ መቅረባቸውን አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopua
#update የሚድሮክ ለገደምቢ የወርቅ ማምረቻ ኩባንያ የፈቃድ ዕገዳ አለመነሳቱን የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር አስታውቋል። የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫው፥ የሚድሮክ ለገደምቢ የወርቅ ማምረቻ ኩባንያን ፈቃድ ከአካባቢው ህዝብ በቀረበ ጥያቄና አቤቱታ ምክንያት ከግንቦት 1 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ መታገዱን አስታውሷል።

#ena
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኒፕሲ ገዳይ ማን እንደሆነ ታወቀ‼️

በአባቱ ኤርትራዊ እንደሆነ የተነገረው የራፕ ሙዚቃ አቀንቃኝ ኒፕሲ ሐስልን ገድሏል ተብሎ የተጠረጠረው ግለሰብን ፖሊስ መያዙን አስታወቀ።

ባለስልጣናት እንዳሉት ኤሪክ ሆልደር የተባለው ግለሰብ ከእሁድ ዕለቱ ጥቃት ጋር በተያያዘ በፖሊስ ሲፈለግ ነበር። ኒፕሲ ሐስል በተሰነዘረበት ጥቃት የተገደለው የእራሱ በሆነው የልብስ መደብር አቅራቢያ ነበር። በጥቃቱ ሌሎች ሁለት ሰዎች የመቁሰል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

እሁድ ዕለት በተከፈተበት ተኩስ የተገደለው የራፕ ሙዚቀኛው ኒፕሲ ሐስልን ለማሰብ በተዘጋጀ ሥነ ሥርዓት ላይ በርካታ አድናቂዎቹ የተገኙ ሲሆን በስፍራው በተፈጠረ መጨናነቅ ቢያንስ 19 ሠዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ፖሊስ ገልጿል።

ትክክለኛ መጠሪያው ኤርሚያስ ዳቪድሰን አስገዶም የሆነው ኒፕሲ ሐስል በደቡባዊ ሎስአንጀለስ ውስጥ ያደገ ሲሆን በታዳጊነት እድሜው የአንድ የጎዳና ላይ የወሮበሎች ቡድን አባል ነበረ።

በኋላ ላይ ግን ከቡድኑ በመውጣት በዙሪያው ያለን ማህበረሰብን ማስተባበርና መርዳት ጀምሮ በጥበብ ሥራዎች ውስጥም አስተዋጽኦን ሲያበረክት ቆይቷል። ከመገደሉ ቀደም ብሎ በትዊተር ገጹ ላይ “ጠንካራ ጠላት ካለህ መባረክ ነው” ሲል አስፍሮ ነበር።

Via BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ባለቤት...

ባሳለፍነው ሳምንት የሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ባለቤት የ11.3 ሚሊዮን ብር የፍትሐ ብሔር ክስ ተመሠረተባቸው ተብሎ የተሰራጨው ዜና #የተሳሳተ መረጃ ነው ሲል የናፍያድ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ህዝብ ግንኙነት ክፍል ገለፀ፡፡

እንደ ተቋሙ ገለፃ የተቋሙ ባለቤት #ናፍያድ_ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በሚል ድርጅት ስም በከፈቱት አካውንት ከሳሽ ለተባሉት አቶ አንተነህ ዘለቀ ምንም አይነት ቼክ እንዳልሰጡ እና ከግለሰቡ ጋርም በስራ ዘርፍም ሆነ በሌላ ጉዳይ የማይገናኙ እንደሆኑ ጠቅሶ ተሰጠ የተባለው ቁጥሩ ኤ 4178436 የሆነ ቼክ መሰረቁን ቀደም ተብሎ ለፖሊስ ሪፖርት እንዳደረገ ገልጾአል።

በጉዳዩ ላይ ክስ ተመስርቶ እየታየ እንደነበር የገለፀው የህዝብ ግንኙነት ክፍሉ ለዚህም ድርጅቱ ከሚገኝበት ከኦሮምያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የአዳማ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ፖሊስ የደረሰበትን ውጤት የሚያሳይ ለተቋሙ የተፃፈን ደብዳቤን አቅርቧል፡፡

ፖሊስ ቁጥሩ ኤ 4178436 የሆነ ቼክ ከወጋገን ባንክ አዳማ ቅርንጫፍ ስለመሰረቁ በተመለከተ እየተደረገ ስላለው የወንጀል ምርመራ በሚመለከት የፃፈው ደብዳቤ ጉዳዩ ላይ ምርመራ እያደረገ መሆኑንም ይጠቁማል፡፡

"በዚህ ጉዳይ ከሳሽ ነኝ ያሉት አቶ አንተነህ ዘለቀ የተባሉት ግለሰብ በጠፋው ቼክ ጉዳይ ተጠርጥረው በአዲስ አበባ ፖሊስ እና በኦሮምያ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩ እና በዋስ መብት የተለቀቀቁ" ናቸው ያለው የህዝብ ግኝኑነት ክፍሉ “ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮኃል እንዲሉ በተገላቢጦሽ ግለሰቡ ከሳሽ ሆኖ መቅረባቸው አስገራሚ ሆኖብናል” ያለ ሲሆን ጉዳዩ በህግ የተያዘ መሆኑን አስታውሶ "ክሱ ሆን ተብሎ የድርጅቱን ባለቤት እና የተቋሙን መልካም ስም ለማጉደፍ የተቀናባበረ" መሆኑንም ጠቅሷል፡፡

Via ሸገር ታይምስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia