TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
ሰበር ዜና‼️

የተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመረጃ ሳጥን (black box) #ሙሉ_መረጃው ሊያስገኝ በሚችል ደረጃ ላይ መሆኑን ምርመራውን ያከናወነው የፈረንሳዩ ቢ.ኢ.ኤ የአውሮፕላን አደጋ ምርመራ ኤጀንሲ ማስታወቁን የትራንስፖርት ሚኒስቴር ገለጸ፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት መረጃዎቹን #መረከቡን የትራንስፖርት ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስ ለኢቢሲ ተናግረዋል፡፡

ዝርዝር #ትንተናው በቅርቡ በአንድ ወር ውስጥ ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግም ተገልጿል፡፡ ከመረጃ ሳጥኑ የሚገኙ መረጃዎች በቅርቡ ለ157 ሰዎች ህይወት ማጣት ምክንያት ለሆነው የቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን መከስከስ ምክንያት ፍንጭ እንደሚጠቁም የሮይተርስ ዘገባ ያስረዳል፡፡

Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia